10/03/2022
በመከር የእግዚአብሔር ቤተክርስቲያን -ኢትዮጵያ
የካ አጥቢያ
ረቡዕ የካቲት 30 ቀን 2014 ዓ/ም
ክፍለ ምንባብ:- (1ኛ ቆሮንቶስ 1፡4-9)
በወ/ም ኢዩኤል ሰይድ
ጳውሎስ ስለ ቆሮንቶስ ቤ/ክ ሁል ጊዜ ጌታን ያመሰግናል።ለመሆኑ ይህቺ ቤ/ክ ጳውሎስ በጌታ ፊት ቀርቦ እንዲያመሰግን የሚያደርግ ምን መልካም ነገር አላት? ለምስጋና የሚሆን ነገር ይኖራት ይሆን?
ምንም እንኳን ቤተ ክርስቲያኒቱ ብዙ የሚያስነቅፉ ነገሮች ቢኖሩባትም ጳውሎስ ግን ጌታን በእነርሱ ምክንያት እንዲያመሰግን የሚያነሳሳውን ምክንያት በእነዚህ ክፍሎች ያነሳል።
ስለእነርሱ ጌታ በምን ምክንያት ያመሰግናል?
👉 በመካከላቸው በተገለጠው በፀጋ ስጦታ ምክንያት። ጳውሎስ በቤተ ክርስቲያኒቱ ውስጥ የፀጋ ስጦታ አጠቃቀም ችግር እንዳለባቸው ቢያውቅም ስለተሰጣቸው የፀጋ ስጦታ ግን ጌታን ያመሰግናል።
እነዚህ መንፈሳዊ ስጦታዎች፦
1. ክርስቶስ ኢየሱስን በማመን የሚሰጡ ናቸው (1:4-6)
* ይህ የጸጋ ስጦታ የተሰጣቸው ከሌሎች የተለዩ ስለሆኑ ሳይሆን በክርስቶስ በማመናቸው ምክንያት የተሰጣቸው ነው።"በእርሱ" ባለጠጋ ተደርገዋል።
2. የኢየሱስ ክርስቶስን መገለጥ እየተጠባበቅን ስንኖር ሳይሰጠን የሚቀር አንድም መንፈሳዊ ስጦታ የለም። /1:7/
"ማንኛውም መንፈሳዊ ስጦታ አይጎድልባችሁም"
"የክርስቶስን መገለጥ ስትጠባበቁ ሳይሰጣችሁ የሚቀር አንድም መንፈሳዊ ስጦታ የለም"
👉 የትኛዋም ቤ/ክ የፀጋን ስጦታን መጠባበቅ የለባትም።የፀጋን ስጦታ ልንጠባበቀው የሚገባ ጉዳይም አይደለም።ይልቁንም ቤ/ክ ልትጠባበቀው የሚገባ ጉዳይ አለ።እርሱም፦ የጌታ የኢየሱስ መገለጥ/መምጣትን ነው።
• ስለዚህ ቤ/ክ ልትጠባበቅ የሚገባት የፀጋ ስጦታዎችን፣ ተአምራትን፣ ፈውስን፣ ምልክትን፣ ድንቅን ... አይደለም።የጌታ የኢየሱስ መገለጥን ነው።
• ይህ ሲሆን ማለትም የጌታን መገለጥ ስንጠባበቅ ቤ/ክ አንድም የፀጋ ስጦታዎች (መንፈሳዊ ስጦታዎች) አይጎድልባትም።ለመተናነጽ የሚጠቅመን መንፈሳዊ ስጦታ ሁሉ ይበዛልናል።
* ቤ/ክ ክርስቶስን የምታጎላ እና የምትናፍቅ ናት እንጂ ከክርስቶስ በላይ የመንፈሳዊ ስጦታን አልያም በመንፈሳዊ ስጦታ የሚያገለግለውን ሰው ናፋቂ አይደለችም።
3. መንፈሳዊ ስጦታዎች፦ ቅዱሳንን ለክርስቶስ መገለጥ ቀን (ለጌታ ቀን) ያዘጋጃሉ። /1:8/
የመንፈሳዊ ስጦታዎች አላማ በዚያን ቀን ያለነውርና ያለነቀፋ እንድንገኝ ቅዱሳንን ለክርስቶስ ቀን ማዘጋጀት ነው።
ለዚያን ቀን እንድንዘጋጅ የማያደርገን የትኛውም በመንፈሳዊ ስጦታ ስም የሚከናወን አገልግሎት መንፈሳዊ ስጦታ ተብሎ ሊጠራ አይገባውም።
* እርስ በርስ እንድንበረታታ፣ እንድንተናነጽ፣ እንድንመካከር፣ እንድንረዳዳ መንፈሳዊ ስጦታዎች ለአካሉ ጥቅም ተሰጥተዋል።