ማርያም ፊደል ናት ኑ እንማራት

ማርያም ፊደል ናት  ኑ እንማራት ያለ እመቤቴ ክርስቶስ ያለ ክርስቶስ ክርስትና የለም አትሳቱ ሀይማኖት እስኪ ጠይቁ ከሚያውቁት

15/03/2024
13/03/2024

ናታኔም የወጣቶች መንፈሳዊ ማህበር

13/03/2024

#እንኳን አደረሳቹህ
ይህን መዝሙር ልንጋብዛቹህ ወደድን
ገብረህይወት ገብረህይወት
ከኒሳ መጣ ሊባርካት
ኢትዮጵያ መጣ ሊጠለልባት(×2)
በዝቋላ ገዳም መቶ ዓመት ፀለየ
አባታችን ለኛ ጌታን ተማፀነ
በባህር ውስጥ ጠልቀህ ማርልኝ ብለሀል
ለኢትዮጵያውያን ምህረት ለምነሀል
ገብረህይወት ገብረህይወት
ከኒሳ መጣ ሊባርካት
ኢትዮጵያ መጣ ሊጠለልባት(×2)
አንበሳ ነብር ይከታተልሀል
በፀጋህ ተሞልተው ላንተ ተገዝተዋል
የቅዱሳን ራስ ገብረ መንፈስ ቅዱስ
ቃል ኪዳን ተሰጠህ ምድረ ከብድ ስትደርስ
ገብረ ህይወት ገብረ ህይወት
ከኒሳ መጣ ሊባርካት
ኢትዮጵያ መጣ ሊጠለልባት(×2)
የናትክን ጡት ሳትቀምስ የኖርክ በበረሀ
ልብስህ ፀጉር ብቻ ግሩም የአምላክ ስራ
እንማፀናለን ሁላችን በአንድነት
ፀሎትህ እንዲያወጣን ከሀጢያት ከመቅሰፍት
ገብረ ህይወት ገብረህይወት
ከኒሳ መጣ ሊባርካት
ኢትዮጵያ መጣ ሊጠለልባት(×2)💟💟💟💟
ለዘማሪ እንግዳወርቅ ዝማሬ መላእክት ያሰማልን!!!💟💟💟አሜን💟💟💟

👏                 ⛪    (((የአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ታሪክ ባጭሩ)))                                                             🍁⛪   ...
13/03/2024

👏

(((የአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ታሪክ ባጭሩ)))
🍁⛪
🌿 የገዳም መብራት ፃድቁ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ
ከአባታቸው ከ ስምኦን ከእናታቸው አቅሌስያ በንዒሳን
/ግብፅ/ መጋቢት 29 ቀን ተፀንሰው። ታህሳስ 29 ቀን
ተወለዱ። አባታችን በተወለዱ ግዜ ከእናታቸው እቅፍ በመውረድ ከጨለማ ወደ ብርሀን ያወጣኸኝ አምላክ ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ምስጋና ይገባል በ ማለት ሶስት ጊዜ ሰግደው አመስግነዋል ።ገብረ መንፈስ ቅዱስ ማለት የመንፈስ ቅዱስ ባሪያ ማለት ነው።
🌷 አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ብዙ አናብርትና አናብስት
የተገዙላቸው ታላቅ ፃድቅ ናቸው መጋቢት 5 ቀን በክብር
አርፈዋል።
የፃድቅ መታሰቢያ ለበረከት ነው፤ የኀጥዐን ሰም ግን
ይጠፋል። ምሳሌ 10:7
የፃድቁ አባታችን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ፀጋ ልመና ረድኤት በረከታቸው ከሁላችን ጋር ይሁን👏
አሜን(፫)💚💛❤🙏

ወስብሐት ለ እግዚአብሔር
((አሜን))

ይሄ የእናታችን ቅድስት ስዕለአድኖህ ማን ትባላለች ??
03/11/2023

ይሄ የእናታችን ቅድስት ስዕለአድኖህ ማን ትባላለች ??

ይህ የምታየው እሳት ወይ ሌላ ነገር ሊመስልህ ይችላል ግን እንደ ፀሀይ የሚያበራው / የሚያብረቀርቀው / የተዋህዶ ልጆች ናቸው
03/11/2023

ይህ የምታየው እሳት ወይ ሌላ ነገር ሊመስልህ ይችላል
ግን እንደ ፀሀይ የሚያበራው / የሚያብረቀርቀው / የተዋህዶ ልጆች ናቸው

.......…ማርያም እንወድሻለን /2/…....…........ስለወለድሽ የሕይወት ምግብን…….............ማርያም እንወድሻለን….….....…ድክመቴን አትይ-------------------ማ...
01/11/2023

.......…ማርያም እንወድሻለን /2/…....…........ስለወለድሽ የሕይወት ምግብን…….............ማርያም እንወድሻለን….….....…
ድክመቴን አትይ-------------------ማርያም
በሃጥያት መውደቄን---------------ማርያም
ተስፋዬ አንቺ ነሽ ------------------ማርያም
እስከ እለተ ሞቴ-------------------ማርያም
ላልከዳሽ ምያለሁ------------------ማርያም
ከስርሽ ላልጠፋ--------------------ማርያም
ገፀ በረከቴ ------------------------ማርያም
የሕይወት ዋስትና--------------------ማርያም
/አዝ/……………….
የምእመናን ውበት ----------------ማርያም
ዘውድ አክሊላቸው----------------ማርያም
ድንግል አንቺ እኮ ነሽ --------------ማርያም
የመንገድ ስንቃቸው ---------------ማርያም
ምስክር ነን ላንቺ ------------------ማርያም
እንደ ነቢያቱ----------------------ማርያም
ስጦታ መሆንሽን-------------------ማርያም
ለአዳም ልጆች ሁሉ ----------------ማርያም
/አዝ/……………….
ሞገስና ፀጋ ----------------------ማርያም
በጌታ ፊት ያለሽ--------------------ማርያም
ከሰይጣን መሸሻ -------------------ማርያም
ዋስ ጠበቃችን ነሽ------------------ማርያም
እንዴት ነበር ያኔ--------------------ማርያም
ጌታን ስትወልጂ--------------------ማርያም
የእረኞቹ ደስታ----------------------ማርያም
የመላእክት ዝማሬ-------------------ማርያም

07/09/2023
07/09/2023

[ጳጉሜን 3 በዓሉ የሚከበርለት የሊቀ መላእክት የቅዱስ ሩፋኤል ታሪክ]
✍በመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ
♥ ቅዱስ ሩፋኤል ቊጥሩ ከሰባቱ ሊቃነ መላእክት ሲኾን፤ ሩፋ ማለት ሐኪም፤ ኤል ማለት እግዚአብሔር ማለት ሲኾን ሩፋኤል ማለት “እግዚአብሔር ሐኪሜ ነው” ማለት ነው፤ ሄኖክም “በሰው ቁስል ላይ የተሾመ ከከበሩ መላእክት አንዱ ቅዱስ ሩፋኤል ነው” ይለዋል (መጽሐፈ ሄኖክ 6፥3)::

♥ ይኽ መልአክ በራማ ሰማይ ያሉ ነገደ መናብርትን የሚመራቸው ነው፡፡ ነገደ መናብርት ያላቸው ቅዱስ ሩፋኤል የሚመራቸው በራማ ሰማይ የሚኖሩ ነገደ መላእክት ናቸው፡፡

♥ ቅዱስ ኤጲፋንዮስም በሥነ ፍጥረት መጽሐፉ ላይ “ወለዳግም ጾታ ዐሠርቱ ስሞሙ መናብርት ወሊቆሙ ሩፋኤል እሉ እሙንቱ እለ ይቀልል ሩጸቶሙ እምነፋስ ወእለ ይጸውሩ ወላትወ መብረቅ ወኲናተ እሳት ዘይነድድ ወአንበሮሙ በዳግሚት ሰማይ” ይላል በራማ ሰማይ የሚገኘውን ኹለተኛውን ዐሥሩን ነገድ መናብርት ሲላቸው አለቃቸው ቅዱስ ሩፋኤል ነው፤ እነዚኽም ረቂቅ የኾነ የመብረቅ ጋሻ የእሳት ጦር ይዘው ከነፋስ ይልቅ የፈጠኑ ሲኾኑ በራማ በኹለተኛው ክፍል ላይ አስፍሯቸዋል፡፡ ቅዱስ ሩፋኤል ከሚመራው ከዚኽ ነገድ 24ቱ ካህናተ ሰማይ ወጥተዋል፡፡

♥ አባ ጊዮርጊስም በሰዓታቱ ላይ ስለነዚኽ መላእክት ፡-

“ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር ጽርሐ አርያም ማኅፈዱ
መካነ ትጉሃን ዐጸዱ ካህናተ ሰማይ ቅዉማን በዐውዱ አክሊላቲሆሙ ያወርዱ ቅድመ መንበሩ እንዘ ይሰግዱ ይርዕዱ ወኢይዝብጦሙ ሶበ ይበርቅ ነዱ”

(ጽርሐ አርያም አዳራሹ፤ የትጉሃን መኖሪያ ቦታው የሚኾን እግዚአብሔር ቅዱስ፣ ቅዱስ፣ ቅዱስ ተብሎ በአንድነት በሦስትነት ይመሰገናል፤ ካህናተ ሰማይ በዙሪያው ይቆማሉ፤ በዙፋኑ ፊት እየሰገዱ አክሊሎቻቸውን ያወርዳሉ፤ እሳትነቱ (ባሕርዩ) በሚበርቅ፣ ወገግ በሚል ጊዜ እንዳይመታቸው ይንቀጠቀጣሉ) ይላል

♥ ሊቁ እንደጠቀሰው በዕለተ እሑድ ሥሉስ ቅዱስ ሰባቱን ሰማያት ፈጥረዋል፤ ከዚያም ልዑል እግዚአብሔር በዕለተ እሑድ ሰባቱን ሰማያት ከፈጠረ በኋላ ሊቁ በአክሲማሮስ እንደገለጸው ከቅዱሳን መላእክት መኻከል፡-

“ወእምዝ ነሥአ እግዚአብሔር እምሰራዊተ ሩፋኤል ፳ወ፬ተ ሊቃናተ ወአቀሞሙ ዐውደ መንበሩ፤ ወሰመዮሙ ለእሙንቱ ካህናተ ሰማይ ወወሀቦሙ ማዕጠንታተ ዘእምወርቀ እሳት ወአክሊላተ ብርሃን ዘእምጳዝዮን ወአብትረ ዘከተማሆን መስቀል ወአልበሶሙ አልባሰ ክህነት” እንዲል ከሰራዊተ ሩፋኤል ፳፬ት ሊቃናትን መርጦ በመንበረ ስብሐት በመጋረጃዋ ውስጥ ዙሪያዋን ክንፍ ለክንፍ ገጥሞ አቁሟቸዋል (ሕዝ ፩፥፲፩-፲፪)።

♥ ቊጥራቸውን ኻያ አራት ማድረጉ በኻያ አራቱ ጊዜያት ጸልየው ሌላውንም ራሳቸውንም ጠብቀው ዋጋቸውን ተቀብለው የሚኖሩ በመኾናቸው ሲኾን እነዚኽንም መላእክት “ካህናተ ሰማይ” ሲላቸው የእሳት የወርቅ ጽና ሲያሲዛቸው የብርሃን አክሊል ጳዝዮን የሚባል የብርሃን ዘውድ ደፍቶላቸዋል፤ የብርሃን ዘንግ ማኅተሙ መስቀል የኾነ ሲያሲዛቸው የብርሃን ካባ ላንቃ ሕብሩ መብረቅ የመሰለ አልብሷቸዋል ( ራእ ፬፥፬-፭፤፲-፲፩)።

♥ እነዚኽ ከሰራዊተ ሩፋኤል የወጡ ሰማያውያን ካህናት በአንድ ላይ ባጠኑ ጊዜ ዛሬ በክረምት ጊዜ ጉም ተራራውን እንደሚሸፍነው ከማዕጠንታቸው የሚወጣው ጢስ መልኩ መብረቅ፣ ድምፁ ነጐድጓድ፣ መዐዛው መልካም የኾነና ጽርሐ አርያም፣ መንበረ መንግሥት የተባሉትን የብርሃን ሰማያት የሚሸፍንና የሚጋርድና ከጢሱ ጋር የቅዱሳን ጸሎት ዐብሮ ወደ እግዚአብሔር ፊት ይወጣል።

✍ “ሌላም መልአክ መጣና የወርቅ ጥና ይዞ በመሠዊያው አጠገብ ቆመ፤ በዙፋኑም ፊት ባለው በወርቅ መሠዊያ ላይ ለቅዱሳን ኹሉ ጸሎት እንዲጨምረው ብዙ ዕጣን ተሰጠው የዕጣኑም ጢስ ከቅዱሳን ጸሎት ጋር ከመልአኩ እጅ በእግዚአብሔር ፊት ወጣ” እንዳለ ዮሐንስ በራእዩ (ራእ ፰፥፫-፭)፡፡

♥ ቅዱስ ኤጲፋንዮስ በአክሲማሮስ ላይ “ወቦ ኪሩቤል ይቀውሙ በየማን በአምሳለ ቀሳውስት ወሱራፌል ይቀውሙ በአምሳለ ዲያቆናት ወድኅሬሆሙ ካህናተ ሰማይ ወቦ እልፍ አእላፋት ወትእልፊተ አእላፋት መብረቅ ወነጐድጓድ ወሠረገላሆሙኒ ምሉኣነ አዕይንት” እንዳለ
★ ኪሩቤል በቀኝ ሱራፌል በግራ ከፍ ብለው የሩፋኤል ሰራዊት ካህናተ ሰማይ ክንፍ ለክንፍ ገጥመው በስተኋላቸው ሲታዩ በሰማይ ውዱድ ዙሪያ እልፍ አእላፋት መብረቅ፣ ነጐድጓድ፣ ሠረገላ፣ እንደ መስታየት ብሩህ የኾነ ሲኖርበት እነዚኽ ቅዱሳን መላእክትም ሳያቋርጡ “ቅዱስ፣ ቅዱስ፣ ቅዱስ እግዚአብሔር” እያሉ ፈጣሪያቸውን በአንድነቱ በሦስትነቱ ያመሰግኑታል (ራእ ፬፥፰)፡፡

♥ ይኽ መልአክ ሩፋኤል ጦቢትን የተራዳ መልአክ ነው፤ ይኽ ጦቢት ዐሥሩ ነገድ በ፯፻፳ ቅድመ ልደተ ክርስቶስ ሲማረኩ ዐብሮ የተማረከ ጻድቅ ሰው ነው፤ ይኽ ሰውን በመርዳት በደግነቱ የታወቀው ጦቢት ከመንገድ ወድቆ የተገኘ በድን ቀብሮ፤ በዚያው ሌሊት ከቅጥሩ አጠገብ ፊቱን ተገልጦ ተኝቶ ሳለ አዕዋፍ ትኩስ ፋንድያ ዐይኑ ላይ ጥለውበት እንደ ብልዝ ያለ ወጥቶበት ዐይኑ ጠፋ፤ ሚስቱም ባለማስተዋል “አይቴ ውእቱ ምጽዋትከ ወጽድቅከ” (በጐነትኽ ምጽዋትኽ ያዳነኽ ወዴት ነው?) በማለት በተናገረችው ጊዜ ዐዝኖ ሞትን ተመኘ (ጦቢ ፪፥፲፬)፡፡

♥ ያን ጊዜ መልአኩ ሩፋኤል ባሎቿ ስለሞቱባት ቤተሰቦቿ ያንቋሽሿት የነበረችውን የራጉኤል ልጅ ሳራን ለማዳን ተልኮ በመምጣት አስቀድሞ በርሷ ላይ ዐድሮ ባሎቿን ይገድልባት የነበረውን ጋኔን አስወጥቶላት የጦቢት ልጅ ጦብያ እንዲያገባት አድርጓል፤ በዚኽም “ፈታሔ ማሕፀን” ተብሏል "ለሰብእ ወለእንስሳ ፈታሔ ማሕፀኖሙ አንተ" እንዲለው፡፡

♥ በኋላም ወደ ጦቢት በመኼድ ረዥም ዘመን የታወረ ዐይኑን አብርቶለት “አነ ውእቱ ሩፋኤል መልአክ አሐዱ እምነ ሰብዐቱ ቅዱሳን መላእክት” (ከሰብዐቱ ሊቃነ መላእክት አንዱ ሩፋኤል እኔ ነኝ) ብሏቸው ተሰውሯል (ጦቢ ፲፪፥፲፭)፡፡
✍በመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ ተጻፈ
[የቅዱስ ሩፋኤል በረከት ይደርብን]

ክብር ለአባቶቻችን የአባቶቻች ቀን መልካም ትጉ የሆንትን አባቶች እስኪ እናበረታታ ዛሬ በዚህ ቀን በውስጥ መስመር ላኩል ፎቶቸውን እመሰግናቸዋለን ሼር ሼር ይደረግ
07/09/2023

ክብር ለአባቶቻችን የአባቶቻች ቀን መልካም ትጉ የሆንትን አባቶች እስኪ እናበረታታ ዛሬ በዚህ ቀን በውስጥ መስመር ላኩል ፎቶቸውን እመሰግናቸዋለን ሼር ሼር ይደረግ

Address

Medhanealm
Addis Ababa
IPPP

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ማርያም ፊደል ናት ኑ እንማራት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to ማርያም ፊደል ናት ኑ እንማራት:

Share