Kolfe Full Gospel Church Youth Ministry የኮልፌ ሙሉ ወንጌል ቤ/ክ ወጣቶች አገልግሎት

  • Home
  • Ethiopia
  • Addis Ababa
  • Kolfe Full Gospel Church Youth Ministry የኮልፌ ሙሉ ወንጌል ቤ/ክ ወጣቶች አገልግሎት

Kolfe Full Gospel Church Youth Ministry  የኮልፌ ሙሉ ወንጌል ቤ/ክ ወጣቶች አገልግሎት በወጣቶች ህይወት የእግዚአብሔር የፈቃዱ እውቀት መንፈሳዊ ጥ?

23/03/2022
እርሱ አስቀድሞ ወዶናልና እኛ እንወደዋለን።                                                            1ኛ ዮሐ 4 : 19
26/10/2020

እርሱ አስቀድሞ ወዶናልና እኛ እንወደዋለን።

1ኛ ዮሐ 4 : 19

22/09/2020

ዛሬ ማክሰኞ ምሽት 12:00 የወጣቶች ፕሮግራም ይጀመራል። ኑ ጌታን በአንድነት እናምልክ።

ሙሽሪት ተዘጋጅታለች? ሙሽሪት የበጉ ሰርግ ስለደረሰ ተዘጋጅታለች? ሙሽሪት ሙሽራው የሚመጣበትን ቀን በጉጉት ትጠባበቃለች?ከብቸኝነት ሊለያት፤ ከመከራዋ ሊያሳርፋት በርግጥ ሙሽራው ይመጣል። በዚ...
26/08/2020

ሙሽሪት ተዘጋጅታለች? ሙሽሪት የበጉ ሰርግ ስለደረሰ ተዘጋጅታለች? ሙሽሪት ሙሽራው የሚመጣበትን ቀን በጉጉት ትጠባበቃለች?
ከብቸኝነት ሊለያት፤ ከመከራዋ ሊያሳርፋት በርግጥ ሙሽራው ይመጣል። በዚያ ቀን ደስታ እንዲሆን ሲፈልጋት እንዳያጣት ሙሽሪት ተዘጋጅታለች?

20/08/2020

ወንድሞችና እህቶች በዚህ ፈታኝ ግዜ በጨለማ ለተዋጠችው ዓለም ከጌታ ዘንድ ምህረትን ልንጠይቅ እንዲሁም እግዚአብሔርን መፍራት በምድራችን ላይ እንዲወድቅ ሳንታክት ልንፀልይ ይገባናል ። ይህ ገፅ (page) በኮልፌ ሙሉ ወንጌል ወጣት አገልግሎት የተለያዩ ኘሮግራሞች እየተዘጋጁ የሚቀርቡበት ገፅ ነው። የህብረት ጓደኞቻችሁን (invite) በመጋበዝ እንድትተባበሩ በጌታ ፍቅር እንጠይቃለን። ተባረኩ።

"ደግሞ መንግሥተ ሰማያት በእርሻ ዉስጥ የተሰወረዉን መዝገብ ትመሰላለች ሰዉም አግኝቶ ሰወረዉ ከደስታዉም የተነሳ ሄዶ ያለዉን ሁሉ ሸጠና ያን እርሻ ገዛ፡፡" ማቴ 13፤44ከዕንቁም በላይ ዉድ ...
29/06/2020

"ደግሞ መንግሥተ ሰማያት በእርሻ ዉስጥ የተሰወረዉን መዝገብ ትመሰላለች ሰዉም አግኝቶ ሰወረዉ ከደስታዉም የተነሳ ሄዶ ያለዉን ሁሉ ሸጠና ያን እርሻ ገዛ፡፡" ማቴ 13፤44

ከዕንቁም በላይ ዉድ የሆነዉን ኢየሱስን አግኝተነዋል፡፡ የኢየሱስን ህይወት ለመግዛት(የራሳችን ለማድረግ) ያለንን ምን አልባትም የሚጠቅመንን ሁሉ ስለ ክርስቶስ ብንተዉ ካገኘነዉ ከኢየሱስ ዋጋ አንጻር ስናስተያይ ምንም ነዉ!!! ጳዉሎስ ስለ ክርስቶስ"... ሁሉን እንደ ጉድፍ ቆጥራለሁ..." ያላቸዉ ነገሮች በራሳቸዉ ጉድፍ አልነበሩም ከክርስቶስ አንጻር ሲያየዉ እንጂ!!
ለተቀበልነዉ ለዚህ ዕንቁ ህይወት የማይመጥኑ ሆነዉ ያገኘናቸዉ … ነገር ግን ልንተዋቸዉ ያቃቱን ነገሮች ሁሉ ከተከፈለልን ከውድ ዋጋና ካገኘነው ዕንቁ ህይወት አንጻር ምናምንቴ እንደሆኑ የምናይበት አይን እግዚብሔር ይስጠን፡፡
ፀጋዉ ይብዛልን!!

" ከመታወቅ የሚያልፍ አምላክ " [ መዝ 145 ፥3 ]  እግዚአብሔር በሰው የዓይምሮ ጥበብ የማይደረስበት ምጡቅ የሆነ አምላክ ነው ። እግዚአብሔር በራሱ ፈቃድ ራሱን ለሰዎች ካልገለጠ በስተቀ...
26/06/2020

" ከመታወቅ የሚያልፍ አምላክ " [ መዝ 145 ፥3 ] እግዚአብሔር በሰው የዓይምሮ ጥበብ የማይደረስበት ምጡቅ የሆነ አምላክ ነው ። እግዚአብሔር በራሱ ፈቃድ ራሱን ለሰዎች ካልገለጠ በስተቀር ማንም ሰው በትክክል ሊረዳው እና ሊያውቀው ከቶ አይችልም ። ፍጥረት ፈጣሪውን በማወቅ እና ከእርሱም ጋር ጤናማ ህብረት በማድረግ የሚገኘውን የነፍስ ዕረፍትና የስጋ ባርኮት ተካፋይ እንዲሆኑ እግዚአብሔር ፈቃዷል!!! በዚህም ምክንያት "እግዚአብሔር አምላክ ነው ለእኛም በራልን" ተብሎ እንደተጻፈ ፥ ትልቁ እግዚአብሔር በፊቱ ታናናሽ የሆነውን እኛን ሳይንቅን ፥በቅዱስ ቃሉ እና በክርስቶስ በኩል ራሱን በመግለጥ እንድናውቀው አድርጎናል ። ከላይ በተጠቀሰው ክፍል ውስጥ ዳዊት በመንፈስ ቅዱስ ረድኤት የተገለጠለትን የእግዚአብሔር ማንነት በሰፊው ያብራራል ። ከዚህም ባሻገር ከእግዚአብሔር ጋር ህብረት ያደርጉ ዘንድ በክርስቶስ የተመረጡትን ቅዱሳን በዚህ አምላክ ፊት እንዴት መኖር እንዳለባቸው ይመክራል ። የዚህ ጹሑፍ አቅራቢ ጹሑፉን ለሚመለከቱ አንባቢያን በግል የጥሞና ጊዚያቸው የመዝሙር 145 ን ሙሉ ሃሳብ በማንበብና በማጥናት የአምላካቸውን ማንነት እንዲረዱና የራሳቸውን ኃላፊነት በዛ ውስጥ እንዲመለከቱ ያበረታታል ።............

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Kolfe Full Gospel Church Youth Ministry የኮልፌ ሙሉ ወንጌል ቤ/ክ ወጣቶች አገልግሎት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category