Bible Army - Army Chapel

Bible Army - Army Chapel "Raising People that Bring Righteous Impact up on Nations"

15/09/2026

“የድል ቁመና”

እነሆ መልካም ዜና!

ከመጪው እሁድ ጀምሮ ለተከታታይ አራት እሁዶች፣ ቶማስ ምትኩ (ሐዋርያ) ከቤተክርስቲያኒቱ አገልጋዮች እንዲሁም ከተጋባዥ ዘማሪያን ጋር በመሆን በልዩ የበረከትና የድል ፕሮግራም ያገለግላሉ።

ይህን የተባረከ ጊዜ ከእኛ ጋር ያሳልፉ!
እግዚአብሔር የድል ቁመናን ይስጣችሁ!

አድራሻ፦ ቦሌ ቡልቡላ፣ ግራር አካባቢ፣ ኦሮሚያ ባንክ በሚገኝበት ሕንፃ 2ኛ ፎቅ።

📞 ተጨማሪ መረጃ፦ 0911 645 468

🙏 የምስጋና ሕይወት📖 ዋና ጥቅስ፦ መዝሙር 110፥1–5🎙️ አገልጋይ፦ ፓስተር እስራኤልእግዚአብሔር በሚያመሰግነው ሕዝብ መካከል ይከበራል። ምስጋናም በአፋችን ብቻ ሳይሆን፣ የሕይወታችን አካል ...
14/09/2026

🙏 የምስጋና ሕይወት

📖 ዋና ጥቅስ፦ መዝሙር 110፥1–5
🎙️ አገልጋይ፦ ፓስተር እስራኤል

እግዚአብሔር በሚያመሰግነው ሕዝብ መካከል ይከበራል። ምስጋናም በአፋችን ብቻ ሳይሆን፣ የሕይወታችን አካል መሆን አለበት።

በደስታም ሆነ በመከራ፣ በበረከትም ሆነ በጉድለት፣ ጌታን ማመስገን አለብን። ምክንያቱም እግዚአብሔር ያደረገልን ከሚያጋጥመን ችግር እጅግ ይበልጣል።

እንዴት እናመስግነው?

🔹 በአንደበታችንና በንግግራችን
🔹 በዝማሬና በአምልኮ
🔹 በቅዱስ ኑሮአችንና በመልካም ሥራችን
🔹 በእምነት፣ በተስፋና በመከራ ጊዜ

መቼ እናመስግነው?

✅ እግዚአብሔር ጸሎታችንን ከመለሰ በኋላ — ዘጸአት 15፥1
✅ መልሱን ከማየታችን በፊት — 2ኛ ዜና 20፥22
✅ በመከራና በፈተና ጊዜ — የሐዋርያት ሥራ 16፥25
✅ ሁልጊዜ! — ፊልጵስዩስ 4፥4

“በጌታ ሁልጊዜ ደስ ይበላችሁ፤ ደግሜም እላለሁ፥ ደስ ይበላችሁ።”
ፊልጵስዩስ 4፥4

ወገኖቼ፣ ምስጋናችን በሁኔታዎች ላይ ሳይሆን፣ በማይለወጠው በእግዚአብሔር ላይ ይመሥረት። ነፍሳችንም ሁልጊዜ ጌታን ታመስግን!

#የምስጋናሕይወት

📢 የአዲስ ዓመት የምስጋና ጥሪነገ እሁድ ከጠዋቱ 4፡00 ጀምሮ በመጽሐፍ ቅዱስ ሠራዊት ዓለም አቀፍ ቤተክርስቲያን አርሚ ቡልቡላ አጥቢያ እንገናኝ! 🙏አዲሱን ዓመት በምስጋና እና በጸሎት አብረ...
12/09/2026

📢 የአዲስ ዓመት የምስጋና ጥሪ

ነገ እሁድ ከጠዋቱ 4፡00 ጀምሮ በመጽሐፍ ቅዱስ ሠራዊት ዓለም አቀፍ ቤተክርስቲያን አርሚ ቡልቡላ አጥቢያ እንገናኝ! 🙏

አዲሱን ዓመት በምስጋና እና በጸሎት አብረን እንጀምር። የጌታን ቸርነት እያወሳን፣ ለአዲሱ ዘመን በበረከት እንሻገር!

“እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ መልካም ነውና፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና።” — መዝሙር 107፥1

📍 አርሚ ቡልቡላ አጥቢያ
⏰ ነገ እሁድ፣ ከጠዋቱ 4፡00 ጀምሮ

ኑ! አመቱን በምስጋና እንጀምር! 🙌

የ2019 ዓ.ም. ዋዜማ ምሽት — የፎቶ ማስታወሻ 📍 በቦሌ ቡልቡላ አርሚ አጥቢያ“እግዚአብሔር ድንቅ ነው! ጊዜ ሰጠን፣ ጸጋው ጠበቀን፣ በቸርነቱም እስከዚህ አደረሰን።” 🙏❤️ከ2018 ዓ.ም. ...
11/09/2026

የ2019 ዓ.ም. ዋዜማ ምሽት — የፎቶ ማስታወሻ

📍 በቦሌ ቡልቡላ አርሚ አጥቢያ

“እግዚአብሔር ድንቅ ነው! ጊዜ ሰጠን፣ ጸጋው ጠበቀን፣ በቸርነቱም እስከዚህ አደረሰን።” 🙏❤️

ከ2018 ዓ.ም. ወደ 2019 ዓ.ም. ስንሻገር፣ በምስጋና፣ በጸሎት ያሳለፍነው የተባረከ የዋዜማ ምሽት።

“እስከዚህ ድረስ እግዚአብሔር ረድቶናል።”
— 1 ሳሙኤል 7፥12

🙏 ለሰጠን ጊዜ፣ ለጠበቀን ጸጋ፣ ለሰጠን አዲስ ዓመት ምስጋና ይሁን!

🎉 መልካም 2019 ዓ.ም.!
አዲሱ ዓመት የበለጠ ጸጋ፣ አንድነት፣ ኃይልና የመንግሥቱ ሥራ የሚፋጠንበት ዓመት ይሁን!

#2019ዓም #ዋዜማ #አርሚአጥቢያ #የፎቶማስታወሻ #መልካምአዲስዓመት

አዲስ ዓመትን በፍቅርና በአንድነት! የመጽሐፍ ቅዱስ ሠራዊት ዓለም አቀፍ ቤተክርስቲያን ዋና ቢሮ፣ ከቦሌ ቡልቡላ አርሚ አጥቢያ እና ከወሰን አካባቢ ጎልደን አጥቢያ ጋር በመተባበር፣ አዲሱን ዓ...
10/09/2026

አዲስ ዓመትን በፍቅርና በአንድነት!

የመጽሐፍ ቅዱስ ሠራዊት ዓለም አቀፍ ቤተክርስቲያን ዋና ቢሮ፣ ከቦሌ ቡልቡላ አርሚ አጥቢያ እና ከወሰን አካባቢ ጎልደን አጥቢያ ጋር በመተባበር፣ አዲሱን ዓመት በፍቅር፣ በምስጋናና በማጋራት ጀምረናል።

በቦሌ ቡልቡላ አካባቢ በሚገኘው ** የአረጋውያን ማረፊያ** ስፍራ በመገኘት፣ ለ201 አረጋውያን የበሬ ሰንጋን ይዘን በመሄድ የመዓድ ማጋራት፣ የፍቅርና የህብረት ጊዜን አብረን በማሳለፍ ልዩ የጉብኝት ጊዜ አድርገናል።

በዚህም ጊዜ አብረን ጌታን በዝማሬ አክብረናል፤ ዘላለማዊ የሆነውን የእግዚአብሔርን ቃል ከአረጋውያኑ ጋር ተካፍለናል። እንዲሁም ለዝማሬና ለምስጋና አገልግሎታቸው የሚያግዛቸውን የሙዚቃ መሣሪያ በስጦታ አበርክተናል።

ከአረጋውያኑ ጋር ያሳለፍነው ጊዜ የፍቅር፣ የህብረት፣ የአንድነትና የደስታ ጊዜ ነበር። እኛም ከእነርሱ የአባታዊ እና እናታዊ ባርኮትን ተቀብለናል።

አዲሱ ዓመት የፍቅር፣ የማካፈል፣ የማገልገልና የበረከት ዓመት ይሁንልን!

መልካም አዲስ ዓመት!

#መጽሐፍቅዱስሠራዊት #የፍቅርአገልግሎት #የአረጋውያንጉብኝት #አዲስዓመት #አንድነት #ህብረት #የእግዚአብሔርቃል

ሻሎም ቅዱሳን በቦሌ ቡልቡላ አካባቢ የምትገኙ!የፊታችን ሐሙስ 10:30 ላይ በመምጣት በፀሎት፣ በቃልና በዝማሬ አዲሱን ዓመተ የምንቀበልበት ጌታን የምናመልክበት እና መልካሙን ዜና የምናበስርበ...
07/09/2026

ሻሎም ቅዱሳን በቦሌ ቡልቡላ አካባቢ የምትገኙ!
የፊታችን ሐሙስ 10:30 ላይ በመምጣት በፀሎት፣ በቃልና በዝማሬ አዲሱን ዓመተ የምንቀበልበት ጌታን የምናመልክበት እና መልካሙን ዜና የምናበስርበት ቀን ስለሆነ የእግዚአብሔርን ፀጋ እንድትካፈሉ ተጋብዘዋል።

አድራሻ:- ቦሌ ቡልቡላ ግራር አካባቢ ኦሮሚያ ባንክ በሚገኝበት 2ተኛ ፎቅ እንገኛል።
ተጨማሪ መረጃ 0911645468

ሻሎም ቅዱሳን በቦሌ ቡልቡላ አካባቢ የምትገኙ!የፊታችን አርብ 11:30 እና እሁድ 3:30 ሰዓት በመምጣት በፀሎት፣ በቃልና በዝማሬ ጌታን የምናመልክበት ቀን ስለሆነ የእግዚአብሔርን ፀጋ እንድ...
03/09/2026

ሻሎም ቅዱሳን በቦሌ ቡልቡላ አካባቢ የምትገኙ!
የፊታችን አርብ 11:30 እና እሁድ 3:30 ሰዓት በመምጣት በፀሎት፣ በቃልና በዝማሬ ጌታን የምናመልክበት ቀን ስለሆነ የእግዚአብሔርን ፀጋ እንድትካፈሉ ተጋብዘዋል።

አድራሻ:- ቦሌ ቡልቡላ ግራር አካባቢ ኦሮሚያ ባንክ በሚገኝበት 2ተኛ ፎቅ እንገኛል።
ተጨማሪ መረጃ 0911645468

You all are invited to join Vacation Bible School for Kids up to 12years.  For three days starting from Thursday to Satu...
02/09/2026

You all are invited to join Vacation Bible School for Kids up to 12years. For three days starting from Thursday to Saturday. Blessings!

ሻሎም ቅዱሳን!ቦሌ ቡልቡላ አካባቢ ያላችሁ!  የጌታ ፀጋ ይብዛላችሁ!እሁድ ጌታ መልካም የአምልኮ ጊዜ ሰጠን!በዝማሬ ከዘማሬ አምልኮ ከዘማሪ ዙሪያሽ ጋር እና ከፓስተር እስራኤል ጋር ፀጋ ተካፈ...
02/09/2026

ሻሎም ቅዱሳን!
ቦሌ ቡልቡላ አካባቢ ያላችሁ! የጌታ ፀጋ ይብዛላችሁ!

እሁድ ጌታ መልካም የአምልኮ ጊዜ ሰጠን!
በዝማሬ ከዘማሬ አምልኮ ከዘማሪ ዙሪያሽ ጋር እና ከፓስተር እስራኤል ጋር ፀጋ ተካፈልን “ኃያል የሆነው የእግዚሐብሄር ድምፅ” በሚል ዋና ርዕስ በመዝሙር 29 ለይ ተመስርቶ ድንቅ የእግዚአብሔርን ቃል ተካፈልን።
“በዙሪያችን የከበᎅን ድምፆች አሉ የሰይጣን ድምፅ፣ የዓለምን ድምፅ፣ የነፍስን ድምፅ እና ሌሎች ድምፆችን ሁሉ የሚሽር ድምፅ የእግዚሐብሄር ድምፅ አለ። በሚል ድንቅ ጊዜ ነበረን።
“4 የእግዚአብሔር ድምፅ በኃይል ነው፤ የእግዚአብሔር ድምፅ በታላቅ ክብር ነው።
5 የእግዚአብር ድምፅ ዝግባን ይሰብራል፤ እግዚአብሔር የሊባኖስን ዝግባ ይቀጠቅጣል።”

ክብር ለጌታ ይሁን! ኑ ቃሉን እንማር እንለወጣለን!

አድራሻ:- ቦሌ ቡልቡላ ግራር አካባቢ ኦሮሚያ ባንክ በሚገኝበት 2ተኛ ፎቅ እንገኛል።
ተጨማሪ መረጃ 0911645468

Address

BAIC-Army Chapel
Addis Ababa
BULBULA

Opening Hours

Tuesday 08:30 - 18:30
Wednesday 06:00 - 17:30
Thursday 08:30 - 17:30
Friday 08:30 - 20:30
Saturday 14:30 - 18:00
Sunday 08:00 - 13:30

Telephone

+251911627856

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Bible Army - Army Chapel posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share