የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ Ircaa

የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ Ircaa We work to be an excellent and united Inter –Religious Forum!!

 #የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የ2019 ዓ.ም የአዲስ ዓመት የመልካም ምኞት  #መልዕክትየአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ አዲሱ ዓመት ለመላው የአዲስ አበባ ነዋሪዎች፣ ለመላ...
10/09/2026

#የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የ2019 ዓ.ም የአዲስ ዓመት የመልካም ምኞት #መልዕክት

የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ አዲሱ ዓመት ለመላው የአዲስ አበባ ነዋሪዎች፣ ለመላው ኢትዮጵያውያን እና በዓለም ለሚትገኙ ኢትዮጵያዊያን በሙሉ የሰላም፣ የአንድነት፣ የፍቅር፣ የተስፋና የብልጽግና ዓመት እንዲሆንላችሁ ይመኛል።

አዲስ ዓመት አዲስ ዘመን ብቻ ሳይሆን፣ አዲስ ተስፋ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ትብብርና የተሻለ ነገን በአዲስ መልክ ለመጀመር ዕድል የሚሰጠን ዓመት ነው። ስለዚህ በአዲሱ ዓመት ከፍርሃት ይልቅ ተስፋን፣ ከጥላቻ ይልቅ ፍቅርን፣ ከመከፋፈል ይልቅ አንድነትን፣ ከግጭት ይልቅ ሰላምን እንድናስቀድም በጉባኤያችን ስም ጥሪያችንን እናቀርባለን።

#ኢትዮጵያ በብዝሃነት ደምቃ የተለያዩ ሃይማኖቶች፣ ማህበረሰቦች ተከባብረው የሚኖሩባት የብዝሀ የማንነት ሀገር ናት። ይህ ብዝሃነት የመከፋፈል ምክንያት ሳይሆን የጋራ ጥንካሬያችን የሀገራችን መገለጫ እና የጋራ ሀብታችን እንዲሆን ሁላችንም እንደ ቀድሞ ሁሉ በአዲሱ ዓመትም የድርሻችንን ልንወጣ ይገባል።

የሃይማኖት ተቋማት እንደ ሁልጊዜው ሰላምን ለመገንባት፣ ማህበራዊ ትብብርን ለማጠናከር፣ የሰው ልጆች ክብር እንዲጠበቅ መስራት፣ ርህራሄንና መተሳሰብን ለማሳደግ እና ለሀገራዊ ሰላም፣ ልማትና ልዕልና ከመፀለይና ዱኣ ከማድረግ ባለፈ እንደ ቀድሞ ሁሉ በጋራ ለመስራት አጋርነታችንንና ቁርጠኝነታችንን የምናሳይበት ዓመት ሊሆን ይገባል።

በዚህ #አዲስ ዓመት ለወጣቶቻችን አዲስ ተስፋና ዕድል፣ እንዲሆንላቸው ለመላው ማህበረሰባችን ፍቅርና ሰላም፣ ለሀገራችን አንድነት መረጋጋት፣ ዕድገት ልማት እና የተሻለ ሰላማዊ ኑሮ እንዲሆንላቸው እንመኛለን።

ዓመቱ የሰላም ዓመት፣ የአንድነት ዓመት፣ የተስፋ ዓመት የመልካም ለውጥና ዕድገት ዓመት እንዲሆንልን እየተመኘን ፈጣሪ ለአዲስ አበባና ለመላው ኢትዮጵያዊያን ሰላሙን፣ ፍቅሩንና በረከቱን እንዲያበዛልን እንመኛለን።

በመጨረሻም አዲስ ዓመት ስንቀበል ለአቅመ ደካሞች ካለን በማካፈል በመደገፍ የታመሙትን በመጠየቅ የታረዙትን በማልበስ አምላክ ለሰው ልጆች ያሳየውን ፍቅር በማሳየት አዲሱን ዓመት እንድንቀበል በጉባኤያችን ስም ጥሪያችንን እናቀርባል።

በድጋሚ #እንኳን ለአዲሱ ዓመት በሠላም በጤና አደረሳችሁ! እያልን አዲሱ ዓመት የሰላም የፍቅር የአብሮነት የመከባበር የዕድገትና የበረከት ዓመት እንዲሆንላችሁ እንመኛለን።

የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ 2019ዓ.ም

ጳጉሜ 4/2019ዓ.ም

በማህበራዊ ሚዲያዎች #ቤተሰብ ይሁኑ !!! መረጃዎችን ባሉበት ሆነው ይከታተሉ!!
➽ የዩቲዮብ ገጻችን Subscribe
https://www.youtube.com/
➽የቴሌግራም ገጻችን Subscribe ያድርጉ
https://t.me/IRCAA2020
➽ ዌብ ሳይታችንን ይጎብኙ
https://ircaddisababa.org/

የአዲስ አባባ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ከአዲስ አበባ የአመራር አካዳሚ እና ከአዲስ አበባ የሰላም እና ጸጥታ ቢሮ ጋር በመተባበር ሲያካሂደው የነበረው የአሰልጣኞች ስልጠና ተጠናቀቀ።በአዲስ አበ...
04/09/2026

የአዲስ አባባ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ከአዲስ አበባ የአመራር አካዳሚ እና ከአዲስ አበባ የሰላም እና ጸጥታ ቢሮ ጋር በመተባበር ሲያካሂደው የነበረው የአሰልጣኞች ስልጠና ተጠናቀቀ።

በአዲስ አበባ አመራር አካዳሚ የስልጠና ማዕከል ለ4 ቀን ሲሰጥ የነበረው የአሰልጣኞች ስልጠና በዛሬው እለት ተጠናቋል።

በመረሃ ግብሩ መዝጊያ ላይ የአዲስ አባባ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ም/ዋና ጸሐፊ ሼህ አብዱልሃሚድ አሕመድ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን በመልዕክታቸውን ጉባኤያችን ለከተማችን የሰላም እሴት ግንባታ እና ሞራል እሴት ላይ ሲሰራ የነገ ሀገር ተረካቢ የሆኑት ትውልዶች እራሳቸውን ብቁ እና ተወዳዳሪ አድርገው እንዲያዘጋጁ ሰላሟ የተጠበቀ አዲስ አበባን አልፎን ኢትዮጵያን እንዲረከቡ ያለመ መሆኑን ጠቅሰው ለዚህ ደግሞ ዛሬ በዚህ ስልጠና የተሳተፋችሁ አመራሮች ከፍተኛ ድርሻ አለባችሁ ብለዋል።

ም/ዋና ጸሐፊው አክለው ብቁ በሆኑ አመራሮች ሲሰጥ የቆየው ስልጠና እራሳችሁ ተጠቅማችሁ ሌሎችን እንድትጠቅሙ ያለመ ስለሆነ ከዚህ ሰዓት ጀመሮ ሌሎችን በስልጠና ለማስታጠቅ ተዘጋጁ ብለዋል።

የአዲስ አበባ አመራር አካዳሚ የፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አሰፋ አሰፈራሁ በበኩላቸው ለከተማችን አዲስ አበባ አዲስ ነገርን ለማበርከት በሰለጠናችሁት ልክ ልትሰሩ ይገባል ያሉ ሲሆን የሃይማኖት መሪዎችን ብዙዎች ስለሚሰሙ የሰለጠናችሁትን ለሌሎች ለማሰልጠን ተዘጋጁ ሰላም ላይ ለመስራት ተዘጋጁ ብለዋል።

የአመራር አካዳሚውም በቀጣይ ያለውን ግንኙነት አሳድጎ ለከተማችን ብቁ አመራሮችን ከማፍራት አንጻር አብሮ እንደሚሰሩ ተናግረዋል።

የሰላም እሴት ግንባታን በማጠንከር ብቁ የሆኑ አመራሮችን ከማፍራት አንጻር ተቋማቸው የተጀመረውን ስራ አጠንክሮ እንደሚቀጥል የተናገሩት ደግሞ የአዲስ አበባ የሰላም እና ጸጥታ አስተዳደር ም/ቢሮ የሆኑት ክብር አቶ ብርሃኑ ረታ ናቸው። ክቡር አቶ ብርሃኑ በመድረኩ በመገኘት ተቋሙ የአሰልጣኞች ስልጠና እየወሰዱ ያሉ ሰልጣኞች ያበረታቱ ሲሆን በሚቀጥለው ተጨማሪ ስልጠናዎችን በመስጠት መሪዎች ብቁ እንዲሆኑ እና ለከተማቸው አልፎም ለሀገራችን አበርክቶዓቸው ከፍ እንዲል እንደሚሰሩ ተናግረዋል።

በዛሬው የማጠቃለያ መድረክ ሰልጣኞች ካገኙት ልምድ አንጻር ያላቸውን ተሞክሮ ያካፈሉ ሲሆን የአሰልጣኞች ስልጠና (TOT) ተከታትለው ላጠናቀቁ በአመራሮች አመካኝነት የምስክር ወረቀት በመስጠት መረሃ ግብሩ ተጠናቋል።

የአዲስ አባባ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ለከተማችን የሰላም እሴት ግንባታ እና ሞራል እሴት ግንባታ ላይ ሲሰራ መሪዎች ብቁ እንዲሆኑ ተመሳሳይ ይዘት ያላቸውን ስልጠና አጠንክሮ የሚቀጥል ይሆናል።

በማህበራዊ ሚዲያዎች #ቤተሰብ ይሁኑ !!! መረጃዎችን ባሉበት ሆነው ይከታተሉ!!
➽ የዩቲዮብ ገጻችን Subscribe
https://www.youtube.com/
➽የቴሌግራም ገጻችን Subscribe ያድርጉ
https://t.me/IRCAA2020
➽ ዌብ ሳይታችንን ይጎብኙ
https://ircaddisababa.org/

የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ከአዲስ አበባ አመራር አካዳሚ እና ከአዲስ አበባ የሰላም እና ጸጥታ ቢሮ ጋር በቅንጅት እያካሄደ ያለው የአሰልጣኞች ስልጠና እንደቀጠለ ነው።አራት ኪሎ ...
03/09/2026

የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ከአዲስ አበባ አመራር አካዳሚ እና ከአዲስ አበባ የሰላም እና ጸጥታ ቢሮ ጋር በቅንጅት እያካሄደ ያለው የአሰልጣኞች ስልጠና እንደቀጠለ ነው።

አራት ኪሎ በሚገኘው በአዲስ አበባ ስራ አመራር አካዳሚ እየተሰጠ በሚገኘው በዚህ የአሰልጣኞች ስልጠና 60 የሚደርሱ ከሁሉም አባል ቤተዕምነቶች የተወጣጡ ሰልጣኞች እየተሳተፉበት የሚገኝ ሲሆን ተሳታፊዎቹ ከዚህ የአምስት ቀን ቆይታ በኋላ ለግላቸውና ለተቋማቸው የሚጠቅም ቁም ነገር ይዘው እንደሚወጡ ይጠበቃል።

በስልጠናው አንድ አሰልጣኝ ለሌሎች ዕውቀቱን በሚያካፍልበት ጊዜ ሊኖረው የሚገባው ክህሎት፤ መከተል ያለበት የአሰለጣጠን ዘዴ፤ የአሳታፊነቱ ጉዳይና ሌሎችም ጠቃሚ ነጥቦች ተነስተዋል።
Addis Ababa City Peace and Security Administration Bureauአዲስ አበባ አመራር አካዳሚ Addis Ababa Leadership Academy

በማህበራዊ ሚዲያዎች #ቤተሰብ ይሁኑ !!! መረጃዎችን ባሉበት ሆነው ይከታተሉ!!
➽ የዩቲዮብ ገጻችን Subscribe
https://www.youtube.com/
➽የቴሌግራም ገጻችን Subscribe ያድርጉ
https://t.me/IRCAA2020
➽ ዌብ ሳይታችንን ይጎብኙ
https://ircaddisababa.org/

1501ኛውን የነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) መውሊድ ምክንያት በማድረግ በቃሊቲ ማረሚያ ማዕከል ለሚገኙ ታራሚዎች የማዕድ ማጋራትና የዚያራ ፕሮግራም ተካሄደ።በታላቁ አንዋር መስጂድ ኮሚቴ፣ በመስጂዱ አስተ...
03/09/2026

1501ኛውን የነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) መውሊድ ምክንያት በማድረግ በቃሊቲ ማረሚያ ማዕከል ለሚገኙ ታራሚዎች የማዕድ ማጋራትና የዚያራ ፕሮግራም ተካሄደ።

በታላቁ አንዋር መስጂድ ኮሚቴ፣ በመስጂዱ አስተዳደር እና በመስጅዱ የወጣት ጀመዓ በጥምረት በተዘጋጀው በዚህ ፕሮግራም፤ የነብዩ መሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) 1501ኛውን መውሊድ ምክንያት በማድረግ በፌደራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን የከፍተኛ ጥበቃ ማረሚያ ማዕከል ከታራሚዎች ጋር የማዕድ ማጋራት፣ የዚያራ እና የበዓል አከባበር ስነ-ስርዓት በደመቀ ሁኔታ ተከናውኗል።

በፕሮግራሙ ላይ የማረሚያ ቤቱ እና የመስጂዱ ከፍተኛ ሃላፊዎች ተገኝተው ከታራሚዎች ጋር በጋራ ያሳለፉ ሲሆን፣ የማህበረሰብ አንድነትንና መደጋገፍን በሚያጠናክር መልኩ በዓሉ ተከብሮ ውሏል።

በዕለቱ በቦታው ተገኝተው በዓሉን ያከበሩት ኮሚሽነር ጀነራል ዩኑስ ሙሉ፣ የቃሊቲ ማረሚያ ማዕከል ዳይሬክተር ኮሚሽነር ፍቃዱ፣ የጥበቃና ደህንነት ኮማንደር ሙህዲን፣ የመስጂዱ ኮሚቴ አባላት ሸህ አብዱሹኩር እና ሸህ ያሲን ሰልማን፣ እንዲሁም የወጣት ጀመዓው አሚር ወጣት ኢሳ ሙዘይን እና የታላቁ አንዋር መስጂድ ወጣቶች ናቸው።

የወጣት ጀመዓው የፕሮግራሙን መሳካት በማስመልከት ለተባበሩት የመንግስት አካላት፣ ለመስጂዱ ጀመዓዎች እና ተሳትፎ ላደረጉ ግለሰቦች ሁሉ የላቀ ምስጋናውን አቅርቧል።

ምንጭ Nejashi TV ነጃሺ ቲቪ

በማህበራዊ ሚዲያዎች #ቤተሰብ ይሁኑ !!! መረጃዎችን ባሉበት ሆነው ይከታተሉ!!
➽ የዩቲዮብ ገጻችን Subscribe
https://www.youtube.com/
➽የቴሌግራም ገጻችን Subscribe ያድርጉ
https://t.me/IRCAA2020
➽ ዌብ ሳይታችንን ይጎብኙ
https://ircaddisababa.org/

ወቅታዊ የኩነት ምዝገባን ለማሳደግ ከሀይማኖት ተቋማት ጋር በቅንጅት መስራት አስፈላጊ መሆኑ ተገለፀ።የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ከሀይማኖት ተቋማት መሪዎች፣ ባለሙያዎች ...
02/09/2026

ወቅታዊ የኩነት ምዝገባን ለማሳደግ ከሀይማኖት ተቋማት ጋር በቅንጅት መስራት አስፈላጊ መሆኑ ተገለፀ።

የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ከሀይማኖት ተቋማት መሪዎች፣ ባለሙያዎች እና ከባለድርሻ አካላት ቅንጂታዊ አሰራርን በማጎልበት የ2019 በጀት ዓመት ወቅታዊ የኩነት ምዝገባን ለማሳደግ የሚያስችል የንቅናቄ መድረክ አካሂዷል፡፡

የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮሴፍ ንጉሴ በ119 ወረዳዎች ፣ በ157 የጤና ተቋማት እንዲሁም በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ እና በሸሪዓ ፍርድ ቤቶች ኩነቶችን እየመዘገበ እንደሚገኝ ገልፀው በሀይማኖት ተቋማት የሚከሰቱ ኩነቶች በወቅቱ አለመመዝገብ ለስታስቲካዊ መረጃ ለመንግስት የፖሊሲ ቀረፃ ላይ ተፅዕኖ የሚያሳድር በመሆኑ ቅንጅታዊ አሰራር በመዘርጋት ማስተካከል እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጂ በቢሮ ኃላፊ ማዕረግ የአገልግሎት አሰጣጥ ዘርፍ ኃላፊ ዶ/ር ተፈራ ሞላ ኤጀንሲው ሰፊ እና መሰረታዊ ሪፎርም በማድረግ ፈጣን፣ ቀልጣፋ እና በቴክኖሎጂ የተደገፈ የህዝብ አገልግሎት ስጭ ተቋም ማድረግ መቻሉን ጠቅሰው የተሟላ የኩነት ምዝገባ ለማድረግ ከሀይማኖት ተቋማት ጋር ቅንጂታዊ አሰራር በመዘርጋት እና የሚከሰቱ ኩነቶችን በወቅቱ በማስመዝገብ የተጀመረውን የስማርት ከተማነት ማፋጠን እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

ስለ ወቅታዊ ኩነት ምዝገባ አስፈላጊነት፣ ለሀገር እና ለግለሰቦች የሚያበረክተው ጠቀሜታ እና አሁናዊ ነባራዊ ሁኔታ እንዲሁም ኤጀንሲው የኩነት ምዝገባን ለማሳደግ እያደረገው ያለው እንቅስቃሴ ዙሪያ በኤጀንሲው የጥናትና ስልጠና ቡድን መሪ አቶ ደረጃ ፈንታ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሰነድ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡

በመድረኩ የተሳተፉ የሀይማኖት ተቋማት መሪዎች እና ባለሙያዎች ከኤጀንሲው ጋር በጋራ ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውን የገለፁ ሲሆን በኩነት ምዝገባ ዙሪያ ለቀረቡ ጥያቄዎች እና አስተያየቶች በኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ የሴፍ ንጉሴ እና በእለቱ የክብር እንግዳ ዶ/ር ተፈራ ሞላ ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቷል፡፡

Addis Ababa CRRSA - Civil Registration and Residency Service Agency

ነሃሴ 27/2018 ዓ.ም
አዲስ አበባ

በማህበራዊ ሚዲያዎች #ቤተሰብ ይሁኑ !!! መረጃዎችን ባሉበት ሆነው ይከታተሉ!!
➽ የዩቲዮብ ገጻችን Subscribe
https://www.youtube.com/
➽የቴሌግራም ገጻችን Subscribe ያድርጉ
https://t.me/IRCAA2020
➽ ዌብ ሳይታችንን ይጎብኙ
https://ircaddisababa.org/

የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ከአዲስ አበባ አመራር አካዳሚ እና ከአዲስ አበባ የሰላም እና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ጋር በመተባበር የአሰልጣኞች ስልጠና መስጠት ጀመረ።በመረሃ ግብሩ የ...
02/09/2026

የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ከአዲስ አበባ አመራር አካዳሚ እና ከአዲስ አበባ የሰላም እና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ጋር በመተባበር የአሰልጣኞች ስልጠና መስጠት ጀመረ።

በመረሃ ግብሩ የአዲስ አበባ አመራር አካዳሚ የስልጠና ካታሎግ በማስመረቅ የ2019 በጀት ዓመት የስልጠና ፕሮግራሙን በይፋ ማስጀመሩን አሳውቋል።

በስነ-ስርዓቱ ላይ አቶ አሰፋው አስፈራ የፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ኃላፊ አካዳሚው ለመንግስትና መንግስታዊ ላልሆኑ ተቋማት ስልጠና በመስጠት፣ ጥናትና ምርምር በማካሄድ፣ የማማከርና የማህበረሰብ አገልግሎት የመስጠት ሀላፊነት እንዳለበት የጠቆሙ ሲሆን ከባለድርሻ አካላት ጋር በየሩብ ዓመቱ እየተገናኙ አፈጻጸምን መገምገም ለላቀ ውጤት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው ገልጸዋል።

አቶ ድርሻዬ አለማየሁ የመማክርት ጉባኤ ሰብሳቢ በበኩላቸው የስልጠና ማስጀመሪያው በ2018 በጀት ዓመት የታዩ ክፍተቶችን በመለየት በ2019 የተሻለ ስራ ለመስራት ጥሩ አጋጣሚ መሆኑን ገልጸዋል። አካዳሚው በቴክኖሎጂ የተደገፈ አገልግሎት በመስጠት የተገልጋዮችን እርካታ ለማሳደግ እንደሚሰራና የመማክርት ጉባኤውም አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል።

"ስልጠና ወፎች እንዲዋኙና አሳዎች እንዲበሩ አያደርግም፤ ለተፈጠሩበት ዓላማ ግን በተሻለ መልክ እንዲሰሩ ያደርጋል" ያሉት ደግሞ የከተማ አመራር ልማት ዘርፍ ምክትል ፕሬዝዳንት የሆኑት ዶክተር ተስፋዬ ኤባ ናቸው።

ሀገራችን በምታደርገው የማንሰራራት ጉዞ ውስጥ በእውቀት፣ በክህሎትና በአስተሳሰብ መታጠቅ ለሀገር ግንባታ ወሳኝ መሆኑን ጠቁመው፣ ተቋማት የተቋቋሙለትን ዓላማ ከግብ ለማድረስና የአመራሩና የባለሙያውን አቅም ለመገንባት አካዳሚው የስልጠና ካታሎግ አዘጋጅቶ ወደ ስራ መግባቱን አስረድተዋል።

በመጨረሻም የሀይማኖት ተቋማት፣ የመማክርት ጉባኤው እና ባለድርሻ አካላት አመራሮች ከአካዳሚው ጎን በመሆን ድጋፋቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅርበዋል።

ስልጠናው እስከ ነሃሴ 30/2018 ዓ.ም የሚቀጥል ይሆናል።

በማህበራዊ ሚዲያዎች #ቤተሰብ ይሁኑ !!! መረጃዎችን ባሉበት ሆነው ይከታተሉ!!
➽ የዩቲዮብ ገጻችን Subscribe
https://www.youtube.com/
➽የቴሌግራም ገጻችን Subscribe ያድርጉ
https://t.me/IRCAA2020
➽ ዌብ ሳይታችንን ይጎብኙ
https://ircaddisababa.org/

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የምስረታ 15ኛ ዓመት እና 18ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ እየከናወነ ይገኛል።በመረሃ ግብሩ ላይ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀሥላሴን ጨምሮ የኢትዮጵያ የሃይ...
01/09/2026

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የምስረታ 15ኛ ዓመት እና 18ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ እየከናወነ ይገኛል።

በመረሃ ግብሩ ላይ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀሥላሴን ጨምሮ የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የበላይ ጠባቂ አባቶች ፤ የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ቦርድ አመራሮችና የክልል ጉባኤ አመራሮች ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸው ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች እየተሳተፉ ይገኛል።

"15 ዓመታት እምነትን በቀጣይነት፣ ሰላምን ህብረብሔራዊ ልማት በኢትዮጵያ" በሚል መሪ ቃል እየተከናወነ ባለው መረሃ ግብር በክብር እንግዳነት የተገኙት የኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት ክቡር ታዬ አጽቀስላሴ የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ለ15 ዓመታት ያካሄደው የጋራ ጉዞ በእምነት ተቋማት ትብብርን በማጠናከር፣ ሰላምንና ማህበራዊ ውህደትን በማሳደግ ለሀገራዊ እድገትና ልማት ወሳኝ ሚና ተጫውቷል ብለዋል።

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጠቅላይ ጸሐፊ ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ በበኩላቸው የጋራ ሀብታችን የሆነው ሰላም መጠበቅ እና ማበልጸግ የሚቻለው ሁላችንም ኃላፊነታችንን መወጣት ስንችል ነው ያሉ ሲሆን ሁላችንም ባለንበት አካባቢ እና ተቋም ውስጥ ለሰላም ግንባታ አስተዋጽኦ በማበርከት የሰላም ምሳሌ በመሆን ሰላምን ልናጸና ይገባናል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

የሃይማኖት ተቋማት የሀገራችንን ሰላምና አብሮነት ላይ ላለፉት አስራ አምስት አመታት በመስራት ታሪካዊ ድል ማስመዝገቡን የተናገሩት ደግሞ የኢፌዲሪ የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር አቶ ሙሀመድ ኢድሪስ ናቸው።

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የጠቅላላ ጉባዔና የሥራ አመራር ቦርድ አባል የሆኑት ዑስታዝ ሀሰን ዓሊ ባደረጉትን ንግግር አባል የሃይማኖት ተቋማቱ ከመንፈዊ አገልግሎታቸው ጎን ለጎን በጋራ ሀገራዊ የሰላም፣ የልማት ስራ ባሻገር በሃይማኖት ተቋማትና የሃይማኖት አባቶች መካከል የእርበእርስ ግንኙነት እንዲጠናከር ማድረጉን ተናግረዋል።

በመድረኩ ለጉባኤው ስኬት የሙያዊና የፋይናንስ ድጋፍ ላደረጉ ተቋማትና ግለሰቦች በበላይ ጠባቂዎች አባቶች አማካይነት የዕውቅና ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

በመርሃ ግብር ላይ ጉባኤው ባለፉት 15 ዓመታት በሀገሪቱ ሰላም፣ አብሮነት እና ህብረብሔራዊ ልማት እንዲጸና ያከናወናቸው አዎንታዊ ተግባራት የሚገመገሙ ሲሆን፣ በቀጣይ አቅጣጫዎችና በ18ኛው መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ውሳኔዎች ላይም ምክክር ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል።

በማህበራዊ ሚዲያዎች #ቤተሰብ ይሁኑ !!! መረጃዎችን ባሉበት ሆነው ይከታተሉ!!
➽ የዩቲዮብ ገጻችን Subscribe
https://www.youtube.com/
➽የቴሌግራም ገጻችን Subscribe ያድርጉ
https://t.me/IRCAA2020
➽ ዌብ ሳይታችንን ይጎብኙ
https://ircaddisababa.org/

28/08/2026

ከሃይማኖት ተቋማት ጋር በመቀናጀት ትውልድን በእሴት የመገንባት እና ማህበራዊ አብሮነትን የማጠናከር ስራዎችን አጠናክሮ የመቀጠል ስራ እየተሰራ እንደሆነ ተገለጸ።

AMN-Addis Media Network እንደዘገበው

በማህበራዊ ሚዲያዎች #ቤተሰብ ይሁኑ !!! መረጃዎችን ባሉበት ሆነው ይከታተሉ!!
➽ የዩቲዮብ ገጻችን Subscribe
https://www.youtube.com/
➽የቴሌግራም ገጻችን Subscribe ያድርጉ
https://t.me/IRCAA2020
➽ ዌብ ሳይታችንን ይጎብኙ
https://ircaddisababa.org/

“ወጣቶች ለውይይት ለእርቅና ለሰላም ግንባታ የሚኖራቸው አስተዋጽኦ” በሚል መሪ ቃል ከ100 በላይ ወጣቶች የተሳተፈበት ምክክር ተካሄደ።የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ከአሜን ኢትዮጵያ...
27/08/2026

“ወጣቶች ለውይይት ለእርቅና ለሰላም ግንባታ የሚኖራቸው አስተዋጽኦ” በሚል መሪ ቃል ከ100 በላይ ወጣቶች የተሳተፈበት ምክክር ተካሄደ።

የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ከአሜን ኢትዮጵያ ጋር በመሆን የወጣቶች የምክክር መድረክ በሶር አምባ ሆቴል አካሂዷል።

መድረኩ ወጣቶች በሃይማኖቶች መካከል ያለውን መከባበር እንዲያጠናክሩ ልዩነቶችን በውይይት እንዲፈቱ እንዲሁም ለእርቅና ለሰላም ግንባታ ግንባር ቀደም ሚና እንዲጫወቱ ለማስቻል ታስቦ የተዘጋጀ መድረክ መሆኑን የአሜን ኢትዮጵያ አስተባባሪ ወንድም ሰለሞን ተናግረዋል።

የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የክፍለ ከተማዎች መምሪያ ኃላፊ አቶ ለሜሳ ጉተታ በበኩላቸዉ ጉባኤያችን በከተማችን አዲስ አበባ የወጣቶችን ሥነምግባር ከማነፅ እና ወጣቶች ለሀገራቸዉ ሲያበረክቱ የቆዩትን አስተዋፅኦ እና በፅ/ቤት ደረጃ የተሰሩ ስራዎችን በዝርዝር ያቀረቡ ሲሆን “ሃይማኖትና ሰላም” ላይ ያተኮሩ ጉዳዮችን በማንሳት ማብራሪያ ሰጥተዋል።

አቶ እንድሪያስ ካቻሮ በበኩላቸው "እርስ በእርስ መተዋወቅ እና መረዳዳት ፣ ታሪካችን ፣ ማንነት እና ልዩነት" በሙሉ ሃሳቦች ላይ ፅሁፍ አቅርበዋል።

በመድረኩ ከተለያዩ አባል የጉባኤያችን አባል ቤተ እምነቶች የተወጣጡ ወጣቶች በትውልዱ መካከል ሰላምን ስለማስፈንና አብሮነትን ስለማጠናከር በስፋት የተወያዩ ሲሆን፣ ለሰላም ግንባታ የበኩላቸውን ድርሻ ለመወጣት መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል።

ጉባኤያችን የወጣቶችን ተሳትፎ ለማሳደግ ከዚህ ቀደም ተመሳሳይ መድረኮችን ያከናወነ ሲሆን በቀጣይ ለከተማችን ሰላም የወጣቶችን ድርሻ ከማሳደግ አንፃር ምክክሮችን አጥንክሮ የሚቀጥል ይሆናል።

ነሃሴ 21/2018
አዲስ አበባ

የሀይማኖት ተቋማት ሰዉ ተኮር የበጎ አድራጎት ስራዎች ላይ ያበረከቱትን አስተዋጽኦ አጠናክረዉ እንደሚቀጥሉ ገለፁ። ጉባኤያችን ከአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የሀይማኖት እና...
27/08/2026

የሀይማኖት ተቋማት ሰዉ ተኮር የበጎ አድራጎት ስራዎች ላይ ያበረከቱትን አስተዋጽኦ አጠናክረዉ እንደሚቀጥሉ ገለፁ።

ጉባኤያችን ከአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የሀይማኖት እና ሰላም እሴት ግንባታ ዘርፍ ጋር በመሆን ሰው ተኮርና በጎ ፈቃድ ስራዎች ላይ ያደረጉትን አስተዋጽኦ ግምገማና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ውይይት እንዲሁም የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ አሰራርና አደረጃጀት ላይ ግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ አካሂደዋል።

በመድረኩ የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ም/ዋና ፀሐፊ ሼህ አብዱልሀሚድ አህመድ በሰላምና ማህበራዊ ስራዎች ላይ በርካታ ስራዎች እንደተሰሩና እየተሰሩም እንደሆነ ገልፀው አብሮነትን በማጠናከር በዓላት በሰላም ተከብረው እንዲውሉ በስነ ምግባር የታነጸ ማህበረሰብ መፍጠር ላይ የሚሰሩትን ስራ አጠናክረው የሚቀጥሉ መሆናቸውን ገልፀዋል።

ሼህ አብዱልሃሚድ አክለው በቀጣይም በከተማው ላይ ለሚከናወን የሰዉ ተኮር ስራዎች ላይ በመሳተፍ ሀላፊነታቸውን እንደሚወጡና የሀገርን አንድነት በጽኑ መሰረት ላይ እንድትቆም ሁሉም በየቤተ እምነቱ አስተምህሮ እንዲሰሩ አሳስበዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የሀይማኖት እና ሰላም እሴት ግንባታ ዘርፍ ሀላፊ አቶ ብርሀኑ ረታ በበኩላቸው የመጣንበትን በመፈተሽ የትናንት ውጤትን በመሰነቅ አካሄድን በማስተካከል በርካታ ስራዎችን እየተሰሩ መሆናቸውን አንስተው ቢሮው በሀገር ግንባታ ላይ ከሁሉም ቤተ እምነቶችና አባቶች ጋር በዋነኝነት የሰው ልብና አዕምሮ ላይ በመንፈስ በአካል አንድ የሆነ ማህበረሰብ ለመፍጠርና የማይናወጥ ሀገር መገንባትም ላይ በልዩ ትኩረት እየሰራ መሆኑን አብራርተዋል።

ትውልድን በመገንባት ሂደት ላይ የየቤተ እምነቱ አባቶች በትኩረት መስራት እንደሚጠበቅባቸው የገለፁት የዘርፉ ኃላፊ የህዝብ ትስስር መሳሪያ የሀገር ቅርስ መጠበቅ ማለት ነገን አሻግረን የምናይበት ሀገርን በፅኑ መሰረት ማቆም ነው ለዚህም የሀይማኖት ተቋማት ትልቁን ሚና መወጣት እንዳለባቸው ገልጸዋል።

አቶ ብርሀኑ አያይዘውም ቢሮው ህዝቡን የሰላም ባለቤት በማድረግ በከተማው ላይ በሚሰራው ስራ ላይ ውጤታማ መሆኑን አስታውሰው በአለም መድረክ ላይም እንደ ሀገር ሽልማትን ማግኝት ችለናልም ሲሉ ለጸጥታ ስራ የሁሉም ማህበረሰብን ትጋት የሚጠይቅ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ እሱን በቀጣይ አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባልም ሲሉ ተደምጠዋል።

የአዲስ አበባ የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ የኮሙኒኬሽን መምሪያ ሐላፊ አቶ ዮሐንስ ግርማ የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ አሰራር እና የወረዳ አደረጃጀቶችን ማጠናከር ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷል።

ስልጠናውም ስለሰላምና አብሮነት፣ ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚተላለፍ የቆዩ ሃይማኖታዊና ባህላዊ እሴቶች ዙሪያ ያተኮረ ነው።

አቶ ታጠቅ ነጋሽ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የሀይማኖት ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት በሰው ተኮርና የበጎ ፈቃድ ስራዎች ግምገማና የ2019 ዕቅድ ላይ ጽሁፍ ያቀረቡ ሲሆን በሰው ተኮር የበጎ ፈቃድ ስራዎች ላይ በደም ልገሳ፣ በቤት እድሳት ሌሎችም ስራዎች እንደተሰሩ አብራርተው በቀጣይም ስለሚሰሩ ስራዎች ላይ የትኩረት አቅጣጫ አስቀምጠዋል።

ተሳታፊዎች በበኩላቸው በመልካም አስተዳደር ብልሹ አሰራር ላይ የሚነሱ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ቢደረግ፣ በየ ቤተእምነቱ ያሉ ችግሮችን በማረም ተጠናክረው እንደሚሰሩ በጎ ተግባር ላይ በመሳተፍ ሀላፊነታቸውን እንደሚወጡ ተናግረዋል።

ከተሳታፊዎቹ ለተነሳው ሀሳብና አስተያየት በመድረኩ ላይ አቶ ብርሀኑ ረታ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የሀይማኖት እና ሰላም እሴት ግንባታ ዘርፍ ሀላፊ፣ ሼህ አብዱልሀሚድ አህመድ የአዲስ አበባ የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ ም/ዋና ጸሀፊ ምላሽ እና ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በዉይይት መድረኩ የሁሉም ቤተ እምነት አባቶች፣ የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ የወረዳና የክ/ከተማ አመራሮች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተሳትፈዋል።

ነሀሴ 21/2018 ዓ.ም
አዲስ አበባ

በማህበራዊ ሚዲያዎች #ቤተሰብ ይሁኑ !!! መረጃዎችን ባሉበት ሆነው ይከታተሉ!!
➽ የዩቲዮብ ገጻችን Subscribe
https://www.youtube.com/
➽የቴሌግራም ገጻችን Subscribe ያድርጉ
https://t.me/IRCAA2020
➽ ዌብ ሳይታችንን ይጎብኙ
https://ircaddisababa.org/

Address

Addis Abeba, Ethiopia AMBASSADOR
Addis Ababa
1000

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ Ircaa posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ Ircaa:

Shortcuts

Share