08/05/2026
✨ ✨
✨🙏🏾 እንኳን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም
የልደት በዓል መታሰቢያ በሰላም አደረሳችሁ
የእመቤታችንን ፍቅሯን በልባችኝ
ጣዕሟን በአንደበታችን ያኑርልን ✨🙏🏾
+ + + + +
+ ትወፅእ በትር እምሥርወ ዕሴይ ወየዐርግ ጽጌ እምኔሃ፡
ከዕሴይ ሥር በትር ትወጣለች፤
አበባም ከእርሷ ይወጣል፡፡ ✨ ኢሳ 11፡1 ✨
💫 ቁጥሩ ከዐበይት ነቢያት ወገን የሆነው ነቢዩ #ኢሳይያስም ጥበብንና እውቀትን በሚገልጽ ስለሚመጣውም ነገር ትንቢትን በሚያናግር በመንፈስ ቅዱስ ተመርቶ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ከነገደ ዕሴይ እንደሚሆንና እርሷም ጽጌ (አበባ) የተባለ አካላዊ ቃል ክርስቶስን በሕቱም ድንግልና እንደምትወልድ ተገልጾለት “
/ በትር_ትወጣለች ፤ / ›› በማለት ታላቅ ትንቢትን ተናግሮ ነበር፡፡
✨ ይህች በትርም ከእሴይ ዘር የተገኘችው በዚህች ዕለት ነውና ልደቷን በታላቅ ድምቀት እናከብራለን፡፡ ይህንን መሰረት በማድረግ ሊቁ ቅዱስ ኤፍሬም ‹‹ ሆይ ደስ ይበልሽ፤ ከእሴይ ሥር የተገኘሽ መዓዛሽ ያማረ አበባ አንቺ ነሽ›› በማለት በውዳሴ አመስግኗታል፡፡
✨ ‹‹በአባቶችሽ ፈንታ ልጆች ተወለዱልሽ (መዝ 131፡13)›› የተባለልን የአባቶቻችን ልጆች እኛም እንዲሁ እያልን እናመሰግናታለን፡፡ ✨
✨✨✨✨✨✨✨✨
የሐና የኢያቄም የእምነታቸው ፍሬ
🌺 በእግዚአብሔር ፈቃድ ተወለደች ዛሬ🌺
የኢያቄም ስዕለቱ የሐና እምነት 👏🏾
ለምኝልን ለኛ ኪዳነ ምሕረት 👏🏾
✨ + + + + + ✨
።
✨ አማኑኤል የማይተረጎም የሥጋን ልብስነት
ከአንቺ የለበሳት መሥሪያ ነሽ።
ዝሐውን ከአዳም ጥንተ ሥጋ አደረገ ማጉም የአንቺ ሥጋ ነው። መወርወሪያውም ቃል እርሱ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።
✨ መሕኑም ከልዕልና የወረደ
የልዑል እግዚአብሔር አምሳል ነው።
ሠሪውም መንፈስ ቅዱስ ነው።
✨ ወዮ ይህ ነገር እጹብ ድንቅ ነው።
የቀደሙ አባቶች ከሞት ወደ ሕይወት የተሸጋገሩብሽ ድልድይ ሆይ ከምድር እስከ ሰማይ የምትደርሺ መሰላል ሆይ የፍጥረት ሁሉ መጀመሪያ በአንቺ ታደሰ ።
🙏🏽ከገነት #በተሰደደ ጊዜ የአዳም ተስፋው አንቺ ነሽ ።
/ ቅዳሴ ማርያም ቁ.29 - 31/
✨🙏🏾 እንኳን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም
የልደት በዓል መታሰቢያ በሰላም አደረሳችሁ
የእመቤታችንን ፍቅሯን በልባችኝ
ጣዕሟን በአንደበታችን ያኑርልን ✨🙏🏾