Kidist Arsema

Kidist Arsema Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Kidist Arsema, Religious Center, united state, Addis Ababa.

13/09/2026
 ።ሩፋኤል ማለት   ማለት ነውሣልሳይ ሊቀ መላእክት ነው በኃያላት ላይ የተሸመ የመላእክት አለቃ ሩፋኤል ነው።  መንገድ መሪም ይባላል፡፡ ከበሩት ከሰባቱ ሊቃነ መላእክት አንዱ እኔ ሩፋኤል ነ...
08/09/2026


ሩፋኤል ማለት ማለት ነው
ሣልሳይ ሊቀ መላእክት ነው

በኃያላት ላይ የተሸመ የመላእክት አለቃ ሩፋኤል ነው።
መንገድ መሪም ይባላል፡፡
ከበሩት ከሰባቱ ሊቃነ መላእክት አንዱ እኔ ሩፋኤል ነኝ።_
(ጦቢት 12 ፥13)

ቅዱስ ሩፋኤል ሆይ የጦቢትን ዓይን በሰው ተመስለህ እንደ ፈወስከው ሁሉ የኛንም ሰውነት ከደዌ ሐጢአት ትፈውሳት ዘንድ ከረድኤትህ ቅብዓ መድኃኒትን ቀባት ኣሜን

24/08/2026

ተናገሩ ድንቅ ስራውንም መስክሩ።
እንዲህ አይነት ነገር ስፖስት ሼር ብታደርጉት በጋራ መመስከር እንችል ነበር። ችግሩ እንዲህ አይነት ነገር ሼር አታረጉም 😑

እንኳን ለእመቤታችን ትንሣኤና ዕርገት በአል በሰላም አደረሳችሁ!       ነሐሴ 16 ቀን የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያምን ትንሣኤና ዕርገት በአል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክ...
22/08/2026

እንኳን ለእመቤታችን ትንሣኤና ዕርገት በአል በሰላም አደረሳችሁ!
ነሐሴ 16 ቀን የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያምን ትንሣኤና ዕርገት በአል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያ አማኞች ዘንድ በየአመቱ በታላቅ መንፈሳዊ ሥነ ሥርአት ይከበራል ። ይህ በዓል የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን የንጽሕና፣ የታማኝነትና የክብር መገለጫ ነው።

ቅዱስ ዳዊት በመዝሙሩ «አቤቱ ወደ ዕረፍትህ ተነሥ፤ አንተና የመቅደስህ ታቦት» (መዝ. 131፥8) በማለት አስቀድሞ የተናገረው ትንቢት ፍጻኔ ያገኘው ዛሬ ነው ። እውነተኛዋ የቃል ማደሪያ ታቦት ድንግል ማርያም በልጇ ሥልጣን ከመቃብር ተነሥታለች።

መጽሐፍ ቅዱስ «የሞት ደመወዝ ኃጢአት ነው» (ሮሜ 6፥23) ይላል፤ እመቤታችን ደግሞ ከኃጢአት ርቃ በቅድስና የኖረች ንጽሕት በመሆኗ መቃብር ይዟት ሊቀር አልቻለም። የልጇ ትንሣኤ ለሁላችን የትንሣኤ በኩር እንደሆነ ሁሉ፣ የእመቤታችን ትንሣኤም ለሰው ልጆች ሁሉ የትንሣኤ ተስፋ ማረጋገጫ ነው።

ታላቁ የቤተክርስቲያን አባት ቅዱስ ያሬድ በመቤታችን ላይ ሞት ስልጣን እንዳልነበረው ሲገልጽ በዜማው፡ እንዲህ ሲል ይገልጸዋል ።

«ሞትሰ ለመዋቲ ይደሉ፤ ሞታ ለማርያም የዐጽብ ለኵሉ» (ሞት ለማናቸውም ሟች የሚገባ ነው፤ የማርያም ሞት ግን ሁሉን ያስደንቃል) በማለት የዕረፍቷንና የትንሣኤዋን ነገር ገልጿል።

ሊቁ። አባታችን ቅዱስ ኤፍሬምም በውዳሴ ማርያም ድርሰቱ እርሷን «የሕይወት መገኛ» ብሎ እንደጠራት፣ ሕይወትን የወለደች የሕይወት መገኛ እመቤታችንም በልጅዋ ፈቃድ በመቃብር አልቀረችም፤ ይልቁንም እንደ ልጇ በሦስተኛው ቀን ተነሥታ ወደ ሰማይ ዐርጋለች።

የበዓሉ መንፈሳዊ መልእክት የእመቤታችን ትንሣኤና ዕርገት እኛንም ክርስቲያኖችን በቅድስናና በንጽሕና ሕይወት እንድንመላለስ፣ ምድራዊውን ፈተና በትዕግሥት አሳልፈን ዘላለማዊውን ክብር ተስፋ እንድናደርግ ያስተምረናል።

የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት፣ ጸሎትና በረከት ከሁላችን ጋር ይሁን። መልካም በዓል ይሁንላችሁ!

12/08/2026

14/07/2026

‹‹ሐምሌ 7›› አጋዕዝተ ዓለም ስላሴ በአብርሃም ቤት ተገኝተው ቤቱን የባረኩበት የአንድነታቸውንና ሶስትነታቸው ሚስጢር የገለጹበት ታላቅ በዓል ነው።

በዚችም ቀን ልዩ የሆኑ ሦስቱ አካላት /ቅድስት ሥላሴ/ በኦሪት መጽሐፍ እንደ ተጻፈ ወደ አብርሃም ቤት ገቡ ያቀረበላቸውንም ተመገቡ፡፡

የሥላሴን አንድነትና ሦስትነት ለመረዳት በሥላሴ ፈቃድ መጻሕፍት እንዳስተማሩ ሊቃውንት እንደተረጉሙልን እንጂ ማንም በገዛ ፈቃዱ ተመራምሮ አይደርስበትም፡፡

የሐምሌ 7 ቀንም ሥላሴ በአብርሃም ቤት ገብተው ቸርነታቸውና ፍቅራቸውን የገለጹበት፣ ስለሆነ በዓሉን ስናዘክር ሥላሴን እናመሰግናለን፡፡

በአጠቃላይ በዚህ ዕለት በአብርሃም ቤት እግዚአብሔር የተስተናገደበት፣ አንድነቱና ሦስትነቱ የተገለጠበት፣ አብርሃም እና ሣራ ካረጁ በኋላ ልጅ እንደሚወልዱ የተበሠረበት፣ ይሰሐቅንም እንደሚወልድ የተነገረበት ዕለት ነወ።

ለአብርሃም ምሥጢሩን የገለጠ እግዘአብሔር ለሁላችን ይግለጥልን🙏

የጻድቁ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ምልጃ እና ረድኤት አይለየን🙏በበረሀ የሚጮኽ የፍጹም ባህታዊ ድምጽ 🙏በሉቃስ 1÷14 እንደተጻፈው ቅዱስ ገብርኤልና አባቱ ትንቢት የተናገሩለት፤ ከሕፃንነቱ...
07/07/2026

የጻድቁ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ምልጃ እና ረድኤት አይለየን🙏

በበረሀ የሚጮኽ የፍጹም ባህታዊ ድምጽ 🙏

በሉቃስ 1÷14 እንደተጻፈው ቅዱስ ገብርኤልና አባቱ ትንቢት የተናገሩለት፤ ከሕፃንነቱ ጀምሮ እግዚአብሔርን ያገለገለ፤ በፍጹም ልቡ ዓለምን የናቀ፤ ከተድላዋና ከደስታዋም የተለየ፤ አምላክን ለማጥመቅ የታደለ ሐዋርያ፣ መምህር፣ ሰማዕት፣ ባሕታዊ፣ ነቢይ፣ ጻድቅ ነው መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ተወለደ። ዮሐንስ ማለት እግዚአብሔር ጸጋ ነው ማለት ነው፡፡ ካህኑ ቅዱስ ዘካርያስና ሚስቱ ቅድስት ኤልሳቤጥ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ሁሉ በመፈጸም ያለ ነቀፋ የሚኖሩ ጻድቃን ነበሩ፡፡ ኤልሳቤጥም መካን ነበረች ልጅ እንዲሰጣቸው እግዚአብሔርን ዘወትር ይማጸኑት ነበር። ካህኑ ዘካርያስ ወደ ቤተ መቅደስ ገብቶ ዕጣን በማሳረግ ላይ ሳለም የእግዚአብሔር መልአክ በዕጣኑ መሠዊያ ቀኝ ቆሞ ጸሎቱ እንደ ተሰማ ነገረው፡፡

ሚስቱ ቅድስት ኤልሳቤጥ እንደምትወልድ፣ ስሙንም ዮሐንስ እንደሚለው፤ ከእናቱ ማኅፀን ጀምሮ መንፈስ ቅዱስ እንደሚሞላበት ነገረው፡፡ ካህኑ ዘካርያስም መልአኩን “እኔ ሽማግሌ ነኝ፤ ሚስቴም አርጅታለችና ይህን በምን አውቃለሁ?” አለው፡፡ መልአኩም “እኔ በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው ገብርኤል ነኝ፤ እነሆም በጊዜው የሚፈጸመውን ቃሌን ስላላመንህ ይህ ነገር እስከሚኾን ዲዳ ትሆናለህ፤ መናገርም አትችልም” አለው፡፡ የማገልገሉም ወራት ሲፈጸም ወደ ቤቱ ሔደ፤ ከሁለት ቀን በኋላም አረጋዊቷ ቅድስት ኤልሳቤጥ ፀነሰች፡፡ ቅድስት ኤልሳቤጥም በመካንነቷ ከሰዎች የሚደርስባት ሽሙጥ ተወግዷላታልና “እግዚአብሔር በዚህ ወራት ከሰው ስድቤን ያርቅ ዘንድ እንዲህ አደረገልኝ” ስትል ለአምስት ወራት ተሸሸገች፡፡

ጌታችን ሊወለድ ስድስት ወራት ሲቀረው፣ ሰኔ 30 ቀን ንዑድ፣ ክቡር የሆነው መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ተወለደ፡፡ አንደበቱ ተይዞ የነበረው ካህኑ ዘካርያም ስሙ “ዮሐንስ” ይባል ብሎ ሲጽፍ አፉ ተከፈተ፤ አንደበቱም ተፈታ፡፡ በመንፈስ ቅዱስ ተቃኝቶም የቅዱስ ዮሐንስን ነቢይነትና አጥማቂነት ተናገሯል፡፡ በዚህም ምክንያት መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ በበረሀ የሚጮኽ የአዋጅ ነጋሪው ቃል ተብሎ ይገለጻል፡፡ ወስብሀት ለእግዚአብሄር ::

Address

United State
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Kidist Arsema posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to Kidist Arsema:

Shortcuts

Share