Living Light - ሕያው ብርሃን

Living Light - ሕያው ብርሃን ለህይወቶ ትርጉም ይሰጣል! giving your life a meaning

💫RHAPSODY OF REALITIES 💫(Amharic) 🇪🇹🇪🇹🇪🇹Friday 24, July 2026 አርብ፥ ሐምሌ 17 ቀን 2018 ዓ.ም.📜ለስኬት በቃሉ የታነጻችሁ▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬📖 “በ...
24/07/2026

💫RHAPSODY OF REALITIES 💫
(Amharic) 🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Friday 24, July 2026
አርብ፥ ሐምሌ 17 ቀን 2018 ዓ.ም.

📜ለስኬት በቃሉ የታነጻችሁ
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

📖 “በአንተ ታምናለችና በአንተ ለምትደገፍ ነፍስ ፈጽመህ በሰላም ትጠብቃታለህ።”(ኢሳይያስ 26፡3)

👤 ፓስተር ክሪስ
════════
ገና በለጋነቴ፣ ጌታ እየጨመረ ለሚሄድ ስኬትና ተጽዕኖ መንገዴን አቅንቶታል። ገና በልጅነቴ ነው ከቃሉ ጋር የተዋወቁት ለዚህም ደግሞ ጌታን ለዘለአለም አመሰግነዋለሁ። ዳግም የተወለድኩት ገና ዘጠኝ አመት ሳይሞላኝ ነበር፤ ከዚያ ወንጌልን መስበክ ስጀምር ብዙም አልቆየሁም። ጓደኞቼን ለክርስቶስ መማረክ ጀመርኩ፣ ወዲያውም ህብረት ማድረግ ጀመርኩ። በአስራ አምስት አመቴ፣ የወንጌል ዘመቻ እያደረኩ ነበር። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ጉዞዬ ከክብር ላይ ክብር ነው።

ቃሉ እንደሚናገረው እግዚአብሔር በመንገድ ሲመራችሁና በእርሱ ላይ ስትታመኑ በእርሱ ላይ ተደግፋችኋልና ፈጽሞ በሰላም ይጠብቃችኋል። ያ ሰላም የብልጽግና ሰላም ነው፤ ያለማቋረጥ ወደ ፊት የሚሄድ ህይወት ነው።

መዝሙር 1፡3 ይህንን ህይወት በግልጽ ያብራራዋል፥”እርሱም በውኃ ፈሳሾች ዳር እንደ ተተከለች፥ ፍሬዋን በየጊዜዋ እንደምትሰጥ፥ ቅጠልዋም እንደማይረግፍ ዛፍ ይሆናል፤ የሚሠራውም ሁሉ ይከናወንለታል።” ቃሉ ህይወታችሁን እንዲቀርጸው ትኩረት ስትሰጡ፣ የሚሆነው እንዲህ ነው። ውጤቱ አስደናቂ ነው። እናንተ በውኃ ፈሳሾች ዳር እንደተተከለች፣ ፍሬዋንም በጊዜዋ እንደምትሰጥ ዛፍ ናችሁ። በህወታችሁ ውድቀት የለም።

የአምፕሊፋይድ ትርጉም ኢያሱ 1፡8ን የሚያብራራበት መንገድ ደስ ይለኛል፥”ይህ የሕግ መጽሐፍ ከአፍህ አይለይ፤ ነገር ግን የተጻፈውን ሁሉ ትጠብቅና ታደርግ ዘንድ በቀንም በሌሊትም አሰላስልበት፤ የዚያን ጊዜ መንገድህ ይቃናልሃል፥ ከዚያም በጥበብ ትሠራለህ፥ መልካምም ትሆናለህ።" ለቃሉ እራሳችሁን ስትሰጡ፣ በጥበብ ታደርጋላችሁ ይከናወንላችሁማል።

ምን አይነት ህይወት ነው፤ ለስኬት ብቻ የተሰራ ህይወት። ይህ ቃሉን የማሰላሰል ውጤት ነው፤ ቃሉ ራሱን በእናንተ ውስጥ ያበዛል። የእግዚአብሔር ቃል ዘር ነው። ማሰላሰል ቃሉ በመንፈሳችሁ ስር እንዲሰድና ሃሳባችሁን በመቆጣጠር ቃሉን ብቻ እንድታወሩና በቃሉ እንድትመላለሱ ያደርጋችኋል። ህይወታችሁ የቃሉ መገለጫ ይሆናል። ሃሌሉያ!

🙏 ጸሎት
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
ውድ አባት ሆይ፣ ቃልህ በህይወቴ ላይ ስላለው ኃይልና ውጤት አመሰግናለሁ። በአንተ እደገፋለሁ በፍጹም ሰላምና በማያቋርጥብልጽግና እመላለሳለሁ። ራሴን ሙሉ ለሙሉ ለቃልህ እሰጣለሁ፣ በቀንም በሌሊትም አሰላስላለሁ፣ የማያቋርጥ ስኬትና ፍሬያማነት በእኔ ይፈጥራል። ህይወቴ የቃልህ ነጸብራቅ ነው፤ ሁል ጊዜ በድል እመላለሳለሁ፣ በኢየሱስ ስም። አሜን።

📖 ለተጨማሪ ጥናት
├─ቆላስይስ 3፡16
├─ዕብራውያን 4፡12
├─ያዕቆብ 1፡22

━━━━//━━━

💫RHAPSODY OF REALITIES 💫(Amharic) 🇪🇹🇪🇹🇪🇹Thursday 23, July 2026 ሐሙስ፥ ሐምሌ 16 ቀን 2018 ዓ.ም.📜መለኮታዊ መዳረሻ (ፍጻሜ)▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬📖...
23/07/2026

💫RHAPSODY OF REALITIES 💫
(Amharic) 🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Thursday 23, July 2026
ሐሙስ፥ ሐምሌ 16 ቀን 2018 ዓ.ም.

📜መለኮታዊ መዳረሻ (ፍጻሜ)
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

📖 “ለእናንተ ያለኝን ዕቅድ እኔ ዐውቃለሁ” ይላል እግዚአብሔር፤ “ዕቅዱም ፍጻሜው ያማረና ተስፋ የሚሰጣችሁ፣ የሰላም ሐሳብ እንጂ ለክፉ አይደለም” (ኤርምያስ 29 :11) ።

👤 ፓስተር ክሪስ
════════
እግዚአብሔር እያንዳንዱን ነገር ያለ ዓላማ እንዳልፈጠረ ታውቃላችሁ? እያንዳንዱ ሰው ምድራዊ መዳረሻ እና መለኮታዊ መዳረሻ አለው። ምድራዊ መዳረሻ ልክ ቃሉ እንደሚለው— ምድራዊ ነው። ምድራዊ መዳረሻ ላይ የሚከተሉት ምክንያቶች ማለትም የወላጆቻችሁ ማንነት፣ የተወለዳችሁበትና ያደጋችሁበት ስፍራ፣ ጎደኞቻችሁ፣ ዘመዶቻችሁ እና ጊዜያችሁን የምታጠፉበት ቦታ ሁሉ ተፅዕኖ ያደርጉበታል። እነዚህ ሁሉ በእናንተ ላይ ተፅዕኖ አላቸው።

ያነበባችኋቸው መፅሐፍቶች፣ የተመለከታችሁት ፊልሞች፣ እና አጣጥማችሁ ወደ ውስጣችሁ ያስገባችኋቸው መረጃዎች ሁሉ ምድራዊ መዳረሻችሁን ይቀርፁታል። ነገር ግን ሌላ መዳረሻ አለ፣ መለኮታዊ መዳረሻ የሚባል፣ ይህም ማንኛውንም ምድራዊ መዳረሻ ደምስሶ የእናንተ ፍጻሜ ይሆናል። በዚህ መለኮታዊ መዳረሻ ላይ ከላይ የተዘረዘሩት ምክንያቶች ሁሉ ምንም ተፅዕኖ ማምጣት አይችሉም፣ የእናንተን የወደፊት ማንነት መወሰን አይችሉም። የእናንተን ማንነት ለመግለፅ አቅም ያጣሉ። እግዚአብሔር የላቀ ሕይወትን አሳውቆናል ይህም ሕይወት የኋላ ታሪክን፣ ማንኛውም ዓይነት ገደቦችን እና ሰዎች የሚገጥሟቸው ሁኔታዎችን ሁሉ ይሽራል።

ይህ መለኮታዊ መዳረሻ(ፍጻሜ) በሕይወታችሁ እውነት ሆኖ እንዲገለጥ እግዚአብሔር ምን ማድረግ እንዳለባችሁ ነግሯችኋል። ምድራዊ መዳረሻ ኑሯችሁን እንዳይገዛ ወይም ከሕልውናችሁ ጋር የተያያዙ ሁኔታዎች ላይ እንዳይወስን እግዚአብሔር ትእዛዞች እና አቅጣጫ ሰጥቷችኋል። ከእግዚኣብሔር የላቀ ዓላማ ጋር ተስማምታችሁ እንድትቀጥሉ የእግዚአብሔር ቃል መሳሪያችሁ ነው።

መፅሐፍ ቅዱስ ይህን ይላል የእግዚአብሔር እቅድ ሁሌም መልካም ነው እንዲሁም ለእናንተም ለመልካም ነው። ለእናንተ ያለው እቅድ ታላቅ ነው። እርሱ እራሱ ታላቅ ነው፣ ስለዚህ ታላላቅ የሆኑ ወንዶችንና ሴቶችን ብቻ ነው ሊያስነሳ የሚችለው። እርሱ የሚሰራበት መንገድ ይህ ብቻ ነው። ውድቀትን ማባዛት አይችልም። ስኬትን ብቻ ነው የሚያራባው። ንጉስነትን ብቻ ነው የሚያራባው። ስለዚህ፣ ቃሉን በምትከተሉ እና በእርሱ አመራር በምትራመዱ ጊዜ፣ መለኮታዊ መዳረሻ በሕይወታችሁ እውነት ሆኖ ይገለጣል፣ እንዲሁም ምድራዊ ተፅዕኖዎች ሁሉ ለቀዋችሁ ይሄዳሉ።

🙏 ጸሎት
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
ውድ አባት ሆይ፣ ከማንኛውም ምድራዊ ተፅዕኖ በላይ ስለሆነውና በእኔ ሕይወት ላይ ስላቀድከው መለኮታዊ ዓላማህ አመሰግንሃለው። በመንፈስ ቅዱስ እየተመራሁ እና ለእኔ ያቀድከውን ዓላማ ሁሉ እየፈፀምኩ በቃልህ ብርሃን እራመዳለሁ። በበፊት ታሪክና እና ሁኔታዎች መገደብን አልቀበልም ምክንያቱም እኔ የአንተ ታላቅነት ውጤት እና የፍቃድህ መገለጫ ነኝ፣ በኢየሱስ ስም። አሜን።

📖 ለተጨማሪ ጥናት
├─ኤርምያስ 1:5
├─ኤፌሶን 2:10
├─ሮሜ 8:29

━━━━//━━━

💫RHAPSODY OF REALITIES 💫(Amharic) 🇪🇹🇪🇹🇪🇹Friday 17, July 2026 አርብ፥ ሐምሌ 10 ቀን 2018 ዓ.ም.📜ስጋችሁን አስገዙ▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬📖እንግዲህ፥ ወ...
17/07/2026

💫RHAPSODY OF REALITIES 💫
(Amharic) 🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Friday 17, July 2026
አርብ፥ ሐምሌ 10 ቀን 2018 ዓ.ም.

📜ስጋችሁን አስገዙ
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

📖እንግዲህ፥ ወንድሞች ሆይ፥ ሰውነታችሁን እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝና ሕያው ቅዱስም መሥዋዕት አድርጋችሁ ታቀርቡ ዘንድ በእግዚአብሔር ርኅራኄ እለምናችኋለሁ፥ እርሱም ለአእምሮ የሚመች አገልግሎታችሁ ነው (ሮሜ 12፡1)

👤 ፓስተር ክሪስ
════════
መንፈሳችሁ ቅድስተ ቅዱሳን መሆኑንና መሪነቱን መያዝ እንዳለበት፥ እንዲሁም ነፍሳችሁ እንድትከተል መሰልጠን እንዳለባት ከተረዳችሁ በኋላ አንድ ተጨማሪ አስፈላጊ ነገር ይቀራል። እርሱም ስጋችሁ ነው። ስጋችሁ መንፈሳችሁ ውስጥ ካለው ከእግዚአብሔር ሕይወት ጋር ራሱን በራሱ እንዲሁ አያስማማም። ወደ መገዛት እንዲመጣ መደረግ አለበት።

ቃሉ "...ሰውነታችሁን... መሥዋዕት አድርጋችሁ ታቀርቡ ዘንድ..." የሚለው ለዚህ ነው። እግዚአብሔር መንፈሳችሁን ዳግመኛ በመፍጠር የእርሱን ድርሻ ፈጽሟል። ስጋችሁን ማስገዛት፥ ለእርሱም ህያው መስዋዕት አድርጎ ማቅረብ ግን የእናንተ ሃላፊነት ነው። ሐዋርያ ጳውሎስ ተጨማሪ ምልከታን ይሰጣል፡ "ነገር ግን ...ሥጋዬን እየጎሰምሁ አስገዛዋለሁ" (1ኛ ቆሮንቶስ 9፡27)።

ይህ ማለት ከመንፈሳችሁ ጋር ይስማማ ዘንድ ስጋችሁ መለማመድና መሰልጠን አለበት ማለት ነው። ስጋ ዝንባሌዎች አሉት፤ ለስሜቶች፥ ለፍላጎቶችና ከውጪ ለሆኑ ቀስቃሽ ነገሮች ምላሽ ይሰጣል። በተሰማው ስሜት መሰረት ድርጊትን ለመፈፀም ይፈልጋል። ነገር ግን እናንተ በስጋ ውስጥ የሚኖሩ መንፈስ የሆኑ ፍጡሮች ናችሁ እንጂ ስጋ አይደላችሁም። ስለዚህ ስሜቶቻችሁ እንዲገዟችሁ መፍቀድ የለባችሁም። መጽሐፍ ቅዱስ "እንደ ሥጋ ፈቃድ ብትኖሩ ትሞቱ ዘንድ አላችሁና..." ይላል (ሮሜ 8፡13)።

በስጋ ፈቃድ መኖር ማለት በስጋችሁና በስሜቶቹ መገዛት ማለት ነው፣ ነገር ግን የእናንተ ሕይወት ያ አይደለም። እናንተ የምትኖሩት በመንፈስ ነው። እንዲሁም የሮሜ 8፡13 መዝጊያ ክፍል "በመንፈስ ግን የሰውነትን ሥራ ብትገድሉ በሕይወት ትኖራላችሁ።" ብሎ እንደሚያውጀው ትኖራላችሁ። ይህ ማለት በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት የስጋ ስራዎችን ትገድላላችሁ፥ ስሜቶቹን ትሽራላችሁ፥ እንዲሁም ስጋችሁን ከእግዚአብሔር ፈቃድና አላማ ጋር ወደመስማማት ታመጡታላችሁ ማለት ነው።

ይህ ጭቆና ሳይሆን ስጋ ላይ መግዛት ነው። መንፈሳችሁ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር አንድ ሆኖና በእግዚአብሔር ሕይወት ተሞልቶ የስልጣን ስፍራውን ይይዛል። ነፍሳችሁ፣ በቃሉ በመታደስ ትስማማለች። ከዚያም ስጋችሁ ወደ መታዘዝ ይመጣል። በቅደም ተከተል መንፈስ፥ ነፍስና ስጋ ከእግዚአብሔር ቃል ጋር የተስማሙ መሆን የክርስቲያናዊ ሕይወት ሙሉ ስርዓት ነው።

ስጋችሁ ሕይወታችሁን እንዲያዝ ወይም ምላሾቻችሁን እንዲቆጣጠር አትፍቀዱለት። ድካም፥ ፍላጎት፥ ወይም የትኛውም አይነት ግፊት ቢሆን ከመንፈሳችሁ የስልጣኑን ስፍራ ያዙና ስጋችሁን ለእግዚአብሔር አቅርቡ። አላማውን እንዲያገለግል አድርጉት። የበሽታ ምልክቶች ከተሰሟችሁ፡ "አይሆንም! ስጋዬ የመንፈስ ቅዱስ ቤተ-መቅደስ ነው፤ ስለዚህ በበሽታ፥ በህመምና በደዌዎች የማይበገር ነው" ብላችሁ አውጁ። በስጋችሁ ውስጥ በሽታ እንዲኖር አትፍቀዱ፤ ይህ ስጋችሁን ከእግዚአብሔር ጋር የማስማማትና ለእርሱ የማስገዛት አንድ ክፍል ነው።

🙏 ጸሎት
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
ውድ አባት ሆይ፤ በውስጤ ስላለው የመንፈስህ ስልጣን አመሰግንሃለሁ። ስጋዬ የመንፈስ ቅዱስ ቤተ-መቅደስ ነው። እናም ከፈቃድህና ከመንገዶችህ በታች በማስገዛት ህያው መስዋዕት አድርጌ አቀርበዋለሁ። በስሜቶችና በተፈጥሯዊ ግፊቶች መገዛትን እቃወማለሁ። ሁልጊዜም ከመንፈስህ ጋር በመዋሃድና ከፍፁም ፈቃድህ ጋር በመስማማት እመላለሳለሁ፤ በኢየሱስ ስም። አሜን።

📖 ለተጨማሪ ጥናት
├─1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 9፡27
├─ወደ ሮሜ ሰዎች 8፡13
├─ወደ ገላትያ ሰዎች 5፡24

━━━━//━━━

16/07/2026
💫RHAPSODY OF REALITIES 💫(Amharic) 🇪🇹🇪🇹🇪🇹Thursday 16, July 2026 ሐሙስ፥ ሐምሌ 09 ቀን 2018 ዓ.ም.📜መንፈሳችሁን ይከተል ዘንድ ነፍሳችሁን አሰልጥኑ▬▬▬...
16/07/2026

💫RHAPSODY OF REALITIES 💫
(Amharic) 🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Thursday 16, July 2026
ሐሙስ፥ ሐምሌ 09 ቀን 2018 ዓ.ም.

📜መንፈሳችሁን ይከተል ዘንድ ነፍሳችሁን አሰልጥኑ
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

📖...በልባችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉ (ሮሜ 12፡2)

👤 ፓስተር ክሪስ
════════
ጳውሎስ በሮሜ 1፡9 ላይ "በልጁ ወንጌል በመንፈሴ የማገለግለው እግዚአብሔር ምስክሬ ነውና..." ብሎ በተናገረበት ጊዜ መሰረታዊ የሆነ ነገርን ገልጧል፤ እርሱም እግዚአብሔርን የምናገለግለው በመንፈሳችን መሆኑን ነው። ነገር ግን ከመንፈሳችሁ ባለፈ ሌላ የማንነታችሁ አስፈላጊ ክፍል አለ፤ ያም የእውቀታችሁ፥ የፈቃዳችሁና የስሜቶቻችሁ ስፍራ የሆነው ነፍሳችሁ ነው።

አእምሮአችሁ ሊሰለጥንባችሁ አይገባም። ስሜቶቻችሁ ሊሰለጥኑባችሁ አይገባም። ፈቃዳችሁ ሊሰለጥንባችሁ አይገባም። በዚያ ፈንታ በመንፈስ ቅዱስ ተፅእኖ ስር ሆነው ወደ መገዛት ሊመጡ ይገባል።

በብሉይ ኪዳን ቤተ-መቅደስ መሰረት፣ ነፍስ የምትመሳሰለው ካህናቱ ከሚያገለግሉበት ከቅድስት ስፍራ ጋር ነው። የእነርሱ ተቀዳሚ ሃላፊነት ምን ነበር? ማስተማር ነበር። ካህናቱ የህጉ ጠባቂና አስተማሪዎች ነበሩ። ይህ ነፍሳችሁ መማር እንዳለባት ያሳያል። አእምሮአችሁ በቃሉ መሰልጠን አለበት። ስሜቶቻችሁ በቃሉ መገዛት አለባቸው። ፈቃዳችሁ በቃሉ ስርዓት መታነፅ አለበት።

"ማድረግ የምፈልገው ይህን ነው፤ የወሰንኩት ይህን ነው" የምትሉበት ጊዜዎች አሉ። ነገር ግን ቃሉ የተለየ ነገር ካሳያችሁ፤ በዚያን ጊዜ ፈቃዳችሁ መገዛት አለበት። "የእኔ ፈቃድ ሳይሆን የእግዚአብሔር ፈቃድ ይሁን፤ የእኔ መንገድ ሳይሆን የእግዚአብሔር መንገድ ይሁን" ትላላችሁ።

ስለስሜቶቻችሁም እንደዚሁ ነው። ወደ ሆነ አቅጣጫ ያዘነበላችሁ መስሎ ሊሰማችሁ ይችላል፤ ነገር ግን ቃሉ የሚገልጠው የተለየ በሚሆንበት ጊዜ፣ ታቆማላችሁ። ቃሉ ስሜቶቻችሁን እንዲገዛ ትፈቅዳላችሁ። ነፍሳችሁ በቁጥጥር ስር የምትሆነው እንደዛ ነው።

በቅድስት ስፍራ፣ ሶስት አስፈላጊ ነገሮች ነበሩ፤ እነርሱም መቅረዝ፥ የገጽ ህብስት ገበታና የዕጣን መሰዊያ ናቸው። መቅረዙ ብርሃንን ይሰጥ ነበር፤ ይህ በሕይወታችሁ ውስጥ ያለ የቃሉ ማብራት ነው። የገጽ ህብስት ገበታው ለእድገት የሚያስፈልጋችሁን ያቀርባል፤ ይህም ቃሉ መንፈሳችሁን ሲመግብ ነው። የዕጣን መሰዊያው ደግሞ ጸሎትን ይወክላል፤ ይህም ከእግዚአብሔር ጋር ያላችሁ ግንኙነት ነው።

እንዴት እንደሚገናኙ ተረድታችኋል? ቃሉን ስታጠኑ ብርሃን ይመጣና መንፈሳችሁ ይመገባል። በመቀጠል በዚያ ምክንያት ለጸሎት ትነሳሳላችሁ። ጸሎታችሁም እንደ ዕጣን በእግዚአብሔር ፊት ይወጣል። ስለዚህ ሁለት ሃይሎች በነፍሳችሁ ውስጥ በቋሚነት ይሰራሉ፤ እነርሱም ቃሉና ጸሎት ናቸው።

ቃሉን በይበልጥ በተቀበላችሁ መጠን ለመጸለይ በይበልጥ ትነሳሳላችሁ፤ በይበልጥ በጸለያችሁ መጠን ደግሞ ለቃሉ በይበልጥ ንቁ ትሆናላችሁ። ነፍሳችሁ የምትሰለጥነው እንደዚያ ነው። በቃሉ ተፅእኖ ስር አድርጋችሁ በማቆየት፤ አስተሳሰባችሁ፥ ምርጫዎቻችሁና ምላሾቻችሁ ከእግዚአብሔር ፈቃድ ጋር የተስማሙ መሆናቸውን በማረጋገጥ ትሰለጥናለች። መንፈሳችሁ ወደሚመራበት ስፍራ ነፍሳችሁ ስትከተል፤ ይህ ብስለት ነው።

🙏 ጸሎት
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
ውድ አባት ሆይ፤ አእምሮዬን ስለሚያድሰውና ነፍሴን ስለሚያሰለጥናት ቃልህ አመሰግንሃለሁ። ፈቃዴን ለአንተ አስገዛለሁ፤ በስሜቶቼ ወይም በተፈጥሯዊ ምክንያታዊነት መገዛትን እቃወማለሁ። አሁንም ሆነ ሁልጊዜ አእምሮዬ በብርሃን የተሞላ ነው፥ መንፈሴ የታነፀ ነው፤ እንዲሁም ሕይወቴ ከፍፁም ፈቃድህ ጋር ይስማማል፤ በኢየሱስ ስም። አሜን።

📖 ለተጨማሪ ጥናት
├─ወደ ሮሜ ሰዎች 12፡2
├─የያዕቆብ መልእክት 1፡21
├─ወደ ዕብራውያን ሰዎች 5፡14

━━━━//━━━

💫RHAPSODY OF REALITIES 💫(Amharic) 🇪🇹🇪🇹🇪🇹Tuesday 14, July 2026 ማክሰኞ፥ ሐምሌ 07 ቀን 2018 ዓ.ም.📜መንፈሳችሁ መሪነቱን ይውሰድ▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬...
14/07/2026

💫RHAPSODY OF REALITIES 💫
(Amharic) 🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Tuesday 14, July 2026
ማክሰኞ፥ ሐምሌ 07 ቀን 2018 ዓ.ም.

📜መንፈሳችሁ መሪነቱን ይውሰድ
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

📖“በልጁ ወንጌል በመንፈሴ የማገለግለው እግዚአብሔር ምስክሬ ነውና…” (ሮሜ 1፥9)።

👤 ፓስተር ክሪስ
════════
አሁን ካነበብነው ጥቅስ የወጣው የሐዋርያው ጳውሎስ ይህ አባባል ምንኛ ጥልቅ ነው። ለእግዚአብሔር የሚቀርብ እውነተኛ አገልግሎት ከየት እንደሚመጣ ያሳያችኋል። በሰውነታችሁ ወይም በአእምሮአችሁ የሚሆን አይደለም። ለእግዚአብሔር የሚቀርብ እውነተኛ አገልግሎት ከመንፈሳችሁ የሚሆን ነው። በ (ዮሐንስ 4፥24) ላይ ጌታ ኢየሱስ፣ “እግዚአብሔር መንፈስ ነው፥ የሚሰግዱለትም በመንፈስና በእውነት ሊሰግዱለት ያስፈልጋቸዋል።” በማለት ተናግሯል።

ከእግዚአብሔር ጋር ያላችሁ ኅብረት መንፈሳዊ ነው፤ ስለዚህ፣ አገልግሎታችሁ ከዚያው ተመሳሳይ ምንጭ መፍሰስ አለበት። ዳግመኛ ስትወለዱ፣ የተቀየረው ሰውነታችሁ አይደለም፣ እናም ደግሞ አዲስ ሆኖ የተፈጠረው አእምሮአችሁ አልነበረም፤ አዲስ ሆኖ የተፈጠረው መንፈሳችሁ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ በ (2 ቆሮንቶስ 5፥17) ላይ ሲናገር፣ “ስለዚህ ማንም በክርስቶስ ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው…” ይላል።

ያ አዲስ ፍጥረት መንፈሳችሁ ነው። የእግዚአብሔር ሕይወት ያለበት ቦታ ያ ነው። ለዚህ ነው አንድ ሰው ዳግመኛ ተወልዶ ሳለ አሁንም በተወሰኑ ነገሮች ሊታገል የሚችለው። ቶሎ የሚቆጣ፣ በቀላሉ የሚቀየም እና የሚበሳጭ ወይም አሁንም የተሳሳቱ ሐሳቦችን የሚያስብ ሰው ልታገኙ ትችላላችሁ። ይህ የሆነው የእግዚአብሔር ሕይወት ስለሌለው አይደለም፤ አእምሮው ስላልታደሰ ነው።

መጽሐፍ ቅዱስ በ (ሮሜ 12፥2) ላይ፣ “…በልባችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉ።” በማለት የሚናገረው ለዚህ ነው። መንፈሳችሁ አስቀድሞ አዲስ ሆኖ ተፈጥሯል፣ ነገር ግን አእምሮአችሁ በክርስቶስ ካለው አዲስ ሕይወት ጋር እንዲስማማ መሰልጠን አለበት። ሰውነታችሁም ቁጥጥር ሥር መዋል አለበት። መጽሐፍ ቅዱስ በ (ሮሜ 12፥1) ላይ፣ “…ሰውነታችሁን እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝና ሕያው ቅዱስም መሥዋዕት አድርጋችሁ ታቀርቡ ዘንድ…” ይላል።

ይህንን የሚያቀርበው ማነው? መንፈሳችሁ ነው። ስለዚህ፣ በእግዚአብሔር ዘንድ ሕያው የሆነው፣ መንፈሳችሁ፣ መሪነቱን መውሰድ አለበት። ከመንፈሳችሁ በመነሳት፣ አእምሮአችሁን ትገዛላችሁ። ከመንፈሳችሁ በመነሳት፣ ሰውነታችሁን ታስገዛላችሁ። መንፈሳችሁ መሪነቱን እንዲወስድ ካልፈቀዳችሁለት፣ የስሜት ሕዋሳቶቻችሁ መሪነቱን ይወስዳሉ። ስሜቶቻችሁ ይገዟችኋል። አሮጌው የአስተሳሰብ ዘይቤአችሁ ይመራችኋል። እናንተ ግን ልትኖሩበት የተጠራችሁት ሕይወት ይህ አይደለም።

ከውስጥ፣ ከመንፈሳችሁ እንድትኖሩ ተጠርታችኋል። የመንፈስ ቅዱስ ምሪት ያለው በዚያ ነው። የእግዚአብሔር ሕይወት የሚሠራው በዚያ ነው። መንፈሳችሁ አስተማማኝ መሪ ነው ምክንያቱም ከቅዱስ መንፈስ ጋር የተዋሃደ ነው። እናንተ ከእርሱ ጋር አንድ ናችሁ፦ “ከጌታ ጋር የሚተባበር ግን አንድ መንፈስ ነው።” (1 ቆሮንቶስ 6፥17)። ስለዚህ፣ መንፈሳችሁ ሐሳባችሁን እና ተግባራችሁን እንዲመራ ፍቀዱለት። እርሱ ምላሻችሁን እንዲመራ እና እንዲወስን ፍቀዱለት። በክርስቶስ ያለውን የላቀ ሕይወት የምትኖሩት በዚህ መንገድ ነው።

🗣️ ጸሎት
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
ውድ አባት ሆይ፣ በመንፈሴ ውስጥ ስላለው ስለ እግዚአብሔር ሕይወት አመሰግንሃለሁ። በእኔ ውስጥ ያለው መንፈስ ቅዱስ ከመንፈሴ ጋር በመዋሐድ ሐሳቤቦቼን እና ተግባሮቼን ይመራል። ስለዚህ፣ መንፈሴ ምላሾችን የሚወስን እና የሚመራ አስተማማኝ መሪ ነው። አእምሮዬ በቃሉ የታደሰ ነው፤ እኔም በሥልጣን፣ ከክብር ወደ ክብር እኖራለሁ፣ በኢየሱስ ስም። አሜን።

📖 ለተጨማሪ ጥናት
├─ዮሐንስ 4:24
├─ሮሜ 12:1–2
├─2ኛ ቆሮንቶስ 5:17

━━━━//━━━

💫RHAPSODY OF REALITIES 💫(Amharic) 🇪🇹🇪🇹🇪🇹Monday 13, July 2026 ሰኞ፥ ሐምሌ 06 ቀን 2018 ዓ.ም.📜ቤተ ክርስቲያን ከሕንጻ በላይ ናት▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬...
13/07/2026

💫RHAPSODY OF REALITIES 💫
(Amharic) 🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Monday 13, July 2026
ሰኞ፥ ሐምሌ 06 ቀን 2018 ዓ.ም.

📜ቤተ ክርስቲያን ከሕንጻ በላይ ናት
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

📖“በክርስቶስ ኢየሱስ አብረውኝ ለሚሠሩ ለጵርስቅላና ለአቂላ ሰላምታ አቅርቡልኝ፤ እነርሱም ስለ ነፍሴ ነፍሳቸውን ለሞት አቀረቡ፥ የአሕዛብም አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ የሚያመሰግኑአቸው ናቸው እንጂ እኔ ብቻ አይደለሁም፤ በቤታቸውም ላለች ቤተ ክርስቲያን ሰላምታ አቅርቡልኝ። ከእስያ ለክርስቶስ በኵራት ለሆነው ለምወደው ለአጤኔጦን ሰላምታ አቅርቡልኝ።” (ሮሜ 16፥3-5)።

👤 ፓስተር ክሪስ
════════
የሮሜን መጽሐፍ በጥንቃቄ ስታጠኑ፣ በተለይም አሥራ ስድስተኛውን ምዕራፍ፣ ስለ ጥንቷ ቤተ ክርስቲያን አንድ አስደናቂ ነገር ታስተውላላችሁ። አንድ ማዕከላዊ ጉባኤ አልነበረም፤ ይልቁንም በተለያዩ ቦታዎች የሚሰበሰቡ በርካታ ኅብረቶች እና የተለያዩ የእግዚአብሔር ሕዝብ ቡድኖች ነበሩ፣ ሆኖም ግን ሁሉም የዚችው የአንዲቱ ቤተ ክርስቲያን አካል ነበሩ።

ይህ ደግሞ ጳውሎስ ለሮሜ ሰዎች የጻፈውን መልእክት መግቢያ ስታነቡ የበለጠ ግልጽ ይሆንላችኋል። “በእግዚአብሔር ለተወደዳችሁና ቅዱሳን ልትሆኑ ለተጠራችሁ በሮሜ ላላችሁት ሁሉ” (ሮሜ 1፥7)።

አብያተ ክርስቲያናቱ በብዙ ቦታዎች ተሰራጭተው ነበር፤ በየቤቱ የሚደረጉ ኅብረቶች እና በየቤቶቻቸው የሚሰበሰቡ የክርስቲያን ቡድኖች ነበሩ። ለዚህ ነው በሮሜ 16:3-5 ላይ፣ ለጵርስቅላና ለአቂላ እንዲሁም በቤታቸው ላለች ቤተ ክርስቲያን ሰላምታ አቅርቡልኝ ያለው።

በተጨማሪም፣ በ10ኛው ቁጥር ላይ፣ “…ከአርስጣባሉ ቤተ ሰዎች ላሉት ሰላምታ አቅርቡልኝ።” ብሏል፤ በመቀጠልም በ11ኛው ቁጥር ላይ፣ “…ከንርቀሱ ቤተ ሰዎች በጌታ ላሉት ሰላምታ አቅርቡልኝ።” በማለት ተናግሯል። እነዚህ ተራ ቤተሰቦች ብቻ አልነበሩም፤ እነዚህ የጳውሎስ አገልግሎት ሕያው መግለጫዎች እና ማራዘሚያዎች የነበሩ አብያተ ክርስቲያናት ነበሩ። ይህ አንድ ጥልቅ እውነትን ይገልጣል፦ ቤተ ክርስቲያን ሕንጻ አይደለችም፤ ቤተ ክርስቲያን የእግዚአብሔር ሕዝብ ናት።

የጥንቷ ቤተ ክርስቲያን እንደ ብዙ አብያተ ክርስቲያናት የተዋቀረች ነበረች፣ ሆኖም ግን አንድ አካል ነበሩ። ስብሰባዎቹ ብዙ ሊሆኑ ይችላሉ፣ ነገር ግን እያንዳንዳቸው ሕያው፣ ንቁ እና የተሳሰሩ ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የሐዋርያት ሥራ 2፥46) ላይ ሲናገር፣ “በየቀኑም በአንድ ልብ ሆነው በመቅደስ እየተጉ በቤታቸውም እንጀራ እየቈረሱ…” ይላል። ትላልቅ ስብሰባዎች ነበሩ፣ ነገር ግን ቃሉን የሚካፈሉባቸው፣ አብረው የሚጸልዩባቸው እና አብረው የሚያድጉባቸው ትናንሽ ኅብረቶችም ነበሩ።

እንዲህ ዓይነቱ መዋቅር ቤተ ክርስቲያንን ጠንካራ እና የማይበገሩ አድርጓታል። በስደት ዘመንም እንኳ፣ ማደግ ቀጥላ ነበር። ሕንጻን ልታፈርሱ ትችላላችሁ፣ ቤተ ክርስቲያንን ግን ማፍረስ አትችሉም። ሕዝቡ እስካለ ድረስ፣ ቤተ ክርስቲያን አለች። ለዚህ ነው ኅብረት በጣም አስፈላጊ የሆነው።

ክርስቲያኖች በጌታ ስም በሚሰበሰቡበት ቦታ ሁሉ፣ እርሱ በመካከላቸው አለ፤ እናም ያ ቤተ ክርስቲያን ናት። በ (ማቴዎስ 18፥20) ላይ ጌታ ኢየሱስ፣ “ሁለት ወይም ሦስት በስሜ በሚሰበሰቡበት በዚያ በመካከላቸው እሆናለሁና።” በማለት በተናገረ ጊዜ የትንሿን ጉባኤ ኃይል አፅንዖት ሰጥቶታል።

ስለዚህ ቤተ ክርስቲያንን በአንድ ቦታ ወይም በሕንጻ ብቻ አትወሰኑ። እውነተኛ ተፈጥሮዋን ተረዱ፦ እርሷ በሕዝቦቿ በኩል፣ በኅብረት፣ በአንድነት እና በዓላማ የምትገለጥ የክርስቶስ ሕያው አካል ናት። የዚህ መገለጫ አካል ሁኑ። አጠናክሩት። ገንቡት። ቤተ ክርስቲያን የምታድገው እና መንግሥቱም ከክብር ወደ ክብር የሚሸጋገረው በዚህ መንገድ ነው። ሃሌሉያ!

🙏 ጸሎት
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
ውድ አባት ሆይ፣ የክርስቶስ ሕያው አካል የሆነችውን የቤተክርስቲያን አካል ስላደረግኸኝ አመሰግንሃለሁ። ለሌሎች እድገት እና ጥንካሬ የበኩሌን አስተዋጽኦ በማበርከት፣ በኅብረት ውስጥ በንቃት እሠራለሁ። በእኔ በኩል የአንተ ሕይወት ተገልጧል፣ እናም የአንተ መንግሥት ዛሬ ተስፋፍቷል፣ በኢየሱስ ስም። አሜን።

📖 ለተጨማሪ ጥናት
├─ሮሜ 1:7
├─የሐዋርያት ሥራ 2:46
├─1ኛ ቆሮንቶስ 16:19

━━━━//━━━

💫RHAPSODY OF REALITIES 💫(Amharic) 🇪🇹🇪🇹🇪🇹Sunday 12, July 2026 እሁድ፥ ሐምሌ 05 ቀን 2018 ዓ.ም.📜“የተቀደሰ አሳሳም”—ትርጉሙ ምንድን ነው?▬▬▬▬▬▬▬▬...
12/07/2026

💫RHAPSODY OF REALITIES 💫
(Amharic) 🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Sunday 12, July 2026
እሁድ፥ ሐምሌ 05 ቀን 2018 ዓ.ም.

📜“የተቀደሰ አሳሳም”—ትርጉሙ ምንድን ነው?
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

📖 “በተቀደሰ አሳሳም እርስ በርሳችሁ ሰላምታ ተሰጣጡ። የክርስቶስ አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ ሰላምታ ያቀርቡላችኋል።” (ሮሜ 16፥16)።

👤 ፓስተር ክሪስ
════════
ሐዋርያው ጳውሎስ፣ “በተቀደሰ አሳሳም እርስ በርሳችሁ ሰላምታ ተሰጣጡ።” ብሎ ሲጽፍ፣ የአምልኮ ሥርዓትን እያስተዋወቀ አልነበረም፤ ይልቁንም በእግዚአብሔር ሕዝቦች መካከል ስላለው የግንኙነት ቅንነት መናገሩ ነበር። ይህንን ለመረዳት፣ ከላይ ላዩ ከሚታየው ነገር ባሻገር ማየት አለባችሁ። በዚያ ዘመን፣ መሳሳም የተለመደ የሰላምታ ዓይነት ነበር። ነገር ግን ጳውሎስ “የተቀደሰ” የሚል ገላጭ ቃል ጨመረበት። ምክንያቱም እያንዳንዱ የፍቅር መግለጫ እውነተኛ አይደለምና።

ጌታ ኢየሱስ ራሱ ይሁዳ አሳልፎ ሊሰጠው በመጣ ጊዜ ይህንን ጉዳይ አጉልቶ አሳይቷል። መጽሐፍ ቅዱስ በ (ማቴዎስ 26፥49–50) ላይ፣ “ወዲያውም ወደ ኢየሱስ ቀረበና፦ መምህር ሆይ፥ ሰላም ለአንተ ይሁን ብሎ ሳመው። ኢየሱስም፦ ወዳጄ ሆይ፥ ለምን ነገር መጣህ? አለው። በዚያን ጊዜ ቀረቡ እጃቸውንም በኢየሱስ ላይ ጭነው ያዙት።” በማለት ይናገራል። የይሁዳ መሳም እውነተኛ አልነበረም። ክህደትን የሸፈነ ነበር። በ (ሉቃስ 22፥47-48) የሚገኘውን የሉቃስን ዘገባ ስታነቡ ደግሞ፦ “ገናም ሲናገር እነሆ፥ ሰዎች መጡ፤ ከአሥራ ሁለቱ አንዱም ይሁዳ የሚባለው ይቀድማቸው ነበር፥ ሊስመውም ወደ ኢየሱስ ቀረበ። ኢየሱስ ግን፦ ይሁዳ ሆይ፥ በመሳም የሰውን ልጅ አሳልፈህ ትሰጣለህን? አለው።” በማለት ይናገራል።

የጳውሎስን መመሪያ በተመለከተ መሰረታዊው አውዱ ይህ ነው። እርሱ እርስ በርሳችሁ በምታደርጓቸው መግለጫዎች ውስጥ ቅንነትን፣ ታማኝነትን እና እውነተኛነትን አበክሮ እያሳሰበ ነበር። በውስጣችሁ ጥላቻን እና መጥፎ ሐሳብን ይዛችሁ በውጭ ፍቅርን አታሳዩ። እውነተኛ ፍቅርን ግለጡ። ያለ ግብዝነት እና ያለምንም ማስመሰል ታማኞች እና ሐቀኞች ሁኑ።

መጽሐፍ ቅዱስ በ (ሮሜ 12፥9) ላይ፣ “ፍቅራችሁ ያለ ግብዝነት ይሁን…” ይላል። ፍቅራችሁ የተሸሸገ ክፉ ዓላማ አይኑረው። ይህ ከአካላዊ የመግለጫ ምልክቶች በላይ የሚሄድ ነው። ስለ አጠቃላይ ባህሪያችሁ ይናገራል—እንዴት ሰላምታ እንደምትሰጡ፣ ግንኙነታችሁ እንዴት እንደሆነ፣ በክርስቶስ አካል ውስጥ ለሌሎች የምትሰጡት ምላሽ እንዴት እንደሆነ ይናገራል፤ ግብዝነት ሊኖር አይገባም።

የእግዚአብሔር ሕዝብ እንደመሆናችሁ መጠን፣ በጥርጣሬ ወይም በሁለትዮሽ አስተሳሰብ ሳይሆን፣ በቅንነት እና በእውነት ወደተመሠረተ ከፍ ያለ የሕይወት እና የግንኙነት ደረጃ ተጠርታችኋል። አንድ ነገር ተናግራችሁ ሌላ ነገር አታስቡ። በአንድ መንገድ እየሠራችሁ በሌላ መንገድ አታስቡ። ሕይወታችሁ ወጥ መሆን አለበት፤ ልባችሁ፣ ቃላችሁ እና ተግባራችሁ መገጣጠም አለባቸው።

በተጨማሪም፣ ጥበብን መለማመድ ወይም መጠቀም አለባችሁ። ዘመናቱ ተለውጠዋል፣ እናም መግለጫዎችም እንደየባህሉ ሊለያዩ ይችላሉ። ዋናው ነገር ውጫዊ መግለጫው ሳይሆን፣ ከጀርባው ያለው መንፈስ ነው፤ እርሱም በንጽሕና እና በማስተዋል የሚገለጥ እውነተኛ ፍቅር ነው። ስለዚህ ለሌሎች ፍቅርን እና አክብሮትን ስታሳዩ፣ እውነተኛ ይሁን። ቅን ይሁን። በልባችሁ ውስጥ ያለውን የክርስቶስን ፍቅር የሚያንጸባርቅ ይሁን። ቅዱስ የሚያደርገው ያ ነው።

🙏 ጸሎት
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
ውድ አባት ሆይ፣ በልቤ ውስጥ ስላለው ስለ ክርስቶስ ፍቅር አመሰግንሃለሁ። ለሌሎች በቅንነት፣ በሐቀኝነት እና በእውነተኛ ፍቅር እመላለሳለሁ። ቃላቶቼ እና ተግባሮቼ ወጥ የሆኑ እና በእኔ ውስጥ ያለውን የእግዚአብሔርን ተፈጥሮ የሚያንጸባርቁ ናቸው። መለኮታዊ ፍቅርን በንጽሕና እና በጥበብ እገልጣለሁ፣ በኢየሱስ ስም። አሜን።

📖 ለተጨማሪ ጥናት
├─ሮሜ 12:9
├─1ኛ ጴጥሮስ 1:22
├─2ኛ ቆሮንቶስ 6:6

━━━━//━━━

💫RHAPSODY OF REALITIES 💫(Amharic) 🇪🇹🇪🇹🇪🇹Friday 10, July 2026 አርብ፥ ሐምሌ 03 ቀን 2018 ዓ.ም.📜የሰውነትን እንቅስቃሴዎችን ግደሉ▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬...
10/07/2026

💫RHAPSODY OF REALITIES 💫
(Amharic) 🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Friday 10, July 2026
አርብ፥ ሐምሌ 03 ቀን 2018 ዓ.ም.

📜የሰውነትን እንቅስቃሴዎችን ግደሉ
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

📖 “እንደ ሥጋ ፈቃድ ብትኖሩ ትሞቱ ዘንድ አላችሁና፤ በመንፈስ ግን የሰውነትን ሥራ ብትገድሉ በሕይወት ትኖራላችሁ።” (ሮሜ 8፥13)።

👤 ፓስተር ክሪስ
════════
ከላይ ባለው ጥቅስ ውስጥ ልትረዱት የሚገባ ጥልቅ ሚስጥር አለ። ሐዋርያው ጳውሎስ ስለ “ሰውነት ሥራ” ሲናገር፣ ስለ ድርጊቶች ወይም ስለ ልማዶች ብቻ መናገሩ አይደለም። እርሱ እየተናገረ ያለው ከዚያ ጠለቅ ስላለው ነገር ነው፤ ይኸውም ስለ ሰውነት እንቅስቃሴዎች ወይም የሰውነት የሥራ ግንኙነቶች ነው።

ሰውነት የራሱ የሆኑ ክዋኔዎች ወይም ተግባራት አሉት። ተግባራቱን የሚያከናውነው በስሜት ሕዋሳት በኩል ነው—ለምታዩት፣ ለሚሰማችሁ እና በአካል ለምትለማመዱት ነገር ምላሽ በመስጠት ነው። በእነዚህም አማካኝነት ወደ ሕይወታችሁ የተለያዩ ዘገባዎችን እና ሁኔታዎችን በማምጣት “ጉዳዩን” ያከናውናል። አንዳንድ ጊዜ፣ ሰውነት “አንድ ነገር ይዞ ወደ ቤት ይመጣል”፤ ይህም ከተፈጥሯዊ ሂደቶች የሰበሰባቸው የበሽታ ምልክት፣ ድካም፣ ወይም ምቾት ማጣት ሊሆን ይችላል።

ነገር ግን እናንተ በእነዚያ እንቅስቃሴዎች ተጽዕኖ ሥር እንዳልሆናችሁ እንዳልሆናችሁ ማወቅ አለባችሁ። በዚህ ምድራዊ ዓለም መሠረታዊ ሕግጋት ወይም ሥርዓት መመራት የለባችሁም፣ ነገር ግን ከእነርሱ በላይ መኖር አለባችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ በ (ሮሜ 8፥6) ላይ፣ “ስለ ሥጋ ማሰብ ሞት ነውና፥ ስለ መንፈስ ማሰብ ግን ሕይወትና ሰላም ነው።” በማለት ይናገራል። ስለ ሥጋ ማሰብ ማለት በሰውነት ትእዛዝ እና ዘገባዎች መመራት፣ እንዲሁም ሰውነት ለሚለው እና ለሚሰማው ነገር ምላሽ መስጠት ማለት ነው። ይህ ግን የእናንተ ሕይወት አይደለም።

በመንፈስ እንድትኖሩ ተጠርታችኋል። ቃሉ ሲናገር በመንፈስ የሰውነትን ሥራ ብትገድሉ በሕይወት ትኖራላችሁ ይላል። ይህ ማለት በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት፣ እነዚያን የሰውነት እንቅስቃሴዎች ማሽመድመድ ትችላላችሁ ማለት ነው። የሰውነትን አሠራር ከንቱ ማድረግ ወይም ማፍረስ ትችላላችሁ። ተግባራቱንም ማስገዛት ትችላላችሁ። ሰውነታችሁ ሁኔታችሁን እንዲወስን ወይም እውነታችሁን እንዲገልጽ አትፍቀዱለት።

በእናንተ ውስጥ ያለው ሕይወት ታላቅ ነው። እርሱ የእግዚአብሔር ሕይወት ነው። እናም ያ ሕይወት በሰውነት ላይ ሥልጣንን ይሰጣችኋል። መጽሐፍ ቅዱስ በ (ሮሜ 8፥11) ላይ፣ “ነገር ግን ኢየሱስን ከሙታን ያስነሣው የእርሱ መንፈስ በእናንተ ዘንድ ቢኖር…ለሚሞተው ሰውነታችሁ ደግሞ ሕይወትን ይሰጠዋል።” ይላል። እርሱ ለሥጋዊ አካላችሁ ሕይወትን ይሰጣል። ውስንነቱንም ይሽራል።

ስለዚህ፣ ሰውነት ዘገባውን ይዞ ሲመጣ፣ እናንተ በመንፈስ ምላሽ ስጡ። ድክመትን ሲጠቁም ወይም ሲያመላክት፣ እናንተ በሕይወት ምላሽ ስጡ። ማንኛውንም ሁኔታ ሲያመጣ፣ እናንተን በሚገዛው በክርስቶስ ኢየሱስ የሕይወት መንፈስ በሆነው ከፍ ባለ የመንፈስ ሕግ ትመራላችሁ። ሃሌሉያ! ስለዚህ ኃላፊነትን ውሰዱ፤ እናም በሰውነታችሁ ላይ ሥልጣንን እና የበላይነትን ተለማመዱ። በእግዚአብሔር ቃል እና በመንፈስ ቅዱስ ኃይል በጤንነት ጠብቁት።

🙏 ጸሎት
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
ውድ አባት ሆይ፣ በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት በሰውነቴ ላይ ስላለኝ ሥልጣን አመሰግንሃለሁ። በስሜት ሕዋሳት ለመመራት እምቢ እላለሁ፤ ይልቁንም፣ በሕይወት፣ በብርታት እና በሥልጣን ለመመላለስ እመርጣለሁ፣ በኢየሱስ ስም። አሜን።

📖 ለተጨማሪ ጥናት
├─ሮሜ 8:6
├─ሮሜ 8:11
├─ ገላትያ 5:16

━━━━//━━━

💫RHAPSODY OF REALITIES 💫(Amharic) 🇪🇹🇪🇹🇪🇹Wednesday 08, July 2026 ረቡዕ፥ ሐምሌ 01 ቀን 2018 ዓ.ም.📜 ሁሉን ነገር የሚቀይር ህብረት▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬...
08/07/2026

💫RHAPSODY OF REALITIES 💫
(Amharic) 🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Wednesday 08, July 2026
ረቡዕ፥ ሐምሌ 01 ቀን 2018 ዓ.ም.

📜 ሁሉን ነገር የሚቀይር ህብረት
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

📖 “የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ የእግዚአብሔርም ፍቅር የመንፈስ ቅዱስም ኅብረት ከሁላችሁ ጋር ይሁን። አሜን።”
(2ኛ ቆሮንቶስ 13፡14)

👤 ፓስተር ክሪስ
════════
ከላይ ያለው የመክፈቻ ጥቅስ ኃይለኛ ቡራኬ ነው። መለኮታዊ ሥርዓትን ያሳያል፤ የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ፣ የእግዚአብሔር ፍቅር እና የመንፈስ ቅዱስ ኅብረት። ጸጋው የሚመጣው ከጌታ ኢየሱስ ነው። ፍቅር ከአብ ነው። ነገር ግን እግዚአብሔር ለእናንተ ያቀረበላችሁ ደስታ፣ የኑሮ ተሞክሮ የሚመጣው ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ባላችሁ ኅብረት ነው።

ስለ ጸጋ ማውራት እና የእግዚአብሔርን ፍቅር ማክበር ትችላላችሁ። ነገር ግን እነዚህ በህይወታችሁ ውስጥ ሕያው እውነታዎች የሚሆኑት በመንፈስ ቅዱስ በኩል ነው። እነዚህን በዕለት ተዕለት ልምዳችሁ ውስጥ የሚያመጣቸው እና ተጨባጭ የሚያደርጋቸው እርሱ ነው። መንፈስ ቅዱስን ስታውቁ ሁሉም ነገር ይለወጣል። በሕይወታችሁ ውስጥ የሚመጣ ውበት አለ። በጽድቅ በመራመዳችሁ ውስጥ ድምቀት፣ ክብር፣ ብልጽግና አለ። ከውስጣችሁ ኃይል ይሰጣችኋል።

ይሄ መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ውስጥ እና ከእናንተ ጋር ለሆነ ውቅት ብቻ ሳይሆን ሁልጊዜ እና ለዘላለም ነው። ጌታ ኢየሱስ እንዲህ አለ፤ “እኔም ወደ አብ እጸልያለሁ ለዘላለምም ከእናንተ ጋር እንዲኖር ሌላ አጽናኝ ይሰጣችኋል፤” (ዮሐንስ 14፡26)። እርሱ አስተማርያችሁ ነው፤ መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል፤ “. . . ግን መንፈስ ቅዱስ የሆነው አጽናኝ እርሱ ሁሉን ያስተምራችኋል እኔም የነገርኋችሁን ሁሉ ያሳስባችኋል።” በመጽሐፍ ቅዱስ ቃሉ ውስጥ ያለውን የእግዚአብሔርን ጥሪና በረከቶች እንድታውቁ እና በዛም እንድትመላለሱ የእግዚአብሔርን ቃል ጥቅሶች መረዳታችሁን ይከፍተዋል።

1ኛ ቆሮንቶስ 2፡12 ላይ እንዲህ ይላል ”እኛ ግን ከእግዚአብሔር እንዲያው የተሰጠንን እናውቅ ዘንድ ከእግዚአብሔር የሆነውን መንፈስ እንጂ የዓለምን መንፈስ አልተቀበልንም።”። ማስተዋላችሁን ይቀባል፤ ስለ መለኮታዊ እውነቶች እና ስለ መንግሥቱ ምስጢሮች ጥልቅ ዕይታን ይሰጣችኋል። በእርሱ አማካኝነት ሕይወታችሁ ከፍ ያለ ደረጃን ይይዛል። ከተፈጥሯዊ በላይ ታያላችሁ፣ በግልጽነት፣ በዓላማ እና በእርግጠኝነት ትሰራላችሁ።

መንፈስ ቅዱስን ስታውቁ ሕይወት ወሰን የለሽ ይሆንላችኋል። በሁኔታዎች ላይ የተመሰረተ ሳይሆን በውስጣችሁ በሚኖረው ሰው ላይ የተመሰረተ ውስጣዊ የስኬት ማረጋገጫ ትይዛላችሁ። ከመንፈስ ጋር ኅብረታችሁን መገንባታችሁን ቀጥሉ። ከእርሱ ጋር ተመላለሱ፤ ከእሱ ጋር ተነጋገሩ. በየቀኑ እና በሁሉም ነገር ይመራችሁ፣ እናም ሁል ጊዜ በክብር ትራመዳላችሁ።

🙏 ጸሎት
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
ውድ አባት ሆይ፣ ስለ መንፈስ ቅዱስ ስጦታ እና ከእርሱ ጋር የኅብረት እንዳደርግ ስለሰጠኸኝ መብት አመሰግንሃለሁ። በየቀኑ ከእርሱ ጋር ያለኝን ህብረት በመረዳት እመላለሳለሁ፤ እናም ህይወቴ በመገኘቱ የተዋበ፣ የሚመራ እና ኃይል ያለው ነው። በማደርገው ነገር ሁሉ ክብርህን በመግለጽ፣ ከገደብ በላይ እኖራለሁ። በኢየሱስ ስም። አሜን።

📖 ለተጨማሪ ጥናት
├─ዮሐንስ 16፡13
├─ሮሜ 8፡11
├─1ኛ ቆሮንቶስ 2፡12
━━━━//━━━

Address

Addis Ababa
1000

Telephone

+251911067343

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Living Light - ሕያው ብርሃን posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to Living Light - ሕያው ብርሃን:

Shortcuts

Share