10/06/2026
የባሃኢ እምነት በመልክተኞቹ አማካኘኝነት የሚመጣው የእግዚአብሔር ትምህርትና መመሪያ ማለቂያ
እንደሌለው ያስተምራል። ለዘመናት ሁሉ አምላክ የሰው ልጆችን ማስተማር እና መምራት አቁሞ
አያውቅም። ይህ የአምላክ ትምህርትና መመሪያ ወደ ሰው ልጆች የሚመጣው በተከታታይ ግልጸት
አማካኝነት ነው። አዲስ ብርሃን ለመስጠት በየቀኑ ፀሐይ እንደምትወጣ ሁሉ፣ የእግዚአብሔር ትምህርትና
መመሪያ በመልእክተኞቹ በኩል ደጋግሞ ያበራል።