Ergaa kitaaba woyyichaa

Ergaa kitaaba woyyichaa qoonqoo waaqaa tana wolii himaa hubannaa kitaaba woyyichaa kanallle wolii issina/ibsina

Worri waaqaa yomara irra Aana
06/06/2025

Worri waaqaa yomara irra Aana

13/05/2025
Eebba kitaaba woyyicha looga oromoo gujiiEEBBAKITAABA WOYYICHA LOOGA OROMOO GUJIIBULEE HORAA01/10/2016 EC
08/06/2024

Eebba kitaaba woyyicha looga oromoo gujii

EEBBA

KITAABA WOYYICHA LOOGA OROMOO GUJII

BULEE HORAA
01/10/2016 EC

====   እንነሣ ፣ እንሂድ ፣ እርሱን እንመስር ! ====(እንኳን ለዓለም ዓቀፍ ሚስዮን ሳምንት አደረሳችሁ ፤ አደረሰን)"እኛ የኢሱስ ክርስቶስ መስካሪዎች ነን እንጂ የመብቱ ተከራካሪዎች ...
17/01/2024

==== እንነሣ ፣ እንሂድ ፣ እርሱን እንመስር ! ====
(እንኳን ለዓለም ዓቀፍ ሚስዮን ሳምንት አደረሳችሁ ፤ አደረሰን)

"እኛ የኢሱስ ክርስቶስ መስካሪዎች ነን እንጂ የመብቱ ተከራካሪዎች አይደለንም"

# ቤተክርስቲያን የተሰጣትን ዋና ተልዕኮ ፣ አላማና አገልግሎቷን ከረሳች በምድር ላይ መኖሯ ምንም ፋይዳ የለውም። የግለሰቦችን ጥቅማ-ጥቅም ማስከበሪያ ተቋም ወይም የግለሰቦች የምድራዊ ገቢ ማስገኛ ሱቅ ሆና ትቀራለች። ዓላማዋ ግን ወንጌልን መመስከርና ደቀመዝሙር ማድረግ ነው (ማቴ. 28:19-20)።

# ከቤተክርስቲያን በላይ ኢየሱስን ያየ አካል የለም። ኢየሱስን በጨለማ ላለው ለዓለም የሚያሳይ-የሚመሰክር ተቋምም በምድር ላይ የለም። በምድር ላይ ለምንና ለማን እንደምኖሩ ስለገባቸው የኢየሱስ ሐዋርያት "እኛ ያየነውንና የሰማነውን ከመናገር ዝም አንልም" ይሉ ነበር (የሐዋ. 4:20)።

# ዛሬም ይህ ዓላማ የገባው ክርስቲያንና ቤተክርስቲያንን ኢየሱስን ከመስበክ ዝም አይልም ፤ ምድራዊውን ገዳይ ፣ የቤተእምነቱን መብትና ግዴታ ብቻ ፣ የራሱን ክብርና ዝና አይሰብክም።

# እኛ ክርስቲያኖች ድነናል ፤ እንደዳነ ሰው ፤ ከጨለማና ከጥፋት ወደሚደነቅ ብርሃን እንዳመጣ ሰው ሆነን የእርሱን በጎነት እንድናገርና እርሱን እንድንመሰክር አዲስ ትውልድ ሆነን ተመርጠናል (1ጴጥ. 2:9)። የእርሱ ካህናትና ቅዱስ ሕዝብ ሆኖ እንደተመረጠ ሰው ግዴታችንንና ተልዕኮአችንን መወጣት አለብን።

# ኢየሱስ የመንግሥቱን ወንጌል ኢየሰበከ በየአከባቢ ይዞር ነበር። ሕዝብም ይከተሉት ስለ ነበር ብዙዎቹ የጠላት እስራትና ስቃይ ውስጥ እንዳሉና እውነተኛ እረኛ እንደሌላቸው አይተው አዘነላቸው።

# በማቴ. 9:36-38 ላይ ኢየሱስ ብዙ ሕዝብም ባየ ጊዜ ፥ እረኛ እንደ ሌላቸው በጎች ተጨንቀው ተጥለውም ነበርና አዘነላቸው። በዚያን ጊዜ ደቀ መዛሙርቱን እንዲህ አላቸው "መከሩስ ብዙ ነው ፥ ሠራተኞች ግን ጥቂቶች ናቸው ፤ እንግዲህ የመከሩን ጌታ ወደ መከሩ ሠራተኞች እንዲልክ ለምኑት" አላቸው።

# መከሩ ብዙ ነው፤ ሜዳውም ሰፊ ነው ፣ ይበቃናል። ተነስተን ወጥተን የመንግሥቱን ሥራ እንስራ ፣ እንመስክር ፣ እንስበክ።

።።።።=== እንመስክር❤ እንጂ አንከራከር 🙅 !! ===።።።@ singer Dawit BoruMYC YOUTH CLUB

02/01/2024
Hojjatoota Gooftaa Yesuus @highlight
08/12/2023

Hojjatoota Gooftaa Yesuus

@highlight

01/12/2023

Kes Yisahak Yohanis, [11/30/2023 5:54 PM]
Dhikoo tana nami Dr Salli Qilxaa jedhamu barnoota sobaa mataduree jedhuun qabxii 17 qopheesse barnota eenyummaa woldaa Makane Yesuusii ka kitaaba qulqulluurratti hundeefamtee amantoota milyoona kudhaniif lama gula deemtota kirstoosii goote akka barnoota sobaa isiin barsiisa turtteetti godhee maqaa woldaa keennaa fecebookii irratti arabsa ture. Nami akkana woldaa keenna face bookiiraatti arrabsu kun inni eennu? mammaassi biyya waan jedhu "dhakaan ifi hin darbu abbaan ifi hindhaggu" Namni amma maqaa woldaa keenna baleessaa nu arrabsu kun inninu barnoota sobaa ka dispeenseeshinaalummaa jedhamu nama barsiisu. Nama kakuun moofaan gaaddiduu,nu'uuf hin fayyadu jedhu. Nama cubbuun mootummaa Waaqa nama dhooggitu hin jirtu , nami yesuusiin fayye yoo akka fedhe cubbu hujelle hin badu nama jedhe barsiisu. Nama seerri ka hin fayadne waan te'eef diigameera jedhee kitaaba barreesse. Nama Lubi woldaa kirstaanaatiif hin barbaachisu jedhu. barumsa akkanaa kana nami barsiisu maqaa kamiin hamilee kamiin waan barsiisa sobaa barreessuu dande'a? Waan maraafuu amantootni teenna barnoota nama kanaarra aaka ifi eegattanuuf kunoo armaan gaditti qabxillee muraasa barumsi sobaa dispeenseeshinaalummaa jedhamu ittiin beekkamu muraasa isiniif eergeeraa yeroo ittti fudhaadhaa dubbisa. Badhaadhi Waaqaa isinii haa fakkanu ከዲስፔንሰሽናሊዝም Dispensetionalism) እንጠንቀቅ!

የመግቢያ ጥቅስ፡- ልዩ ልዩ ዓይነት በሆነ በእንግዳ ትምህርት አትወሰዱ፤ ልባችሁ በጸጋ ቢጻና መልካም ነው እንጂ በመብል አይደለም፡፡ እብ. 13፡9

መግቢያ፡-
በዘመናችን ከሚታዩ እጅግ ውስብስብና አደገኛ የስህተት ትምህርቶች መካከል አንዱ “ብሉይ ኪዳን ለእስራኤል እንጂ ለእኛ አይደለም፤ ከህግ ነጻ ወጥተናል አይገዛንም፤ ህግ አያስፈልገንም፤ በየጊዜው ንስሐ መግባት አያስፈልገንም፤ “በክርስቶስ ድነናል፤ ነጻ ወጥተናል፤ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ሁሉንም “ተፈጸመ” ብሎ ጨርሶልናል፡፡ ደህንነታችን እንደፈለግን ቢንኖርና ኃጢአት ብንሠራም አይነካም፡፡ የእግዝአብሔርን መንግሥት መውረስ የሚከለክለን ኃጢአት ፈጽሞ አይኖርም፡፡ ከህግ ነጻ ስለሆንን እንደፈለግን መኖር እንችላለንና አትገድቡን፤ ወዘተ… የሚል ትምህርት ነው፡፡ የዚህ አስተምህሮ ምንጩ (Disp

01/12/2023

የዲስፔንሰሽናሎች አስተምህሮ መሥራች “ጆን ነልሰን ዳርቢ(John Nelson Darby) የተባለ የእንግልዝ ሀገር ቄስ ሲሆን የትምህርቱን እንቅስቃሴ የጀመረው ከ1838-1845 እ.ኤ.አ. በቢሪታኒያ በፈረንሳይና በስዊዘርላንድ የወንድማማች ብድን በመመሥረት ነው፡፡ ይህንን የጆን ዳርቢ ትምህርት ያስፋፋውና ለብዙ ሀገሮች ያዳረሰው የትምህርቱ ደጋፊና አቀንቃኝ የነበረው “ሳይረስ ስኮፊልድ” የተባለ የዳላስ የሥነመለኮት ሰሚነሪ መምህር ነበር፡፡ ይህ ሰው አስተምህሮውን በማዳበር ትምህርቱ እንደ ቤተእምነት ሳይሆን እንደ ሥነመለኮት እሳቤ(school of thought) በምሁራን ዘንድ እንድታይ አደረገ፡፡ ቀጥሎም በ19ኛው ክፍለ ዘመን “ሉዊስ እስካፈር” የተባለው ሰው የጆኒ ደርቢና የሳይረስ ስኮፍልድን ትምህርት በመላው ዓለም የራሱ ማተሚያ ቤት በመክፈት በአጭር ጊዜ ውስጥ አሰራጨ፡፡ ይህ ትምህርት በሀገራችን በዚሁ 21ኛው ክፍለ ዘመን የጂማ ከተማን መነሻ አድርጎ “የእውነት ቃል አገልግሎት” (Bible truth ministry) ብሎ ራሱን በሚጠራው የነዳዊት ፋሲል ሚኒስትሪ የስኮፊልድን መጽሐፍትና ሌሎች የማስተማሪያ ጽሁፎችን በአማርኛና በኦሮምኛ በመተርጎም በሀገራችን በርካታ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቻችን መካከል እየተስፋፋ ይገኛል፡፡ የዚህ አስተምህሮ ሀሳብ ባሁኑ ጊዜ ዶ/ር ሣል ቅልጣ በተባለው ሰው “Dhossaa Barabaraa” በሚባል ሪእስ በመጽሐፍ መልክ ታትሞ ወጥቶአል፡፡ እንደ አዲስና ልዩ የተገለጠ የእግዝአብሔር ምስጢር ተደርጎ በየሳምንቱ ለአብዘኛው ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ምእመናን በትምህርት መልክ እየተሰጠ ነው፡፡ ለመሆኑ የዲስፔንሰሽናሊዝም አስተምህሮ በምን ተለይቶ ይታወቃል?
የሚከተሉት ዋና ዋና የትምህርት ነጥቦችን እስቲ እንመልከት፡-
1. ዲስፔንሰሽናሊስቶች እግዝአብሔር ከፍጥረት ጀምሮ እስከ ኣለም ፍጻሜ ድረስ ከሰዎች ጋር የነበረውን ግንኙነትና ወደፍት የሚቀጥለውን ዘመን በተለያዩ የጊዜ መከፋፈል ቀመር ይከፋፍላሉ፡፡ ይኸውም፡-1/ ከአዳም እስከ በኃጢአት መውደቅ ጊዜ ያለውን ዘመን የየዋህነት ዘመን፤ 2/ ከውድቀት እስከ ኖህ ያለውን ጊዜ የንቃተ ህሊና ዘመን፤ 3/ ከጥፋት ውሃ እስከ አብርሃም መጠራት ያለውን የሰው መንግሥት ዘመን ፤ 4/ ከአብርሃም እስከ ከግብጽ መውጣት ያለውን የተስፋ ዘመን፤ 5/ የሙሴ ህግ ከተሰጠበት እስከ ክርስቶስ ትንሣኤ ያለውን ጊዜ የህግ ዘመን፤ 6/ ከክርስቶስ ትንሣኤ እስከ ቤተክርስቲያን መነጠቅ ያለውን ጊዜ የጸጋ ዘመን፤ 7/ ከመነጠቅ እስከ ዳግም ምጽአት ያለውን ጊዜ የክርስቶስ መንግሥት ዘመን ወይም የሺ ዓመተ መንግሥት ዘመን ብለው ዘመናትን በሰባት ይከፍላሉ፡፡ ይህንን የዘመናት ክፍፍል እንደ ዘላለማዊ እግዝአብሔር ሀሳብና ምስጢር ይቆጥራሉ፡፡

Kes Yisahak Yohanis, [11/30/2023 5:54 PM]
ዲስፐንሰሽናሎች የመጽሐፍ ቅዱስ ዘመናትን በተለያዩ ክፍሎች የሚከፋፍሉበት ምክንያት 1/ “ያለንበት ዘመን የጻጋ ዘመን ስለሆነ ህግ አያስፈልገንም” የሚለውን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆነ አስተምህሮአቸውን በትውልድ መካከል ለመዝራት፤ 2/ ጸጋን መሸፈኛ በማድረግ “ክርስቶስ ሃጢአታችንን ሁሉ በመስቀል ላይ ስለፈጸመውና ማንም ኃጢአት ቢሠራም ከአብ ዘንድ ጠበቃ ስላለን(1ዮሐ፣ 2፡6) ንስሐ እየገባን ማልቀስ አያስፈልግም” የሚለውን ሀሰተኛ መርዝ በትውልዱ ልብ ውስጥ ለመርጨት ነው፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ግን በታርክ የተጠቀሱ ዘመናት ከአዳም ጀምሮ እስከ ዳግም ምጽአት ድረስ ክርስቶስን ማእከል አድርጎ ወጥና አንድ ታርክ እንጂ የተከፋፈለ አይደለም፡፡ በየትኛውም የቤተክርስቲያን

01/12/2023

2. እኔ እግዝአብሔር አምላካችሁ ቅዱስ ነኝና እናንተ ቅዱሳን ሁኑ፤ (ዘሌዋ. 19፡2)
3. በባልንጀራህ ግፍ አታድርግ፤ አትቀማውም የሞያተኛው ዋጋ እስከ ነገ ድረስ በአንተ ዘንድ አይደርብህ፤ (ዘሌዋ. 19፤13)
4. ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ ፤ (ዘሌዋ. 19፡18)
5. እኔም እግዝአብሔር ነኝና ሰው ባልንጀራውን አያታልል፤ ነገርግን አምላክህን ፍራ፤( ዘሌዋ.25፤17)
6. በባልንጀራህ ላይ በሀሰት አትመስክር፤ (ዘዳ. 5፤20)
ከላይ እንደተጠቀሰው የእግዝአብሔር ቃል መጽሐፍ ቅዱስ ለትምህርት የተጻፈና እንደማይሻርና ለዘላለም እንደማያልፍ ይነግረናል፡፡ ሉቃ 24፡47፤ ማር 7፡9፤ ማቴ 15፡6፤ ማቴ 5፡17፤ ይመልከቱ፡፡ ስለዚህ ይህ “ብሉይ ኪዳን ክርስቶስን ለማመልከት እንጂ ለእኛ መመርያ ለመስጠት ስላልተጻፈ የእኛ አይደለም” የሚለው የዲስፔንሰሽናሎች ሀሳብ መጽሐፍ ቅዱስ “በመንፈስ ቅዱስ መሪነት የተጻፈ፤ ከጥንት ዘመን ጀምሮ ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱ፤ ሐዋሪያትና የቤተክርስቲያን አባቶች እውነተኛነቱን የመሰከሩት የእግዝአብሔር ቃል ነው” ለሚለው የክርስትና መሠረተ እምነት ሀሳብ ተቃራኒ ስለሆነ ቤተክርስቲያን ይህንን አስተምህሮ አትቀበልም፡፡

Kes Yisahak Yohanis, [11/30/2023 5:54 PM]
3. ዲስፔንሰሽናሎች ህግ እንደተሻረና ለዚህ ዘመን ትውልድ እንደማይጠቅም ያስተምራሉ፡- በዲስፔንሰሽናሊስት አስተምህሮ ህግ የኩነኔ የሞትና የመለኮታዊ እርግማን አገልግሎት እንደሆነና በክርስቶስ እንደተሻረ እንድሁም አማኞች የብሉይ ኪዳን ህግን ከመጠበቅ ነጻ እንደሆኑ ትምህርት ይሰጣል፡፡አሠርቱ ትእዛዛትን ማወቅና መጠበቅም ለክርስቲያኖች አያስፈልግም ይላሉ፡፡ ለምሳሌ ዶ.ር ሣል ቅልጣ በጻፈው መጽሐፍ ውስጥ “Seerri ka hin fayadine waan te’eef diigameera ” ይላል፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ህግን በመጠበቅ ማንም ሊድን እንደማይችል የእግዝአብሔር ቃል ያስተምረናል፡፡ ገላ፡4፡4፡፡ በብሉይ ኪዳን ያሉ ህጎች ለደህንነታችን አይጠቅሙንም እንጂ የጽድቅና የመልካም ኑሮ መመርያ ናቸው፡፡(ገላ. 3:24) ሕግ ወደ ጸጋው የሚመራን መሪያችን ነው፡፡ በህግ ኃጢአተኞች መሆናችንን ተገንዝበን ወደ ክርስቶስ ጸጋ በመቅረብ ከኃጢአታቸንን እንነጻለን፡፡ ስለዚህም ህግ የእግዚአብሔርን ቅዱስ ባህሪውን በመግለጽ እና የእርሱ አምሳል የሆኑ ሁሉም ይህን መልክ እንዲይዙ ወደዚያ የሚያመለክት የመንገድ መሪ ነው። ህግ ወደ ክርስቶስ በመምጣት ሃጢአታችንን እንድንዘዝ የሚመራ ሞግዚት ነው፡፡ ህግ ኃጢአተኞች መሆናችንን የምናይበት መስተዋት ነው፡፡ በጸጋ ድነናል በህግ ሥር አይደለንም የሚለው ሀሳብ መጽሐፍ ቅዱሳዊና እውነት ነው፡፡ ነገርግን በህግ ሥር አይደለንም ማለት ህግ የለም ማለት ሳይሆን ህግ በሰው ላይ በሚያመጣው ፍርድ ሥር አይደለንም ማለት ነው፡፡ ከህግ ፍርድ ያመለጥነው ኃጢአተኞች ስላልሆንን ሳይሆን በየቀኑ ኃጢአታችንን በመናዘዝ የክርስቶስን ጸጋ ስለምንቀበል ነው፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ህግ አስፈላጊነት በማቴዎስ ወንጌል ምእራፍ 5፡17- 19 ላይ ስለ ህ አስፈላጊነት ግልጽ በሆነ መንገድ አስተምሮአል፡፡ በተለይም ቁ. 19 ላይ “ከትእዛዛቱ አንዲቱን የሚሽርና እንደተሻረ ሌሎችን የሚያስተምር ሰው በመንግሥተ ሰማያት ከሁሉ ታናሽ “እንደሚሆን ይናገራል፡፡ ስለዚህ የእግዝአብሔርን ህግ እንደተሻረና እንደማያስፈልግ መቁጠር በመንግሥተ ሰማያት ብቻ ሳይሆን በቤተክርስቲያን ውስጥ ብሎም በምእመናን ፍት ትንሽነት ነው፡፡
4. ዲስፔንሰሽናሊስቶች በእግዝአብሔር ህግና በእግዝአብሔር ጸጋ መካከል ያለውን ልዩነት አላግባብ በማስፋ

Address

Media
Addis Ababa

Telephone

+251965527127

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ergaa kitaaba woyyichaa posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to Ergaa kitaaba woyyichaa:

Share