የክርስቶስ ምስክሮች

የክርስቶስ ምስክሮች ChrstianView

15/03/2026

ክርስትና እንደገባህ የሚታወቀው ደቀ መዝሙር ስትሆን ነው

15/03/2026

በልሳን ካለመናገር በልሳን መናገር ጥሩ ነው።

16/11/2025

ዛሬ ቸርች ምን ተማራቹ ?

15/11/2025

የ health & wealth Gospelን የምታቀወሙ ግን ደግሞ ልክ አንድ ክርስቲያን በተለይ አገልጋይ ሲታመም እግዚአብሔር በሀጢያቱ ምክንያት እንደቀጣው ምታሰቡ ሰዎች ግን ምኑን "የጤናና የብልፅግና ወንጌልን" ተቃወማቹ ታዲያ።

በነገራችን ላይ በሀጢያቱ ምክንያት እንደተመታ ካሰብን ሁላችን አልጋ ቁራኛ በሆንን ነበር እኮ

እኔ በህመም የማልማቅቀው ሀጢያት ስላለሠራው ነው ብሎም ማሰብ ነው።

እያስተዋልና ዘመዴ

13/11/2025

አገልጋይ ስትጋብዙ የአገልግሎት ምስክርነቱን ሰምታችሁ ብቻ ሳይሆን የሕይወት ምስክርነቱንም ሰምታቹ ብትጋብዙ መልካም ነው።

በጣም ብዙ አገልጋዮች(ሰባኪዎች ፣ዘማሪዎች) የመድረክ performance ታይቶ ብቻ መጋበዝ እየተለመደ ከመጣ ሰንበትበት ብሏል። ዋናው ጉባኤውን በስብከቱ አሜን ያስብል እንጂ በዝማሬው ያዘልል እንጂ፤ ማነህ? ፣ ከየት ነህ?፣ ህይወት እንዴት ነው? የሚለውን የሚጠይቅ እና የሚያጠያይቅ ጠፍቷል ።
ወገን የቤተክርስቲያን መድረክ ማንም የሚፈነጭበት የTalent show መስሏል። በጣም የሚያሳዝነው ደግሞ ህይወቱ በሀጢያት እንደጨቀየ እያወቀ መድረክ ላይ ቆሞ ማገልገሉ ሳይሆን ፤ ሚያሳዝነው አገልጋዮ ያለበትን የሀጢያት ልምምድ እያወቅን የምንጋብዝ ሰዎች እናሳፍራለን።

ጳውሎስ በቆሮንጦሳውያን ያዘነው ያ ከ እንጀራ እናቱ ጋር ዝሙት የሰራውን ሰው በጉያቸው ይዘው ማቆየታቸው ነበር። ለዛም ነው እንዲህ ያላቸው 👉“እናንተም ታብያችኋል፤ ይልቅስ እንድታዝኑ አይገባችሁምን? ይህን ሥራ የሠራው ከመካከላችሁ ይወገድ።”
— 1ኛ ቆሮንቶስ 5፥2

የጫት ሱስ እንዳለበት እያወክ፣ የመጠጥ ሱስ እንዳለበት እያወክ፣ በዝሙት የተጨማለቀ ህይወት ዉስጥ እንዳለ እያወክ ላንተ የ Program ማድመቂያ መጠቀምህ ሰዋዊ ደግሞም አጋንንተዊ ነው። ለመንጋህ የማትራራ ሙያተኛ እረኛ መሆንህንም የሚያሳይ ነው።

16/10/2025

እኔ ቆሻሻ ነኝ እርሱ ንጉሥ ነው !

እዉነት እስኪ አሁን መሠረታዊ የክርስትና ት/ት የተማረ ቃሉን ያነበበ የሚፀልይ ጴንጤ እዉነት እዚ ሰዉ ጋር ልገልገል ብሎ ይሄዳል?🙄🙄🙄እዚህ ሰዉ ጋር የሚሄዱት አብዛኞዉ ሰዎች መሠረታዊ ት/ት...
07/03/2025

እዉነት እስኪ አሁን መሠረታዊ የክርስትና ት/ት የተማረ ቃሉን ያነበበ የሚፀልይ ጴንጤ እዉነት እዚ ሰዉ ጋር ልገልገል ብሎ ይሄዳል?🙄🙄🙄

እዚህ ሰዉ ጋር የሚሄዱት አብዛኞዉ ሰዎች መሠረታዊ ት/ት ያልተማሩ ፣ቃሉን የማያውቁ፣ በከፍተኛ የገንዘብ ፍቅር የተነደፉ ሰዎች ናቸዉ። እናንተ ሰዎች ወደ ቃሉ ተመለሱ

07/03/2025

ወንጌል ሳኦልን ጳዉሎስ ያደርጋል

10/07/2024

የዳንነዉ በእምነት ነዉ ያዳነን ፀጋዉ ነዉ

29/05/2024

ጥያቄ፦ እኛ ክርስቲያን የሆንን የሙስሊም አማኞችን ነብይ መሀመድን "ነበዩ መሀመድ" ብለን መጥራት አለበን? ወይስ መሀመድ ብቻ? ምን ይመስላቹሀል?
ሀሳባቹሁን በጨዋነት ደንብ አስቀምጡ።

Address

Ayat
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የክርስቶስ ምስክሮች posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share