22/08/2026
🕎 🕎 🕎 🟢 🟠 🔴 🔵 ✡ ✡ ✡
በምድርና በሰማያት አጽናፋት ያላችሁ ሠራዊተ እግዚአብሔር እትዮጵያውያን እንኳን ለነሐሴ 16 ቀን 2018 ዓ/ዘ ዕለተ ሰንበት ክብርት እትዮጵያ አደረሰን አደረሳችሁ!!!
✡ “ሰንበትን የሚጠብቃት፡ ሰው ኹሉ ከሥራም ኹሉ የሚያርፍባት በዘመኑ ኹሉ እንደ-ዕኛ የተቀደሰና የተባረከ ይኾናል፡፡” (ኩፋሌ 3/14) ከዚህ ሕያው ቃል የምናስተውለው አንዲቷን ሰባተኛዋን ዕለት ቀዳሚትና ደኀራዊት ሰንበትን ከሥራ ኹሉ ተከልክሎ በምስጋና እና በዕረፍት የሚያሳልፍ ከአምላኩ ጋር አብሮ እንደሚያርፍ ነው፡፡ ነገር ግን በሰንበት የማያርፍ የእግዚአብሔርንም ቃል የማይጠብቅ እርሱ ከእግዚአብሔር ጠላቶች ጋር አብሮ ይቅበዘበዛል፡፡
✡ ቅድስት ሀገር እትዮጵያ ሀገረ ሰንበት! ሀገረ እግዚአብሔር ሀገረ ማርያም ናት ስንላችሁ እንደ-ቀልድ በዋዛና በፈዛዛ ያያችሁት እንዴት ጊዜው እንዳለፈባችሁ አስተውሉ!!! እኛ የሚገርመን እትዮጵያ አምላኳ እግዚአብሔር፤ ባለቤቷ እግዚአብሔር፤ ቀኗንም ሌሊቷንም የሚያስተዳድረው እግዚአብሔር፤ ኾኖ እያለ ልክ ዘለዓለም ነዋሪዎች የሚመስሉ በማይመለከታቸው ገብተው እርስ በእርስ ሲፋጁ ሲጣሉ ከበረከት ሲርቁ ስናይ በእግዚአብሔር አደራረግ እንደነቃለን፡፡
✡ ነቢዩ ኢሳይያስ በቅድስት ምድር እትዮጵያ ስለሚመከር ክፉ ነገር እንዲህ ተናገረ፡- “ለዓመፀኞች ልጆች ወዮላቸው… ከእኔ ዘንድ ያልሆነን ምክር ይመክራሉ፥ ኃጢአትንም በኃጢአት ላይ ይጨምሩ ዘንድ ከመንፈሴ ዘንድ ያልሆነውን ቃል ኪዳን ያደርጋሉ። ከአፌም ነገርን ሳይጠይቁ በፈርዖን ኃይል ይጸኑ ዘንድ በግብጽም ጥላ ይታመኑ ዘንድ ወደ ግብጽ እንዲወርዱ ይሄዳሉ። (ኢሳይ/30/1-2)
✡ ነቢዩ ሕዝቅኤልም እንዲህ አለ፡- “ዋይ በሉ፥ ለቀኑ ወዮ ቀኑ ቅርብ ነው፥ የእግዚአብሔር ቀን ቅርብ ነው፥ የደመና ቀን፥ የአሕዛብ ጊዜ ይሆናል። ሰይፍ በግብጽ ላይ ይመጣል፥ ሁከትም በኢትዮጵያ ይሆናል፤ የተገደሉትም በግብጽ ውስጥ ይወድቃሉ፥ ብዛትዋንም ይወስዳሉ፥ መሠረትዋም ይፈርሳል። ኢትዮጵያና ፉጥ ሉድም የተደባለቀም ሕዝብ ሁሉ ኩብም ቃል ኪዳንም የገባችው ምድር ልጆች ከእነርሱ ጋር በሰይፍ ይወድቃሉ። እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። ግብጽን የሚደግፉ ይወድቃሉ፥ የኃይልዋም ትዕቢት ይወርዳል፤ ከሚግዶል ጀምሮ እስከ ሴዌኔ ድረስ በእርስዋ ውስጥ በሰይፍ ይወድቃሉ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር። ባድማም በሆኑ አገሮች መካከል ባድማ ይሆናሉ፥ ከተሞችዋም በፈረሱ ከተሞች መካከል ይሆናሉ። እሳትንም በግብጽ ባነደድሁ ጊዜ ረዳቶችዋም ሁሉ በተሰበሩ ጊዜ፥ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ። በዚያ ቀን መልእክተኞች ተዘልለው የሚኖሩትን ኢትዮጵያውያንን ለማስፈራት ከፊቴ በመርከብ ይወጣሉ፤ እንደ ግብጽም ቀን ሁከት ይሆንባቸዋል፤ እነሆ፥ ይመጣልና።”
(ሕዝቅ/30/2-9)
✡ እነዚህ የነቢያት ትንቢቶች በዚህ ዘመን ስላሉ አመጸኞች የተነገሩ ናቸው፡፡ ቅድስት ሀገር እትዮጵያ የእግዚአብሔር ምድር የዐዳምና የሔዋን መፈጠሪያና መናገሻ የመለኮት መቅደስ የድንግል ማርያም የትውልድ ሀገር ናትና ባለቤት እንደሌላት መቀራመት ፈጽሞ አይቻልም፡፡ ስለዚህም እግዚአብሔር ሀገር ትመሩ ዘንድ የፈቀደላችሁ በቤተ ክህነትና በቤተ መንግሥት ያላችሁ እንዲሁም በቅድስት ሀገር በአራት ማእዘናት ያላችሁ ከእናንተም መካከል በትእቢትና በአመጽ ያላችሁ የእግዚአብሔር ቁጣ በእናንተ ላይ እንደ-ዝናብ ከመውረዱ አስቀድሞ በእጅጉ ወደ-ልቦናችሁ ተመለሱ፡፡ እኛ በቅድስት ምድር እትዮጵያ ላይ የሚመከር ክፉ ነገር ኹሉ እንዳይፈጸም ፈጽሞ እናምናለን፤ እናውቃለን። ነገር ግን ክፉ መካሪዎች ከክፋታቸው ተመልሰው በጽድቅ መንገድ ይሄዱ ዘንድ ዘርአ ዐዳም ወሔዋን ኹሉ በተዋሕዶ ከጥፋት ይድን ዘንድ የዘወትር ልመናችን ነውና ኹልጊዜ እናስጠነቅቃለን፡፡
✡ 7 ሰዎች በአንዲት ከተማ ውስጥ ሲኖሩ በፀሓይ ተጣሉ ይባላል፡፡ ሶስቱ ፀሓይ የኹላችንም ብርሃን ናትና አንዱ ሌላውን ይከለክለው ዘንድ አይቻልም ሲሉ፤ አራቱ ደግሞ ፀሓይ የእኛ ብቻ ናት፤ ከእናንተ ከሶስታችሁ ቀድመን የተወለድነው እኛ ነን፤ ስለዚህ በቀን ፀሓይ ልትሞቁ፣ እህል ልታሰጡ፣ ከብቶቻችሁን በብርሃን ልታሰማሩ አይገባም፤ እናንተ ሌሊት ሌሊት የወደዳችሁትን ከማድረግ በቀር በፀሓይ ጊዜ በቤታችሁ ተቀመጡ፤ በፀሓይ ጊዜ የወደድነውን እናደርጋለን ካላችሁ ስለ-ፀሓያችን ዋጋ ክፈሉን፤ ሳትከፍሉ የእኛን ፀሓይ ከሞቃችሁና ከተገለገላችሁባት እናጠፋችኋለን፤ አሏቸው፡፡ በዚህም የተነሳ ሰባቱ ሰዎች ጦር እና ቀስት መዘው ውጊያ ጀመሩ፡፡ ውጊያቸው በቀን ነበረና በውጊያቸው መካከል ፀሓይ በድንገት ብርሃኗን ከለከለች፤ ለሰባት ቀናትም ከተሠወረችበት አልወጣችም፡፡ ታድያ ከሚዋጉት መካከል ከኹለቱም ወገን አምስቱ ሞተው ከየወገኑ የተረፉት ኹለት ሰዎች ለካስ የምንጣላው የእኛ ባልኾነች ለጋራ በተሰጠችን ስንወድ ልናወጣት ሳንወድ ልናጠልቃት በማንችል በእግዚአብሔር ስጦታ ነው ብለው ተነጋግረው በይቅርታ ሲላቀሱ ፀሓይ እንደ-ገና ብርሃኗን ሰጠች።
✡ በእኛም ሀገር ቅድስት ምድር እትዮጵያ ሀገረ ማርያም፣ ሀገረ እግዚአብሔር ኾና ሳለ፡ ይህ ከተማ የእኛ ነው፤ ያኛው ክፍለ ሀገር የእነ-እገሌ ነው፤ የግእዝ ፊደል ይጥፋ የእትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር ይወገድ፤ እኛ በዚህ እንበልጣለን እነገሌ በዚህ ያንሳሉ፤ በሚል በቅድስት እትዮጵያ የሚጣሉ ኹሉ እንዲሁ በፀሓይ እንደተጣሉት ሰዎች ናቸው፡፡እነርሱ በሰፊ አዳራሽ መከሩ፤ ነገር ግን የባለቤቱን የእግዚአብሔርን ምክር አላወቁም፤ እነርሱ ፍቅርን እግዚአብሔርን ትተው በጸብ ተሞሉ፤ ነገር ግን የቅዱሳንን ሐሴትና ፍርድ አልተረዱም፤ እነርሱ ለነገ መከሩ፤ ነገር ግን ነገን አላወቁትም፡፡
✡ ስለዚህ ነቢዩ ሕዝቅኤል ቅድስት እትዮጵያን ለማስፈራራት የሚመጡ የግብጽ ደጋፊዎች ቅድስት እትዮጵያ ትጥፋ የሚሉ የስም አጠራሯንም አንስማ ያሉ እንደ-ግብጽ ቀን ሑከት እንደሚኾንባቸው የተነገረው ሕያው ቃል ይወድቅባቸው ዘንድ አለና ከክፉ ምክራቸውና ምግባራቸው ተጠብቀው በጽድቅ መንገድ እንዲመላለሱ እናሳስባለን፡፡
✡ እ…ግ…ዚ…አ…ብ…ሔ…ር… አ…ጋ…ዕ…ዝ…ት… መ…ለ…ኮ…ት… አ…ሐ…ዱ… አ…ም…ላ…ክ… ከመላእክቱና ከቅዱሳኑ ጋር በገሃድ በቅድስት እትዮጵያ ተገልጾ የቅድስት እትዮጵያን ክብር እየገለጸ፤ ለቅዱሳኑ የሰንበትን የዕረፍት ዋጋ ሲከፍል በአሕዛብ ላይ ደግሞ መቅሠፍቱን እያወረደ ይገኛል፡፡ በተዋሕዶ እምነት በመታዘዝ ክበሩ፤ በመታዘዝ ዳኑ፤ በመታዘዝ የአጋዕዝት ሥላሴን ቃል በተግባር በመኖር ከፍጻሜው የቁጣ መቅሠፍት አምልጡ፡፡ ለሚያስተውሉ የተገለጸች ለማያስተውሉና ለማይታዘዙ የተሠወረች እውነት አለች፤ እርሷም “እትዮጵያ በተዋሕዶ ዓለምን አንድ አድርጋ እየገዛች ነው፤” የምትለው ናት፤ መጨረሻው ሲገለጥ ለማያምኑትም ኹሉ ይታያል፡፡
✡ በሰንበት የምታርፉ ዘርዐ ዐዳም ወሔዋን የርእሰ ሠራዊተ እግዚአብሔር ኤልያስ መንፈስ እጥፍ ድርብ ኾኖ ይብዛላችሁ፤ ሰንበትን በሰልፍ ላይ ኾናችሁ ለምታከብሩት ርእሰ ኀይላተ እግዚአብሔር ኤልያስ ሰልፋችሁን ይቁረጥላችሁ፤ ነገር ግን በሰንበት ዕረፍታችን በድንግል ማርያም ላይ በምትሳለቁት በቅድስት እትዮጵያ ጠላቶች ላይ ለፍርድ የተገለጸው ሙሽራ ነቢየ እግዚአብሔር ወልድ ዋሕድ ኤልያስ ፍቅሩን ይግለጽባችሁ!!!
🕎 እትዮጵያ!!! ሀገረ እግዚአብሔር ወልድ ዋሕድ፤
🕎 እትዮጵያ ሀገረ ማርያም እመ ኩሉ ፍጥረት ወላዲተ አምላክ፤
🕎 እትዮጵያ ሀገረ ጽዮን መቅደስ፡ ወዙፋነ እግዚአብሔር፤
🕎 እትዮጵያ ሀገረ ኤልያስ ርእሰ ሠራዊተ እግዚአብሔር፤
🕎 እትዮጵያ ሀገረ አድማኤል ኪሩብ/ዐዳም፤
🕎 እትዮጵያ ሀገረ ሕያኤል/ሔዋን፤
🕎 እትዮጵያ ሰማያዊት እየሩሳሌም፤
🕎 እትዮጵያ ሀገረ ሐዋርያተ መለኮት ወልድ ዋሕድ፤
🕎 እትዮጵያ ሀገረ ቅዱሳን፤
🕎 እትዮጵያ ሀገረ መላእክት፤
🕎 እትዮጵያ ሀገረ አማልክት፤
🕎 እትዮጵያ ምድረ አርባእቱ መዛግብት፤
🕎 እትዮጵያ ምድረ ግእዝ፤
🕎 እትዮጵያ ምድረ ተዋሕዶ፤
🕎 እትዮጵያ ምድረ ሰንበት፤
🕎 እትዮጵያ ምድረ ገነት፤
🕎 እትዮጵያ ሰማየ ሰማያት፤
🕎 እትዮጵያ ምድረ ፍትሐ ፍጻሜ፡፡
ሞዓ አንበሳ እግዚአብሔር ወልድ ዋሕድ በአካል ለፍጻሜ ፍርድ ተገልጾ ከነገሠባት መቅደሱ እም ሀገረ እግዚአብሔር ወማርያም ወምድረ ገነት ቅድስት እትዮጵያ
አልሰማሁም የሚል ይስማ
አላዳመጥኩም የሚል ያድምጥ፡
For any elaboration or spiritual questions:
ጥያቄ/ማብራርያ ለምትሹ፤
Contact with 0910-12-72-72
Everyday from Monday to Friday mid-day 6:30-7:30, night time 1-3 and on Sunday at any time.
ዘወትር ሰኞ እስከ ዐርብ ከቀኑ 6፡30 እስከ 7፡30 ማታ ከምሽቱ 1-3 ሰዓት እና እሑድ ሙሉ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ስልክ ደውላችሁ ልታገኙን ትችላላችሁ፡፡
መንግሥተ ሥላሴ ዘደቂቀ ኤልያስ አሐቲ ጉባኤ ሰማያዊት።
#ሰንበት #ተዋሕዶ #እትዮጵያ
በፌስቡክ፦ https://facebook.com/mengesteselassie
በዩቲዩብ፦ https://www.youtube.com/
በቲክቶክ፦ https://tiktok.com/
የእትዮጵያ አምላክ እግዚአብሔር ለመጨረሻው ፍርድ በአካል እንደመጣና አሮጌው ሰማይና ምድር እያለፈ፥ አዲስ ሰማይና ምድርም እየተዘረጋ መሆኑን ለፍጥረት ሁሉ ማወጅ