Ethio orthodox

Ethio orthodox news about ethiopian orthodox church

ነሀሴ 7 ፥- እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የተጸነሰችበት ቀን ነው፡፡
13/08/2022

ነሀሴ 7 ፥- እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የተጸነሰችበት ቀን ነው፡፡

የ2014 ዓ.ም ጾመ ፍልሰታ በተመለከተ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ከሀገረ አሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ ያስተላለፉት መልዕክትበስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ...
05/08/2022

የ2014 ዓ.ም ጾመ ፍልሰታ በተመለከተ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ከሀገረ አሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ ያስተላለፉት መልዕክት
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡
በሀገር ውስጥም ሆነ በመላው ዓለም ዙርያ የምትገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምእመናንና ምእመናት፣ እንዲሁም ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት በሙሉ እንኳን ለጾመ ፍልሰታ ለማርያም በሰላም አደረሳችሁ !!
“ወተዘከረ ሣህሎ ዘይቤሎሙ ለአበዊነ ለአብርሃም ወለዘርዑ እስከ ለዓለም፤ ለአባቶቻችን ለአብርሃምና ለዘሩ የነገራቸውን ይቅርታውን ለዘላለሙ አሰበ” (ሉቃ.፩፥፶፭ )
ማኅደረ መለኮት፣ ማኅደረ መንፈስ ቅዱስ የሆነች እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም፣ በመንፈስ ቅዱስ ተሞልታ እግዚአብሔርን ባመሰገነችበት ምስጋናዋ፣ ከላይ የተጠቀሰውን ይህንን ዐረፍተ ነገር መናገሯን በቅዱስ ወንጌል ተጽፎልናል፡፡
ቅድስት ድንግል ማርያም በዚህ ምስጋናዋ የገለፀችው ዓቢይ መልእክት የክብር አምላክ እግዚአብሔር የተናገረውን የማያስቀር አምላክ መሆኑን ነው፤ ኤልሻዳይ እግዚአብሔር የተስፋ አምላክ ነውና በየጊዜው ለፍጡራኑ የተስፋ ቃል ይሰጣል፣ ቃል ኪዳንም ይገባል፣ እግዚአብሔር በክዋኔው ዘላለማዊ እንደሆነ ሁሉ ቃል ኪዳኑም ዘላለማዊ እንደሆነ “ወተዘከረ ኪዳኖ ዘለዓለም፣ ማለትም ዘላለማዊ ቃል ኪዳኑን አሰበ” በማለት ቅዱስ መጽሐፍ ያስተምረናል፡፡
እግዚአብሔር መፍቀሬ ሰብእ ከሆነ አምላካዊ ጠባዩ በመነጨ ፍቅሩ ከመጀመሪያው ሰው ከአዳም ጀምሮ ለአበው ቃል ኪዳን እንደገባላቸው ተጽፎልናል፣ ይልቁኑም ለአብርሃም “በዘርእከ ይትባረኩ ኲሎሙ አሕዛበ ምድር ማለትም የምድር አሕዛብ ሁላቸው በዘርህ ይባረካሉ” ብሎ ለዓለም ሁሉ የሚሆን በረከትና ድኅነት ከእርሱ እንደሚገኝ ቃል ኪዳን ገብቶለታል፤ ቅድስት ድንግል ማርያም “ለአብርሃምና ለዘሩ የተናገረውን ቃል አሰበ” ብላ የገለፀችውም ይህንን ቃል ኪዳን ነው፤ ምክንያቱም የምድር አሕዛብ ሁሉ የሚባረኩበት ዘር ኢየሱስ ክርስቶስ በወቅቱ በማኅፀኗ እንዳለ ታውቃለችና ነው፡፡
የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናት
ከቅድስት ድንግል ማርያም ምስጋና የምንማረው ዓቢይ ትምህርት ሁሌም የእግዚአብሔርን ድንቅ ፍቅር በማስታወስ፣ በመናገርና በመመስከር ማመስገን፣ ማሰብና ማስታወስ እንደሚገባን ነው፡፡ እግዚአብሔርም ይህንን እንደሚወድ “ወተዘከሩ መንክሮ ዘገብረ፤ ያደረገውን ድንቅ ሥራ አስቡ” ብሎ ነግሮናል፡፡
እግዚአብሔር የተናገረውን የማያስቀር ታማኝ አምላክ ነውና ለአብርሃምና ለዘሩ የገባውን ቃል ኪዳን እነሆ ከዛሬ ሁለት ሺሕ ዐሥራ አምስት ዓመታት በፊት ቃል ኪዳኑን እንደተስፋ ቃሉ በተግባር ፈጽሞአል፤የምድር አሕዛብ ሁሉ የሚባረኩበት ወይም የሚድኑበት ዘር እርሱም መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የአብርሃም ዘር ከሆነች ከቅድስት ድንግል ማርያም ተወልዶ የምድር አሕዛብ የሆነውን በሙሉ በደመ መስቀሉ ባርኮ አንጽቶና ቀድሶ አድኖአል፡፡ እግዚአብሔር የምድር አሕዛብ ሁሉ በምሕረትና በይቅርታ እንድንባረክበት የሰጠን ዘር አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንደሆነ ሁላችንም መገንዘብና ማመን ይገባናል፣ ይህንን ማወቅ፣ ማስተዋልና ማመን ብፅዕና ማግኘትን ያስከትላል፡፡ ቅድስት ድንግል ማርያም “ከዛሬ ጀምሮ ትውልድ ሁሉ ብፅዕት ነሽ ይሉኛል” ስትል የተናገረችው ቃለ ትንቢት የእግዚአብሔር ማደሪያ ቤተ መቅደስ መሆኗን ስለተረዳች ነው፡፡
እኛም እንደእሷ “አንትሙ ውእቱ ታቦቱ ለመንፈስ ቅዱስ ማለትም እናንተ የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ ናችሁ” ተብለናል፤ ቅድስት ድንግል ማርያም ማኅደረ መለኮት የሆነችው በሃይማኖት በትሕትና ነው፤ ከዚህ አንጻር እኛም በሃይማኖት ጥላ ሥር ሆነን በትሕትና በፍቅር በአንድነት የምንኖር ከሆነ የእግዚአብሔር ማደሪያ ለመሆናችን ሌላ ምስክር አያስፈልገንም፡፡ ምክንያቱም ጌታችን “ተፋቀሩ በበይናቲክሙ ወእምከመ ተፋቀርክሙ በበይናቲክሙ የአምረክሙ ዓለም በዝንቱ ከመ አርዳእየ አንትሙ፤ እርስ በርሳችሁ አብዝታችሁ ተፋቀሩ፤ እርስ በርሳችሁ ከተዋደዳችሁ ደቀመዛሙርቴ እንደሆናችሁ ዓለም በዚህ ያውቃል” ብሎ እንዳስተማረን ምስክሮቻችን ፍቅር አንድነትና ትሕትና ይሆናሉና ነው፡፡
የተወደዳችሁ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናት
ከነገው ዕለት ጀምሮ የምንጾመው የጾመ ማርያም ዋና ዓላማ ጠብንና ጥላቻን ማሸነፍ የሚያስችል የይቅርታን የፍቅርንና የአንድነትን ኃይል በመለኮት ፈቃድ ለማጐልበት ነው፤ የተለየ የጾም፣ የጸሎት፣ የንሥሐ ጊዜ ወስኖ እግዚአብሔርን መለመንና ከእርሱ ጋር መገናኘት ከጥንት ጀምሮ የሃይማኖት መርሕ ነው፡፡ በዚህ መርሕ ተመርተው ሕዝባቸውንና ሀገራቸውን ከመከራና ከፈተና የታደጉ ቅዱሳን ብዙ ናቸው፡፡ የልቡናቸውን መልካም ምኞት ያገኙም እንደዚሁ ብዙ ናቸው፡፡
እኛም ሐዋርያዊት ቤተ ክርስቲያን በደነገገችው የቀኖና ድንጋጌ መሠረት የምንጾመው ጾመ ማርያም፣ ቅዱሳን ሐዋርያት ጌታችን የልቡናቸውን መሻት እንዲፈጽምላቸው የጾሙትና የለመኑትን ያገኙበት ኩነት መነሻ አድርገን እግዚአብሔር እንደነሱ የልቡናችንን መሻት እንዲፈጽምልን በማመንና ተስፋ በማድረግ ነው፤ ከዚህ አንጻር የቅድስት ድንግል ማርያም ነገረ ትንሣኤ ወፍልሰት በማሰብ ከእግዚአብሔር ጋር ለመገናኘት በብርቱ እንጥራለን፣ እንጾማለን፣ እንጸልያለን፣ በንሥሐም ወደ እርሱ እንቀርባለን፣ ቅዱስ ምሥጢረ ቊርባንንም እንቀበላለን፤ በዚህም ከእግዚአብሔር ጋር እንገናኛለን፡፡ ይህ ሲሆን እግዚአብሔር የልባችንን መሻት በብሩህ ገጽ ተቀብሎ ይፈጽምልናል፡፡ ሁላችንም እንደምንገነዘበው በአሁኑ ጊዜ የኢትዮጵያ ሕዝብ ፍላጎት ፍጹም ሰላም ያላት ሀገር እንድትኖረው ነው፤ ይህ ትክክለኛ ፍላጎት ነው፡፡ ይሁንና ያለ እግዚአብሔር ፈቃድ ሁሉም ነገር ስለማይሆን ፍጹም ሰላም በሀገር ሰፍኖ ሕዝባችን እግዚአብሔር በሰጠው ምድር በፍቅር፣ በአንድነት በነጻነትና በእኩልነት እንዲኖር ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት ሁሉ በዚህ ወቅት የቅድስት ድንግል ማርያምን ጸሎትና ስእለት ተማኅፅኖና አስተበቊዖት አጋዥ አድርገን በልዩ ሱባዔ ወደ እግዚአብሔር በመቅረብ በንሥሐ፣ በጾም፣ በጸሎት፣ ነዳያንን በመርዳትና ቅዱስ ቊርባንን በመቀበል እሱን መማፀን ይኖርብናል፡፡
በመጨረሻም
በሀገራችን የተከሠቱት ያላስፈላጊ ግጭቶችን በድርድር ለመፍታት እየተሞከሩ ያሉ አንዳንድ የሰላምና የውይይት ድምፆች ተስፋ ሰጪ ስለሆኑ ሥር ሰደው፣ በተግባር ተተርጉመው፣ ለተጐዳው ሕዝባችን መጠገኛ ይሆኑ ዘንድ፣ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት ሁሉ በዚህ ዙርያ በሱባዔው ወቅት ወደ እግዚአብሔር አቤት በማለትና ሂደቱን በመደገፍ የበኩላቸውን ጥረት እንዲያደርጉ፣ መንግሥትም ሆነ የዓለም አቀፉ ማኅበረ ሰብ በዚህ በጎ ሐሳብ እንዲገፉበትና ሕዝባችንንና ሀገራችንን ከጥፋት እንዲታደጉ አባታዊ መልእክታችንን በእግዚአብሔር ስም እናስተላልፋለን፡፡
እግዚአብሔር አምላክ ጾሙን የሰላም የሥርየት የፍቅር የአንድነት ጾም ያድርግልን፡፡
ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ
ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን
አባ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ
ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት
ዋሽንግተን ዲሲ አሜሪካ ፡፡

ፍልሰታ ደርሰች ፥ የደስታችን ጊዜ ቀረበ
03/08/2022

ፍልሰታ ደርሰች ፥ የደስታችን ጊዜ ቀረበ

"እረኛ በጎቹን ይሸጣል ክርስቶስ ግን ስለ በጎቹ ተሸጧል ፣ እረኛ የበጎቹን ሥጋ ይበላል የክርስቶስን ሥጋ ግን እኛ በጎቹ እንበላለን ፣እረኛ የበጎቹን ቆዳ ይለብሳል ክርስቶስ ግን ስለ በጎቹ ...
31/07/2022

"እረኛ በጎቹን ይሸጣል ክርስቶስ ግን ስለ በጎቹ ተሸጧል ፣
እረኛ የበጎቹን ሥጋ ይበላል የክርስቶስን ሥጋ ግን እኛ በጎቹ እንበላለን ፣እረኛ የበጎቹን ቆዳ ይለብሳል ክርስቶስ ግን ስለ በጎቹ ዕርቃኑን ተሰቅሏል።"
•የተዋህዶ መዶሻ የቤተ ክርስቲያን ዓይን ሐምሌ 24 1962 ዓ.ም አረፉ።
ዝክረ ሊቃውንት ሊቁ መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ
በረከታቸው ይደርብን።
Tegu netsi

መልካም እለተ ሰንበት
31/07/2022

መልካም እለተ ሰንበት

ማኅበረ ቅዱሳን ለደብረ ወገግ አሰቦት ቅድሥት ሥላሴና አቡነ ሳሙኤል አንድነት ገዳም መነኮሳት ሕክምና ሰጠ::የአሰቦት ገዳም መነኮሳት በውሀ እጥረት ምክንያት ለተለያዩ በሽታዎች እየተጋለጡ እን...
30/07/2022

ማኅበረ ቅዱሳን ለደብረ ወገግ አሰቦት ቅድሥት ሥላሴና አቡነ ሳሙኤል አንድነት ገዳም መነኮሳት ሕክምና ሰጠ::የአሰቦት ገዳም መነኮሳት በውሀ እጥረት ምክንያት ለተለያዩ በሽታዎች እየተጋለጡ እንደሆነ ይታወቃል፡፡

የመናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ከአድዋ መልስ ከ10 ዓመታት ቆይታ በኋላ የካቲት 23 ቀን 1900 ዓ.ም ዐፄ ምኒልክ መኳንንቱና ሕዝቡ በተሰበሰበበት በአቡነ ማቴዎስ መሠረቱ...
30/07/2022

የመናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ከአድዋ መልስ ከ10 ዓመታት ቆይታ በኋላ የካቲት 23 ቀን 1900 ዓ.ም ዐፄ ምኒልክ መኳንንቱና ሕዝቡ በተሰበሰበበት በአቡነ ማቴዎስ መሠረቱ ተጣለ የግንባታው ወጪ በአብዛኛው የተሸፈነው በመንግሥት ነው ዐፄ ምኒልክ 40 ሺ ብር አውጥተዋል
የቤተክርስቲያኑ አርክቴክት አርፋንዲስ የተባለ ግሪካዊ ሲሆን መሐንዲሱ ደግሞ ሙሴ ካስታኛ የተባለ ጣልያናዊ ነበር ድንጋዩ ከኮተቤ ቀበናና አምቦ በአህያና በበቅሎ በሚጎተት ጋሪ ተጭኖ ቀርቧል ሥራውን ለማፋጠን ዐፄ ምኒልክ የሰርኪስ የተባለ የጢስ ባቡር ከአውሮፓ አስመጥተው ነበር የደብሩ መገንቢያ ድንጋይ የተመላለሰው በዚሁ ባቡር ነው የቤተክርስቲያኑ ጉልላት ከፈረንሳይ የመጣ ነው ከዳግማዊ ምኒልክ ቤተመንግሥት እስከ ቤተክርስቲያኑ የሚደርስ መንገድ ተሠርቶ ነበር
አቡነ ማቴዎስ ባርከው ስሙንም ገነተ ጽጌ ብለው ሰይመውታል
ዐፄ ምኒልክ በአድዋ ጦርነት ለረዳቸው ሰማዕት ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ለሀገራቸውና ለቤተክርስቲያናቸው ሰማዕነትን ለተቀበሉ የአድዋ ጀግኖች መታሰቢያ ይሆን ዘንድ ቤተክርስቲያኑን አሠሩ
🙏

+++ "ልጆቼ ከመሸ ተገናኘን" +++ ያኔ የገዳሙ መጋቢ የነበሩት አባ ተጠምቀ በጭንቅ ተውጠዋል። ከአቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ እግር ስር ወድቀው "ግድ የልዎትም አባ የዛሬው ጉዞ ይቆይዎ። እኔ ...
29/07/2022

+++ "ልጆቼ ከመሸ ተገናኘን" +++

ያኔ የገዳሙ መጋቢ የነበሩት አባ ተጠምቀ በጭንቅ ተውጠዋል። ከአቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ እግር ስር ወድቀው "ግድ የልዎትም አባ የዛሬው ጉዞ ይቆይዎ። እኔ ጥሩ ሕልም አላየሁም። እባክዎ እግርዎን ከዚህ ቤት አያንሡ፤ እንደው እባክዎ" እያሉ ይለምኗቸዋል። አቡነ ጎርጎርዮስ ግን ወደ መቂ ጊዮርጊስ ለአገልግሎት ለመሄድ ቆርጠው ተነሥተው ነበርና ሳልሄድ አላድርም ብለው እምቢ አሉ። በእርግጥ በዚያች የጉዞ ቀን ምን ሊሆኑ እንደሚችሉ ቀድመው ሳይረዱት ቀርተው አይመስልም። ምክንያቱም "ዛሬ ጥሩ ሕልም አላየሁምና አይሂዱ" ላሏቸው አባ ተጠምቀ " እኔስ ብሆን አንዳች ምልክት ያላየሁ ይመስልሃል። ዛሬ ጠዋት ሱሬን ስታጠቅ ሰባት ጊዜ መልሶ ሲፈታብኝ ነበር" ሲሉ መልሰውላቸዋል። ይሁን እንጂ በመቂ የሚገኝ እጅግ ሕመም የጸናበት አንድ የሚያውቁት ክርስቲያን ስለ ነበር ከራሳቸው ሕይወት ይልቅ ለዚያ ሰው ነፍስ ዋጋ ሰጥተው "ኸረ ሳላቆርበው እንዳይሞትብኝ" እያሉ አባ ጎርጎርዮስ ወደ መኪናው ፈጥነው ወጡ። ነገር ግን ከዚያ መኪና በሕይወት አልወረዱም። ከአዲስ አበባ ሕዝብ ጭኖ ከመጣ ተሽከርካሪ ጋር እርሳቸው ያሉበት መኪና ተጋጭቶ እሑድ ኃምሌ 22 ቀን ጠዋት አንድ ሰዓት ገደማ እኛ ደግ እና ባለ ብዙ ራእይ አባት አረፉ።

ብፁዕነታቸው ከማረፋቸው ከ15 ቀናት በፊት በአላጌ ሕፃናት አምባ የልጆች ማሳደጊያ ተገኝተው በዚያ ቦታ ለሚሠራ ቤተ ክርስቲያን መሠረት ካኖሩ በኋላ "ሰው የሚፈልገውን ከሠራ የሚጠብቀው ሞቱን ነው" ብለው ተናግረው ነበር። በውስጣቸውም የነበረው የአገልግሎት እሳት ገና እየተቀጣጠለ ቢሆንም በዚህች ምድር የሚቀራቸው የእንግድነት ዘመን ግን ጥቂት መሆኑን ስለተረዱ በዚያ ለነበሩት መንፈሳዊ ልጆቻቸው እየደጋገሙ "ልጆቼ ከመሸ ተገናኘን" ይሏቸው ነበር። ከዚህች ክፋት ከነገሠባት ዓለም ጠልቀው ፈጣሪያቸው ካለበት መንፈሳዊ አገር የሚወጡበት ጊዜ መቃረቡን ቀድመው የተረዱ አባት ነበሩ።

አቡነ ጎርጎርዮስ ከዘመናቸው ቀድመው የኖሩ፣ ትውልዱ ሃይማኖቱን ያቆዩለትን አባቶች እንዲያውቅና የኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ እምነቱንም ታሪክ ከመሠረቱ ተረድቶ ቤተ ክርስቲያኑን እንዲያፈቅር በቃልም በመጽሐፍም የተጉ አባት ናቸው። ቅዱስ አባታችን የነበሩበትን ዘመን አልፎ በሚሄደው ተራማጅ አሳቢነታቸውና ለቤተ ክርስቲያን ሁለንተናዊ ዕድገት ያሳዩት በነበረው ትጋት አሁን ላይ ላሉትና ወደ ፊትም ለሚነሡ በእውነት ለሚደክሙ ቅን አገልጋዮች ሁሉ ትልቅ አርአያ ይሆናሉ።

የአገልግሎት ድካማቸው በረከት በሁላችን ላይ ይደርብን። እኛንም የአባቶቻችን ልጆች ያድርገን!!!

(*የያኔው አባ ተጠምቀ የአሁኑ ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ሣልሳይ የምሥራቅ ሸዋ አገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ናቸው።)

ዲያቆን አቤል ካሳሁን
ሐምሌ 22፣ 2014 ዓ.ም.
ዝዋይ (ብፁዕነታቸው ብዙ ሥራ በሠሩበት ክፍለ አገር ሆኜ)

ቤተሰብ ይሁኑ
https://t.me/Dnabel
https://www.facebook.com/AbelKassahunMekuria12
https://youtube.com/channel/UCRvatZyeFOJtXnAjZSOdrZg

29/07/2022

ርእሰ ሊቃውንት አባ ገ/ኪዳን ስለ መልካም ወጣት የተናገሩት፦
" #ኦፈሳምኒት የምትባል ወፍ አለች። የመጨረሻው ዘመን ወፍ ይሏታል አባቶች። የምትኖረው በባህር ነው።በባህር ላይ እየኖረች ውሃ ሲጠማት ከባህር ወጥታ ጤዛ ነው እምትልሰው። መልካም ወጣት የሚባለው እንደዛ ማለት ነው።"
ሁሉ ሙሉ ከሆነች ቤተክርስቲያን(ባህረ ጥበባት) እየወጡ ትናንሽ ፍርፍሪ ወዳለበት የሚንከራተቱ ወጣቶች በዚች ወፍ ይመሰላሉ።
ወፏ ባህር ላይ እየኖረች ውሃ ሲጠማት ከባህሩ መጠጣት ሲገባት ጠዋት ጠዋት ጠብቃ ከጤዛ ትጠጣለች። መልካም ወጣት ትሆናለህ እየተባለ እየተታለለ ከባህር(ቤተክርስቲያን) ወጥቶ ጠብታ ውሃ ፍለጋ የሚባዝን እንደ ማለት ነው።"
🙏

29/07/2022
ሀምሌ 22የሁለት ታላላቅ አባቶች የእረፍት ቀን ነው፡፡በፋሽስት ኢጣሊያ የተገደሉት አቡነ ጴጥሮስ እና የማህበረ ቅዱሳን መስራቹ አቡነ ጎርጎርዮስ፡፡በረከታቸው ይደርብን፡፡
29/07/2022

ሀምሌ 22
የሁለት ታላላቅ አባቶች የእረፍት ቀን ነው፡፡በፋሽስት ኢጣሊያ የተገደሉት አቡነ ጴጥሮስ እና የማህበረ ቅዱሳን መስራቹ አቡነ ጎርጎርዮስ፡፡
በረከታቸው ይደርብን፡፡

   ይህች ቀን ለኔ ልዩ ናት እናቴ እንደነገረችኝ ገና የ40 ቀን እያለው ነበር የአይኔ ብሌንያለማቋረጥ ይንቀጠቀጥ የነበረው ሆኖም ይድናል ፣ ምንም አይላትም ይተዋል ስታድግ ፣ በቃ ተበላሸች...
29/07/2022



ይህች ቀን ለኔ ልዩ ናት እናቴ እንደነገረችኝ ገና የ40 ቀን እያለው ነበር የአይኔ ብሌን
ያለማቋረጥ ይንቀጠቀጥ የነበረው ሆኖም ይድናል ፣ ምንም አይላትም ይተዋል ስታድግ ፣ በቃ ተበላሸችባት ፣ በሚል የቤተሰብ እና ጎረቤት የቅርብ ወዳጆች ግምት እየታለፈ በህክምናም ሊረጋ ያልቻለው የአይኔ ብሌን 1ዓመት ከ 9 ወርን አስቆጠረ ቀኑ ነበር የክርስትና እናቴ ለ ወላጅ እናቴ ቅ/ዑራኤል እንድትወስደኝ አሳሰበቻት ቅ/ዑራኤል ስሙን እንጂ ቤተ-ክርስቲያኑ የት እና ቦታውን የማታውቀው እናቴ እኔን አለባብሳ አዝላኝ ከቤት ስትወጣ ይሄነው የማይባል በረዶና መብረቅ የቀላቀለ ሀይለኛ ዝናብ ጣለ ያ ሁሉ ዶፍ እኔን እንዳዘለች እየደበደባት ዝናብ ሳያግዳት እየጠየቀች ቅ/ዑራኤል ቤተከርስቲያን ደረሰች ከአሸንዳ በሚወርድው የጎርፍ የዝናብ ውሃ አወላልቃ አንተ ማራት እንደፈለክ አድርጋት እኔ አቅም የለኝም ብላ በእንባ ቅዱስ ዑራኤልን እየተማፀነች በሚወርደው ውሃ ላይ ነከረችኝ የሚያልፍ የሚያገድመው ኧረ ብርድ አስመታሻት ፣ ውይ ጭካኔሽ .... እያሉ ቢያልፏትም ይማርልሽ በሉኝ እያለች ታለቅስ ነበር። ወደ ቤት ስንመለስ እንቅልፍ ወስዶኝ ስለነበር አስተኝታኝ ወደ ስራዋ ሄደች እናቴ ቤት ስትመለስ ግን ያልተጠበቀ ነገር ተከሰተ ከእንቅልፌ ስነሳ የአይኔ ብሌን መንቀጥቀጥ አቆመ እረጋ ቤት ሁሉም ደነገጠ በደስታ እንባ ተራጩ በሰአታት ውስጥ ታሪኬ ተቀየረ !!!
ይህ ቀን ነው የብርሃን መልአክ ቅዱስ ዑራኤል እጅግ ድንቅ ተአምሩን የሰራልኝ ከልጅነት ጀምሮ ጥበቃው ያልተለየኝ አሁንም የሚጠብቀኝ የልቤን መሻት እየፈጸመልኝ እንደኔ ክፉት እና ቸልተኝነት ሳይሆን እንደሱ ቸርነት እየጠበቀኝ ሁሌም ስጠራው የማያሳፍረኝ አባቴ ነው 🙏

ዑራኤል" ማለት ትርጉሙ "የብርሃን ጌታ" የአምላክ ብርሃን ማለት ነው ።

"ዑራኤል" ሆይ እኔ ሳዝበት አረካሁበትም እና በሀሳቤ አንተ አስብበት በአንደበቴ አንተ ተናገርበት በሰውነቴ አንተ እዘዝበት የክፋት ተራ እንዲያበቃ መቅፀፍትና ደንዳና ልብ እንዲወገድ አቤቱ ሆይ እለምንካለው🙏 ችግሬን የምታውቅልኝ ሀሳቤን የምትረዳልኝ በደካማው ጎኔ ምትደግፈኝ በእንባዬ እራሱ አይኖቼን የምታደርቅልኝ ለምርኮ የተዘረጋውን እጄን ከሽንፈት የምትሰበስብልኝ በቃ ስል ገና ነው የምትለኝ ወደቀች ጠፉች ስባል የምታለመልመኝ አንተ ጌታዬ ነህ አንተ ማዕረጌ ነህ አንተ መልኬ ነህ በተዘጋው ዘመን በሬ አንተ ነህ በፍቅርህ ውስጥ ሰውረኝ ከማያቸው ሰዎችና ሁኔታዎች ይልቅ አንተ ጎልተክ ታየኝ የኔ ንጉሥ ሁሌም ክበርልኝ የኔ ጌታ 💖🙏 ለኔ የደረሰልኝ ለናንተም ይድረስላችሁ🙏

ሜሎን

Address

4 Kilo
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethio orthodox posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share