28/06/2023
፦
✔️እኔ፦ "... ሰላም ነዎት ? አልኳቸው!
✔️እሳቸውም፦ ጌታ ይመስገን ምን አሳጣኝ! አሉኝ🤔
፦ግን ኮ🤔
✔እግራቸው ቁስል በቁስል ነው
✔ተርበዋል
✔ጎዳና ላይ ነው ውሎ አዳራቸው
በዚህ ሁኔታ ላይ እያሉ ማመስገንና በኩራት ምን አሳጣኝ ያሉት ነገር ደነቀኝ! ለካስ ምን አሳጣኝ! ያሉት የዚህን ዓለም ነገር አልነበረም!🙏
መጠየቅ ቀጠልኩ..
✔️አባባ ምሳ በሉ እንዴ? አልኳቸው
✔️እሳቸውም፦ መጽሐፉን እያነበቡ ቀና'ም ሳይሉ አይ ልጄ ከዚህ የሚበልጥ ምግብ አለ እንዴ? አሉኝ
✔️እኔም፦ አዎ! እሱማ ልክ ኖት ግን ለማንበብ የስጋ ድካም እንዳይዞት ለብርታት ያህል...
✔️እሳቸውም፦እሺ የስጋማ ከሆነ አላገኘውም ለመብላት ገንዘብም የለኝም አሉ
✔️እሺ አልኩና ተረባርበው የአቅሜን ያህል አደረኩ አጠገባቸው ተቀመጥኩ ምሳዬን ከእሳቸው ጋር በላሁ ከመጽሐፍ ቅዱስ አንድ ክፍል አነበቡልኝ "ኢሳ 62፥1'ን
ከዚያም ህይወታቸውን ማጫወት ጀመሩ.....
✔️መጠየቅ አይሰለቸኝ፦አባባ ግን እግሮች ቆስሎ እያሉ እንደት በዚህ ሁኔታ ተንበረከኩ በዛ ላይ ተንበርክኮ ያሉት በድንጋይ ላይ ነው? አልኩዋቸው
✔️እሳቸውም፦ቀልድ በሚመስል ሳቅ ከሳቁ ቦኃላ ልጄ ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቃየሁ ለእኔ ለከንቱ አይደለም! የእኔ መንበርከክ ያንስበታል እንጂ አይበዛም
✔ለካ ስንነካ የሰማዩ ምስጥር፣ኢየሱስ ለእኛ የሰራው ሲገባን ያለን ሁኔታን ያስረሳል፤ የክርስቶስ ስራ ከሁኔታዎች በላይ እንደሆነ እንረዳለን።
✔️በጥያቄ ተወጠርኩ ውስጠ ጥያቄ በጥያቄ ሆነ
1.
2. /በመንገድ ዳር ናቸው
3.
4. ተንበርከኩ
እኔስ?🤔 ማለት ጀመርኩ..
ሰው እንዲህ ተጨንቆ እያለ ሲያመሰግን፣ ስፀልይ መጽሐፍ ቅዱስን ሳይሰላች ሲያነብ!
እኔስ?🤔
Via Aroŋ Demĩse
እግዚአብሔር ቢፈቅድ ብንኖር ቢያንስ መጠለያ የሚያገኙበትን ሁኔታ እናመቻቻለን።"
እስተማሪ ሆኖ ካገኙት ላይክ እና ሼር ያድርጉት!