30/09/2025
‹‹እናንተ የአባቴ ብሩካን ታምሜ ጎብኝታችሁኛልና በእኔ ካመኑ ከእነዚህ ከታናናሾች ወንድሞቼ ለአንዱ ያደረጋችሁትን ዅሉ ለእኔ አደረጋችሁት›› ማቴ. ፳፭፥፵
ወንድማችን ወጣት ኤርሚያስ በዛብህ የጅማ ፈለገ ሰላም ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሎዛ ሰንበት ት/ቤት ሰብሳቢ ባጋጠመው ድንገተኛ ሕመም Guillain-Barré Syndrome (GBS). ለተባለ የእጅና የእግር ነርቮች አለመነቃቃት ወይም ሥራ የማቆም በሽታ ተጋልጦ በጅማ ዩኒቨርሲቲ ሪፈራል ሆስፒታል ተኝቶ ሕክምና በመከታተል ላይ ይገኛል።
ወጣት ኤርሚያስ በዛብህ ከዚህ በሽታው ለማገገም የተጠየቀው የሕክምና መድኃኒት ዋጋ ከቤተሰቦቹ አቅም በላይ ስለሆነ የወንድማችንን ሕይወት ለማትረፍና በሽታው ጊዜ ከተሰጠው ወደቀሪ የሰውነቱ ክፍሎች ተዛምቶ ከፍተኛ ጉዳት ከማድረሱ በፊት የአቅማችንን በማድረግ እንድንታደገው ስንል በፈጣሪ ስም እንማጸናችኋለን።
ከታች በተገለጸው የራሱ አካውንት (ሒሳብ ቁጥር) ድጋፍ በማድረግ የወጣት ኤርሚያስ በዛብህን የነገ ተስፋ እንድናለመልም እንማጸናችኋለን።
1000320044948 (CBE)
Ermiyas Bezabih
አስተባባሪ፦ የጅማ ፈ/ሰ/ቅ/ገብርኤል ቤ/ክ ፍኖተ ሎዛ ሰንበት ት/ቤት