Z orthodox

09/02/2024
☞ ሳይጠይቁት የሚሰጥ አምላክ አንድ ሰው ሳይጸልይ የእግዚአብሔርን ጸጋ ፤ ኃይል ፤ መንግስት ወይም ጽድቅ እንዴት በተስፋ ሊያገኝ ይችላል ? እንደዚህ ዓይነት ሰው ድኅነቱንስ እንዴት ሊያገኝ ...
24/01/2024

☞ ሳይጠይቁት የሚሰጥ አምላክ

አንድ ሰው ሳይጸልይ የእግዚአብሔርን ጸጋ ፤ ኃይል ፤ መንግስት ወይም ጽድቅ እንዴት በተስፋ ሊያገኝ ይችላል ? እንደዚህ ዓይነት ሰው ድኅነቱንስ እንዴት ሊያገኝ ይችላል ?
" የሰው ልጅ የጠፋውን ሊፈልግና ሊያድን መጥቶአል " [ ሉቃ 19*10] ተብሎ በተጻፈው ቃል መሠረት ድኀነት የተሰጠው ለሁሉም ሰው ነው ። አምላካችን ድኀነትህን አንተ ከምትፈልገው በላይ እርሱ ስለሚፈልገው ሳትጠይቀው ይሰጥሃል ። እርሱ ማንኛውንም ነገር የሚሰጠን ሳንጠይቀው ነው ።
ከእግዚአብሔር የጠየቅነውን ነገር ማግኝታችን አስደሳች ሲሆን ያልጠየቅነውን መቀበላችን ደግሞ የበለጠ አስደሳች ነው ። እግዚአብሔር ለሰው የሚያስፈልገውን የሚያውቀው ከጥልቅ_ፍቅሩና_ከቸር_አባትነቱ የተነሳ ከመሆኑም በላይ ይህንኑ ጥልቅ ፍቅሩን የሚለግሰንም ለጸሎታችን ምላሽ እንዲሆን በማለት አይደለም ።

ወንድሞቼ ይህን እውነታ ደግሞ በብዙ ምሳሌዎች የተደገፈ ነው ። ከእነዚህ ምሳሌዎች መካከል እናንተ እግዚአብሔር ለእናንተ በሚፈጽመው ሥራ ውስጥ ተስፋ እንድታደርጉ ጥቂቶቹን እጠቅስላችኀለሁ ። ገና በስነ ፍጥረት ጊዜ የእግዚአብሔር ባሕርይ የተገለጠው ማንም ሳይጠይቀው በመስጠቱ ነው ። ክፉም ይሁን ደግ ለሁሉም ሰዎች ሕልውናቸውን የሰጠው አሁንም ይህንን እንዲያደርግ ሳይጠይቅ ነው ። እርሱ ይህንን ለመጠየቅ ሕሊና ካልነበረው ነገር ነው ሁሉንም ካለመኖር በማምጣት የፈጠረው ።
እግዚአብሔር በምሳሌውና በአርአያው የፈጠረን ማንም ሳይጠይቀው ነው ። የማይቻለው ተችሎ በአንድ በሆነ አምሳያ እንድንፈጠር መጠየቅ ብንችል እንኳ እርሱ በእርሱ ምሳሌና አርአያ እንድንፈጠር የመውደዱን ያህል እኛ ላንወድ እንችላለን ። እግዚአብሔር ተፈጥሮን ፈጥሮ ካዘጋጀ በኋላ ነው እኛን የፈጠረን ።
አምላካችን ሰማይን እንደ አጎበር ከዘረጋልን ምድርን እንራመድባት ዘንድ ጥርጊያዋን ካስተካከለ በኋላ ነው እኛን የፈጠረን ።
ቅ/ጎርጎርዮስ በቅዳሴው ላይ እንዲህ ብሏል ፦ " አክብረህ ከፈጠርከው ነገር ሁሉ ምንም ያጎደልክብኝ ነገር የለም ። አንተ ባሕርን ጸጥ አድርገህልኛል እንስሳት እንዲለምዱኝ አድርገህልኛል ...

"
እግዚአብሔር ለእኛ ዛፎችንና ፍሬዎቻቸውን ተክሎችንና ዘራቸውን አበቦችንና አዕዋፋትን እንዲሁም ብርሃንንና የሰማያትን ሕግጋት ሳንጠይቀው ፈጥሮ አዘጋጅቷልና ። ይህ ብቻ አይደለም በፍቅሩ እንዲህ ብሎናል ፦ ብዙ ተባዙ ምድርንም ሙሏት ግዟትም ፤ የባሕርን አሶችና የሰማይን ወፎች በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትንም ሁሉ ግዙአቸው ። [ዘፍ 1*28] ። እግዚአብሔር ሔዋንን ለአዳም የፈጠረው ገና ሳይጠይቀው ነው ። እግዚአብሔር አዳም ከሌሎች ፍጥረታት ሁሉ ከእርሱ ጋር የምትነጻጸርለት ረዳት እንደሌለው ስለሚያውቅ ሔዋንን ለእርሱ ፈጠረለት ። ስለዚህ ሰዎች ስለ ተባዙ ምድርንም በመሙላት ማንም ስለዚህ ጉዳይ ሳይጠይቅ በእርሷ ላይ መኖር ጀመሩ ። ይህም የሆነው አፍቃሪ አባትና መልካም እረኛ በሆነው በእግዚአብሔር መንገድ ነው ።
እርሱ ልጆቹ ወይም ወገኖቹ ወይም ፍጥረቱ የሚያስፈልጋቸውን እስኪጠይቁት ድረስ ጠብቆ የሚሰጥ አምላክ አይደለም ። ይልቁንም የሚያስፈልጋቸውን ሁሉ በእርሱ አነሳሽነት ሳይጠይቁት የሚሰጥ አምላክ ነው ። በእርግጥ ሕጻን ልጅ የሚፈልገውን ነገር እንዴት አውቆ ሊጠይቅ ይችላል ? ይሁን እንጂ አባት ለልጁ የሚያስፈልጉትን ነገሮች በሙሉ ሕጻኑ ልጅ ሳይጠይቀው በፊት ይሰጠዋል ።በሰማይ አባታችንና በእኛ መካከል ያለው እንደዚሁ ነው ። እርሱ ምን ጊዜም የምንፈልገውን ስለሚያውቅ ለእያንዳንዱ እና ለሁሉም የሚያስፈልጋቸውን የሚሰጥ ሰውን ሁሉ ወዳጅ ጌታ ነው ። ይህ አምላካችን ሰዎች ለራሳቸው ጥቅም ሆነ ለሌሎች በዙሪያቸው ላሉ ሰዎች ጥቅም ብለው የፈለጉትን ነገር ሁሉ ሳይጠይቁ ይሰጣቸዋል ።
እግዚአብሔር ሕዝቡን የሚጠብቀው ከፍቅሩ የተነሳ እንጂ ማንም ይህንን እንዲያደርግ በጠቆመው መሠረት አይደለም ። ይሁን እንጂ እኛ የሚያስፈልገንን የምንጠይቀው የእግዚአብሔር የልጅነት መንፈስ እንዲሰማንና የምንፈልገውን ስናገኝ ውስጣዊ ደስታ እንዲሰማን ነው ። ይህ ስለሆነም ነው መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለደቀ መዛሙርቱ " እስከ አሁን በስሜ ምንም አልለመናችሁም ፤ ደስታችሁ ፍጹም እንዲሆን ለምኑ ትቀበሉማላችሁ ። [ ዮሐ 16*24] በማለት የተናገራቸው ። በዚህ መሠረት እንድንጠይቅ የሚያደርገን የሚመለስልን መልስ ደስታ ወይም የመግባባታችን ስሜት ነው ። እግዚአብሔር የሚስፈልገንን ነገርሁሉ ባንጠይቀውም እንኳ እርሱ ይሰጠናል ።
አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ

የገና በዓል የማያከብሩትና ዲሞኪራሲ የሚባል ሕግ የማያቁት ሀገራት15 ሲኾኑ አጠቃላይ ከዓለማችን ሀገራት ገና የማያከብሩት 50 ናቸዉ 15ቱ ሀገራት ገናን ሲታከብር ከተገኘ ከእስራት እስከ ሞት...
27/12/2023

የገና በዓል የማያከብሩትና ዲሞኪራሲ የሚባል ሕግ የማያቁት ሀገራት15 ሲኾኑ አጠቃላይ ከዓለማችን ሀገራት ገና የማያከብሩት 50 ናቸዉ 15ቱ ሀገራት ገናን ሲታከብር ከተገኘ ከእስራት እስከ ሞት ይቀጧል ።ሌሎቹ 35ቱ ግን ያንን ያህል አላከረሩም ከታች የተዘረዘሩት ሀገራት ይመልከቱ ።

፩። ቻይና በይፋ ሀይማኖት የሌላት ሀገር ስትሆን የገናን በዓል ማክበርም ህገወጥነት ነው ተብሏል። የገና ቀንም እንደሌሎች ቀናት የሥራ ቀን ተብለዉ ይጠራል ይሰራል ።በዓሉን ሲታከብር ከተገኘም ትቀጣለህ ።

፪። አፍጋኒስታን ሌላኛዋ የገናን በዓል የማታከብር ሀገር ስትሆን አብዛኛው የሀገሪቱ ዜጎች ሙስሊሞች መሆናቸው ለበዓሉ አለመከበር ዋነኛው ምክንያት እንደሆነ ተገልጿል።በዓሉን ሲታከብር ከተገኘ የሞት ቅጣት ይጠብቃል ።

፫.,,አፍሪካዊቷ አልጀሪያ ሌላኛዋ የገና በዓል የማይከበርባት ሀገር ስትሆን በተለይም ከቅኝ ግዛት ነጻ ከወጣችበት 1962 ጀምሮ የገናን በዓል አክብራ አታውቅም።አይፈቀድም።

፬።።ኮሞሮስ 98 በመቶ የእስልምና እምነት ተከታዮች ህዝብ ያላት ኮሞሮስ የገናን በዓል የማታከብር ሌላኛዋ የዓለማችን ሀገር ናት።

፭..,,ሊቢያ የገና በዓል የማይከበር ተጨማሪ የአፍሪካ ሀገር ሲትኾን የክርስትና ዕምነት ተከታዮች አለመኖር ደግሞ ለበዓሉ አለመከበር ዋነኛው ምክንያት ነው ተብሏል።

፮።። ሞንጎሊያ እስያዊቷ ሞንጎሊያ የገና በዓል የማይከበርባት ስትሆን የሀገሪቱ ዜጎች የቡድሂስት እምነት ተከታዮች ናቸው ተብሏል። ገናን ምን እንደኾነም አያዉቁም።

፯።ሰሜን ኮሪያ ።ሌላኛዋ የእየሱስ ክርስቶች ልደት ወይም ገና የማይከበርባት ሀገር አመጸኛዋ ሰሜን ኮሪያ ናት። በዚህ ሀገር የገናን በዓል ማክበር ለእስር እና ለሞት እንደሚዳርግ በህግ መደንገጉ ተገልጿል።

፰ ።ፓኪስታን። ሌላኛዋ የዓለማችን ሀገር ስትሆን ዓለም በታህሳስ 25 በየዓመቱ የገናን በዓል ሲያከብር እሷ ግን የፓኪስታን መስራች የሚባሉትን መሀመድ አሊ ጅናህን አስባ ትውላለች።የሞት ቅጣት አለ ።

፲..፤ሳውዲ አረቢያ የገናን በዓል ማክበር የከለከለች ሀገር ሲትሆን በዓሉን የሚያመለክት የገና ዛፍ እና ሌሎች መሰል ድርጊቶችን ማከናወን ለቅጣት ይዳርጋል ተብሏል።ተጨማሪም በሞት ቅጣት ትቀጣለች ።

፲፩ ። ሶማሊያ ከፈረንጆቹ 2009 ጀምሮ የገና በዓል በሀገሯ እንዳይከበር በህግ ያገደች አፍሪካዊት ሀገር እንደሆነች ተገልጿል። ማነሸዋ የቅዱሳን ሀገር የምትባለዉ ሶማሊያ ገናን ማክበር ወንጀል መኾኑን ገልጻለች ።

፲፪.,,ታጃኪስታን፣ የእስርና የብር ቅጣት
፲፫..ቱኒዝያ፣ ከሀገር ማባረርና የብር ቅጣት ፲፬
ኡዝበኪስታንየሞት ቅጣት ፲፭ የመን የሞት እንዚህ ሀገራት የገና በዓል በሀገራቸው እንዳይከበር ህግ የደነገጉና የገና በዓል ሲያከብር የተገኘ ግለሰብ ከእስራት እስከ ሞት ይቀጣል ፣።ዲሞኪራሲ አፈር ደቼ ያበሏት ሀገራት ይባላሉ ።ክርስትና አኹንም ስደት ላይ ነው 😔 ምንጭ አል-ዐይንና ሊሲ ዳንሲ ተንሽ ማብራሪያ ተጨምረዉበት።
Z orthodox

የበጎቹ ጠባቂ ደጉ አባት በጦርነት ወቅት እንኳን ለሕዝቡ ያደረጉት ነገር መቸም አንረሳም ፣
20/11/2023

የበጎቹ ጠባቂ ደጉ አባት በጦርነት ወቅት እንኳን ለሕዝቡ ያደረጉት ነገር መቸም አንረሳም ፣

ለመዳን ምን ያስፈልገናል? በጽሞና ያንብቡ ፣✍ 1.እምነትና ሥራ በምድር ላይ ጊዜ ላለው ሰው ለመዳን እኩል ያስፈልጉታል፤ ምክንያቱም መዳናችን በእርግጠኝነት እጃችን የሚገባው በመጨረሻው የፍር...
20/11/2023

ለመዳን ምን ያስፈልገናል? በጽሞና ያንብቡ ፣

✍ 1.እምነትና ሥራ በምድር ላይ ጊዜ ላለው ሰው ለመዳን እኩል ያስፈልጉታል፤ ምክንያቱም መዳናችን በእርግጠኝነት እጃችን የሚገባው በመጨረሻው የፍርድ ቀን መሆኑን መረዳት ( 1ጴጥ1፡5)
✍ 2. መዳናችን ዕለት ዕለት በጎ ፈቃዱን በመፈለግና በማድረግ የምንፈጽመው (ፊሊጵ . 2፡ 12 -15) ፣ በመከራ በመጽናት በቆምን ቁጥር የምንቀበለው መሆኑን መረዳት ( 1ጴጥ. 1፡ 7 -9) ፣
✍ 3. እምነት ያለ ሥራ እንደ ሰርዴስ ቤተክርስቲያን ሥም ያለን ሙቶች እንደሚያደርገን መገንዘብ ( ራዕ . 3፡1-2) ፣
✍ 4. የመጨረሻቀው ፍርድ ለአማኞች በሥራ ( 1ጴጥ. 1፡ 17 ፤ 2ቆሮ . 5፡ 10 ፤ ማቴ. 25፡ 31- 46፤ ዮሐ 5፡ 28 -29) ላላመኑ ደግሞ በእምነትና በሥራ ማለትም የሕይወት መጽሐፍንና የሥራ መጽሐፍትን በመግለጥ እንደሚሆን መረዳት( ራዕ . 20 ፡11-15 ) ፣ አንደበትና ሀሳብ ለገሀነም ሊዳረጉ እንደሚችሉ መገንዘብ ይኖርብናል( ማቴ. 12፡ 35- 37፤ ያዕ . 3፡ 6፤ ሮሜ. 2፡ 1-6)፡፡
✍ 5.ስለዚህ፣ ሕይወትን
የሚወድ፣ መልካም ቀኖችን ሊያይ የሚፈልግ፣ ምላሱን ከክፉ፣ ከንፈሮቹንም ተንኮል ከመናገር ይከልክል፡፡ ከክፉ ይራቅ፤ መልካምንም ያድርግ፤ ሰላምን ይፈልግ ይከተላትም ( 1ጴጥ 3፡10-11) ፡፡ ፍርድ ከእግዚአብሔር ቤት የሚጀምርበት ጊዜ ደርሶአልና፡፡ እንግዲህ ፍርድ የሚጀምረው በእኛ ከሆነ ለእግዚአብሔር ወንጌል የማይታዘዙ ሰዎች መጨረሻቸው ምን ይሆን ? እንግዲህ፣ ጻድቅ የሚድነው በጭንቅ ከሆነ፣ ዐመፀኛውና ኃጢአተኛው እንዴት ሊሆን ይሆን ? ስለዚህ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ መከራ የሚቀበሉ ነፍሳቸውን ለታነመነ ፈጣሪ ዐደራ ሰጥተው መልካም ማድረጋቸውን ይቀጥላሉ ( 1ጴጥ 4፡ 17 -19 ) ፡፡
✍ 6. እምነትነታችን መታተም አለበት ይህን ማለት እምታችንን የምናረጋግጥባቸውና ከእግዚአብሔር ጋር አንድ
የሚያደርገንን ነገር መፈጸም አለብን፡ እነዚህም  ጥመቀትና መንፈስ ቅዱስን መቀበል ናቸው ፤ከውሃና ከመንፈስ መወለድ ማለት ነው ። ዮሐ 3፤5 እውነት እውነት እልሃለሁ፥ ሰው ከውኃና
ከመንፈስ ካልተወለደ በቀር ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ሊገባ
አይችልም።  ቲቶ 3፡5 እንደ ምሕረቱ መጠን ለአዲስ ልደት
በሚሆነው መታጠብና በመንፈስ ቅዱስ በመታደስ አዳነን  ማር 16፤16 ያመነ የተጠመቀ ይድናል ያላመነ ግን ይፈረድበታል እንዳለ ያለ ጥምቀት ድህነት የለም።  በቤተ ክርስቲያን
መንፈስ ቅዱስን መቀበል በሜሮን ይፈጸማል። ሜሮን ቃሉ የግሪክ ሲሆን ትርጉሙም ቅብእ ማለት ነው።  ቤተ ክርስቲያን መንፈስ ቅዱስን በሜሮን አማካኝነት መስጠት የጀመረችው
በሐዋርያት ዘመን ነው። 1ኛ ዮሐ 2፤20 እናንተም ከቅዱሱ ቅባት ተቀብላችኋል፥ ሁሉንም ታውቃላችሁ። እንዲሁም 1ኛ
2፤27 እናንተስ ከእርሱ የተቀበላችሁት ቅባት በእናንተ ይኖራል፥ ማንም ሊያስተምራችሁ አያስፈልጋችሁም፤ ነገር ግን የእርሱ ቅባት ስለ ሁሉ እንደሚያስተምራችሁ፥ እውነተኛም እንደ ሆነ ውሸትም እንዳልሆነ፥ እናንተንም እንዳስተማራችሁ፥ በእርሱ ኑሩ።
 ዘጸ 30፡22-25 ምስጢረ ሜሮን ምሳሌው በብሉይ ኪዳን
ነበረ፡ የብሉይ ኪዳን ንዋያተ ቅዱሳት ይቀቡ ነበር
✍ 7. ከክርስቶስ ጋር አንድ መሆን አለብን፡ ሰው ለመዳን ከክርስቶስ ጋር ህብረት እንዲኖረው ያስፈልጋል። በዮሐ 6፤56 ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ በእኔ ይኖራል እኔም በእርሱ እኖራለሁ። ዮሐ 6፡54 ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ የዘላለም ሕይወት አለው፥
✍ 8. ላለመሰናከል፣ ፍሬ ቢስ እንዳንሆን፣ መመረጣችንን እና መጠራታችንን በማጽናት በሙላት ወደ መንግሥቱ ለመግባት ከፈለግን ትጋትን፣ በጎነትን ፣ ዕውቀትን፣ ራስን መግዛትን፣
መጽናትን ፣ እውነተኛ መንፈሳዊነትን፣ ወንድማዊ መተሳሰብን እና ፍቅርን በእምነታችን ላይ መጨመር ግድ የሚል መሆኑን መረዳት ይገባል ( 2ጴጥ. 1፡ 511 ) ፡፡

👉 ማብራሪያ:-ቅዱስ ጳውሎስ ‹‹ጸጋው በእምነት አድኖአችኋልና ይህም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው እንጂ ከእናንተ አይደለም ማንም እንዳይመካ ከስራ አይደለም ›› ኤፌ2፡8 ይህን ማለቱ በቸርነቱ በእምነት ድነናል ፡፡ያዳነንም እግዚአብሔር በቸርነቱ ነው ፡፡ይህ
ድኅነት ለሰዎች ሁሉ በመስቀል ላይ የተፈፀመው በእግዚአብሔር
ቸርነት እንጂ በማንም ስራ አለመሆኑን ይገልጻል ኤፌ 2፡ 4፤ሮሜ4፡4-5 ይህንንም ጸጋ ቸል ልንለው አይገባም ይሁ4 በዚህ በቅዱስ ጳውሎስ መልእክት ክፍል ውስጥ ሰው የዳነው
በራሱ ስራ ሳይሆን በእግዚአብሔር ስጦታ /ጸጋ/እና ቸርነት በኢየሱስ ክርስቶስ በደሙ ቤዛነት ነው ፡፡ይህ ማለት ግን ለመዳን ስራ አያስፈልግም ማለት ሳይሆን አዳም ካመጣብን በደል እና ኃጢአትየምንድነው ነጻ የምንወጣው በስራችን አይደለም ይህም በእምነት መዳንን የሚያሳይ ሲሆን ‹‹በእምነት
ብቻ መዳን›› ከሚለው ሀሳብ እና አስተምህሮ ይለያል፡፡ አንድ ሰው በክርስቶስ ኢየሱስ አምኖ እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ከሰጠው የማዳን ጸጋ በምስጥራቱ አማካኝነት/በምስጢረ ቁርባን እና በምስጢረ ሜሮን እንዲሁም በምስጢረ ጥምቀት/
ይደርሰዋል ይህም ለመዳን የሚያደርገውን ጉዞ ጸጋው ያግዘዋል
ለመዳናችን ከእግዚአብሔር የሚጠበቀው ነገር ሁሉ የተፈጸመ
ሲሆን ከእኛ የሚጠበቅ ነገር እንዳለ ሳያል ፡፡ ማቴ 25:14-46 በዚህ ምዕራፍ ክርስቶስ በ 2 ምሳሌዎች ለሚያምን ሰው መዳን በስራ እንደሆነ ያስረዳበት አንቀጽ ነው!
እነዚህም ምሳሌዎች
✍ 1ኛ)ለመዳን በዚህ ምድር ምን ማድረግ እንዳለበን በ3ቱ መክሊት ተቀባይ አገልጋዮች ሲናገር (25:14-30)...
✍ 2ኛ)ጌታ በሰማይ ምን ብሎ እንደሚጠይቀንና መንግስቱን ለመውረስ ምን እንደሚጠበቅብን ይናገራል
(25:31-46):: ብዙ ሰዎች እንዴት ነው የዳነው? እና እንዴት ነው የምንድነው?የሚሉትን ጥያቄዎች ባለመረዳት የአንዱ መልስ ከሌላው ጋር ሲደባልቁ እናያለን! ከዚህ አልፈውም መዳን በእምነት ብቻ ነው;፣ ሰው በስራ አይድንም በማለት የሚባክኑም
አልጠፉምና እውነቱን እንገልጥ ዘንድ ወደድን!
1)እንዴት ነው የዳነው? ይሄ ጥያቄ ክርስቶስ ከሰማያት ወርዶ እንዴት እንዳዳነን የሚያጠይቅ ነው:: ክርስቶስ ወደኛ የመጣው እኛ ወደርሱ መሄድ ስላቃተን ነው! ሊያድነን የመጣው በራሳችን መዳን ስላልቻልን ነው! ስለዚህም እንደ ጸጋው ስጦታ አዳነን! ያዳነውም በርሱ ያምኑ የነበሩትን 120 ሰዎች ብቻ አልነበረም! ዓለሙን ሁሉ እንጂ! ...

👉 ታድያ ከምን አዳነን?
✍ 1)ከአዳም መርገም
✍ 2)ከዲያብሎስ ባርነት
✍ 3)የተዘጋችውን ገነት በመክፈት

👉 .... አሁን ክርስቲያን ቢሆን አሕዛብ ጥንተ አብሶ ይዞ የሚወለድ የለም! የዳንነው በእምነታችን አይደለም! እንዲያ ቢሆንስ ኖሮ የእምነት አባታችን አብርሃም በዳነ ነበር! በምግባራችንም አይደለም! ነቢያት ሁሉ መዳን ይችሉ ነበረና! ሁሉም እምነታቸውና ምግባራቸው ከንቱ ሆነ! ያድናቸውም ዘንድ ልዑል ክንዱን ላከ! ስለዚህም የዳንነው በጸጋው ብቻ ነው!! በቸርነቱ ብቻ!! ግን አሁን ድነናል በማለት መቀመጥ አለብን? አይደለም!
የሞተልንን ጌታ በማመን፣ ያደረገልንም ውለታ እያሰብን፣ በእምነት ተመስርተን በምግባርም ጸንተን ፊልጵ 2:12 ....
ታድያ አሁን በክርስቶስ ጸጋ ከዳንን አሁን ለመዳን ምን እናድርግ?...

👉 2)እንዴት ነው የምንድነው?... ይህ፣ አሁን ሁላችንም መጠየቅ ያለብን ጥያቄ ነው! ለመዳን ከኛ ምን ይጠበቃል? ምን ብናደርግስ ነው መንግስቱን የምንወርሰው? የመጽሐፍቅዱስ ዓላማም የዚህን ጥያቄ መልስ ማብራራት ነው! ሰው ለመዳን ወይም መንግስቱን ለመውረስ 2 ነገሮች
ያስፈልጉታል!
1)ማመን:- ይሄም ኢየሱስ አምላክ እንደሆነ፣ ስለ ዓለም ኃጢአት እንደሞተና እንደተነሳ፣ አሁንም በመንበሩ
ተቀምጦ እንደሚፈርድና ሊያድነንም የታመነ እንደሆነ አምኖ መቀበል ማለት ነው! 1ዮሐ5:12 በክርስቶስ ያላመነ ሁሉ አሁን ተፈርዶበታል! ይፈረድበታልም!.

👉 2)መልካም ምግባር:-የሚያምን
ሰው የሚያምነውን በስራ እስካልገለጠ ድረስ እምነቱ የሞተ ነው! (ያዕ2:17)... መልካም ስራ የማያደርጉ ሰዎች ደግሞ
የእግዚአብሔር መንግስት አይወርሱም (ገላ5:21) ወዳጄ ሆይ በጎና ታማኝ አገልጋይ ተብሎ የተሸለመው በእምነቱ ነው ወይስ በምግባሩ? የዳነውስ ስላመነ ነው ወይስ ስለታመነ? በጥቂቱ
ታምነሃል በብዙ እሾምሃለሁ የተባለ አይደለምን? (ማቴ25:23)
ደግሞስ ክፉና ሃሰተኛ ባርያ ተብሎ ወደ እሳት(ሲኦል) የተጣለው ሰው እምነት ስለጎደለው ነው ወይስ ምግባር
ስላልነበረው?....

👉 ጌታ በሰማይ ምን ብሎ እንደሚጠይቅህ ታውቃለህን? በእኔ ስላመንክ ደስ ይበልህ ይለሃል? ወይስ
ምግባር ስላለህ ደስ ይበልህ የሚልህ ይመስለሃል? መንግስቱን የሚወርሱትስ ሰዎች እናንተ የአባቴ ቡሩካን፥ ኑ የተዘጋጀላችሁን መንግሥት ውረሱ ተርቤ አብልታችሁኛልና፥ ተጠምቼ
አጠጥታችሁኛልና... የሚላቸው አይደለምን? ወደ እሳቱ የሚጣሉት ሰውችን ወደ ዘላለም እሳት ከእኔ ሂዱ ተርቤ አላበላችሁኝምና፥ ተጠምቼ አላጠጣችሁኝምና... አላልቸውምን?
ማቴ 25 :31.... በዚህም እምነት ያላቸው ክርስቲያኖች በስራ
እንደሚድኑ አረጋገጠ!
ይቆየን
ምንጭ ዲ/ን ሸዋፈራ አለነ ከ6ዓመት በፊት የተጻፈ።

👉 በዘፈን የደነቆረን ጆሮ መዝሙር እንዲሰማ አድርጉት፤👉ሴትን በመመኘት የታወረውን ዐይን ፈጣሪውን እንዲያይ አዲርጉት፤👉 በስርቆት የሰለለ እጅ በምጽዋት እንዲዘረጋ አድርጉት፤👉 ወደ ኃጢዓት ቤ...
19/11/2023

👉 በዘፈን የደነቆረን ጆሮ መዝሙር እንዲሰማ አድርጉት፤
👉ሴትን በመመኘት የታወረውን ዐይን ፈጣሪውን እንዲያይ አዲርጉት፤
👉 በስርቆት የሰለለ እጅ በምጽዋት እንዲዘረጋ አድርጉት፤
👉 ወደ ኃጢዓት ቤት በመሄድ ሽባ የሆነውን እግር ወደ እግዚአብሔር ቤት እንዲሮጥ አዲርጉት፤
👉 ሐሜትን በማውራት ዲዳ የሆነውን ከንፋር መልካም ንግግርን እንዲናገር አድርጉት፤
ከታዓምራት ኹሉ የበለጠ ተዓምር ይህ ነው።
✍ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ✍
መልካም ዕለተ ሰንበት

እርሱ ሰላማችን ከኛጋር ነው ✝️✝️✝️
18/11/2023

እርሱ ሰላማችን ከኛጋር ነው ✝️✝️✝️

18/11/2023

ቅዱስ ጳውሎስ የቤተ ክርስቲያን ብርሃን ፣ የክርስቶስ ምርጥ ዕቃ ፣ የመናንያን አርኣያ ፣ የሰባኪያን መምህር ፣ የአገልጋዮች ሁሉ አርማ ነው:: ከመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ብዙ መጻሕፍትን የጻፈውን ይህንን ሐዋርያ ማወቅ ሐዲስ ኪዳንን ለማወቅ እጅግ ወሳኝ የሆነ ቅድመ ሁኔታ ነው::

የሮሜ መልእክትን በሳምንት ሦስት ጊዜ ደጋግሞ ያነብብ የነበረው ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅን ጨምሮ ለብዙ ሊቃውንት ቅዱስ ጳውሎስ ክርስትናን የተመለከቱበት መነፅራቸው ነው::

የቅዱስ ጳውሎስ ክብር በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ከፍ ብሎ የሚታየው በቅዳሴዋ ላይ በሠጠችው ሥፍራ ነው:: የቅዳሴውን ሁለተኛ ምዕራፍ የትምህርት ክፍልን (የንዑሰ ክርስቲያን ቅዳሴን) በሐዋርያው የግዝት ቃል የምትጀምረው ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን በቅዳሴ ላይ ከሚነበቡ መልእክታትና ወንጌላት በተለየ ዘወትር በቋሚነት የምታነበው የቅዱስ ጳውሎስን መልእክታት ነው::

በቅዳሴ ላይ ወንጌላትም ሆነ መልእክታት ተነበው ሲያበቁ የሚዜመው መርገፍ ጸሐፊያኑን የሚመለከት አይደለም:: የቅዱስ ጳውሎስ መልእክት ከተነበበ በኋላ ግን የሚዜመው ከሌሎች መልእክታት በተለየ በቀጥታ ቅዱስ ጳውሎስ በማወደስና በመማጸን ላይ ያተኮረ "ቅዱስ ሐዋርያ ጳውሎስ መልእክቱ ያማረ ድውያንን የሚፈውስ ነው:: አክሊልን የተቀበልህ ሆይ በምሕረቱና በቸርነቱ ነፍሳችንን ያድን ዘንድ ፈጽመህ ለምልን" የሚል ምስጋና ነው::

የቅዱስ ጳውሎስን መልእክታት ለብቻቸው ትርጓሜ ሠርታ በምታስተምረው ቤተ ክርስቲያናችን መልእክታቱን ከሚተረጉሙ ሥራዎች ባሻገር ለብቻው የቅዱስ ጳውሎስን ሕይወትና አገልግሎት በተመለከተ የተሠሩ ሥራዎች ላይ ከፍተኝ እጥረት ይስተዋላል::
ብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደ ሥላሴ የሠሩት "ነቅዕ ንጹሕ | ጥሩ ምንጭ" የተሰኘው በምርምር የተሠራ የዜና ሐዋርያት መጽሐፍ እስከ አሁንም ድረስ በቅዱስ ጳውሎስ ሕይወት ዙሪያ የተሠራው ትልቁ ማመሳከሪያ ነው::

እልፍ መጻሕፍት ሊጻፉበት የሚገባውና የሚችለውን ይህንን ሐዋርያ ለማውሳትና ሕይወቱን ለመተንተን ግን ገና ብዙ ብዕሮች ሊቀሰሩ እንደሚገባም የታመነ ነው::

መልአከ ሰላም ቀሲስ ያሬድ ገብረ መድኅን በሐመርና ስምዐ ጽድቅ መጽሔት ላይ በጻፉባቸው በርካታ ርእሰ ጉዳዮች እንዲሁም ኆኅተ ሰማይን በመሳሰሉ መጻሕፍቶቻቸው የቤተ ክርስቲያኒቱ ዘመነኛ የአማርኛ ሥነ ጽሑፍ ታሪክ ላይ አሻራቸውን ከተዉ ቀደምት ጸሐፍት መካከል አንዱ ናቸው:: በትንታግ አንደበታቸው በሰበኳቸው ድንቅ ትምህርቶቻቸውና "ስምሽን ጠርቼ መቼ አፍራለሁ?"ን በመሳሰሉ ውብ የዝማሬ ግጥሞቻቸው ብዙ የተጠቀምንባቸው መልአከ ሰላም ያሬድ አሁን ደግሞ የቅዱስ ጳውሎስን ሕይወት የሚዳስስ እና ከመጠራቱ እስከ ዕረፍቱ ድረስ ያለውን ሐዋርያዊ ጉዞ የሚያስቃኝ በደንብ የተደከመበት ሥራ ይዘውልን ብቅ ብለዋል:: ቅዱስ ጳውሎስ ስለ ክርስቶስ ይናገር ዘንድ ምርጥ ዕቃ እንደነበረ ይህ ሰፌልያ የተሰኘ መጽሐፍም መጽሐፍ ቅዱስ ጥናታዊ ይዘት ያለው ስለ ጳውሎስ ይናገር ዘንድ የተዘጋጀ ምርጥ ዕቃ ነው::

ሰፌልያ ነገ እሁድ ይመረቃል ። ከ3 pm ጀምሮ በሚኖረው መርሐ ግብር ላይ መሳተፍ ይቻላል ።

👉የምርቃቱ ቦታ፡- የኆኀተ ምስራቅ ኪዳነ ምሕረት ቤተክርስቲያን Maryland ,USA.

👉አድራሻ:- 6509 Riggs Road , Hyattsville , MD , 20782

አበዉ እንዲህ ያስተምራሉ· ‹‹እግዚአብሔር ሆይ አፈርና ትቢያ ሆኜ ሳለ ጻድቅ አድርገው ከሚቆጥሩኝ ሰዎች አድነኝ››አባ እንጦንስ· ‹‹ፍጡራንን መርምሮ ማወቅ ካልተቻልን ሁሉን የፈጠረ እርሱን ...
18/11/2023

አበዉ እንዲህ ያስተምራሉ

· ‹‹እግዚአብሔር ሆይ አፈርና ትቢያ ሆኜ ሳለ ጻድቅ አድርገው ከሚቆጥሩኝ ሰዎች አድነኝ››
አባ እንጦንስ
· ‹‹ፍጡራንን መርምሮ ማወቅ ካልተቻልን ሁሉን የፈጠረ እርሱን መርምሮ ማወቅ
እንደምን ይቻልናል››
ቅዱስ አትናቴዎስ
· ‹‹ወርቅ በእሳት እንደሚፈተን ሁሉ የክርስቶስንም ፀጋና ክብር ሳይፈተኑ ማግኘት
አይቻልም የዚህ ዓለም ፈተናና እሳት ቶሎ ያልፋል ይጠፋል ኃጢያተኞች የሚገቡበት
የገሀነም እሳት ግን ለዘላለም እንደ ነደደ ይኖራል››
ቅዱስ ሚናስ
· ‹‹በማንም ላይ ክፈትን አትስሩ አትፍርዱ ይህንን ከጠበቃችሁ ርስቱን ትወርሳላችሁና››
ታላቁ አባ መቃርስ
· ‹‹ብዙ ጊዜ ብዙ እናገራለሁ በመናገሬም አዝናልሁ በዝምታዬ ግን ያዘንኩበት ጊዜ
የለም››
ቅዱስ አርሳንዮስ
· ‹‹ቤተክርስትያን መጠጊያችን ነች ቤተክርስትያን የኖኅ መርክብ ነች በውስጧ
እንጠለላልን ከውጭዋ ግን ማዕበልና ቀላያት ተከፍተዋል››
ቅዱስ እንድርያስ
· ‹‹ልባችንን ጠፊና በስባሽ ከኾነው ከምድራዊው ምኞት አርቀን ከበደል በንስሐ ነጹሕ
ካደረግነው በጸጋ መንፈስቅዱስ የተሞላን እንሆናለን››
አባ አብርሃም መፍቀሬ ነዳያን
· ‹‹ስጋዊ ፍላጎቶችን ማሸነፍ ለአክሊለ ህይወት የሚያበቃ ሰማዕትነት ነው››
ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ
· ‹‹የቤተክርስቲያን ህይወት በመስቀል ላይ ስለሆነ ፈተና ይበዛበታል ስለዚህ ከግል
ህይወታችሁ ይልቅ የቤተክርስቲያናችሁን አቋም አጠንክሩ››
ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ
· ‹‹ከመኝታህ በፊት የምታደርገውን ፀሎት ትተህ እንድትተኛ መንፈስህ ሲገፋፋህ እሺ
ብለህ አትቀበለው፡፡ እንዲያውም መዝሙረ ዳዊትን ጨምርና ሌሊቱን በሙሉ ስትፀልይ
እደር››
ቅዱስ ይስሀቅ ሶርያዊ
· ‹‹ኃጥያታችንን እኛ እያሰብን የምንፀፀት ከሆነ እግዚአብሔር ይረሳልናል ኃጥያታችንን እኛ
እረስትን የምንፅናና ከሆነ እግዚአብሔር ያስብብናል››
ቅዱስ እንጦስ
o ለተወሰን ጊዜ ለሀይማኖት መከራከር፤ጠበቃ መሆን፤መዋጋት ብሎም መሞት
አይከፋም ሁልጊዜ ለሀይማኖት መኖር ግን ከሁሉ የበለጠ መስዋእትና ክብር ያለው
ህይወት ነው፡፡
o የረብዑ ምግብ ለሀሙስ የአርብ ምግብ ለቅዳሜ ይጠቅማል ነገር ግን የማክሰኞ
ምግብ ለረብዑ አይጠቅምም የሀሙስ ምግብ ለአርብ አይሆንም የነፍስና የስጋ ነገርም
እዲሁ ነው፡፡
o የነፍሳችን ነገር ትተን የስጋችንን ብቻ የምናደልብ ከሆነ ነፍስን በስጋ መቃብር
እየቀበርናት መሆኑን አንርሳ
o አንድ በርሜል ወተት በአንድ ጠብታ ኮምጣጤ የበጣጠሳል የብዙ ጊዜ ተጋድሎንም
ጠብታ የሀጢያት ኮምጣጤ ያበላሸዋል
o ራስህን በሀሰት አትውቀስ፡፡ራስህ መክሰስ ትህትና አይደለም፡፡ ታላቅ ትህትና ሰዎች
ሲወቅሱህ መታገስ ነው
o ትዕቢት ሰይጣን ያለመው ጦር ነው
o ትህትና ህፀፅን የምታስታውቅ መስታወት ናት
o ክርስትና ማለት የሰውን ሸክም መሸከምና እስከሞት ድረስ መፅናት ማለት ነው
o በባልንጀራው ላይ ክፋትን የሚያስብ ሰው ያችው የሚያስባት ክፋት ራሱን ትጎዳዋለች፡፡
በየትና ምን ጊዜ እደምትጥለው ግን አያውቅም
o ስንፍናውን ወደጥበብ፤አላዋቂነቱን ወደእውቀት ፤መጥፎ ጠባዩን ወደበጎነት የሚመልስ
ሰው ብርቱ ነው
o ፀሎት ገንዘብን ሊያመጣ ይችላል፡፡ ገንዘብ ግን ፀሎትን አያመጣም፡፡

Address

Kera
Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Z orthodox posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to Z orthodox:

Share