Tewodros Techan - ባለ ዐደራ

Tewodros Techan - ባለ ዐደራ Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Tewodros Techan - ባለ ዐደራ, Religious organisation, Addis Ababa.

25/10/2022
ትዕቢት በቁሙ"አልሆን ያለህ እንደሁ መጉላትና መግዘፍ   ከትልቆች መሃል አንዱን መርጠህ ዝለፍ"                                   ያሬድ ጥላሁን                 ...
23/10/2022

ትዕቢት በቁሙ

"አልሆን ያለህ እንደሁ መጉላትና መግዘፍ
ከትልቆች መሃል አንዱን መርጠህ ዝለፍ"
ያሬድ ጥላሁን

ክርስትና ከሚያስተምረን ዋና ነገሮች አንዱ "ትህትና" ነው። በተለይ አገልጋይ የሆነ ሰው የዚህ ባህሪ ባለቤት ለመሆን ሳያሰልስ መትጋት አለበት። በተለይ ደግሞ በአገልግሎታችን የተሳካልን ሲመስለን ካልተጠነቀቅን አደጋ አለው የትዕቢት መንፈስ በደጅ ነውና። "እኔ የዋህ በልቤም ትሁት ነኝ" ያለው ዝቅ ብሎ የተከታዮቹን እግር ያጠበው የጌቶች ጌታ ኢየሱስ ለማገልገል ተፍ ተፍ የሚሉ ደቀ መዛሙርቱን "የማልጠቅም ባሪያ ነኝ በሉ" ሲል ገና በጠዋቱ ያዘዘውም ለዚህ ነው።

እኔ ትልቅ ነኝ!

እንደምናስታውሰው ከሰሞኑ ወንጌላዊ ያሬድ "የድህነትን አዙሪት ለመስበር ራዕይ ተሰጥቶኛል" "የእግዚአብሔር መንግስት ማዕከላዊ መልዕክትም ድሆች ናቸው" "የዳነ ሰው የሚለካው ለድሆች ባለው ልብ ብቻ ነው" ወዘተ ማለቱን ተከትሎ አንዳንዶቻችን መሳሳቱን የሚገፅ ተቃውሞ አቅርበን ነበር።
ከሰሞኑም በምኩራብ ሾው ላይም ይቀርባል ሲባልም ይህ ወንድማችን በአግባቡ ይቅርታ ይጠይቅና የቃላትም ሆነ የአመለካከት ስህተቱን ያርማል ብለን ጠብቀን ነበረ። ነገር ግን እኔን ታዋቂውን ትልቁንና ግዙፉን ሰው መቃወማችሁ ለመታወቅ ብላችሁ እንጂ ምንም የተሳሳትሁት ነገር የለም ብሎ ለረጅም ዘመን ካገለገለ ሰው የማይጠበቅ "እኔ ትልቅ ነኝ" የሚል ፍፁም ትህትና የጎደለው ቋንቋ ይዞ ብቅ አለ።

ከወሎ አገኘሁት ብሎ ተቃዋሚዎቹን ለመቃወም የተጠቀመበትም ተረት "እኔ ትልቅ ነኝ" እና አትንኩኝ ለማለት የቀረበ መሆኑ ግልጥ ነውና። ይህ ደግሞ ትዕቢት ነው። አንዳንድ ምስኪኖች "ተረት አኮ ነው" ይሉ ይሆናል። ነገር ግን ከተረቱ ጋር አያይዞ የተናገራቸው "የታወቀን ሰው በመቃወም እውቅና ለማግኘት ጥረት ሲደረግ አያለሁ"፣ ይሄ "መንጠልጠል ነው" የሚሉ ቃላቶቹ ጉዳዩ ልማዳዊ ተረት የመተረት ዘዬ ሳይሆን ከማን አለብኝነት የመነጨ እንደሆነ ያሳያል። በአጭሩ የተረቱና የንግግሩ ድምፀት "እኔ ግዙፍ ነኝ" የሚቃወሙኝ እኔ በጣም ታዋቂ ስለሆንኩ እኔን በመቃወም መታወቅ ፈልገው የሚል ነው። ትዕቢት በቁሙ ማለት ይኸው ነው።

ድምፅ ማሰማት!

ቡሽሪ ዘርፎ ከሄደ በኋላ በጉዳዩ ዙሪያ በተዘጋጀ አንድ መድረክ ላይ አስታውሳለሁ ወንጌላዊ ያሬድ በርዕሰ ጉዳዩ ላይ ሃሳብ እየሰጠ በመካከል አንዲት ቃል ተጠቅሞ ነበር "ድምፅ ማሰማት ያስፈልጋል" የሚል ። ስህተትን እያየን ዝም ማለት የለብንም! ማለቱ ነበር በወቅቱ። ዛሬም እኔም ሆንኩ ሌሎች ወገኖች ያንኑ መርህ ነው የተከተልነው "ድምፅ ማሰማት" ስህተትን በተለይ የአደባባይ ስህተትን ሲያዩ ድምፅ ማሰማት።

በበኩሌ ያሬድን የተቃወምሁት "እግዚአብሔር ተናገረኝ" ስላለ አይደለም። እግዚአብሔር የሚናገር አምላክ መሆኑን አምናለሁ። ነገር ግን ያሬድን የተቃወምሁት "የእግዚአብሔር መንግስት ማዕከላዊ መልዕክት ድሆችን መርዳት ነው" "መዳናችን የሚለካው ድሆችን በመርዳታችን ብቻ ነው" ስላለ ነው። ይሄ ስህተት ነው። ሲያልፍም የስህተት ትምህርት ነው። በዚህ ስህተት ላይ ደግሞ ድምፅ ማሰማት ተገቢ ነው። በዚህኛውም ቃለ ምልልሱ ከማድበስበስ እና ከማፈግፈግ ውጪ በጠራ መልኩ እንኳን መሳሳቱን አልገለጠምና።

በጣም ያሳዝናል!

"ሰው መንፈስ ነው" ብለው የሚያስተምሩትንም ከስህተት መምህርነት መፈረጅ ከብዶት ሲንገዳገድ ማየት ያሳዝናል። የስህተት መምህራን ሳይሆኑ "ሲሰሩ የሚሳሳቱ" ብለን እንድንቀበላቸውም ያግባባናል። ግን ለመሆኑ ማን ነው "ሲሰራ የተሳሳተው" ጃፒ ይሆን ተዘራ ይሆን ዘላለም ወይስ ሐይሉ እና መሰሎቻቸው? የትኛው ነው እነጩፋንና መሰሎቹን ይሆን?..... በጣም ያሳዝናል።

ሌላው ደግሞ የሰውን ማንነት ሶስት ቦታ ነጣጥሎ (ገነጣጥሎ) በማቅረብ ባልተገባ ስነ አፈተታት ያልበሰሉትን ማሳሳቱ ሳያንስ "የዳነው መንፈሳችን ነው" ብሎ የአንዲት ጥቅስ እንኳን ድጋፍ የሌለው ትምህርት በማስተላለፉና "ለመንፈሶቹ" ዱላ ማቀበሉ በጣም ያሳዝናል። እንዲህ እያልን ብንቆጥር.....ወደ ኋላም ሄደን ደግሞ የቀድሞ ትምህርቶቹን ብንመረምርና እነ ማይልስና ዎች ማን ኒን እየመዘዝን ብናወጣ ደግሞ ብዙ ጣጣ ልናመጣ ነው። ቢበቃንስ???

ለማንኛውም "ትዕቢት ውድቀትን ትቀድማለች" የሚለውን ቃል ማስታወስ ለሁላችን የጠቅማል። እላለሁ!

ቴዎድሮስ ተጫን

"ዶሚኒየኒዝም - ቀጣዩ የቤተክርስቲያን አደጋ"አጠር ያለች ዶክመንታሪ በቅርብ ቀን
15/08/2022

"ዶሚኒየኒዝም - ቀጣዩ የቤተክርስቲያን አደጋ"

አጠር ያለች ዶክመንታሪ በቅርብ ቀን

Religious organization

የተሰበረ ልብየሳሚ የአደባባይ ንሰሃ እና ይቅርታ እጅግ ልብ የሚነካ እና አስተማሪ ነው። ሰው በዚህ ደረጃ ራሱን ሲያዋርድ እና በተሰበረ ልብ በአምላኩ ፊት ሲቀርብ በጣም ደስ ይላል። እግዚአብ...
25/07/2022

የተሰበረ ልብ

የሳሚ የአደባባይ ንሰሃ እና ይቅርታ እጅግ ልብ የሚነካ እና አስተማሪ ነው። ሰው በዚህ ደረጃ ራሱን ሲያዋርድ እና በተሰበረ ልብ በአምላኩ ፊት ሲቀርብ በጣም ደስ ይላል። እግዚአብሔር ዘመኑን እና ትዳሩን ይባርክለት። የቤተክርስቲያኒቱ መሪዎች እና አገልጋዮችም የወሰዱት አቋም የሚደነቅ ነው።

ይህ ወንድማችን በተሻለ ህይወትና አገልግሎት እንደሚገለጥ ተስፋ አደርጋለሁ።

ቴዎድሮስ ተጫን

ሊታይ የሚገባው
25/07/2022

ሊታይ የሚገባው

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Tewodros Techan - ባለ ዐደራ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share