የመዳን ወንጌል አገልግሎት /Yemedan Wengel Agelgilot

የመዳን ወንጌል  አገልግሎት /Yemedan Wengel Agelgilot ዓላማዉ
የመዳንን ወንጌል ለሰው ሁሉ መስበክና ጤናማውን የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ማስትማር ነው።
ኤፌ 1:13

12/07/2025

በእግዚአብሔር ልባችን እናበርታ።

በከባድና አስጨናቂ ሁኔታ ውስጥ ከማለፋችን የተነሳ ዝለትና የተስፋ መቁረጥ ስሜት ከቦንና ተጭኖን ሊሆን ይችላል:ነገር ግን አይዞን ዛሬም ቢሆን እስከለዘላለም በእርሱም የምንታማመንበት እግዚአብሔር ረዳታቻን መታመኛችንና ብርታታችን ነው።
ስለዚህ ምስጋና የሚገባውን
እግዚአብሔርን እጠራለን፥ ምክኒያቱም እርሱ በኃይሉና በችሎቱ ብርታት ከከበቡን ሁኔታዎች ሁሉ በላይ በድል አድራጊነት ያቆመናልና ወደ እርሱ እንጣራ አናቋርጥ እንጩህ ያየናል ሰምቶም ይመልስልናል::
ታዲያ እንዲ እንዲህ እንበለዋ:-
ጌታ ሆይ ወደማን እንሄዳለን? አንተ የዘላለም ሕይወት ቃል አለህ፤ አዎን የሚያድን ቃል:የሚፈውስ ቃል :የሚያጽናና ቃል: ያለህ አንተ ብቻ ነህና ጌታችን ሆይ አበርታን::

11/05/2025

ተዉአት፤ ስለ ምንታደክሙአታላችሁ?

መልካም ሥራ ሠርታልኛለች የተቻላትን አደረገች እውነት እላችኋለሁ፥ ይህች ድሀ መበለት ከሁሉ ይልቅ አብልጣ ጣለች
የክርስቶስ ስለ ሆናችሁ በስሜ ጽዋ ውኃየ ሚያጠጣችሁ ሁሉ ዋጋው እንዳይጠፋበት እውነት እላችኋለሁ በጎ ፈቃድ ቢኖር
እንዳለው መጠን የተወደደ ይሆናል እንጂ እንደሌለው መጠን አይደለም ስለዚህ ወገኖች ሆይ በሥራና በእውነት እንጂ በቃልና በአንደበት አንዋደድ:: ይህንም እላለሁ፦ በጥቂት የሚዘራ፡ በጥቂት ደግሞ ያጭዳል፥ በበረከትም የሚዘራ፡ በበረከት ደግሞ ያጭዳል።እግዚአብሔር በደስታ የሚሰጠውን ይወዳልና እያንዳንዱ በልቡ እንዳሰበ ይስጥ፥ በኀዘን ወይም በግድ አይደለም ::
እንዲሁ እኛም ደግሞ የታዘዝነውን ሁሉ ባደረግን ጊዜ :- የማንጠቅም ባሪያዎች ነን ልናደርገው የሚገባንን አድርገናል፡ እንበል::

ማር.14 ÷8 ሉቃ. 21÷3 .ማር 9÷41 .2ቆሮ 8÷12.1ዮሐ3÷18.ያዕ2÷15-16.2ቆሮ9÷6-7.ሉቃ17÷10

25/04/2025

ከኃጢአታቸው ያድናቸዋልና ስሙን ኢየሱስ ትለዋለህ
እርሱም ኃጢአትንሊያስወግድ እንደ ተገለጠ ታውቃላችሁ፥ በእርሱም ኃጢአት የለምና ። ለኃጢአት ሞተን ለጽድቅ እንድንኖር፥ እርሱ ራሱ በሥጋው ኃጢአታችንን በእንጨት ላይ ተሸከመ፤ በመገረፉ ቁስል ተፈወሳችሁ።በእርሱ ወደ እግዚአብሔር የሚመጡትን ፈጽሞ ሊያድናቸው ይችላል እርሱ ግን ስለ መተላለፋችን ቈሰለ፥ ስለ በደላችንም ደቀቀ፤ የደኅንነታችንም ተግሣጽ በእርሱ ላይ ነበረ፥ በእርሱም ቍስል እኛ ተፈወስን: እኛ ሁላችን እንደ በጎች ተቅበዝብዘን ጠፋን፤ ከእኛ እያንዳንዱ ወደ ገዛ መንገዱ አዘነበለ፤ እግዚአብሔርም የሁላችንን በደል በእርሱ ላይ አኖረ። ክርስቶስ መከራ ይቀበላል በሦስተኛውም ቀን ከሙታን ይነሣል፥ በስሙም ንስሐና የኃጢአት ስርየት ከኢየሩሳሌም ጀምሮ በአሕዛብ ሁሉ ይሰበካል፡ እንዲህ ቢሆንስ፥ ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ ብዙ ጊዜ መከራ ሊቀበል ባስፈለገው ነበር፤ አሁን ግን በዓለም ፍጻሜ ራሱን በመሠዋት ኃጢአትን ሊሽር አንድ ጊዜ ተገልጦአል:: እግዚአብሔር፥ የኃጢአትንም ስርየት ይሰጥ ዘንድ፥ ራስም መድኃኒትም አድርጎ በቀኙ ከፍ ከፍ አደው። እንግዲህ ወንድሞች ሆይ፥በእርሱ በኩል የኃጢአት ስርየት እንዲነገርላችሁ፥
በሙሴም ሕግ ትጸድቁበት ዘንድ ከማይቻላችሁ ሁሉ ያመነ ሁሉ በእርሱ እንዲጸድቅ በእናንተ ዘንድ የታወቀ ይሁን ::
ኃጢአታችሁ ስለ ስሙ ተሰርዮላችኋልና።

ማቴ.1:21 ,1ዮሐ3:5 1ጴጥ.2:24
ዕብ.7:25, ኢሳ.53:5-6, ሉቃ.24:46-47
ዕብ.9:36, የሐዋ.ሥ 5:31,የሐዋ.ሥ 13:38-39, 1ዮሐ.2:12

24/09/2023

እግዚአብሔር እኛን አይተወንም።

ባሪያዎቹ ነንና፥ አምላካችን ግን በባርነታችን አልተወንም፤ የሕይወት መታደስን ይሰጠን ዘንድ፥ አሰቀድሞም ያዘጋጀውን መልካሙን ሥራ እንሠራ ዘንድ በክርስቶስ የፈጠረንእግዚአብሔር አምላካችንና አባታችን፥ የተፈታውንም እንጠግን ዘንድ፥ በሁሉ ፊት ምሕረቱን ሞገሱን ሰጠን።ወዳጆች ሆይ፥ በእኛ መካከል እንደ እሳት ሊፈትን ስለሚሆነው መከራ ድንቅ ነገር እንደ መጣብን አንደነቅ፤ ስለዚህ ለመቀጣት እንታገሰ ፤ እግዚአብሔር እንደ ልጆችጸ
ያደርግልናልና፤ ምክንያቱም አባቱ የማይቀጣው ልጅ ማን ነው? ነገር ግን ሁሉ የቅጣት ተካፋይ ሆኖአልና ያለ ቅጣት ብንኖር ዲቃላዎች እንጂ ልጆች አይደለንም።
እኛበእርሱ የተወወደድን:በረድኤቱ ጥላ ስር ተማምነን የምንኖር በማይጥሉ ቡሩካን እጆቹ በሀይል ለዘለአለም የተያዝን ሕዝቡ የሆንን: ዘውትር በእግሮቹ አጠገብ ተቀምጠን ፈዋሽ; ጣፋጭ: አጽናኝ እና መካሪ የሆኑ ሕያዉ ቃሎቹን የምንቀበል ቅዱሳኑ ነን።እግዚአብሔር ለእርሱ ሕዝብ ያደርገን ዘንድ ወድዶአልና እግዚአብሔር ስለ ታላቅ ስሙ እኛን አይተውም።
እግዚአብሔር አሁን እንዲህ ይለናል :-"በውኑ ሴት ከማኅፀንዋ ለተወለደው ልጅ
እስከማትራራ ድረስ ሕፃንዋን ትረሳ ዘንድ ትችላለችን? አዎን፥እርስዋ ትረሳ ይሆናል፥ እኔ ግን አልረሳችሁም"።
ተስፋችን በአምላካችንበእግዚአብሔር የሆነልን ሰዎችስለሆንን ብጹዐን ነን፤ ምክንያቱም እርሱ የማይጥለን ረዳታችን ነውና።
ታድያ ! እግዚአብሔር ቀንና ሌሊት ወደ እርሱ ለምንጮህ ለሚታገሠንም ምርጦቹ አይፈርድልንምንእላችኋለሁ፥ ፈጥኖ ይፈርድልናል።

#እዝ 9:9 #1ጴጥ 4:12 #ዕብ12:7-8 #ዘዳ 33:3 #1ሳሙ12:22 #ኢሳ49:15 # መዝ145" 5 #ሉቃ18:7-8
ጸጋና ሰላም ይብዛልን
ወንድም ጎርፋ ባሩዳ

11/09/2021
11/09/2021

2 ቆሮንቶስ 5 :17-18

17፤ ስለዚህ ማንም በክርስቶስ ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው፤ አሮጌው ነገር አልፎአል፤ እነሆ፥ ሁሉም አዲስ ሆኖአል።
18፤ ነገር ግን የሆነው ሁሉ፥ በክርስቶስ ከራሱ ጋር ካስታረቀን የማስታረቅም አገልግሎት ከሰጠን፥ ከእግዚአብሔር ነው፤
2 ቆሮንቶስ 5 :17-18

24/08/2021

God is Good

26/04/2021

It is useful for our encouragement,thus listen it with understunding.

05/03/2021

ተወዳጆች ቅዱሳን :
" ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን"።
ኤፌ 1፥2
ይህ መንፈሳዊአገልግሎት የምንሰጥበት ይፋዊ ፔጃችን ነው።
የመዳንን ወንጌል እንሰብካለን ጤናማውን የመጽሐፍ ቅዱስ አሰተምሕሮ እናስተምራለን።
ወንድም ጎርፉ ባሩዳ ።

05/03/2021

ተወዳጆች ቅዱሳን :
" ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን"።
ኤፌ 1፥2
ይህ መንፈሳዊአገልግሎት የምንሰጥበት ይፋዊ ፔጃችን ነው።
የመዳንን ወንጌል እንሰብካለን ጤናማውን የመጽሐፍ ቅዱስ አሰተምሕሮ እናስተምራለን።

ወንድም ጎርፉ ባሩዳ ።

Address

Addis Ababa

Telephone

+251911770327

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የመዳን ወንጌል አገልግሎት /Yemedan Wengel Agelgilot posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share