Yemafed Debre Kidusan Medhani Alem Gedam Ya-የማፌድ ደብረ ቅዱሳን መድኃኔዓለም ገዳም ወማ

  • Home
  • Ethiopia
  • Addis Ababa
  • Yemafed Debre Kidusan Medhani Alem Gedam Ya-የማፌድ ደብረ ቅዱሳን መድኃኔዓለም ገዳም ወማ

Yemafed Debre Kidusan Medhani Alem Gedam Ya-የማፌድ ደብረ ቅዱሳን መድኃኔዓለም ገዳም ወማ የማፌድ ደብረ ቅዱሳን መድኃኔዓለም ገዳም ወጣቶች ማህበር ይፋዊ የፌስቡክ ገጽ

28/04/2026
በሥመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜንየዘንድሮ የመጋቢት መድኃኒዓለም ክብረ በዓል በማፌድ ደብረ ቅዱሳን መድኃኒዓለም ገዳም በደማቅ ሁኔታ ይከበራል። ስለሆነም በዚህ የበረከት ...
22/03/2026

በሥመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
የዘንድሮ የመጋቢት መድኃኒዓለም ክብረ በዓል በማፌድ ደብረ ቅዱሳን መድኃኒዓለም ገዳም በደማቅ ሁኔታ ይከበራል። ስለሆነም በዚህ የበረከት ጉዞ መሳተፍ የምትፈልጉ በሙሉ ከታች ባለዉ አድራሻ መመዝገብ ትችላላችሁ
የጉዞ መነሻ ቀን እና ሰዓት፡ መጋቢት 26 2018 ዓ.ም ከለሊቱ 12፡00 ጀምሮ
የጉዞ መነሻ ቦታ፡ መስቀል አደባባይ ቅዱስ እስጢፋኖስ ቤተ ክርስተያን
የጉዞ ዋጋ፡ 1500 ብር ምሳን ጨምሮ
የጉዞ መመለሻ ቀን፡ በእለቱ ከንግስ በኋላ
 ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጠር
 0912 467473 ወንድም አባይነህ ደለሺ
 0911554229 ወንድም ብርኃኑ ክፍሌ

በሥመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜንታላቅ መንፈሳዊ ጉባኤክፉን በክፉ አትመልሱ፤ ስድብንም በስድብ አትመልሱ፤ ነገር ግን በረከትን ትወርሱ ዘንድ ለዚህ ተጠርታችኋልና።” የማፌ...
19/12/2025

በሥመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
ታላቅ መንፈሳዊ ጉባኤ
ክፉን በክፉ አትመልሱ፤ ስድብንም በስድብ አትመልሱ፤ ነገር ግን በረከትን ትወርሱ ዘንድ ለዚህ ተጠርታችኋልና።
” የማፌድ ደብረ ቅዱሳን መድኃኒዓለም ገዳም ወጣቶች ማህበር የማህበሩ 20ኛ ዓመት ምስረታ በማስመልከት በዓይነቱ ልዩ የሆነ መርሃ ግብረ አዘጋጅቶ ይጠብቃችኃል።”
ቀን፡- ታህሳስ 26 2018 ዓ.ም
ቦታ፡- ደብረ ጽጌ ቅዱስ ዑራኤል ሰ/ት ቤት አዳራሽ
ሰዓት፡- ከጠዋቱለ 5፡00 ጀምሮ
በእለቱ እና በሰዓቱ በመገኘት በተዘጋጀዉ መንፈሳወዊ መርሃ ግብረ ላይ እንድትሳተፉ ተጋብዛችኋል።
ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን!

በሥመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።ታላቅ መንፈሳዊ ጉዞ ወደ ማፌድ ደብረ ቅዱሳን መድኃኒዓለም ገዳምወደ እግዚአብሔር ቤት እንሂድ ባሉኝ ጊዜ ደስ አለኝ፡፡ መዝ 121፡ 1የ...
09/10/2025

በሥመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።

ታላቅ መንፈሳዊ ጉዞ ወደ ማፌድ ደብረ ቅዱሳን መድኃኒዓለም ገዳም
ወደ እግዚአብሔር ቤት እንሂድ ባሉኝ ጊዜ ደስ አለኝ፡፡ መዝ 121፡ 1
የጉዞ መነሻ ቀን ጥቅምት 26-02-2018 ዓ.ም
የጉዞ መመለሻ ቀን በማግስቱ
የጉዞ ዋጋ 1200 መስተንግዶ ጨምሮ

ለበለጠ መረጃ
0912 111328 / 0913 766860

መንፈሳዊ አለባበስ ይጠበቅ
የጉዞ አዘጋጅ፡ የማፌድ ደብረ ቅዱሳን መድኃኒዓለም ገዳም ወጣቶች ማህብር

የማፌድ ደብረ ቅዱሳን መድኃኔዓለም ገዳም ወጣቶች ማህበር የዘንድሮ 2017 ዓ.ም የመንደሮች መንፈሳዊ ጉባኤ ከግንቦት 22-24 በተሳካ ሁኔታ አካሂዷል። ጉባኤዉም በ8 በተመረጡ መንደሮች የተካ...
11/06/2025

የማፌድ ደብረ ቅዱሳን መድኃኔዓለም ገዳም ወጣቶች ማህበር የዘንድሮ 2017 ዓ.ም የመንደሮች መንፈሳዊ ጉባኤ ከግንቦት 22-24 በተሳካ ሁኔታ አካሂዷል። ጉባኤዉም በ8 በተመረጡ መንደሮች የተካሄደ ሲሆን 9ኛዉ ጉባኤ ደግሞ በማፌድ ደብረ ቅዱሳን መድኃኔዓለም ገዳም ግቢ ዉስጥ ብጹእ አቡነ መልከ ጸዴቅ የጉራጌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የቅዱስ ዜና ማርቆስ መንፈሳዊ ኮሌጅ መስራችና የበላይ ጠባቂ የቅዱስ ሲኖዶስ አባል በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ ተከናዉኗል ። በእለቱ የማፌድ እና የኤነር ምእመናን አንድ ላይ በመሆን ከ300 በላይ ምእመናን የጌታችን የአምላካችን የመድሐኒታች የኢሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ስጋዉና ክቡር ደሙ ተቀብሏል። ማህበራችን የመንደሮች ጉባኤ ሲያካሂድ ዘንድሮ ለ6ኛ ጊዜ ሲሆን የዘንድሮ ከባለፉት ጊዜያት ከተደረጉት ጉባኤዎች ለየት የሚደርገዉ አንደኛ ብጹእ አባታችን በማጠቃለያ መርሐ ግብሩ መገኘታቸዉ ሲሆን ሁለተኛዉ ደግሞ ቁጥራቸዉ ከ300 ባለይ የሚሆኑ ከማፌድና ከኤነር ቅዱስ አማኑኤል ገዳም የመጡ ምእመናን አንድ ላይ ስጋወደሙ መቀባላቸዉ የዘነድሮ ጉባኤ ለየት አድርጎታል። ከመረሃ ግበሩ ፍጻሜ በኃላም ማኅበራችን ከብጹ አባታችን ለየት ያለ ቆይታ ያደረገ ሲሆን ብጹእ አባታችን ስለ ማህባራችን ዘርዘር ያለ መረጃ ጠይቆ በማህበራች ሰብሳቢ ወንድ ብሩክ ታደሰ በኩል ማብራሪያ የተሰጣቸዉ ሲሆን ብጹእ አባታችን ማህበራችን እያከናወነዉ በሚገኘዉ አገልግሎት እጅግ በጣም እንደተደሰቱና አዲስ አበባ ጠቅላይ ቤተክህነት ስር የሚገኘዉ የማህበራት አስተዳደር ማደራጃ እና መምሪያ ስር እንዲመዘገብ አባታዊ መመሪያ አስተላልፈዉ ቡራኬያቸዉ ተቀብለን መርሃ ግብራችን በሰላም ተጠናቋል። ይህን ሁሉ እንዲሆን ያደረገ ቸሩ መድኃኒዓለም ሥሙ ይክበር ይመስገን አሜን!

መረሃ ግብራቸን ማጠቃለያ እሁድ 24-09 2017  ብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ የጉራጌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ የቅዱስ ዜና ማርቆስ መንፈሳዊ ኮሌጅ መሥራች እና የበላይ ኃላፊ፣ የማዕከላዊ ኢት...
28/05/2025

መረሃ ግብራቸን ማጠቃለያ እሁድ 24-09 2017 ብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ የጉራጌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ የቅዱስ ዜና ማርቆስ መንፈሳዊ ኮሌጅ መሥራች እና የበላይ ኃላፊ፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ሰብሳቢ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል እንደሚገኙ ስንነግራቸሁ በታላቅ ደስታ ነዉ። በእለቱ ብዙ አባቶችና እናቶች ከቅዱስ ቁርባኑ የሚሳተፉ ሲሆን በዚህ በተቀደሰ መርሃ ግብር በመገኘት የበረከቱ ተሰታፊ እንድንሆን በቸሩ መድሃኒዓለም ስም ጥሪያችን እናስተላልፋለን

በሥመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ፩ዱ አምላክ አሜን።መዝ 117፡246ኛዉ በማፌድና አካባቢ የሚካሄድ የመንደሮች መንፈሳዊ ጉባኤከግቦት 22-24 በ8 በተመረጡ መንደሮች በእለት አርብ (22-0...
07/05/2025

በሥመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ፩ዱ አምላክ አሜን።
መዝ 117፡24

6ኛዉ በማፌድና አካባቢ የሚካሄድ የመንደሮች መንፈሳዊ ጉባኤ

ከግቦት 22-24 በ8 በተመረጡ መንደሮች

በእለት አርብ (22-09-2017) በአራ (4) በተለያዩ መንደሮች የሚደረግ ሲሆን
1ኛ. እቃያገበያይ (ጌቴ ሰማኒ) ሲሆን
2ኛ. ባሩኝ(እየሩሳሌም)
3ኛ. አድርሽ (ገነት ሰፈር)
4ኛ. ጎዴሳይ (ገዳም ሰፈር)

ቅዳሜም (23-09-2017) በአራ (4) በተለያዩ መንደሮች የሚደረግ ሲሆን
1ኛ. ታች ቦርኪስ(ቢታንያ)
2ኛ. አርጉኛድ(ገሊላ)
3ኛ. ሳዌተድ(ኤማሁስ)
4ኛ. እሮራ(ቤተሳይዳ)

እሁድ (24-09 2017) ከቅዳሴ በኋላ በማ/ደ/ቅ/መ/ዓ/ ገዳም ግቢ ዉስጥ

በሥመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ፩ዱ አምላክ አሜን።እግዚአብሔር የሠራት ቀን ይህች ናት፡በእርሷ ሐሴት እናድርግ ደስም ይበለን።መዝ 117፡24                           ልዪ ...
28/04/2025

በሥመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ፩ዱ አምላክ አሜን።
እግዚአብሔር የሠራት ቀን ይህች ናት፡በእርሷ ሐሴት እናድርግ ደስም ይበለን።መዝ 117፡24
ልዪ መንፈሳዊ ጉባኤ
በፍሬ ሐይማኖት ማፌድ ማዕከል በየ 3ወሩ የሚዘጋጀዉ የአንድነት ጉባኤ ግንቦት-03-2017 ዓ.ም ሲሆን በእለቱ ለነፍሳችን ስንቅ የሚሆኑ
ቃል እግዚአብሔር
ዝማሬ እና ስነ ጽሁፎችን ሌሎች አስተማሪ መርሃ ግብሮች ስለተዘጋጁ በተዘጋጀዉ መርሃ ግብር እንድትሳተፉ ስንል መንፈሳዊ ጥሪያችን እናስተላልፋለን
ተረኛ አዘጋጅ፡ የማፌድ ደብረ ቅዱሳን መድኃኒዓለም ገ/ ወ/ማ እና ማህበረ ቁስቋም ዘአስጠር
ሁላችሁም ተጋብዛችኋል
ጉባኤው የሚካሄደዉ ከ4:30-7:00 ሰዓት ሲሆን በሰዓቱ እንገናኝ
ቦታ፡ ጎላ ቅዱስ ሚካዔል ቤተ-ክርስቲያን መሰብሰቢያ አዳራሽ

የዘንድሮ የ2017 ዓ.ም የቸሩ መድኃኒዓለም ጥንተ ስቅለት(በዓል መጋቢት ድኃኒዓለም ክብረ በዓል)" ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ የጉራጌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ የቅዱስ ዜና ማርቆስ መንፈሳዊ ኮ...
07/04/2025

የዘንድሮ የ2017 ዓ.ም የቸሩ መድኃኒዓለም ጥንተ ስቅለት(በዓል መጋቢት ድኃኒዓለም ክብረ በዓል)" ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ የጉራጌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ የቅዱስ ዜና ማርቆስ መንፈሳዊ ኮሌጅ መሥራችና የበላይ ኃላፊ፣ የቅዱስ ሲኖዶስ አባልና የማዕ/ኢት/ክልል የሃይ/ተ/ጉ/ ሰብሳቢ በተገኙበት በማፌድ ደብረ ቅዱሳን መድኃኔ ዓለም ገዳም በድምቀት ተከበረ።

Address

Addis Abeba
Addis Ababa
NA

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Yemafed Debre Kidusan Medhani Alem Gedam Ya-የማፌድ ደብረ ቅዱሳን መድኃኔዓለም ገዳም ወማ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to Yemafed Debre Kidusan Medhani Alem Gedam Ya-የማፌድ ደብረ ቅዱሳን መድኃኔዓለም ገዳም ወማ:

Share