Meleket / የመለከት ድምፅ

Meleket / የመለከት ድምፅ የመለከት ድምጽ አገልግሎት ዓላማ የእግዚያብሄርን ቃል በማስተማር ሰዎች ለተጠሩለት ጌታ እንዲዘጋጁ ማንቃት ነው።
Voice of the Trumpet serves to be the voice of Jesus.

06/01/2024

የዕብራውያን መልዕክት ጥናት በሄኖክ አፈወርቅ(ፓ/ር)"ወደ ዕረፍቱ ለመግባት እንትጋ""ልባችሁን እልከኛ አታድርጉ""ሁሉን ያዘጋጀ እግዚአብሄር ነው።"

የዕብራውያን መልዕክት ጥናት ሶስተኛው ክፍል በYouTube ቻናላችን ተለቛል። ጥያቄ ካሎት በInbox እንዲሁም በComment ማስቀመጥ ይችላሉ።
05/01/2024

የዕብራውያን መልዕክት ጥናት ሶስተኛው ክፍል በYouTube ቻናላችን ተለቛል። ጥያቄ ካሎት በInbox እንዲሁም በComment ማስቀመጥ ይችላሉ።

የዕብራውያን መልዕክት ጥናት በሄኖክ አፈወርቅ(ፓ/ር)የኢየሱስ የክህነት አገልግሎት እንደ መልከጸዴቅ አይነት ነው።የመለከት ድምፅ አገልግሎት

የዕብራውያን መልዕክት ጥናት ሁለተኛው ክፍል በYoutube ቻናላችን ላይ ተለቋል። ጥያቄዎች እና ሀሳብ ካሎት በInbox እንዲሁም በcomment ማስቀመጥ ይችላሉ።
27/12/2023

የዕብራውያን መልዕክት ጥናት ሁለተኛው ክፍል በYoutube ቻናላችን ላይ ተለቋል። ጥያቄዎች እና ሀሳብ ካሎት በInbox እንዲሁም በcomment ማስቀመጥ ይችላሉ።

የዕብራውያን መልዕክት ጥናት በሄኖክ አፈወርቅ(ፓ/ር)"ወደ ዕረፍቱ ለመግባት እንትጋ""ልባችሁን እልከኛ አታድርጉ""ሁሉን ያዘጋጀ እግዚአብሄር ነው።"

የዕብራውያን መልዕክት ጥናት የመጀመሪያውን ክፍል በYoutube ቻናላችን ላይ ተለቋል። ጥያቄዎች እና ሀሳብ ካሎት በInbox እንዲሁም በcomment ማስቀመጥ ይችላሉ።
11/12/2023

የዕብራውያን መልዕክት ጥናት የመጀመሪያውን ክፍል በYoutube ቻናላችን ላይ ተለቋል። ጥያቄዎች እና ሀሳብ ካሎት በInbox እንዲሁም በcomment ማስቀመጥ ይችላሉ።

የዕብራውያን መልዕክት ጥናት በሄኖክ አፈወርቅ(ፓ/ር)መልአክት ከኢየሱስ ጋር ለምን ተነፃፀሩ?የመለከት ድምፅ አገልግሎት

11/01/2021

"የዮሐንስ ራዕይ ማብራሪያ" መጽሐፍ የት እንደሚገኝ ለጠየቃችሁኝ፣ ሁለተኛውን እትም በመሰረተ ክርስቶስና በራዕይ መጽሐፍት መደብር ታገኛላችሁ!! ይህ መጽሐፍ በነገረ ጉዳዩ ላይ መሰረታዊ መረዳት እንዲኖራችሁና የዮሐንስን ራዕይ ለሌሎች ማጋራት እንድትችሉም ያደርጋል።

20/06/2020

ለምን እግዚያብሄር ያቺን ዛፍ በገነት አበቀለ?

በገነት ውሰጥ የሕይወት ዛፍ ብቻ ሳይሆን ሌሎች ዛፎችም በየዓይነታቸው ነበሩ (ዘፍ 2፡ 9-10)፤ በተለይም ደግሞ መልካሙንና ክፉውን የሚያሳውቅ ሌላ ዛፍ በአንጻሩ ተጠቅሶ ይገኛል። ስለዚህች ዛፍ ብዙ ነገር ሲባል ይደመጣል። ከእነዚህም፤ እግዚያብሄር ለምን አበቀላት?! ሰው እንዲወድቅ ስለተወሰነበት ነው!? የመሳሰሉ ናቸው። ደግሞ እግዚያብሄር በሰው ውደቀት ለመክበር አቅዷል ለማለት የሚዳዳውም ይመስላል። እውነት ግን አይመስለኝም።

ሁለቱ ዛፎች በኤደን ገነት መቀመጣቸው በትንሹ ሁለት ነገር ጠቋሚ ናቸው።

የመጀመሪያው ሰው ነጻ ምርጫ ኖሮት እንደ ተፈጠረ ማረጋገጫው ይህች ዛፍ ናት ለማለት ይቻላል። ሕይወት ወይም ሞት በፊቱ የተሰጡ የሕይወት ምርጫዎች ናቸው። ከእግዚያብሔር ጋር ለመኖር ወይም ከገነት ውጭ ለመኖር ፈቃድ ነበረው። እነዚህ ዛፎች ባይኖሩ ሰው ምርጫ ያለው ፍጥረት መሆኑ ግልጽ አይሆንም ነበር። የሕይወትን ዛፍ ብቻ ቢሰጠውና ሕይወት እንዴት ነው? ተብሎ ይህ ሰው ቢጠየቅ፣ ‘ምን ምርጫ አለኝ የተፈረደብኝን እየኖርኩ ነው ይል ነበር’። አሁን ግን መምረጥ ይችላል፤ ምክንያቱም በፊቱ አማራጭ ቀርቦለታል። መምረጥ መቻሉንም በተግባር አሳይቷል። ሰው ከመውደቁ በፊት ነጻ ፈቃድ እንደነበረው አስመስክሯል።

በተጨማሪም ሁለተኛይቱ ዛፍ የመጀመሪያው ሰው ተወክሎ የሚገዛ ገዥ እንደሆነ እንድታስታውሰው የተሰጠች ትመስላለች። ሁሉን እንዲያደርግ ስልጣን ከእግዚያብሔር ቢሰጠውም ሁሉን ቻይ እንዳልሆነ ትነግረዋለች። የፈለገውን የሚያደርግበት ሥልጣን ቢኖረውም ለዚህ የበላይ አካል እርሱም መገዛት እንዳለበት ‘ከዚህ እንዳትበላ’ የምትለው ዛፍ ታስታውሰዋለች። ምክንያቱም ሁሉን መብላትም ሆነ ማድረግ ይችላል፤ ነገር ግን ከዚህ ‘አትብላ የሚለው ቃል’ ከእርሱ የሚበልጥ ሌላ የበላይ እንዳለው የሚነግር መመሪያ ነው። ይህንም ቃል የምታስታውሰው ይህችው ዛፍ ናት።

ሰው በሁሉም ላይ ስልጣን እንዳለው ሲያስብና ሲያደርግ ይህች ዛፍ እርሱን ደግሞ ያዘዘው ሌላ ኃላፊ እንዳለው እናም እንዳዘዘው ጠቋሚ በመሆን እንድታገለግለው ተሰጥታው ነበር። እርሷን የበላ ቀን አዳም በተግባሩ የተናገረው ከእኔ ሌላ የበላይ የለም አምላክ ‘እኔ ነኝ’ ማለቱ ነው። ይህች ዛፍ ከእርሱ የሚበልጥ አምላክ እንዳለ ባትነግረው ይህንን አላወቅኩም ይል ነበር። አሁን ግን በእውቀትና በምርጫው ሰው ተሳስቷል።

እናም ለመልካም የነበረችው ይህች ትዕዛዝ ሰው በራሱ ምኞት በመጓዙ ሌላኛውን የሕይወት ክፍል አሳየችው እርሱም ለሞት በቃ። ነገር ግን አሁን በራዕይ (2፡7) እንደገና ከሞት ወደ ሕይወት የመመለስን ተስፋ ጌታ ኢየሱስ ድል ለነሳው ቤ/ክ ያስታውሳል።

12/06/2020

እርጉዟ ሴት ማን ናት?

በራዕይ 12 አንድ የሚያስደንቅ ምልክት በሰማይ እንዳየ ዮሐንስ ተናግሯል። በምዕራፉም አራት ማንነቶች በግልጽ ተነግረዋል (እርጉዟ ሴት፣ ወንድ ልጇ፣ ዘንዶው/ሰይጣን/ና ሚካኤል ናቸው)። የዘንዶውና የሚካኤል ማንነት በምሁራኑ አከባቢ ብዙም አሻሚ ሆኖ አይታይም። ምክንያቱም ክፍሉ ራሱ ዘንዶው ሰይጣን እንደ ሆነ በግልጽ ስለሚናገርና ሚካኤል ደግሞ መልአክ መሆኑ በግልጽ ስለሚታወቅ ነው። ነገር ግን የቀሩት ሁለቱ የክርክር ምክንያት ሆነው ይታያሉ።

አንዳንዶች እንደ ተረጎሙት እርጉዟ ሴት ቤ/ክ ስትሆን ልጇ ደግሞ መሲሁ ነው። ይሁንና ይህ ምልከታ አንዱ ከአንዱ ጋር ያለውን የሃሳብ ግንኙነት ምክንያታዊ በሆነ መንገድ አስረድቷል ብሎ ለመናገር ያስቸግራል። ምክንያቱም ቤ/ክ ኢየሱስን እንደወለደችው ፍንጭ የሚሰጥ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ክፍል መገኘቱን እጠራጠራለሁ። በመሆኑም ለቤ/ክ መወለድ ምክንያት ሊሆን የቻለው ኢየሱስ ነው እንጂ የተገላቢጦሽ ሊሆን አይችልም።

በሌላ በኩል ደግሞ ሴቲቱን የኢየሱስ እናት ማርያምን አድርጎ የመመልከት ዝንባሌ ይታያል። አሁንም ክፍሉ በግልጽ እንደሚናገረው ምልክት ከመሆኑ ባሻገር ማርያም በዚህ ክፍል በተጠቀሰው አይነት መንገድ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ እንደ ምልክት ተጠቅሳ አይታይም። በእርግጥ ቅድስት ማርያም ወደ ግብጽ ተሰዳ የነበረችበት ሁኔታ እንደ ነበረ እሙን ነው፤ ይሁንና ከእጮኛዋ ዮሴፍና ከልጇ ኢየሱስ ጋር ነበር። በዚህ ክፍል የምትታየው ሴት ግን ለብቻዋ ወደ ምድረ በዳ መሰደዷ ከኢየሱስ እናት ማርያም የተለየች እንድትሆን ያደርጋታል። በተጨማሪም ይህ ክፍል ልጇ ተነጠቀ ብሎ ይናገራል። ነገር ግን ኢየሱስ እንደ ተወለደ ወደ ሰማይ መወሰዱን የሚያረጋግጥ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል አሁንም አይገኝም።

ይህች ሴት ግን እርጉዝ ናት፣ ዘንዶው የሚወለደውን ልጇን ሊውጥ በፊቷ ተደቅኗል፣ ልጇ ወደ ሰማይ ተነጠቀ፣ እርሷ ግን ወደ ምድረ በዳ ከዘንዶው ፊት 1260 ቀናት ሸሸች።
በዚህ ክፍል የተነገረላት ሴት በዮሴፍ ህልም ውስጥ ያለውን ፍች የምትወክል ማንነት ትሆን እንዴ (ዘፍ 37፡9-10)?

09/06/2020

የዮሐንስ ራዕይ ማብራሪያ የጥናት መምሪያ ተዘጋጅቷል። ራዕይን በቤተሰብም ሆነ በግል ለማጥናት የምትፈልጉ ይህ የጥናት መምሪያ በነፃ ተበርክቷል። እንደምትፈልጉ ብቻ ምልክት ስጡን በኢሜልም ሆነ በሜሴንጀር ልልክላችሁ ዝግጁ ነኝ።

Address

Addis Ababa
1000

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Meleket / የመለከት ድምፅ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share