15/05/2023
የማንነት ጥያቄ
ማን ነኝ? ምንድን ነኝ? የማን ወገን ነኝ?
የዘመናችን የሀገራችን ሰዎች ጥያቄ ነው።
የእግዚአብሔር ጥሪ ወደ ልጁ ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ህብረት ነው። “ወደ ልጁ ወደ ጌታችን ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ኅብረት የጠራችሁ እግዚአብሔር የታመነ ነው።” 1 ቆሮ 1፡9 ይሄ ህብረት ደግሞ እኛን ከእግዚአብሔር ጋር የአባትና ልጅ ግንኙነት የሰጠን ነው። በክርስቶስ ላሉት የእግዚአብሔር ቤተሰብነት ተሰጥቶአቸዋል።
ሰው ከሰማይና ምድር ፈጣሪ እግዚአብሔር ጋር ሕብረት ከፈጠረ፣ አሮጌው ሐጥያተኛ ማንነቱ ተሽሮ በአዲስ ሕይወት መኖር ከጀመረ፣ የትኛው የምድር ህብረት ሊገዛው ይችላል? የእግዚአብሔር ልጅነትን ካገኘን የትኛው የማንነት ቀውስ ያገኘናል? ማንነቴ የእግዚአብሔር ልጅ ህብረቴ ከክርስቶስ ጋር በደሙ ከዳኑት ቅዱሳን ጋር።
በኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በተሰራው የደህንነት ስራ ያልተመለሰ የማንነት ጥያቄ በየትኛውም ምድራዊ ሐይል ሊመለስ አይትችልም።