Exodus/Zetseat Ministries

Exodus/Zetseat Ministries Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Exodus/Zetseat Ministries, Religious organisation, Addis Ababa.

25/05/2022

ሰላም ለሁላችሁ!
በአዲስ አቀራረብ መጥቻለሁ። ከዚህ በመቀጠል ውርጃንና ተያያዥ ችግሮቹን በተከታታይ አብረን አንመለከታልን።

24/06/2020

የአእምሮ ጤንነት /Mental Health

ከትላንትና በስቲያ ማለትም ጥር 16/2010 በጠዋት አንድ አገር በቀል ግብረ ሰናይ ድርጅት ለመጎብኘት ሄድኩኝ። ይህንን ድርጅት እንድጎበኝ ያነሳሳች ቀድሞ እሰራው የነበረውን ስራ የሚገለጥ የማስታወቂያ ትንሽ ጽሁፍ ያነበበች በአካል የማላውቃት ሴት ናት። በጣም ላመሰግናት እፈልጋለሁ!

እዛ እንደደረስሁ በኮረና ወረርሺኝ ምክንያት ሁሉን ተዟዙሮ ለመጎብኘት እድል ባላገኝም ማእከሉ ወንዶችና ሴቶች በተለያየ ጊቢ የሚጠቀሙ እንደመሆኑ እኔ የሴቶቹ ጊቢ ገባሁ። ከማእከሉ መስራችና ዳይሬክተር ጋር ሞቅ ባለ ጨዋታ ውስጥ እያለን በጊቢ ውስጥ ወዲያ ወዲህ ከሚሉት ቀጠን ቀጠን ያሉ ጠያይም ሴቶች፣ አንዳንዶቹም ድንቡሽቡሽ፣ አንዳንዶቹም የልጆች እናት ከነልጆቻቸው፦ በድንገት አንዷ መጥታ ስሞታ ስታቀርብ ሌሎቹም ተከታትለው በመምጣት መወትወት ጀመሩ። ዳይሬክተሯ ሁሉንም በጥሞና በማዳመጥ (ምንም እንኳን የሚያቀርቡት complaints እውነትነት የሌለው ቢሆንም) እንደ አመጣጡ ታስተናግዳለች።
(Born Again Mental Health Rehabilitation and Healing Center, Pastor Kiya...0911247248) በዚህ አድራሻ ታገኙአታላችሁ

እኔ ግን በተቀመጥኩበት እነኝህ አሁን ሁሉን እንደልባቸው የሚናገሩ ፣ ነውር የማይመርጡ፣ በር ተቆልፎባቸው በቁጥጥር ስር የዋሉ ሰዎች በአንድ ወቅት እማወራና አባ ወራ የነበሩ፣ የባለ ብዙ ሞያዎች ባለቤትና ባለ ስራ፣ ባለ ደመወዝ፣ ለእውሩ አይን ለአንካሳው እግር የነበሩ ፣ ጎበዛዝትና ሽማግሌዎች ተነስተው የሚያከብራቸው፣ የሚሰማቸው ጆሮ የሚያያቸው አይን የሚያደንቃቸው የነበሩ እንደሆነ ሳስብ ወይ የስነ አእምሮ ችግር ፤ እናት ልጇን ልጅ እናቷን፣ ወንድም እህቱን እህት ወንድሙን ፣ ባል ሚስቱን ሚስት ባልዋን እማይታገሱበት የሚሰለቻቹበት ህመም ነው አልኩኝ። (ለእውሩ አይን ለአንካሳው እግር የነበሩ)ስል ምነው አካበድሽው እንዳትሉኝ ኃኪሞችም በስነ አእምሮ ህመም ስለሚጠቁ አንዱ ማሳያ ነው።

ውይ የኔ ነገር የመጀመሪያውን መጨረሻ አደረኩት አይደል

ማእከሉ በስነ አዕምሮ ችግር ተጠቅተው ጎዳና የወደቁ ወንዶችና ሴቶች በማንሳት ሁለንተናዊ ድጋፍ ያደርጋል። ጤናቸው ሙሉ በሙሉ ሲመለስ ቤተሰብ ያላቸውን ቤተሰብ በማፈላለግ ያገናኛል፣ የተለያዩ ስልጠናዎችን በመስጠት ራስ ያስችላል ፣ ይድራል፣ ስራ ያስቀጥራል እንደውም የድርጅቱ ሾፌር፣ የምግብ ቤት አላፊዋ፣ የማህበራዊ ሰራተኛውን ጨምሮ ለረጅም አመታት በአዕምሮ ጤና ችግር በጎዳና ላይ የነበሩና አሁን ተፈውሰው በማገልገል ላይ የሚገኙ ናቸው። ማገልገል ያልኩበት ምክንያት ደሞዝ ከማግኘት ባሻገር ችግሮቹን ለመጋፈጥ የተዘጋጀ ማንነት የሚያስፈልግ ስለሆነ ነው።
ይህ ድርጅት ከሁለት መቶ በላይ የሆኑ የስነ አዕምሮ ህመም ያለባቸውን ሰዎች የረዳ እና እየረዳም ያለ ነው።

የሆነስ ሆነና የስነ አእምሮ ህመም ምንድን ነው?

በስሜት ፣ በአስተሳሰብ እና በባህርይ ላይ ተጽዕኖ የሚያሳድሩ የተለያዩ ሁኔታዎች ናቸው። የስነ አእምሮ ህመም ብዙ አይነት ነው። በጠቅላላው ግን፦
በዕለት ተዕለት ሕይወት ውስጥ ጉልህ እክልን የሚያስከትሉ የማያቋርጥ የድብርት ስሜት ወይም በእንቅስቃሴዎች ላይ ፍላጎት ማጣት፣ ጥልቅ ፍርሀት፣ ትኩረት ማድረግ አለመቻል፣ ከልክ ያለፈ ብስጭት፣ ጭንቀት እና ሙሉ ለሙሉ ራስን እስከመጣል (እብደት) ጥቂቶች ሲሆን ምክንያቶቹ የተለያዩ የጤና ችግሮች ፣ አደጋ፣ በቤተሰብ ችግሩ ከነበረ ፣ ሥነ ልቦናዊ እና ማህበራዊ የጭንቀት ምንጮች ጥምርን ያካትታሉ።
እነዚህ ነገሮች በአንጎል ውስጥ የተወሰኑ የነርቭ ሥርዓቶችን እንቅስቃሴ በመቀየር የአንጎል ተግባር ላይ ለውጥ ሊያስከትሉ ይችላሉ።

ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የሚሄድ ጥናት እንደሚያሳየው

በአለም አቀፍ ደረጃ ከአራቱ ሰዎች አንዱ በህይወታቸው ውስጥ በአንድ ወቅት በአእምሮ በሽታ ይጠቃሉ።
በኢትዮጵያ 2016 በወጣ ሪፓርት 15በመቶ የሚሆኑ ሰዎች የጥቃቱ ሰለባ ናቸው። እንደውም በአሁኑ ጊዜ ከተመላላሽ ህመም ታካሚዎች ከአራቱ አንዱ የችግሩ ተጠቂ ነው። ህመምተኛው ላይገነዘበው ቢችልም።

ታዲያ ምን እናድርግ??? በሚቀጥለው የመፍትሔ አሳቦችን ይዤ እመለሳለሁ።

ሰላማችሁ ይብዛ!
መሰረት

16/06/2020

የሴቶች ጥቃት!!

ከሶስት ቀን በፊት በተለያየ ሚዲያ ሲዘገብ እንደሰማነው አንድ ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ 280 ሴቶች እና ህጻናት ጥቃት እንደተፈጸመባቸው በጥናት ተመላክቷል። በእርግጥ ይህ ጥናት ያላካተተው በርካታ ጥቃት እንዳለ ሆኖ።

ከዛሬ ስድስት አመት በፊት በአንድ ቦታ "ከጋብቻ በፊት ከወሲብ መታቀብ ጠቀሜታ" በሚል ወጣቶችን አስተምሬ ስወጣ አንዲት ትንሽ ልጅ ተከትላኝ ወታ እኔ በአክስቴ ልጅ ጥቃት ደርሶብኛል (Same s*x) ብላ ነግራኝ ነበር። ይህንን ያነሳሁበት ምክንያት በየቤቱ ያልተቆጠሩ ስንት ይኖሩ ይሆን?

ከሆነስ ሆነና የሴቶች ጥቃት ምንድን ነው?

የአለም የጤና ድርጅት ጥቃትን ማንኛውም አካላዊ፣ ወሲባዊ፣ እና ስነልቦናዊ ጉዳት ሊያደርስ የሚችል ተግባር ብሎ በሶስት ዋና ዋና ክፍሎች ይከፍለዋል። በሴቶች ላይ የሚደረግ ጥቃት የአጭርና የረጅም ጊዜ ጉዳት በሴቶቹ በራሳቸው ላይ ፣ በልጆቻቸው ላይ፣ በቤተሰቦቻቸው እንዲሁም በማህበረሰቡ ላይ ያስከትላል ።

ለዛሬ ወሲባዊ ጥቃትን አንስተን ብንመለከት

1. ለአጭር ጊዜ ጉዳቱ

• የብልት መድማት
• ያልታቀደ እርግዝናና ጽንጽ ማቋረጥ
• ተላላፊ የአባለዘር በሽታዎች መጠቃት
• የእንቅልፍ አለመተኛት ችግርና ሌሎችንም

2. የረጅም ጊዜ ጉዳቱ

• የመገጣጠሚያ አጥንቶች ህመም
• በትዳር ውስጥ የወሲብ ጊዜ ህመም
• ራስ ምታትና ጭንቀት
• የምግብ ፍላጎት ማጣት
• ለሱስ እና ልቅ ለሆነ ወሲብ ተጋላጭነት
• የስነ-አእምሮ ችግሮችና ሌሎችም ይገኙበታል። እነኝህ ከብዙ በጣም ጥቂቶች ሲሆኑ፦ ይህንን እየጻፍኩ በአገልግሎት የገጠመችኝ የአንዲት ወጣት ልጅ ታሪክ ትዝ አለኝ።

ወላጅ እናቷ በሞት ከተለያች በኋላ በቅርብ ዘመዷ ወሲባዊ ጥቃት ይደርስባታል። በዚህም ምክንያት ጠባይዋ ይቀየራል፣ ከዘመዶቿ ጋር ተስማምታ መኖር ስላልቻለች ወደ ቡና ቤት ትገባለች። በዛ ቦታ ላይ የገጠማትን ሁኔታ በቀላሉ ልትለምደው ስላልቻለች እስክትሰክር ትጠጣለች። ስትጠጣ ትጮሀለች ትረብሻለች። በዚህ ምክንያት ደግሞ ከስራ ትባረራለች፤ አምስት ያህል ቡና ቤቶችን ካዳረሰች በኋላ ያልታቀደ እርግዝና ይከሰታል። በበጎ አድራጎት ሰራተኞች እገዛ ጽንሱ ከመቋረጥ ቢተርፍም በዚሁ ችግሯ ምክንያት ልጇን ተቀምጦ ማሳደግ አልቻለችም። የስነ ልቦና ችግሩ ለረጅም ጊዜ የሚቆይና ራስን እንደሙሉ ሰው ለመቀበል የሚያዳግት በመሆኑ እንኳንስ ለሌላ የሚተርፍ ፍቅር ለመስጠት ለራስዋም የመኖር ህልሟን አጨልሞባታል።
እኔ ስለዚህች ልጅ ስናገር በርካቶች ያልተናገሩትን ይዘው የተቀመጡ፣ ብሶታቸውን አፍነው በየምክንያቱ የሚጣሉ፣ ለበቀል ጊዜ የሚጠባበቁ፣ ወደጎዳና የወጡ፣ የልጅነት ህልማቸው ጨልሞ በየቡና ቤቱ የማይወዱትን ኑሮ በመጠጥ ኃይል የሚጋፈጡ፣ በቤት ውስጥ የመኖር እድሉን ካልተነፈጉ ደግሞ ፈሪና ተጠራጣሪ የሆኑ ስንቶች ይሆኑ? በነኝህ መነጽር ወደፊት ይህ ቢላዋ የተሳለላቸውን ለማዳን ምን ይደረግ??

በሀገራችን በሴቶችና በህጻናት ላይ ይህንን በደል በሚፈጽሙ ሰዎች ምንድን ነው መደረግ ያለበት???

አመሰግናለሁ ግዜያችሁን ሰጥታችሁ ስላነበባችሁና አስተያየታችሁን ስለምታካፍሉ።

መሰረት

06/06/2020

አይዞአችሁ !

21-ሳይበሉም ብዙ ቀን ከቆዩ በኋላ፥ ያን ጊዜ ጳውሎስ በመካከላቸው ቆሞ እንዲህ አለ። እናንተ ሰዎች ሆይ፥ ሰምታችሁኝ በሆነ ኖሮ ከቀርጤስ እንዳትነሡ ይህንም ጥፋትና ጕዳት እንዳታገኙ ይገባችሁ ነበር።

22- አሁንም። አይዞአችሁ ብዬ እመክራችኋለሁ፤ ይህ መርከብ እንጂ ከእናንተ አንድ ነፍስ እንኳ አይጠፋምና። "

25_ ስለዚህ እናንተ ሰዎች ሆይ፥ አይዞአችሁ፤ እንደ ተናገረኝ እንዲሁ እንዲሆን እግዚአብሔርን አምናለሁና።"

የሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ 27፥ 21-22፣25

በዚህ ቦታ ሐዋርያው ጳውሎስ ወደ ቄሳር ይግባኝ ጠይቆ በመርከብ ከሌሎች እስረኞች ጋር በመጓዝ ላይ ሳሉ ከፍተኛ ማእበል እያናወጣቸው ብዙ ቀን ጸሀይንና ከዋክብትን ሳያዩ፣ ለአስራ አራት ቀን ምግብን ሳይበሉ፣ ወደፊት እንድናለን የሚል ተስፋ ሁሉ በተቆረጠ ጊዜ እየደጋገመ " አይዞአችሁ" በማለት ይናገራል። የሚያመልከው አምላክ በደህና እንደሚሻገር ፣ ከዚህ ፈተና ወቶ በቄሳር ፊት እንደሚቆም ተናግሮት ነበርና።

ሐዋርያው ጳውሎስ በነውጥ ውስጥ ካሉት ሰዎች መካከል ነበር፣ ያውም አስቀድሞ መንገዳችን መልካም አይደለምና ጉዞው ቢዘገይ ይሻላል እያለ እየነገራቸው እንቢ ብለው ወተው ነው የመከራው ተካፋይ የነበረው።

ራሱ በመከራ መካከል ሳለ ሌሎችን ማበረታታት እንዴት ይቻላል? በእርግጥ ይቻላል! ምክንያቱ ደግሞ አንድ ብቻ ነው። እርሱም እግዚአብሔር ሲናገርና እኛም ስንሰማው። አሜን!!

01/06/2020

ሙሴ ምን አይነት ትሁት ሰው ነው?

1." አሁን ይህን ኃጢአታቸውን ይቅር በላቸው፤ ያለዚያ ግን ከጻፍኸው መጽሐፍህ እባክህ ደምስሰኝ አለ።"
(ኦሪት ዘጸአት 32:32)

በዚህ ቦታ ተጽፎ የምናነበው የእስራኤል ልጆች የጥጃ ምስል ሰርተው አመለኩት፣ ሰገዱለት ከግብጽ ምድር ያወጣን አምላካችን ብለው አጠኑለት። በዚህም እግዚአብሔርን በበደሉ ጊዜ እግዚአብሔር ቁጣዬ እንዲቃጠልባቸው ተወኝ አንተን ግን ለታላቅ ሕዝብ አደርግሀለሁ ባለው ጊዜ ሙሴ የጸለየውን ጸሎት ነው።

እነኚህ ሰዎች በትክክል ጌታን በድለዋል አንገተ ደንዳናም ናቸው።

ጥጃ ሰርተው? ዘፍነውለት? አምልከውት? ያውም ሙሴ ጾም ጸሎት ላይ እያለ? ከእግዚአብሔር መልካም ተቀብሎ እየመጣ እያለ? ደግሞ የእግዚአብሔር ቁጣ በህዝቡ ላይ ቢነድም ሙሴን ለተሻለ ህዝብ አደርግሃለሁ ተብሏል። ኡፍ ተገላገልኩ ከእነኚህ ሰዎች ጭቅጭቅ የሚያስብል ሆኖ እያለ

ከጻፍኸው መጽሐፍህ እባክህ ደምስሰኝ????

2. " አሁንም፥ አቤቱ፥ ከሕይወት ሞት ይሻለኛልና እባክህ፥ ነፍሴን ከእኔ ውሰድ አለው። "
(ትንቢተ ዮናስ 4:3)

ዮናስ ደግሞ በእኔ ተናግረህ እንዴት አታደርገውም? ሀጢያተኞች ናቸውና መጥፋት አለባቸው የሚል ወገን ነው። አዎ የነነዌ ሰዎች ክፋት ወደ እግዚአብሔር ከፍ ከፍ ብሏል። መልእክተኛው ቅጣት እንደሚደርስባቸው ሰበከ። እነርሱ ተጸጸቱ ተመለሱም። እርሱም መሃሪ ነውና ይቅር አላቸው። ዮናስ ግን ከመቶ ሀያ ሺ በላይ የሆኑ ሰዎችና ብዙ እንስሶች ላሉባት ከተማ ከሚጨነቅ ይልቅ ለራሱ ክብርና ዝና ነበር ያሰበው። ይህ ደግሞ እግዚአብሔርን ደስ አላሰኘውም።

እነኝህን ሁለት አገልጋዮች ስንመለከት የእኛ ወደየትኛው ያመዝናል? ካገለገልን ወይም እግዚአብሔር በእኛ ከተናገረ በኋላ ወድቀን ምህረት እንጠይቃለን ወይስ በኔ ተናግሮ ነበር የጃቸውን አገኙ እንላለን።

አቤቱ መልሰን እኛም እንመለሳለን!!

28/05/2020

ሰበር ወቅታዊ መልእክት

ስለ እናንተ ነቀዙን እገስጻለሁ!
የሁለተኛ ደረጃ ተማሪ እያለሁ አያቴ ልጇን ልትጠይቅ ለአምስት ወራት ስትሄድ እናቴ የቤቱን አስቤዛ ታሟላና ለአንዳንድ ነገር ስትል እጄ ላይ ሳንቲም ታስቀምጣለች(30ብር)። ያን ጊዜ ጌታን ተቀብዬ በከፍተኛ ደስታ ውስጥ የነበርኩበት ጊዜ ነው። በዚህ ሁኔታ ሳለሁ እኔን ሰርቃችኋል የሚል ድምጽ ወደ ውስጤ ይመጣል። በምን ሰረቅሁህ እያልኩ ስጠይቅ: በአስራትና በበኩራት ነው። እኔ ደግሞ አስራት የምሰርቀው ገቢ የለኝ አልኩና መልስ ሰጠሁ። ጌታ ግን እናቴ በየወሩ ስለምትሰጠኝ ሰላሳ ብር ነገረኝ። ሁላችሁም እንደምታውቁት በልጅነታችን ለሚገለጥልን ድምጽ ከስጋና ከደም በመማከር ጊዜ አናጠፋም። ወዲያውኑ 10%(3ብር) መስጠት ጀመርኩ።

ይህ እውነተኛ ታሪክ ነው የምነግራችሁ:- እንደገና ጌታ ስለ እናንተ ነቀዙን እገስጻለሁ አለኝ። ከዚያም በምንኖርበት አካባቢ ከፍተኛ ቅዝቃዜ ገብቶ በሰው ሁሉ ጊቢ የሚገኝ የጓሮ አትክልቶችን አደረቀ። የበአል ጊዜ ነበርና ሰዎች ሁሉ ከእኛ ጊቢ ዳቦ መጋገሪያ የኮባ ቅጠል ሲጠይቁ የተሰጠኝን ቃል አስተዋልኩ(ስለ እናንተ ነቀዙን እገስጻለሁ) ያለውን። እግዚአብሔር ለቃሉ እንዴት ታማኝ እንደነበር ስለተደነቅሁ ቅድመ አያቴ ነበርና ጠየኩት ይህ ነገር ከምን የተነሳ የሆነ ይመስልሀል አልኩት። እርሱም የሰኔ ጎልጎታ ስለምደግምበት ነዋ ብሎ መለሰልኝ። እኔም ስለ ጌታ ድንቅ ስራ ተረክሁለት። ትንሽና ትልቅ መሆኑ አልነበረም፤ቃሉ እንጂ።

ያን ጊዜ ነበር እግዚአብሔር ስለ አስራት ያስተማረኝ። አሁንም ድረስ ቃሉን አከብራለሁ።

ወገኖች ይህንን ለመናገር ያነሳሳኝ ባለፈው ሳምንት የወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ህብረት ሰብሳቢ ፓስተር ጻድቁ አብዶ ከሁለት ሺህ አምስት መቶ በላይ አገልጋዮችና ከአምስት ሺህ አምስት መቶ በላይ ቤተሰቦቻቸው በከፍተኛ ችግር ውስጥ መውደቃቸውን ገልጸዋል ።

እግዚአብሔር እንደዚህ ይላል፦ በቤቴ ውስጥ መብል እንዲሆን አሥራቱን ሁሉ ወደ ጎተራ አግቡ፤ የሰማይንም መስኮት ባልከፍትላችሁ፣ በረከትንም አትረፍርፌ ባላፈስስላችሁ በዚህ ፈትኑኝ። ትን ሚልክያስ 3:10

አስራት የእግዚአብሔር ሆኖ ሳለ መስረቅ ርግማን ነው። መታዘዙ ግን በረከቱ ለእኛው ነው። በተነ ለምስኪኖችም ሰጠ ጽድቁ ለዘለአለም ይኖራል ተብሎ እንደተጻፈ እግዚአብሔር የረዳውና ስጦታ መስጠት የቻለ መልካም አደረገ። ይህን ማድረግ ያልቻልን እስራቱን ደግሞ ከከለከልን በቤቱ መብል እንዳይጠፋ መፍራት አለብን።

ስላዳመጣችሁኝ አመሰግናለሁ!

መሰረት

26/05/2020

22፤ እነሆ፥ እግዚአብሔር በኃይሉ ከፍ ያለውን ነገር ያደርጋል፤

እንደ እርሱስ ያለ አስተማሪ ማን ነው? (መጽሐፈ ኢዮብ ምዕራፍ 36)

23/05/2020

ቀኑን ለሰራዊት ሌቱን ለአራዊት

ይህንን አባባል ይል የነበረው ቅድመ አያቴ ነበር ።

ዛሬ ከእንቅልፌ የነቃሁት ወትሮ ከምነቃበት በጣም ቀደም ብዬ ከመሆኑም ባሻገር በተደጋጋሚ ለሊቱን እነቃ ነበር። ይህ የሆነበትን ምክንያት ጠንቅቄ ባውቀውም ከፍተኛ ድካም ግን ይሰማኛል። በዚህ ምክንያት ስለ እንቅልፍ ጥቅም በደንብ ሳስብ ቆየሁ። ስለዚህ ስለ እንቅፍ ማጣት ችግር ትንሽ ልበላችሁ።

እንቅልፍ ያለመተኛትን ችግር ጌዜያዊ እና የቆየ ብለን ልንከፍለው እንችላለን
ጊዜያዊ የምንለው፦ ከአንድ ለሊት እስከ ጥቂት ሳምንታት ሊቆይ የሚችል ሲሆን
የቆየ የምንለው ደግሞ፦ በሳምንት ሶስት ሌሊቶች ለሶስት ወራት ያክል ሲሆን ነው። በተጨማሪም ይህ እንቅልፍ ማጣት ከምንም ሌላ የጤና ችግር ጋር ያልተገናኘ ነው ወይስ በሌላ የጤና ችግሮች ለምሳሌ እንደ አስማ፣ የጨጓራ ህመም፣ካንሰር ፣ የአዕምሮ ጤና ችግር እና የመሳሰሉት ጋር ተያይዞ የመጣ ነው የሚለውን መለየት።
ከምንም ሌላ የጤና ችግር ጋር ባልተያያዘ ሁኔታ መተኛት ያልቻልን ከሆነ ራሳችንን መጠየቅ ያለብን የሚያስጨንቁ ነገሮች አሉብኝ ወይ፣ ድምጽ ብርሀን ሙቀት ነበር ወይ፣ ወይስ የመኝታ ሰአቴን አዛብቼው ነበር ወይ የሚለውን ለይተን ማወቅ።

በቂ እንቅልፍ ያለማግኘት ከፍተኛ ድካም፣ መፍዘዝ፣ በምንሰራው ስራ ላይ ትኩረት ማድረግ አለመቻል፣ መነጫነጭ እና የምግብ ፍላጎት መቀነስንም ያስከትላል ።

ለአንድ አዋቂ ሰው(ከ24_64 )ዓመት ዕድሜ በቂ የእንቅልፍ ጊዜ የሚባለው ከ7_9 ሰአት ሲሆን ከ6ሰአት ባያንስና ከ9 ባይበልጥ ይመከራል፡ ሁለቱም የየራሳቸው ጉዳት አላቸውና።

በቅርብ ጌዜ የሰማሁት አንድ ተመራማሪ እስሊፕ ቴራፒስት ያሉትን ላካፍላችሁ፦ አንድ ሰው ቀኑን በሙሉ ከሼልፍ ላይ መጽሐፍትን እያወረደ ሲያነብ ቆይቶ ማታ ላይ መጽሐፍቶቹን እያስተካከለ እንደሚደረድር ሁሉ ሰው በእንቅልፍ ሰአት አዕምሮው የቀኑን ዝብርቅርቅ በሙሉ የሚያስተካክልበት ጊዜ ነው ብለዋል። ታዲያ ሳይተኛ ያደረን ሰው አስቡታ!!!!

አላብዛባችሁ ለዛሬ ይህንን ካልኩኝ ዋና ዋና የእንቅልፍ ማጣት ችግሮችና መፍትሔዎችን በቀጣይ ይዤ እመለሳለሁ። ሳገለግላችሁ በጣም ደስ እያለኝ ነው። አመሰግናለሁ! መሰረት

20/05/2020

ለባለ ራዕይ

1. በዘፍጥረት 37:18_21 የዬሴፍ ወንድሞች ከሩቅ አዩትና ኑ እንግደለውና አውሬ በላው እንላለን ተባባሉ።

2. በሐዋ ስራ 12:1_10 ሄሮድስ በቤተክርስቲያን ላይ መከራ ባደረገበት ጊዜ ያዕቆብን በሰይፍ ካስገደለ በኋላ ጴጥሮስን ደግሞ ጨምሮ ያዘው። ነገ ሊያስገድለው ሲያስብ እያለ በቤተ ክርስቲያን አጥብቆ ጸሎት ይደረግ ነበር።

3. በዚሁ በሐዋ ስራ 23:12_30 አርባ የሚያህሉ አይሁድ ጳውሎስን ሳይገድሉ እህል ውሃ ላይቀምሱ ተማማሉ ።

አስገራሚው ነገር ዮሴፍም ነገሰ፣ ጴጥሮስም ባስደናቂ ሁኔታ ወጥቶ ወንጌሉን አጧጧፈው፣ ጳውሎስም እንደዛው።

እነዚህን ሶስት ሰዎች ለአብነት ያህል ላንሳ እንጂ በርካታ ባለ ራዕዮችን ለማስገደል ፣ ህልማቸውን ለማጨናገፍ ብዙ ሴራ ይደረጋል። አሁንም ባለንበት ዘመን ብዙ ህልም ላላቸው ፣ ረጅም እርቀት መጓዝ ለሚችሉ ሁሉ እንቅፋት ለመሆን የተሰራ መሳሪያ አይከናወን። የዚህ አለም ገዢ ምክርና ተግዳሮት በሙሉ በኢየሱስ ስም ይፍረስ።

ለባለ ራዕይ መንገዱ ቀላል ባይሆንም ራዕዩን የሰጠው ታማኝ ስለሆነ መድረሱ አይቀርም። አሜን !

18/05/2020

እኩያህ ማነው?

የንስር ህብረት ለምንድን ነው ከሌሎች አእዋፋት ጋር ያልሆነው ? ከአእዋፋቱ መካከል ቁራንና ድንቢጥን እንኳን ብናነሳ የየራሳቸው መልካም ጎን እንዳላቸው እናውቃለን። በ1ኛ ነገስት ላይ ለኤልያስ ምግብ ያመላልሱ የነበሩት ቁራዎች ነበሩ። ነገር ግን የቁራ ባህርይ በዘፍጥረት 8 ላይ ተልኮ የማይመለስ ዘዋሪ ፣ በዘፍ 15 ላይ ለመስዋዕትነት የቀረበውን ለመብላት የሚፈልግ ፣ ያገኘውን ሁሉ እንቁላል ቢሆን አእዋፍ ቢሆኑ የሞተ ነገር ሁሉ የሚበላ እንዲሁም መጥፎ ወሬንና ሞትን አብሳሪ እንደሆነ ይነገርለታል። ድንቢጥ የደስታ፣ ከለላ የማግኘት ምሳሌ ብትሆንም ነገሮችን አቅሎ መመልከትና ግርግር ይወዳሉ። ለዝሙት እና ለወሲብ ምሳሌ ተደርገውም ይወሰዳሉ።

አንዳንድ ህብረቶች ለመንፈሳዊ ጤንነታችን የማይመቹ ሀሜት፣ ቀልድና ቧልት ፣ ምድራዊ የብልጽግና ፍክክር ያለባቸው፣ ተጠራጣሪነት፣ የጭንቅ ወሬ የሞላባቸው፣ በጎ ህሊናን የሚያስጥሉ እንደ ንስር ተፈጥረን እንደ ዶሮ ሊያስጭሩን ከሚቃጣቸው ፈጥነን እንድናመልጥና ከፍ ብሎ ለመብረር የሚያስችለውን ክንፋችንን እንዳናስመታ መጠንቀቅ አለብን።

ይህንን ለመመርመር ከአሁን የተሻለ እድል የለም። አሜን!

Address

Addis Ababa

Telephone

+251911773784

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Exodus/Zetseat Ministries posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share