Life of Christ channel

Life of Christ channel �� Prayer center��spreading the gospel of the lord Jesus Christ ���christian living� Christian fellow

REBUNI
15/02/2021

REBUNI

*ረቡኒ*

የክርስቶስ ትምህርት ከመምህራን ትምህርት ሁሉ ይበልጣል ፡፡ እርሱ ልጄ እያለ ፣ ፀጉርን እየዳበሰ ፣ ውርስን እዘጋጀto እንደሚያስተምር አባት ነው ፡፡ እርሱ ምን አለህ ? ሳይሆን እኔ አለሁልህ እያለ የሚያስተምር ርእሰ መምህራን ነው ፡፡ መምህራን ለጆሮ ሲናገሩ እርሱ ግን ለልብ የሚናገር ነው ፡፡ ደግሞም የልብ አውቃ ነው ፡፡ በመርማሪ ቃሉ መርምሮን ፣ በፈዋሹ ቃሉ የሚያክመን ነው ፡፡ መምህራን ስለ ችግር ይናገሩ ይሆናል ፤ እርሱ ግን ስለ መፍትሔው ይናገራል ፡፡ እርሱ በጥፋታችን ዝም የማይል የሚቆጭልን መምህር ነው ፡፡ በወደቅን ጊዜም ምሳር የማያበዛብን የማይተቸኝ አጽናኝ አስተማሪ ነው ፡፡ እርሱ ብቻ እያንዳንዱን ቀን ሁለተኛ ዕድል አድርጎ የሚሰጠን በእኛ ተስፋ የማይቆርጥ መምህር ነው ፡፡ እኛ ራሳችንን በጠላነው ሰዓት እንኳ የሚወደን ክርስቶስ ብቻ ነው ፡፡ መምህራን ሁሉ በጠባብ ክፍል ያስተምራሉ ፡፡ እርሱ ግን ትልቁን ዓለም የማስተማሪያ ክፍሉ አድርጎ ያስተምራል ፡፡ ባሕርን ቀለም ፣ እጽዋትን ብዕር ፣ ሰማይን ሰሌዳ ፣ ምድርን የመማሪያ ክፍል አድርጎ የሚያስተምር ሊቅ እርሱ ነው ፡፡

እርሱ የሚያስተምረን ሊቃውንት እንድንሆን ፣ ሊቃውንት ተብለን ለመጠራትና ለመጣላት አይደለም ፡፡ ልጆቹ ወዳጆቹ እንድንሆን ያስተምረናል ፡፡ መምህራን ሁሉ እውቀትን ይሰጣሉ ፡፡ እርሱ ግን በሥጋም በነፍስም ይመግበናል ፡፡ መምህራን ሁሉ ከትምህርት ቤት ውጭ አናገኛቸውም ፡፡ እርሱ ግን በሕይወት እርምጃ ውስጥ ሳይለየን ያስተምረናል ፡፡ መምህራን ሁሉ ትምህርታቸውን ጨርሰው ያስመርቁናል ፤ እርሱ ግን እስክንሞት ያስተምረናል ፡፡ መምህራን ሁሉ ድሆች ናቸው ፤ ክርስቶስ ግን ባለጠጋ መምህር ነው ፡፡ መምህራን ሁሉ በመደበኛ ሰዓትና በታወቀ ሥርዓት የሚያስተምሩ ናቸው ፤ ክርስቶስ ግን በጊዜውም ያለ ጊዜውም የሚያስተምረን ነው ፡፡ መምህራን ሁሉ ኃይለኛ ሲሆኑ ያርቃሉ ፣ ለዘብተኛ ሲሆኑ ያሰንፋሉ ፡፡ እርሱ ግን ፍቅርና ፍርድ የተስማሙለት ነው ፡፡ መምህራን ሁሉ የተወሰነ ዕድል ይሰጣሉ እንጂ ሁልጊዜ የሚወድቀውን አይቀበሉም ፤ ክርስቶስ ግን የውዳቂዎች ሰብሳቢ ነው ፡፡ አዎ እርሱ ርእሰ መምህራን ነው ፡፡
መምህራን እውቀትን ያስተምራሉ ፡፡ ክርስቶስ ግን ራሱ ጥበብ ነው ፡፡ መምህራን ሁሉ ባስተማሩ ቁጥር እውቀታቸው ያድጋል ፡፡ ክርስቶስ ግን እውቀቱ ፍጹም ነውና መጉደልና መጨመር የለበትም ፡፡ መምህራን ስለ ነገ ቢናገሩ ነቢይ ተብለው ይፈራሉ ፣ እርሱ ግን ነገን በማወቁ የነገ ድፍረታችን ነው ፡፡ መምህራን ስሜታቸውን ተማሪዎቻቸው አያውቁላቸውም ፣ እኛም ክርስቶስ ምን ያህል እንደሚያስብልን አናውቅም ፡፡ ተማሪነት ትልቁን ልጅ ያደርገዋል ፣ ሽማግሌው ተማሪ ሲሆን መረበሽ መጮህ ያምረዋል ፡፡ እኛም እንደ ልጆች ስንሆን የሚችለን ክርስቶስ ብቻ ነው ፡፡ የመምህራን ትምህርት በአሸዋ ላይ እንደ ተጻፈ ቶሎ ይጠፋል ፣ የክርስቶስ ትምህርት ግን በዓለት ላይ እንደ ተቀረጸ ዘመናትን ይሻገራል ፡፡ በረዶና ዝናብ የማያጠፋው የዓለቱ ጽሑፍም “ኢየሱስ ክርስቶስ የባሕርይ አምላክ ነው” የሚለው አዋጅ ነው ፡፡
መምህራን በተማሪው ደረጃ ዝቅ ብለው ያስተምራሉ ፡፡ ክርስቶስም ካለንበት ድረስ መጥቶ በሹክሹክታ ያስተምረናል ፡፡ ወደ እኛ ካልመጣ እኛ ወደ እርሱ መሄድ እንደማንችል እያወቀ ሁልጊዜ ይመጣል ፡፡ መምህራን ሳይታዘቡ ያስተምራሉ ፤ እርሱም ባለማወቃችንና በስህተታችን ይራራልናል ፡፡ መምህራን አጢፊውንና ጎበዙን በአደባባይ ይሸልማሉ ፡፡ ክርስቶስም የፍርድ አምላክ ነው ፡፡ መምህራን ቆላ ወርደው ፣ ደጋ ወጥተው ያስተምራሉ ፤ ክርስቶስም ከዳን እስከ ቤርሳቤህ በእግሩ ዞሮ ያስተማረ ነው ፡፡ ካለንበት ድረስም በመጽሐፍ የተናገረን ነው ፡፡ እስከ ምጽአት ድረስ ያለው ዘመኑ የመምህርነትና የምሕረት ነው ፡፡ በዕለተ ምጽአት ግን ፍርድ ይሰጣል ፡፡ አባቱ እርሱን ስሙት ያለው አፈ ማሩ ክርስቶስ ነው ፡፡ ቃሎቹ የሚያጽናኑ የአብ አንድያ ልጅን እርሱን ስሙት ፡፡

16/04/2020

ጸጋ ምንድን ነው? ምንስ ያደርጋል?

ጸጋ ከኃጢአት አገዛዝ በላይ የምንሆንበት ኃይል ነው፡፡

የእግዚአብሔር ጸጋ በኃጢአት ውስጥ ጸንተን ለመኖር ማመካኛ ሊሆነን አይችልም፡፡ ትክክለኛው የጸጋ ትምህርትም ሰዎችን በኃጢአት ጸንተው እንዲኖሩ ፈቃድ የሚሰጥ አይደለም፡፡ ይልቁኑ ጸጋ ከኃጢአት አገዛዝ በላይ የሚያደርገን ኃይል ነው፡፡

የእግዚአብሔር ጸጋ የኃጢአትን ኃይል የሚያስቆም ሰዎችንም ከኃጢአት እስራት የሚፈታ ኃጢአተኝትንና ዓለማዊ ምኞትን የሚያስንቅና የሚያስክድ የእለት ተእለት ኑሯችንን እራሳችንን በመግዛትና በጽድቅ እንዲሁም እግዚአብሔርን በመምሰል እንድናድግ የሚያደርግ ነው፡፡
አንድን ሰው ለኃጢአት ተገስቶ በኃጢአት ውስጥ ፀንቶ እንዲኖር የሚያደርገው ጸጋ ሳይሆን የህግ ትምህርት ነው፡፡

በኃጢአት አገዛዝ ስር ያለን አንድን ሰው ከዚያ አገዛዝ አርነት እንዲወጣና ለጽድቅ ባሪያ እንዲሆን አሁን በቤተክርስቲያን በየመድረኮቻችን ሊሰበክና ሊዘመር የሚገባው ትክክለኛ የሆነ የጸጋ ትምህርት ነው፡፡

የጸጋ ትምህርት ማለት መስቀልን መሰረት ያደረገ እንዲህ ትሆናለህና እንዲህ ሁን ሳይሆን በመስቀሉ ስራ እንዲህ ሆነሀል የሚልና ትክክለኛውን የክርስትያንን ማንነት የሚያሳይ ነው፡፡ በመሰረቱ መስቀሉ ላይ ያልተመሰረተ የትኛውም ዓይነት ትምህርት ትክክል አይደለም በትክክለኛ መንገድም አያራምድም፡፡ ክርስቶስ በመስቀል ላይ የሰራው ስራ እና እኛ በእርሱ ስራ ያገኘነው ማንነት በክርስትና ውስጥ ካልተሰበከና ካልተዘመረ ይሄ ክርስትና ሳይሆን ሀይማኖት ነው፡፡

ከሀጢአት አገዛዝ በላይ ሆኖን ለመኖር ከአእምሯችን ውስጥ የህግን እውቀት በጸጋው አውነት ልንተካው ይገባል፡፡ ምክንያቱም ሰው በኃጢአት የሚገዛው ከህግ በታች እስከ ሆነ ድረስ ብቻ ነው፡፡ በተቃራኒው ከጸጋ በታች የሆነ ሰው ከሀጢአት አገዛዝ በላይ ይሆናል፡፡ በአጠቃላይ ትክክለኛ የጸጋ ትምህርት ለኃጢአት የሚገፋፋ ሳይሆነ ፀረ-ኃጢአታዊ ትምህርት ነው፡፡
ይህም ጸጋ፥ ኃጢአተኝነትንና ዓለማዊን ምኞት ክደን፥ የተባረከውን ተስፋችንን እርሱም የታላቁን የአምላካችንንና የመድኃኒታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ክብር መገለጥ እየጠበቅን፥ ራሳችንን በመግዛትና በጽድቅ እግዚአብሔርንም በመምሰል
በአሁኑ ዘመን እንድንኖር ያስተምረናል፤ ቲቶ 2፡12-13

ኃጢአት አይገዛችሁምና፤ ከጸጋ በታች እንጂ ከሕግ በታች አይደላችሁምና። ሮሜ 6፡14

ክርስቲያን በዚህ የጸጋ ትምህርት ከኃጢያት አገዛዝ በላይ ከሆነ በኃላ በፍፁም ያለፈውን ኃጢአት እያሰበ ሊያዝንና ሊጨነቅ አይገባም፡፡ ይልቁኑ የእግዚአብሔር ጸጋ ካለፈው ኃጢአት በላይ እንደሆነና ከዛ ሁሉ ኃጢአት አንፅቶ እንዳፀደቀው ይህንን መረዳት አለብን፡፡

አስቀድሞ ተሳዳቢና አሳዳጅ አንገላች ምንም ብሆን፥ ይህን አደረገልኝ፤ ነገር ግን ሳላውቅ ባለማመን ስላደረግሁት ምህረትን አገኘሁ፥ የጌታችንም ጸጋ በክርስቶስ ኢየሱስ ካሉ ከእምነትና ከፍቅር ጋር አብልጦ በዛ። 1ኛ ጢሞ 1፡13-14

07/04/2020

የስጦታ ልኩ💝

በጣም ለምትወደው ሰው ስጦታ ለመስጠት አስበህ በእጅህ ያለው ነገር እንደማይመጥነው አስበህ ዝም ብለሃል? ከዚህም የተነሳ አሁን የሌለህን ነገር “በኖረኝና በሰጠሁት!” ብለህ እየተመኘህ ነው?

እንግዲያውስ ልምከርህ፡- የምትወደውን ሰው ለማስደሰት የሌለህን አትመኝ፤ ይልቅ ያለህን ይዘህ ቅረብ! የስጦታ ልኩ የተገዛበት ገንዘብ ሳይሆን የተሰጠበት ልብ ነውና፡፡

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Life of Christ channel posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share