22/08/2026
በመሠረተ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ጊዜያዊ ቀጣና ጠቅላላ የመሪዎች ጉባኤውን አካሄደ።
በመሠረተ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን የማእከላዊ ኢትዮጵያ ጊዜያዊ ቀጣና የመሠረተ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ሊቀ መንበር ዶ/ር ሰይፈ ወዳጅ፣ የቀጣናው አስተዳደር መሪዎች ጉባኤ አባላት፣ የቀጣናው ዋና ጸሐፊ እና በቀጣናው ስር የሚገኙ ክልሎች አስተዳደር መሪዎችና አገልጋዮች በተገኙበት ከነሐሴ 15_16/2018 ዓ.ም በቢሾፍቱ የመሠረተ ክርስቶስ ሴምናሪ ሦስተኛ ጠቅላላ የመሪዎች ጉባኤውን አካሂዷል።
የጊዜያዊ ቀጣናው አሰተዳደር መሪዎች ጉባኤ አባለት ነሐሴ 15/2018 ዓ.ም ስብሰባቸውን ሲያደርጉ የ2018 በጀት አመት ሪፖርትና የ2019 በጀት አመት እቅድ በጊዜያዊ ቀጣናው ዋና ጸሐፊ መጋቢ ተስፋዬ ለገሰ ቀርቦላቸው ሰፊ ውይይት በማድረግ ሪፖርቱና እቅዱ ለጠቅላላ ጉባኤ እንዲቀርብ ተስማምተዋል።
በዚህም መሠረት ነሐሴ 16/2018 ዓ.ም መደበኛ ጠቅላላ የመሪዎች ጉባኤውን ያካሄደው ጊዜያዊ ቀጣናው ስብሰባውን በጸሎት ሲጀምር መጋቢ ዮሐንስ ተሾመ የእግዚአብሔርን ቃል አካፍለዋል።
በእለቱ የቀጣናው ዋና ጸሐፊ የ2018 በጀት አመት ሪፖርት እና የ2019 በጀት አመት እቅድን ሲያቀርቡ ከሰፊ ውይይትና ጥያቄዎች በኋላ በጉባኤው ጸድቋል። እንዲሁም ጉባኤው በልዩ ልዩ አጀንዳዎች ላይ ውይይት በማድረግ አቅጣጫዎች አስቀምጧል።
በመጨረሻም በቤተ ክርስቲያኒቱ ሊቀ መንበር ዶ/ር ሰይፈ ወዳጅ መልእክትና የጋራ ጸሎት ጉባኤው ተጠናቋል።
!
መረጃዎቻችንን በተለያዩ አማራጮች ይከታተሉ 👇
በቲክቶክ: https://www.tiktok.com/
በቴሌግራም: https://t.me/MKC_Official
በዩቱብ: https://youtube.com/
በፌስቡክ: https://www.facebook.com/mkcpresidentoffice