24/11/2025
፨ጾማችን ምን ይምሰል???
*ንጹም ጾመ ወናፍቅር ቢጸነ
ወንትፋቀር በበይናቲነ(ቅ/ያሬድ
*ጾምን እንጹም ባልንጀራችነንም እንውደድ
እርበርሳችንም እንዋደድ( እንተሳሰብ)ይለናል ሃይማኖተኛው ሊቅና ጻድቅ ኢትዮጵያዊ ቅዱስ
*አዋጁ ይኽ ነው ጾሙንም ጀመርነው
ግን እኛ እንዴት ነው የምንጾመው?ሊቁ እንደነገረን
ከባልንጀሮቻችን ጋራ ተስማምተን ተግባብተን እርስበርሳችን ተፋቅረን ከቤተሰቦቻችንስ ጋር ተሳስበን ተከባብረንና ተዛዝነን ነው?
ወይንስ ዝም ብለን በተለምዶ ነው የምንጾመው?
መጠየቅ አለብን እኮ ሰዎች እንደ ባለአእምሮ
በያለንበት እንደተቋም ምን ላይ ነው ያለነው?
እንደ ሀገርስ እንዴት እየኖርን ነው ?
አሁን ለመተርጎም የሚያስቸግር ሁኔታ ነው ያለው
አንባ ጓሮ የበረከተበት ዘመን ፈታኝና መዘዘኛ
ሃይማኖተኛው ጠበኛ ፖለቲከኛው ጦረኛ
በአነስተኛ ኑሮ ውስጥ ያለው ቧልተኛ
ሥራየ ብሎ ነገር እሚያቀሳስር ሟርተኛ
በተለያየ መንገድ ኅነት ያስጨነቀው ወሬኛ
ልዩነትን የበለጠ የሚያሰፋ ቁስል የሚፈጥር እንጅ ፈዋሽ አጽናኝ ያልሆነ የተሰበሰበውን የሚበትን ተስፋ ያለውን ተስፋ የሚያስቆርጥ ሰላማዊውንም አእምሮ የሚበጠብጥ ክፉ ወሬ እያወራን እየሰማን?
እንዴት ነው መጾም ያለብን?
ሁለንተናችን እንዲጾም ወስነን ነው?
እንደሱ ከሆነ ጾማችን ውጤታማ ይሆናል
እንደ አባቶቻችን ጩኸታችን መልስ ያስገኛል
ይኽን ጾም የጾሙት አበው ነቢያት ሲሆኑ የመከራውን ዘመን አርቀውቀታል አሳልፈውበታል
የተነገረውን ተስፋም እውን ሆኖ አይተውበታልና
እኛም እራሳችነን ከክፉ ነገር ሁሉ ቆጥበንና አርቀን
አእምሮአችነንም ሰብስበን በክት ልቡና ከጾምነው
የምንሻውን ውጤት እናገኝበታለን።
ካልሆነ ግን ከንቱ እንደክማለንና ክርስቲያናዊ ምክሬ
እንደ ሊቁ ምክርም እንመጽሐፍ ቃልም እንጹመው