Enkwanm Agegnehegn እንኳንምአገኘኅኝ

Enkwanm Agegnehegn እንኳንምአገኘኅኝ “እንግዲህ እግዚአብሔር በእኛ እንደሚማልድ ስለ ክርስቶስ መልክተኞች ነን፤ ከእግዚአብሔር ጋር ታረቁ ብለን ስለ ክርስቶስ እንለምናለን።”
— 2ኛ ቆሮ 5፥20

With Enkwanm Agegnehegn – I just got recognized as one of their top fans! 🎉
30/04/2026

With Enkwanm Agegnehegn – I just got recognized as one of their top fans! 🎉

Tewodero Demelash የሌለ ነገር ፍለጋ - ከንቱ ድካም!ሰው ቤት ነው ያለሁት፤ እንግድነት ሄጄ፡፡ የጓደኛዬ እኅት ወደ ቀጠሯ ለመሄድ ክፉኛ ትጣደፋለች፡፡ ግን ደግሞ አንድ ዕቃ ያስቀመ...
30/04/2026

Tewodero Demelash
የሌለ ነገር ፍለጋ - ከንቱ ድካም!

ሰው ቤት ነው ያለሁት፤ እንግድነት ሄጄ፡፡ የጓደኛዬ እኅት ወደ ቀጠሯ ለመሄድ ክፉኛ ትጣደፋለች፡፡ ግን ደግሞ አንድ ዕቃ ያስቀመጠችበት ጠፍቷት እዚህም እዚያም ትፈልጋለች፡፡ ደግሞ ትጠይቃለች እንደገና ጎንበስ ቀና ትላለች፡፡ ሳሎን መኝታ ቤት እንደገና ሳሎን መልሳ ደግሞ መኝታ ቤት ትመላለሳለች፡፡ ዕቃው ግን አልተገኘም፡፡ ቤቱ ውስጥ ያለነውን ሰዎች ሁሉ ትኩረት ይዛለች፡፡ ሁላችንም ሐሳብ እንሰጣለን፡፡ አንዳንዶች በፍለጋው ከእርሷ ጋር ወዲህና ወዲያ ይላሉ፡፡ የቀጠሯ ሰዓት ወይ ደርሷል አልያም አልፏልና ቶሎ መውጣት ፈልጋለች፡፡ ዕቃው ግን የለም!! ትዕግስቷ እያለቀ ነው፡፡ ‹‹አከሌ ነክቶብኝ ይሆናል››፣ ‹‹ለምን ክፍሌ ትገባላችሁ?››፣ ‹‹ዕቃዬን አትንኩብኝ አላልኩም ነበር?›› ሌላም ሌላም ትናገራለች፡፡ አልፎ አልፎም ተገቢ ያልሆኑ ቃላት ከአፏ ይወጣሉ፡፡ በዚህ ውጥረት ውስጥ ሆና የቀጠራችት ጓደኛዋ ደወለች፡፡ ስልኩን ሳታነሣው የበለጠ ተናደደች፡፡ አጠገቧ የነበረውን ትንሹን ወንድሟን ‹ዘወር በል ከአጠገቤ›› ብላ አመናጨቀችውና ስልኩን አንስታ ፍጹም በተረጋጋና ለስላሳ ድምጽ ‹‹ሀሎ›› አለች፡፡ ጥቂት ከሰማች በኋላ ‹‹አዎ! ከቤት እየወጣሁ ነው፡፡ ያንን ዕቃ ይዤው ልምጣ ወይስ ልተወው? የሚለውን እያሰብኩ እኮ ነው የደወልሽልኝ›› ብላ ቤቱን ስታምስበት የነበረውን ዕቃ ጠራች፡፡ ከዚያ ወዲያ ምን እየተባለች እንዳለች እንጃ! እኔ ግን ‹ተይው ባለቻት› ብዬ እየተመኘሁ ነበር፡፡ ቤቱ ውስጥ ያሉት ሁሉ እንደ እኔ የተመኙ ይመስለኛል፡፡ ሁላችንም እሷን እያየን ነበር፡፡ ‹‹ኧረ ባክሽ!? እየቀልድሽ መሆን አለበት!?›› የሚለውን ንግግሯን ስንሰማ የሁላችንም ጆሮ ምን ተፈጥሮ ነው? የሚለውን ለመስማት ጓጓ! በተለይማ ፊቷ ላይ የሚታየው ግራ መጋባት ደግሞ ፈገግታ ደግሞም ጥያቄ የሚመስል ግርታ እኛንም ግር አሰኘን፡፡ ‹‹እኔኮ ቤት ውስጥ የቀረኝ ቦታ የለም፡፡ ቤተሰቡን ሁሉ አስጨንቄው ነበር፡፡ በይ በቃ መጣሁ ጠብቂኝ›› ብላ ስልኩን ዘግታ ወደ መኝታ ቤቷ ሮጠች፡፡ ሌሎችም ተከትለዋት ሮጡ፡፡ ሳሎን ውስጥ እኔ ብቻ ቀረሁ፡፡

ልብሴን ልቀይርበት ውጡልኝ ብትልም የተፈጠረው ምንድን ነው? ንገሪን! የሚለው ሰው ቁጥር በርከት ስላለባት ዕቃውን ይዛው የመጣች መስሏት እንጂ እዛው ጓደኛዋ ጋር እንደሆነና ይሄን ያህል በመፈለግ የደከመችው ትናንትና እሷ ጋር እንደነበር ማታ ከጓደኛዋ ጋር ሲለያዩ ጓደኛዋ ቤት ረስታው እንደመጣች ነገረቻቸው፡፡ አንዳንዶች እየተናደዱባት ሌሎቹ እየሳቁ ቀሪዎቹ ደግሞ እየተገረሙ ወደሥራቸው ተመለሱ፡፡ ቤት ውስጥ የሌለን ዕቃ ለማግኘት የተደከመው ድካም ለእኔ ከዚህ በታች ያሰፈርኩትን ሐሳብ እንዳስተውል ረዳኝ፡፡

ብዙዎቻችን በተለይ ቅዱሱ መጽሐፍ ውስጥ የሌለ ነገር ፍለጋ ብዙ ደክመናል፤ አሁንም እየደከምን ነው፡፡ በብዙ ፍለጋ አልገኝ ካሉን ምንባባት ውስጥ አንዱ ‹‹ማርያም ታማልዳለች›› የሚለው ነው፡፡ ይህን ምንባብ ፍለጋ ብዙ መድከሜንና ለማግኘት እንዳልቻልኩ ከዓመታት በፊት ጀምሬ (የማኅበራዊ መገናኛ ብዙአን መጠቀም ከጀመርኩ ጊዜ ጀምሬ) በልዩ ልዩ መንገድ አቅርቤ ‹‹የምታውቁ ካላችሁ እባካችሁ አሳዩኝ›› ብልም እኔ አውቃለሁ የሚል ሰው ላገኝ አልቻልኩም፡፡

ከዚህ ይልቅ በተደጋጋሚ የተሰጠኝ መልስ ‹‹ማርያም አታማልድም የሚል አንተ አሳየኝ›› የሚል ውሃ ወቀጣ የመሰለ የሰነፍ ሰው መልስ ነው፡፡ እንዲህ ላለው ምላሽ የሚከተለውን መልስ ስሰጥ ነበር ‹‹መጽሐፍ ቅዱስ አይልም፡፡ ከዚህ ይልቅ እግዚአብሔር ፍቅር መሆኑን በማሳየት ሰይጣን ፍቅር አለመሆኑን ያስተምራል፡፡ መጽሐፉ ሰይጣን ፍቅር አይደለም አይልምና ሰይጣን ፍቅር ነው ማለት ነውን? መጽሐፉ የሌለን ነገር የለም ብሎ መጻፍ አይጠበቅበትም፡፡ ያለን ነገር ግን አለ በሚል አስረግጦ ማስተማር ባሕርይው ነውና አለ የምትሉ ሰዎች ለመኖሩ ማስረጃችሁን አምጡ፡፡ ለዚህም እኔ ምሳሌ ማቅረብ እችላለሁ፡፡ ሊያውም እናንተ በሄዳችሁበት መንገድ በመሄድ፡፡ ምሳሌዬንም እንካችሁ፡- መጽሐፍ ቅዱስ ኢየሱስ አማላጅ መሆኑን ይናገራል፡፡ አማላጅ አይደለም የምትሉ ከሆነ ኢየሱስ አማላጅ አይደለም የሚል ከመጽሐፍ ቅዱስ አሳዩኝ›› (ይህቺ እንግዲህ እናንተ ያሳያችሁኝ የሰነፍ ሰው መንገድ ብትሆንም እሾህን በእሾህ መሆኑ ነው)፡፡ የጓደኛዬ እኅት የሌለ ነገር በመፈለግ እሷ ደክማ ቤተሰቡን እንዳደከመችው፣ እሷ ተረብሻ ቤተሰቡን እንደበጠበጠችው አሁንም የሌለ ነገር በመፈለግ እና በማስፈለግ እየደከሙና እያደከሙን ያሉ ስንቶች ይሆኑ?

18/04/2026
18/04/2026

አትፍሩ

18/04/2026

የፅዮን_ተጓዥ_ነኝ

ሰው ያረገኝ ፀጋህ ነው
ታሪኬን ለውጦ
ከሞት አስመልጦ
ጌታ ሆይ ተመስገን (2x)

አንተን ካገኘሁ ጀምሮ
ሕይወቴ በአንተ አምሮ
የፍቅርህን ብዛት አልችልም ልገልጻት
የምህረትህን ብዛት አልችልም ልገልጻት (2x)

የዓለም ክብር ሃብት አያጓጓኝም
ከአንተ አይበልጥብኝም
መርጬሃለሁ እከተልሃለሁ

የምህረትህ የፍቅርህ ብዛቱ
አልበረደም ግለቱ
ያዘምረኛል ተድላዬ ሆኖኛል
ያዘምረኛል ሞገሴ ሆኖኛል

ሰው ያረገኝ ፀጋህ ነው
ታሪኬን ለውጦ
ከሞት አስመልጦ
ጌታ ሆይ ተመስገን (2x)

አንተን ካገኘሁ ጀምሮ
ሕይወቴ በአንተ አምሮ
የፍቅርህን ብዛት አልችልም ልገልጻት
የምህረትህን ብዛት አልችልም ልገልጻት

በመረቅህልኝ አዲስ ህያው መንገድ
ደስ እያለኝ ልራመድ
መጨረሻዬ ኢየሱስ ጌታዬ
መጨረሻዬ አንተ ነህ ጌታዬ

የሩቅ አገር የፅዮን ተጓዥ ነኝ
በሠማይ አገር ያለኝ
ታድያለሁ አገሬ ገባለሁ
ታድያለሁ ዘለዓለም አርፋለሁ

ሃሌሉያ

ሰው ያረገኝ ፀጋህ ነው
ታሪኬን ለውጦ
ከሞት አስመልጦ
ጌታ ሆይ ተመስገን (2x)
አገኘው_ይደግ

02/04/2026

05/12/2025

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Enkwanm Agegnehegn እንኳንምአገኘኅኝ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to Enkwanm Agegnehegn እንኳንምአገኘኅኝ:

Share