OJ Kapho Dhoosa

OJ Kapho Dhoosa Itiyophiyu Hawaariyate Amma'nota Kaphonsa Mittu Mittunkunni Kolaanseemmo!! IYESUUSI MOOTICHIMMA DUDUMBEEMMO!! Roomu Sokka 10:9

Yesuusi Mooticha ikkinota, afiikkinni farci'rittoronna Maganu reyotenni kayisinosita wodanikkinni ammanittoro gatatto.

በመጽሐፍ ቅዱሳችን ውስጥ  #እግዚአብሔር የሚል ቃል ከ 8723 ጊዜ በላይ ተጽፏል። ለመሆኑ እግዚአብሔር ማለት ምን ማለት ነው ብላችሁ ጠይቃችሁ፣ አጥንታችሁ፣ የቃሉን ትርጉም ፈልጋችሁ ታውቁ ...
29/08/2026

በመጽሐፍ ቅዱሳችን ውስጥ #እግዚአብሔር የሚል ቃል ከ 8723 ጊዜ በላይ ተጽፏል።

ለመሆኑ እግዚአብሔር ማለት ምን ማለት ነው ብላችሁ ጠይቃችሁ፣ አጥንታችሁ፣ የቃሉን ትርጉም ፈልጋችሁ ታውቁ ይሁን?

" #እግዚአብሔር " ማለት ምን ማለት ነው?

እንማማር እስክ/ቲ!!

29/08/2026

አይ ቢሾፕ ደጉ! ዝም ከማለት ይሻላል ብለው ነው እንጂ ንግግሮት ውሸት መሆኑን እያወቁ ነው የሚያወሩት አይደል?

  〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️የኦጄ ቄሶች፣ "አብና ወልድ አንድ አካል ናቸው፤ ራሱ ኢየሱስ አብ ነው፤ አብ የሚባል ሌላ አካል የለም" ለማለት እንደ ዋነኛ ማስረጃ አድርገው  የዮሐንስ...
29/08/2026



〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️

የኦጄ ቄሶች፣ "አብና ወልድ አንድ አካል ናቸው፤ ራሱ ኢየሱስ አብ ነው፤ አብ የሚባል ሌላ አካል የለም" ለማለት እንደ ዋነኛ ማስረጃ አድርገው የዮሐንስ ወንጌል 10፥30ን ያቀርባሉ።

ክፍሉ እንዲህ ይላል፦ "እኔና አብ አንድ ነን።"

ይህንን ቃል ከነ ሙሉ አውዱና ከቋንቋው አገባብ አንጻር በትክክል እንየው!

👉

በጥቅሱ ላይ ጌታችን ኢየሱስ " " አለ እንጂ " " አላለም። " #ነን" የሚለው ቃል (በግሪኩ " #ኤስመን" - esmen) ብዙ ቁጥርን የሚያመለክት ግስ ነው። ይህ የሚያሳየው " #እኔ" (ወልድ) እና " #አብ" (አባት) ሁለት የተለያዩ አካላት መሆናቸውን ነው።

ኢየሱስ እና አብ አንድ ነጠላ አካል ቢሆኑ ኖሮ " " ይል ነበር እንጂ፣ " #ነን" ብሎ በብዙ ቁጥር ራሱንና አብን አይገልጽም ነበር።

👉 ?

በግሪኩ መጽሐፍ ቅዱስ " #አንድ" ለሚለው ቃል የተለያዩ ቃላት አሉ። ኢየሱስ እዚህ ጋር የተጠቀመው " #ሄን" ( ) የሚለውን ቃል ሲሆን ትርጉሙም በባህርይ፣ በዓላማ፣ እና በስልጣን አንድ መሆንን የሚያሳይ እንጂ አንድ ነጠላ አካል (One person) መሆንን የሚያሳይ አይደለም። ኢየሱስና አብ በባህርይ፣ በኃይልና በስልጣን ፍጹም አንድ አምላክ ናቸው፤ ሆኖም በአካል የተለያዩ ናቸው።

👉

ይህ ጥቅስ ከመነገሩ በፊት ቁጥር 28 እና 29 ላይ ያለውን ስናነብ፣ ኢየሱስ ስለ በጎቹ (ስለ አማኞች) ደህንነት እየተናገረ ነበር። ኢየሱስ " " (ቁ.28) ካለ በኋላ፣ ቀጥሎ ደግሞ " " (ቁ.29) ይላል። የአማኞችን ደህንነት በመጠበቅ ረገድ የልጁ እጅ እና የአብ እጅ እኩል ስልጣንና ኃይል እንዳላቸው ካሳየ በኋላ፣ ይህንኑ የመለኮት አንድነታቸውን ለማጽናት "እኔና አብ አንድ ነን" አለ።

👉

ጌታችን ኢየሱስ በዮሐንስ 17፥22 ላይ ስለ ደቀመዛሙርቱ ወደ አብ ሲጸልይ፦ " ..." ብሏል። ክርስቲያኖች "አንድ" ሲሆኑ ተጨፍልቀው አንድ ነጠላ አካል አይሆኑም፤ ነገር ግን በዓላማ፣ በፍቅር እና በመንፈስ ፍጹም አንድ ይሆናሉ። የሥላሴም አንድነት በባህርይ፣ በስልጣን እና በመለኮት ፍጹም አንድነት ያለው፣ ነገር ግን በአካል የተለየ (አብ፣ ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ) መሆኑን ቃሉ በሚገባ ያብራራል።

〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️

👉

ውድ ወገኖቼ፣ " " የሚለውን ቃል " " ብላችሁ ከምትተረጉሙ፣ ቃሉ ራሱ " #ነን" በሚል የብዙ ቁጥር ግስ አብና ወልድ የተለያዩ አካላት መሆናቸውን እየመሰከረ መሆኑን አስተውሉ!

ቃሉን ከነ ሙሉ ሰዋስዋዊና ትምህርታዊ አውዱ በማንበብ፣ ወደ ቃሉ እውነተኛ ብርሃን እንድትመለሱ በፍቅር እንጠይቃለን!

እውነት አርነት ያወጣል!

29/08/2026
29/08/2026

::
➖➖➖➖➖➖➖➖
ኢየሱስ ብቻውን ጌታ ነው!
አብ ብቻውን ጌታ ነው! በሉ።
መዝ 110:1 ላይ ኢየሱስ ጌታ እንደሆነ፤ አብም ጌታ እንደሆነ ተጽፏል!!

29/08/2026

በ OJ Kapho Dhoosa ገጽ ላይ የምንጽፍ አድሚኖች ደመወዝ ተከፍሎን ነው።

ደመወዛችንም 30,654.954 ብር አይደለም፤ የዘላለም ሕይወት ስለተሰጠን በፍቅር በነጻ ነው የምናገለግለው!!

🙋🙋 ዮሐንስ 14:13-16"¹³ አብ በወልድ እንዲከብር፣ በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ አደርገዋለሁ፤¹⁴  ማንኛውንም ነገር በስሜ ብትለምኑኝ፣ እኔ አደርገዋለሁ።በቁጥር 13 እና 17 ላይ ኢየሱስ ...
28/08/2026

🙋🙋

ዮሐንስ 14:13-16

"¹³ አብ በወልድ እንዲከብር፣ በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ አደርገዋለሁ፤

¹⁴ ማንኛውንም ነገር በስሜ ብትለምኑኝ፣ እኔ አደርገዋለሁ።

በቁጥር 13 እና 17 ላይ ኢየሱስ እራሱ ልመናችንን እንደሚፈጽም ተናግሮ

በመቀጠል 15 ላይ ፤ ይላል።

“¹⁵ ብትወዱኝ ትእዛዜን ትጠብቃላችሁ። ¹⁶ እኔ አብን እለምናለሁ፤ እርሱም ከእናንተ ጋር ለዘላለም የሚኖር ሌላ አጽናኝ ይሰጣችኋል፤”

1. በዚህ ክፍል መሠረት ?

2. በእናንተ አስተምህሮ ይህንን ክፍል እንዴት እንረዳ? ማለትም በሞዳሊዝም አስተምህሯችሁ መሠረት እንዴት እንረዳው?

3. ጸሎትን የሚመልስ ኢየሱስ (የአብ ስጋ ) ነው ወይስ አብ ነው?
3.1 መልሱ አብ ከሆነ ኢየሱስም ልመናችሁን እመልሳለሁ ብሏልና ሁለቱም ይመልሳሉ ማለት ነው?
3.2. መልሳችሁ ኢየሱስ ከሆነ አብ ከኢየሱስ የተለየ መሆኑን አብም በመመለሱ አታምኑም?

28/08/2026

!!

ብዙዎችን ከኦጄ ኑፋቄ እና መንጠቆ እያስመለጠ ነው!!

እናንተስ ከእግዚአብሔር ጋር አብራችሁ ለመሥራት ዝግጁ ናችሁ?

የትርጉም መርሆዎችን አያውቁም። ልያውቁም አይፈልጉም። እንደተሳሳቱ እንዴት ይነገራቸው?አብ፣ ወልድ እና መንፈስ ቅዱስ አንድ አምላክ ይርዳቸው!!
28/08/2026

የትርጉም መርሆዎችን አያውቁም። ልያውቁም አይፈልጉም።

እንደተሳሳቱ እንዴት ይነገራቸው?

አብ፣ ወልድ እና መንፈስ ቅዱስ አንድ አምላክ ይርዳቸው!!

  ➖➖➖➖➖➖ ፤   እንጂ!🏴‍☠️🏴‍☠️🏴‍☠️🏴‍☠️🏴‍☠️🏴‍☠️🏴‍☠️🏴‍☠️🏴‍☠️🏴‍☠️🏴‍☠️ብዙ ጊዜ የኦጄን አስተምህሮ ስንመረምር፣ ይህኮ በ220 ዓ.ም የተወገዘው የሰባሊዮስ ኑፋቄ ነው...
28/08/2026


➖➖➖➖➖➖

፤ እንጂ!
🏴‍☠️🏴‍☠️🏴‍☠️🏴‍☠️🏴‍☠️🏴‍☠️🏴‍☠️🏴‍☠️🏴‍☠️🏴‍☠️🏴‍☠️

ብዙ ጊዜ የኦጄን አስተምህሮ ስንመረምር፣ ይህኮ በ220 ዓ.ም የተወገዘው የሰባሊዮስ ኑፋቄ ነው ብለን በአንድ ፈርጅ ብቻ እንፈርጀዋለን። እውነታው ግን ኦጄ ውስጥ የሌለ የኑፋቄ ዓይነት የለም።

ትምህርታቸውን በጥልቀት ስንፈትሸው ከሰባሊዮስም አልፎ #አርዮሳዊነትን፣ #ዶሴቲዝምን፣ #ሞንታኒዝምን እና ሌሎችንም በጥንቷ ቤተክርስቲያን በጽኑ የተወገዙ ኑፋቄዎችን አዳቅሎ (ሰብስቦ) የያዘ አደገኛ የዶክትሪን ጥርቅም መሆኑን እንረዳለን።

እስኪ የጥንቷ ቤተክርስቲያን ያወገዘቻቸውን ኦጄዎች ጠርቅመው የያዟቸውን ኑፋቄዎችን አንድ በአንድ እንይ።

1. #ሰባሊዮሳዊነት

የሰባሊዮሳዊነት አስተምህሮ እግዚአብሔር አብ፣ ወልድ እና መንፈስ ቅዱስ የሚባሉ ሦስት ዘላለማዊ አካላት የሉትም፤ ይልቁንም አንድ አካል በተለያዩ ጊዜያት የተጫወታቸው ሦስት ሚናዎች ወይም ጭምብሎች ናቸው ይላል።

ኦጄዎች ይህንኑ ቃል በቃል ይደግሙታል። አብ የአምላክ ስሙ፣ ወልድ ሥጋ የለበሰበት ስሙ፣ መንፈስ ቅዱስ ደግሞ በውስጣችን የሚያድርበት ስሙ ነው ይላሉ። ይህ መሠረታዊው የሰባሊዮስ ኑፋቄ ነው።

2. #ሞንታኒዝም

በ2ኛው ክፍለ ዘመን የተነሳው የሞንታነስ ኑፋቄ፣ መሪዎቹ ራሳቸውን ስተው በማያውቁት ቋንቋ (ልሳን) በመጮህና በመንቀጥቀጥ መናገር፣ እውነተኛው የመንፈስ ቅዱስ መገኘት ማረጋገጫ ይህ ብቻ ነው ብለው በማስተማራቸው በቤተክርስቲያን ተወግዘዋል።

ልክ እንደ ሞንታኒስቶች፣ ኦጄዎችም በመንፈስ ቅዱስ የመሞላት ብቸኛው ማረጋገጫ ልሳን መናገር ነው በማለት ስሜታዊ ጩኸትን ከመጽሐፍ ቅዱሳዊው የመንፈስ ፍሬ በማስበለጥ የጥንቱን ኑፋቄ በድጋሚ ይኖሩታል።

3. - ሥርዓት ያድናል የሚል ኑፋቄ

በሐዋርያት ዘመን የተወገዙት ሐሰተኛ አስተማሪዎች፣ በክርስቶስ ማመን ብቻውን አያድንም፤ የግድ መገረዝ አለባችሁ በማለት መዳንን በጸጋ ብቻ ከመሆን ወደ ሥራ ቀይረውት ነበር።

ኦጄዎች የገላትያን ኑፋቄ በአዲስ መልክ ያመጡታል። ኢየሱስ በመስቀል ላይ በፈጸመው የማዳን ሥራ ማመን ብቻውን አያድንም፤ የግድ በውኃ ካልተጠመቃችሁ አልዳናችሁም በማለት መዳንን ከክርስቶስ ጸጋ ነጥቀው በውኃ ውስጥ በሚደረግ ሥርዓት ላይ ያንጠለጥሉታል። ይህም ጳውሎስ በጽኑ ያወገዘው ሌላ ወንጌል ነው።

4. #አርዮሳዊነት

በ325 ዓ.ም በኒቂያ ጉባኤ የተወገዘው አርዮስ፣ ወልድ (እግዚአብሔር ልጅ) ከዘላለም የነበረ አምላክ አይደለም፤ መጀመሪያ አለው ብሎ ያስተምር ነበር።

ኦጄዎችም ልክ እንደ አርዮሳውያን ኢየሱስ አምላክ ነው ቢሉም፣ እግዚአብሔር ወልድ (ልጅ) ከዘላለም አልነበረም፤ ልጅነት የጀመረው ማርያም ማህጸን ውስጥ ነው ብለው ያስተምራሉ። ይህም ልክ እንደ አርዮስ የወልድን ዘላለማዊ ህልውና ክዶ ፍጡር እና ጀማሪ ወደ መሆን ዝቅ ያደርገዋል።

5. #ዶሴቲዝም
ዶሴቲዝም የክርስቶስ ሰው መሆን፣ መጸለይ እና መከራ መቀበል እውነተኛ አልነበረም፤ ሰው መምሰሉ ምትሐት ወይም ትወና ነው ይላል።

መጽሐፍ ቅዱስ ኢየሱስ ወደ አብ ጸለየ ሲለን፣ ኦጄዎች ግን ልክ እንደ ዶሴቲዝም ሥጋው (ሰውነቱ) በውስጡ ወዳለው መለኮት ነው የጸለየው በማለት እውነተኛውን የክርስቶስን ጸሎት እና አማላጅነት ወደ ትወና (ለእኛ አርዓያ ለመሆን የተደረገ ድራማ ነው ብለው) ይቀይሩታል።

6. #ኔስቶሪያኒዝም
ኔስቶሪያኒዝም የክርስቶስን መለኮት እና ሰውነት ፍጹም በማነጣጠል ሁለት የተለያዩ አካላት ለማድረግ የሚሞክር ኑፋቄ ነው።

#ምስሉ፦ ሁሉንም የኦጄዎችን ኑፋቄ የሚገልጽ የአንድ አምላካቸው ቅርጽ እና አካል በ AI Generate የተደረገ ነው።

Address

African Union
Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when OJ Kapho Dhoosa posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to OJ Kapho Dhoosa:

Shortcuts

Share