ካቶሊካዊ ሲኖዶስ 2014-2016

ካቶሊካዊ ሲኖዶስ 2014-2016 The purpose and content of the Synod will be discussed in detail on this page.

Synod has been practiced in the Catholic Church since, and it is planned to go hand in hand with all denominations and all human beings, not just in its own religion.

23/10/2023

ስለ ሲኖዶስ እንጸልይ
#ሲኖድ #አብረንእንጓዝ

23/10/2023
ሲኖ-ኦዶስበገጣሚ አዲስ ኃይሌ በሲኖዶስ ሀሳብ ላይ በአራት ቋንቋ የተዘጋጀ ግጥም
22/07/2022

ሲኖ-ኦዶስ

በገጣሚ አዲስ ኃይሌ
በሲኖዶስ ሀሳብ ላይ በአራት ቋንቋ የተዘጋጀ ግጥም

ሲኖዶሳዊነት በገጣሚ ማንያዝሀል ጌታ ሆይ
22/07/2022

ሲኖዶሳዊነት
በገጣሚ ማንያዝሀል ጌታ ሆይ

21/07/2022
የወጣቶች ተልዕኮ እና አገልግሎት በሚል ከተለያዩ ሀገረስብከት ለተውጣጡ ወጣቶች ስልጠና ተሰጠበኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሀገር አቀፍ የሲኖዶስ ኮሚቴ አዘጋጅነት ሚዲያ ለስብከተ ወንጌል...
04/07/2022

የወጣቶች ተልዕኮ እና አገልግሎት በሚል ከተለያዩ ሀገረስብከት ለተውጣጡ ወጣቶች ስልጠና ተሰጠ

በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሀገር አቀፍ የሲኖዶስ ኮሚቴ አዘጋጅነት ሚዲያ ለስብከተ ወንጌል እና የወጠቶች ተልዕኮ በቤተክርስቲያን በሚል ከተለያዩ ሀገረስብከቶች ለተውጣጡ ወጣቶች እና የሚዲያ ባለሞያዎች ከሰኔ 24-26 ቀን 2014 ዓ.ም. በሞጆ የኮንሶላታ አባቶች ማዕከል ሥልጠና ተሰጥቷል።

ስልጠናው ወጣቶችን በቤተክርስቲያንን ማህበራዊ አስተምህሮ ላይ ያላቸውን እውቀት ለማጎልበት በተለያዩ የትምህርት ርዕሶች እና አስተማሪዎች ተዘጋጅቶ ቀርቧል። የወጣቶች ሚና ለሰላም፣ ለዕርቅ፣ ወንድማማችነት፤ ቤተክርስቲያን ሰብዓዊ እና መለኮታዊ ተቋም፤ የካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ማህበራዊ አስተምህሮ ለሚዲያ እና ለወጣቶች፤ የማህበራዊ ሚዲያ ሚና ለስብከተ ወንጌል እና ወንጌልን እና መዝሙርን ከሲኖዶሳዊት ቤተክርስቲያን ሃሳብ ጋር በማዋሃድ ስልጠና የተሰጠ ሲሆን የልምድ ልውውጥ እና የቡድን ውይይቶችም ተደርገዋል።

ክቡር አባ ገብረማስቀል ሽኩር የሀገር አቀፍ የሲኖዶስ ኮሚቴ ሰብሳቢ ለተወካዮቹ የቤተክርስቲያን ሰብዓዊ እና መለኮታዊ ማንነት የወጣቶችን የሰላም እና የዕርቅ ሚና ከሲኖዶስ የአብሮ መጓዝ በህብረት፣ በተሳትፎ እና ተልዕኮን ግብ አድርገው ይህንንም በማሰብ እንዴት በማህበራዊ ሚዲያ ስብከተ ወንጌል ላይ ማገልገል እንደሚችሉ ጥልቅ ማብራሪያ ሰጥተዋል። ስልጠናው በታሰበበት ዘርፍ ላይ የሚያገለግሉ ባለሙያዎችን አሳታፊ አድርጓል።

በቤትክርስቲያን ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ ላይ የወጣቶች ሚና ሰፊ እንደመሆኑ መጠን በሀገራችን በኢትዮጵያም ወጣቶችን ለማሳተፍ መሰል ስልጠናዎች ወጣቶችን ብቁ እንደሚያደርጉ ተገልጿል። በስልጠናው የተሳተፉ ወጣቶች ከ8 ሃገረስብከት የተውጣጡ መሆናቸው የተሻለ የልምድ ልውውጥ መድረክ እንዲሆን ያገዘ ሲሆን ወጣቶቹ በመጡበት አካባቢ ያለውን ሁኔታ እንዲሁም የወጣቶችን የማህበራዊ ሚዲያ እንቅስቃሴ አካፍለዋል።

ወጣቶቹ በየሃገረስብከቱ ተወክለው የመጡና በጽ/ቤቱ የፌስቡክ ገጽ በተደረገው ጥሪም እና የበይነ መረብ ምዝገባ የተመዘገቡ ናቸዉ። በማጠቃለያውም ላይ እሑድ ሰኔ 26 ቀን 2014 ዓ.ም. ዕለት በሞጆ ኮንሶላታ ገዳም ምዕመናን ጋራ የጋራ መስዋዕተ ቅዳሴ አድርገዋል።

https://youtu.be/xRIxn5O6hmk
23/06/2022

https://youtu.be/xRIxn5O6hmk

አዘጋጅና አቅራቢ እስጢፋኖስ ፍቃዱ #ምስክርነት #የህይወትተሞክሮ #አስተዉሎትየኢትዮጵያ ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን Ethiopian Catholic Church Catholic TV Ethiopia ካቶሊክ ቲቪ ኢትዮጵያ ሚዲያ ኔትወርክ መረ.....

https://youtu.be/uJ4vxexLgTo
09/06/2022

https://youtu.be/uJ4vxexLgTo

አዘጋጅ ሃይማኖት ወንድሙ #ዜና #መረጃየኢትዮጵያ ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን Ethiopian Catholic Church Catholic TV Ethiopia ካቶሊክ ቲቪ ኢትዮጵያ ሚዲያ ኔትወርክ መረጃዎችን በማህበራዊ ሚዲያዎቻችን ባሉበት ....

የምዕመናን ሲኖዶሳዊ ምክክር ተካሄደ  የምእመናን፣ የመንፈሳዊ ማሕበራት እና የወጣቶች እንቅስቃሴዎች ተወካዮች ተካፋይ የሆኑበት ሲኖዶሳዊ ምክክር በአዲስ አበባ ቅዱስ ሚካኤል ሐዋርያዊ እና ማህ...
08/06/2022

የምዕመናን ሲኖዶሳዊ ምክክር ተካሄደ

የምእመናን፣ የመንፈሳዊ ማሕበራት እና የወጣቶች እንቅስቃሴዎች ተወካዮች ተካፋይ የሆኑበት ሲኖዶሳዊ ምክክር በአዲስ አበባ ቅዱስ ሚካኤል ሐዋርያዊ እና ማህበራዊ ማዕከል ግንቦት 30 ቀን 2014 ዓ.ም. ተካሂዷል።
በምክክር ጉበኤው ላይ የብሔራዊ ምእመናን ሐዋርያዊ ተግባር ምክርቤት እና የአዲስ አበባ ምእመናን ሐዋርያዊ ተግባር ምክርቤት ተወካዮች፣ ነዋሪነታቸው በአዲስ አበባ የሆኑ የመንፈሳዊ ማሕበራት እና የወጣቶች መንፈሳዊ እንቅስቃሴዎች ተወካዮች፣ ጥሪ የተደረገላቸው ምእመናን እና ወጣቶች ተሳተፊ ሆነዋል። እንዲሁም ምእመናን በያሉበት በበይነ መረብ ተሳተፊ እንዲሆኑ በቀረበው ጥሪ መሰረት ከተለያዩ ስፍራዎች በበይነመረብ ተሳተፊ ሆነዋል።

ተሳታፊዎቹ እና አጠቃላይ ሲኖዶሰዊ መግለጫ ከተደረገላቸው በኋላ በቡድን ውይይቶች እና በጥያቄና መልሶች ገንቢ ሀሳቦችን ሰንዝረዋል። የቤተክርስቲያን ሲኖዶሳዊ ጉዞ የተሳካ እንዲሆንም ጸሎት ያደረጉ ሲሆን ሲኖዶሱ በተሳካ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ የሚደረገው ጸሎት በየቁምስና፣ በየማሕበራቱ እና በየግልም ተጠናክሮ እንዲቀጥል የየበኩለቸውን ጥረት እንደሚያደርጉ ገልጸዋል።

በምክክር ጉባኤው ላይ ክቡር አባ ገብረመስቀል ሽኩር እንደገለጹት ይህ ሲኖዶሳዊ ጉዞ አንዱ ሌላውን በጥያቄ የሚያፋጥጥበት ሂደት ሳይሆን እያንዳንዱ ምእመን የተጠመቀ በሙሉ “እኔ በጥምቀት አማካኝነት የተቀበልኩትን የስብከተ ወንጌል ተልዕኮ ለመወጣት ምን አድርጌያለሁ? ምንስ ይጎድለኛል? ከዚህ በኋላስ ምን ለማድረግ ቆርጬ ተነስቻለሁ? የሚሉትን ጥያቄዎች ለራሱ የሚጠይቅበት እና ለራሱም መልስ የሚሰጥበት ነው ብለዋል።
በዚህ መንፈስ እያንዳንዱ የቤተክርስቲያን አገልጋይ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር በመካከር የሚያመነጫቸው ሀሳቦች ለቤተክርስቲያን የወደፊት አቅጣጫ ይጠቅሙ ዘንድ እየተጠናቀሩ በየደረጃው ወዳሉ የቤተክርስቲያን መዋቅሮች የሚላኩ ቢሆንም ዋናው ቁም ነገር በየቁምስናው የተነሱ ገንቢ የውይይት ሀሰቦችን በመለየት እና በማደራጀት ለቁምስናው የወደፊት ጉዞ ጠቀሚ ሀሰቦችን ወደ ተግባር መለወጥ እጅግ አስፈላጊ ነው። የሲኖዶሱ ግብም ይኸው ነው።

“የተጠመቁ ሁሉ በንቃት በመሳተፍ አብረው ለተልዕኮ የሚሰማሩባት ቁምስና ተፈጥራ ማየት” የተጠመቁ ሲባል ካህናት፣ ደናግል፣ ምእመናን፣ ወጣቶች፣ ህጻናት፣ አረጋውያን፣ አካል ጉዳተኞች፣ ሌሎችም በሙሉ ማለታችን ነው።

Address

Wawel Street
Addis Ababa
2454

Opening Hours

Monday 08:00 - 17:00
Tuesday 08:30 - 17:00
Wednesday 08:00 - 17:00
Thursday 08:00 - 17:00
Friday 08:00 - 17:00

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ካቶሊካዊ ሲኖዶስ 2014-2016 posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share