Evangelical MEDIA/Council

Evangelical MEDIA/Council የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካውንስል

23/08/2026

የሀይማኖታ አባቶች መልዕክት በሀገራዊ ምክክር ማጠቃለያ!

23/08/2026

ክብር ምስጋና ለክርስቶስ

🇪🇹 ምስጋና ለሁሉም!የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ለ46 ቀናት ሲያከናውነው የቆየው የምክክር መድረክ በሰላም በመጠናቀቁ ደስታችንንና ምስጋናችንን እንገልጻለን።   በዚህ ረጅምና አስፈላጊ...
22/08/2026

🇪🇹 ምስጋና ለሁሉም!
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ለ46 ቀናት ሲያከናውነው የቆየው የምክክር መድረክ በሰላም በመጠናቀቁ ደስታችንንና ምስጋናችንን እንገልጻለን።
በዚህ ረጅምና አስፈላጊ የምክክር ሂደት በኃላፊነት፣ በትዕግሥትና በመከባበር ለተሳተፉ ተሳታፊዎች፣ ለኮሚሽኑ ኮሚሽነሮች፣ ውይይቱን በትጋት ሲያስተባብሩ ለነበሩ ባለሙያዎችና ሠራተኞች ከልብ የመነጨ ምስጋናችንን እናቀርባለን።
በተጨማሪም ተሳታፊዎች በሰላም ወጥተው እንዲገቡና መድረኩ በሰላም እንዲካሄድ፣ ከፈጣሪ ጥበቃ በታች ቀንና ሌሊት የደኅንነትና የሰላም ጥበቃ ሲያደርጉ ለነበሩ ሁሉ ልዩ ምስጋናችን ይድረስ።
ለመላው ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ይህንን የምክክርና የሰላም ጉዞ በጋራ እንድንደግፍ ጥሪያችንን እናቀርባለን። ልዩነቶቻችንን በውይይት እያቀራረብን፣ የሚያግባቡንን የጋራ እሴቶች እያጠናከርን፣ ለትውልድ ሰላማዊ፣ የተረጋጋችና የበለጸገች ኢትዮጵያን በጋራ እንገንባ።
ሰላም የሁላችንም ነው፤ ለሰላም መሥራትም የሁላችንም ኃላፊነት ነው! 🇪🇹

የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካውንስል
የወንጌል አማኞች ድምፅ

የ Evangelical Media/Council የዩቲዩብ ቻናልን
ሰብስክራይብ ለማድረግ ከታች ያለውን ሊንክ ይጠቀሙ
• YouTube: https://youtube.com/
• TikTok: https://www.tiktok.com/.media
• Telegram: https://t.me/EGBCC
• Website: ecgbc.org
የቤተሰባችን አባል ለመሆን Follow, Subscribe, Like እና Share በማድረግ አብረውን ይሁኑ!
ለዜና ሽፋን መልአክት ለመላክ
t.me/evangelicalmedia
📞251 991827226 ላይ ያገኙናል

ናይጄሪያ ከ100 ሺህ በላይ አብያተ ክርስቲያናት በመያዝ በዓለም ሦስተኛ ደረጃ መያዟ ተገለጸ።በStatiSense በተዘጋጀ የደረጃ አሰጣጥ መረጃ መሠረት፣ ናይጄሪያ ከ100 ሺህ በላይ የሚገመቱ...
22/08/2026

ናይጄሪያ ከ100 ሺህ በላይ አብያተ ክርስቲያናት በመያዝ በዓለም ሦስተኛ ደረጃ መያዟ ተገለጸ።

በStatiSense በተዘጋጀ የደረጃ አሰጣጥ መረጃ መሠረት፣ ናይጄሪያ ከ100 ሺህ በላይ የሚገመቱ የአብያተ ክርስቲያናት ሕንፃዎች በመያዝ በዓለም ሦስተኛ ደረጃን ይዛለች።

አሜሪካ ከ350 ሺህ እስከ 380 ሺህ የሚገመቱ አብያተ ክርስቲያናት በመያዝ በደረጃው ቀዳሚ ስትሆን፣ ብራዚል ከ280 ሺህ እስከ 300 ሺህ በሚገመቱ አብያተ ክርስቲያናት ሁለተኛ ደረጃን ይዛለች።

ሩሲያ፣ ሜክሲኮ፣ ፊሊፒንስ እና ቻይናም በዝርዝሩ ውስጥ ተካተዋል። ሆኖም የተጠቀሱት አሃዞች ይፋዊ ዓለም አቀፍ ቆጠራ ሳይሆኑ፣ በStatiSense የተጋሩ ግምታዊ መረጃዎች መሆናቸው ተጠቁሟል።

በዚህም ያልተመዘገቡ አብያተ ክርስቲያናትና በቤት የሚካሄዱ የአምልኮ ጉባኤዎች በቁጥሩ ውስጥ ላይካተቱ ይችላሉ ሲል የStatiSense ያወጣው መረጃ ያመላክታል።

መረጃው የGMM TV ነው

የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካውንስል
የወንጌል አማኞች ድምፅ

የ Evangelical Media/Council የዩቲዩብ ቻናልን
ሰብስክራይብ ለማድረግ ከታች ያለውን ሊንክ ይጠቀሙ
• YouTube: https://youtube.com/
• TikTok: https://www.tiktok.com/.media
• Telegram: https://t.me/EGBCC
• Website: ecgbc.org
የቤተሰባችን አባል ለመሆን Follow, Subscribe, Like እና Share በማድረግ አብረውን ይሁኑ!
ለዜና ሽፋን መልአክት ለመላክ
t.me/evangelicalmedia
📞251 991827226 ላይ ያገኙናል

የኢትዮጵያ የሕይወት ብርሃን ቤተ ክርስቲያን ለሙሉ ጊዜ አገልጋዮቿ የማህበራዊ ዋስትና ሥርዓት ልትዘረጋ ነውአዲስ አበባ — የኢትዮጵያ የሕይወት ብርሃን ቤተ ክርስቲያን ለሙሉ ጊዜ ወንጌል አገል...
22/08/2026

የኢትዮጵያ የሕይወት ብርሃን ቤተ ክርስቲያን ለሙሉ ጊዜ አገልጋዮቿ የማህበራዊ ዋስትና ሥርዓት ልትዘረጋ ነው

አዲስ አበባ — የኢትዮጵያ የሕይወት ብርሃን ቤተ ክርስቲያን ለሙሉ ጊዜ ወንጌል አገልጋዮቿ የማህበራዊ ዋስትና መብት ለማረጋገጥ መወሰኗን የቤተክርስቲያኗ ፕሬዝዳንት መጋቢ ታሪኩ ብርሃኑ አስታወቁ።

መጋቢ ታሪኩ እንደገለጹት፤ ውሳኔው የጸደቀው በቅርቡ በተካሄደው የቤተ ክርስቲያኗ 81ኛ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ነው። ውሳኔውን መሠረት በማድረግ በየደረጃው የሚገኙ የቤተ ክርስቲያኗ መዋቅሮች፣ የክልልና የአካባቢ (አጥቢያ) መሪዎች የአገልጋዮችን የማህበራዊ ዋስትና መብት ሙሉ በሙሉ ወደ ተግባር እንዲቀይሩ ጥሪ አቅርበዋል።

ፕሬዝዳንቱ አገልጋዮች ትኩረታቸው ሳይበታተን ሙሉ አቅማቸውን ለላካቸው ተልዕኮ እንዲያውሉ የቤተ ክርስቲያን ድጋፍ ወሳኝ መሆኑን አፅንኦት ሰጥተውበታል። "ቤተ ክርስቲያን የአገልጋይ ልብ እንዳይከፈል በቂ ክፍያና ድጋፍ ልታደርግለት ይገባል" ያሉት መጋቢ ታሪኩ፤ በአንጻሩ ደግሞ አገልጋዩ ወደ መድረክ ሲመጣ ለመንፈሳዊው መንጋ የሚበቃና የታነጸ መልዕክት ይዞ መቅረብ እንዳለበት አሳስበዋል።

አገልጋዮች መሠረታዊ የኑሮ ፍላጎታቸው ካልተሟላ የመስበክና የመጸለይ አቅማቸው እንደሚፈታተን የጠቆሙት ፕሬዝዳንቱ፤ አብያተ ክርስቲያናት ከአገልግሎቱ ጎን ለጎን ለአገልጋዮቻቸው የኑሮ ሁኔታና ዘላቂ ህልውና ቀዳሚ ትኩረት መስጠት እንዳለባቸው አሳስበዋል።

መረጃው የኢቫንጀሊካል ሚዲያ ኔወርክ ነው

የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካውንስል
የወንጌል አማኞች ድምፅ

የ Evangelical Media/Council የዩቲዩብ ቻናልን
ሰብስክራይብ ለማድረግ ከታች ያለውን ሊንክ ይጠቀሙ
• YouTube: https://youtube.com/
• TikTok: https://www.tiktok.com/.media
• Telegram: https://t.me/EGBCC
• Website: ecgbc.org
የቤተሰባችን አባል ለመሆን Follow, Subscribe, Like እና Share በማድረግ አብረውን ይሁኑ!
ለዜና ሽፋን መልአክት ለመላክ
t.me/evangelicalmedia
📞251 991827226 ላይ ያገኙናል

በሕይወትህ እጅግ ጨለማ በሆኑ ሸለቆዎች ውስጥ ካለህ፣ጨለማው ሊያሸንፈው የማይችለው ብርሃን ኢየሱስ መሆኑን አስታውስ።ወንጌላዊ ቢሊ ግራሃም
21/08/2026

በሕይወትህ እጅግ ጨለማ በሆኑ ሸለቆዎች ውስጥ ካለህ፣ጨለማው ሊያሸንፈው የማይችለው ብርሃን ኢየሱስ መሆኑን አስታውስ።

ወንጌላዊ ቢሊ ግራሃም

21/08/2026

በዚያ ሀዘን የለም፤ መከራና ለቅሶ
መከፋት መጨነቅ፤ ያበቃል ጨርሶ
አዎን እንሄዳለን ፤ ወደ ኢየሩሳሌም
ከጌታችን ጋር፤ ልንኖር ዘላለም።

የመካነ ኢየሱስ ሴሚናሪዮም የቤተ ክርስቲያኒቱ መሪዎች፤ 22ተኛው የቤተ ክርስቲያኒቱ ካውንስል አባላት እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በርካታ አገልግሎቶችን የሚሰጥ ዘመናዊ የነዳጅ...
21/08/2026

የመካነ ኢየሱስ ሴሚናሪዮም የቤተ ክርስቲያኒቱ መሪዎች፤ 22ተኛው የቤተ ክርስቲያኒቱ ካውንስል አባላት እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በርካታ አገልግሎቶችን የሚሰጥ ዘመናዊ የነዳጅ ማደያ አስመርቋል።

ይህም ዘመናዊ ማደያ የነዳጅ፤ የኤሌክትሪክ መኪና ቻርጂንግ፤ ዘመናዊ የመኪና ማጠቢያ፤ ሱፐርማርኬት እና የካፍቴሪያ አገልግሎት የሚሰጥ ይሆናል።

የዚህም ማደያ መጠናቀቅ ሴሚናሪዮሙ ለሚያካሂደው፤ አገልጋዮቹን ለቤተ ክርስቲያኒቱ የማዘጋጀት እና የማብቃት ሥራ፤ ጥሩ ድጋፍ የሚሰጥ እንደሆነ ተገልጿል። የፕሮቸክቱም መጠናቀቅ ሴሚናሪው በልዩ ትኩረት የልማት ሥራዎችን በመሰራት ላይ እንደሚገኝ ማሳያ ሆኗል።

መረጃው የኢትዮጵያ የመካነ ኢየሱስ የቤተክርስቲያን ነው

የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካውንስል
የወንጌል አማኞች ድምፅ

የ Evangelical Media/Council የዩቲዩብ ቻናልን
ሰብስክራይብ ለማድረግ ከታች ያለውን ሊንክ ይጠቀሙ
• YouTube: https://youtube.com/
• TikTok: https://www.tiktok.com/.media
• Telegram: https://t.me/EGBCC
• Website: ecgbc.org
የቤተሰባችን አባል ለመሆን Follow, Subscribe, Like እና Share በማድረግ አብረውን ይሁኑ!
ለዜና ሽፋን መልአክት ለመላክ
t.me/evangelicalmedia
📞251 991827226 ላይ ያገኙናል

“የአገራችንን ዕጣ ፈንታ የሚወስነው ወንጌል ነው”ፓስተር ዶ/ር ጌትነት ለማየኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ጠቅላይ ጸሐፊ ፓስተር ዶ/ር ጌትነት ለማ ሚሽን የእያንዳንዱ...
21/08/2026

“የአገራችንን ዕጣ ፈንታ የሚወስነው ወንጌል ነው”
ፓስተር ዶ/ር ጌትነት ለማ

የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ጠቅላይ ጸሐፊ ፓስተር ዶ/ር ጌትነት ለማ ሚሽን የእያንዳንዱ አማኝ እና የሁላችንም ዋነኛ ጉዳይ ሊሆን እንደሚገባ አሳሰቡ።

ጠቅላይ ጸሐፊው ባስተላለፉት መልዕክት ወንጌልን ማድረስ ሁልጊዜም ቢሆን በአጀንዳዎች በንግግሮች በስብሰባዎቻቸን፣ እንዲሁም በቤትና በሁሉም ስፍራ ቀዳሚውና ታላቁ ትኩረት ሊሆን እንደሚገባው ገልጸዋል።

በሚሽን ጉዳይ ላይ መወያየትና ጥናታዊ ጽሑፎችን ማቅረብ ሰፊ ጊዜ ሊሰጠው የሚገባ ታላቅ ተልዕኮ መሆኑን ያብራሩት ፓስተር ዶ/ር ጌትነት፣ በዚህ ሥራ ላይ በቁርጠኝነት ማቀድና መንቀሳቀስ ካልተቻለ ቤተክርስቲያን በሕይወት አለች ለማለት እንደሚያስቸግር አስገንዝበዋል።

ጠቅላይ ጸሐፊው የአገራችንን ዕጣ ፈንታ የሚወስነው በወንጌል ነው በማለት የወንጌልን ወሳኝነት ላይ አጽንኦት ሰጥተውበታል።

ለኢቫንጄሊካል ቲቪ ፦ ቤተልሔም ደረጀ

የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካውንስል
የወንጌል አማኞች ድምፅ

የ Evangelical Media/Council የዩቲዩብ ቻናልን
ሰብስክራይብ ለማድረግ ከታች ያለውን ሊንክ ይጠቀሙ
• YouTube: https://youtube.com/
• TikTok: https://www.tiktok.com/.media
• Telegram: https://t.me/EGBCC
• Website: ecgbc.org
የቤተሰባችን አባል ለመሆን Follow, Subscribe, Like እና Share በማድረግ አብረውን ይሁኑ!
ለዜና ሽፋን መልእክት ለመላክ
t.me/evangelicalmedia
📞251 991827226 ላይ ያገኙናል

"ለኢትዮጵያ ሰላም መሆን ወንጌል በአራቱም አቅጣጫ መድረስ አለበት" ፓስተር ዶ/ር ጌትነት ለማሙሉ ቪዲዮውን ለማግኘት ከታች ያለውን ሊንክ ይጠቀሙhttps://youtu.be/WjTj9yLfTIk?...
21/08/2026

"ለኢትዮጵያ ሰላም መሆን ወንጌል በአራቱም አቅጣጫ መድረስ አለበት" ፓስተር ዶ/ር ጌትነት ለማ

ሙሉ ቪዲዮውን ለማግኘት ከታች ያለውን ሊንክ ይጠቀሙ
https://youtu.be/WjTj9yLfTIk?si=PO0As6o93LlZpDBJ

Enjoy the videos and music you love, upload original content, and share it all with friends, family, and the world on YouTube.

Address

Bole
Addis Ababa
32753

Opening Hours

Monday 08:00 - 17:00
Tuesday 08:00 - 17:00
Wednesday 08:00 - 17:00
Thursday 08:00 - 17:00
Friday 08:00 - 17:00

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Evangelical MEDIA/Council posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to Evangelical MEDIA/Council:

Shortcuts

Share