ቪክትሪ ፋምሊ ቤተክርስቲያን - Victory Family Church Ethiopia

ቪክትሪ ፋምሊ ቤተክርስቲያን - Victory Family Church Ethiopia ጌታ ይወድሀል! ለጌታ ያስፈልጉታል!በእኛ ዘንድ ስፍራ አሎት!! At Victory Family Church, we want to help you to become the person God made you to be.

So wherever you are at in your life, you have a place here with us.

በክርስቶስ የማይለወጥ ልብ የማይሰበርም አጥር የለም! ።።።።።።።።።። //።።።።።።።።።።።።። ትላንት እሁድ ጠዋት በነበረን አገልግሎት ከአገልጋይ ዮሴፍ ለማ ጋር Jo Yoseph ከሐዋርያት...
24/08/2026

በክርስቶስ የማይለወጥ ልብ የማይሰበርም አጥር የለም!
።።።።።።።።።። //።።።።።።።።።።።።።
ትላንት እሁድ ጠዋት በነበረን አገልግሎት ከአገልጋይ ዮሴፍ ለማ ጋር Jo Yoseph ከሐዋርያት ሥራ 9–11 ቃለ እግዚአብሔርን የተማርን ሲሆን ትምህርቱም ጥቅልል መልዕክት የሚከተለው ነበር
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
“የጌታ ጸጋ አሳዳጁን ሳዎልን ለወጠው ፤ ወንጌልም ከአይሁድ አልፎ በአንጾኪያ ላሉ አሕዛብ ሁሉ በኃይል ደረሰ። እውነተኛ ክርስትና የምቾት መደለያ ሳይሆን ስለ ክርስቶስ ስም ዋጋ ለመክፈል ራስን መስጠትና በቤተክርስቲያን አካል ውስጥ አብሮ መቆም ነው።” ጌታን በመፍራትና በመንፈስ ቅዱስ ሀይል እየተመላለስን እኛም ዛሬ እውነተኛ የክርስቶስ ደቀመዛሙርት ሆነን በድፍረት የኢየሱስን አዳኝነት ልንመሰክር ይገባናል! 🙏🙏🙏

እንዲሁም ከዘማሪ ይስሀቅ ሰድቅ ጋር እግዚአብሔርን አመለክን። ክብር ለእግዚአብሔር ብቻ ይሁን‼️


የእግዚአብሔር መንግስት የሰው እጅ ያልገባባት እንደ ሰናፍጭ ቅንጣት ጀምራ አለምን የምትወርስ ዘላለማዊት የጽድቅና የሰላም መንግስት ናት! ይህ በፓስተር አማረ ተፈሪ Amare Teferi የቀረ...
22/08/2026

የእግዚአብሔር መንግስት የሰው እጅ ያልገባባት እንደ ሰናፍጭ ቅንጣት ጀምራ አለምን የምትወርስ ዘላለማዊት የጽድቅና የሰላም መንግስት ናት! ይህ በፓስተር አማረ ተፈሪ Amare Teferi የቀረበው መልዕክት የሚያስታውሰን የምናመልከው አምላክ በመቃብር የቀረ ታሪክ ሳይሆን ሞትን ድል አድርጎ የተነሳውንና ዛሬም ህያው የሆነውን አሸናፊውን የነገስታት ንጉሥ ኢየሱስን መሆኑን ነው። የሐዋርያት ስራ የትናንት ማስታወሻ ብቻ ሳይሆን ዛሬም ህያዉ ጌታ በመንፈስ ቅዱስ ምሪት በእኛ ውስጥ የሚሰራው ቀጣይነት ያለው የእርሱ ስራ መሆኑን በጥልቀት የሚያስረዳውን ይህንን ትምህርት ይመልከቱት መንፈስዎን ያድሰዋል! ሙሉ ትምህርቱን ይህን የዩቲዩብ ሊንክ በመጫን ያገኙታል https://youtu.be/_AMed-ugH3U?si=gT4C49ceeud8N21a


መደበኛ ፕሮግራሞቻችን ፤- ዘወትር እሁድ ከ4:00 - 6:00 የአምልኮ አገልግሎት .... ማክሰኞ ከ11:3...

እሁድ ነሐሴ 17 ከጠዋቱ 3:09 - 6:30 ሰዐት በሚኖረን ልዩ የአምልኮ አገልግሎት ላይ በመገኝት እግዚአብሔርን አብረውን ያመልኩ ዘንድ በአክብሮት ተጋብዘዋል። አድራሻችንን ይህን የጎግል ካ...
22/08/2026

እሁድ ነሐሴ 17 ከጠዋቱ 3:09 - 6:30 ሰዐት በሚኖረን ልዩ የአምልኮ አገልግሎት ላይ በመገኝት እግዚአብሔርን አብረውን ያመልኩ ዘንድ በአክብሮት ተጋብዘዋል።

አድራሻችንን ይህን የጎግል ካርታ መስፈንጠሪያን በመጫን ያገኙታል https://maps.app.goo.gl/7vxDARHZCzzoYGN96?g_st=ic

የትላንት እስረኛ መሆን ይብቃዎት!።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።። አዲስ እንጀራ ሲጋገር ምጣዱ በሚገባ ካልታሰሰ አዲሱ እንጀራ ተጣብቆ እንደሚበላሽ ሁሉ እግዚአብሔር ዛሬ ያዘጋጀልን...
19/08/2026

የትላንት እስረኛ መሆን ይብቃዎት!
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
አዲስ እንጀራ ሲጋገር ምጣዱ በሚገባ ካልታሰሰ አዲሱ እንጀራ ተጣብቆ እንደሚበላሽ ሁሉ እግዚአብሔር ዛሬ ያዘጋጀልንን አዲስ በረከትና ውብ ምዕራፍ ለመቀበል የትላንትናውን የቂም ፣ የጸጸት እና የውድቀት ቅሪት ከልባችን ማስወገድ አለብን! አንድ ሹፌር የኋላ መስታወቱን ብቻ እያየ መኪናውን ወደ ፊት መንዳት እንደማይችል፣ እኛም በትላንትናው ታሪክ ውስጥ ታስረን የነገን ከፍታ መያዝ አንችልም። የትላንቱን ሽንፈት እና የከበደንን ሸክም በመስቀሉ ስር ጥለን የወደቁትን በሚያነሳው በጌታ ጸጋ በመደገፍ ወደ አዲሱ የክብር ጥሪያችን እንዴት መዘርጋት እንደምንችል የሚያሳየውን ይህንን የህይወት አቅጣጫ የሚቀይር የፓስተር ጌትነት ተፈሪን ትምህርት አሁኑኑ ይመልከቱ። ህይወትዎን ነጻ የሚያወጣ እና ወደ ከፍታ የሚያራምድ ቃል ነው ... በፍጹም እንዳያመልጥዎ! 👇
🔗 ሙሉ ትምህርቱን ዩቲዩብ ላይ ይመልከቱ
https://youtu.be/OUf0zJ_zT_s?si=CnhIsO9pLhTn5_28

መደበኛ ፕሮግራሞቻችን ፤- ዘወትር እሁድ ከ4:00 - 6:00 የአምልኮ አገልግሎት .... ማክሰኞ ከ11:3...

ማክሰኞ ምሽት ድንቅ የፀሎት እና የአምልኮ አገልግሎት 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇“ኢየሱስ በምድረ በዳ በዲያብሎስ ሲፈተን "እንዲህ ተብሎ ተጽፏል" እያለ በቃሉ አሸነፈው። ዛሬ አንተም ፈተና ሲ...
19/08/2026

ማክሰኞ ምሽት ድንቅ የፀሎት እና የአምልኮ አገልግሎት
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
“ኢየሱስ በምድረ በዳ በዲያብሎስ ሲፈተን "እንዲህ ተብሎ ተጽፏል" እያለ በቃሉ አሸነፈው። ዛሬ አንተም ፈተና ሲጸናብህ የምታሸንፈው በራስህ ጉልበት አይደለም ፤ ዓይንህን በኢየሱስ ላይ አድርግና ቃሉን እንደ ሰይፍ ተጠቀምበት። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በምድረ በዳ ድል እንዳደረገ ሁሉ አንተም በስሙና በቃሉ ቆመህ ይህንን ፈተና ድል ንሳው!” ፓስተር አማረ ተፈሪ Amare Teferi


ቪክትሪ የክረምት ካምፕ VICTORY WINTER CAMP የልጆች የመፅሀፍ ቅዱስ ትምህርት .... የጨዋታ ክፍለጊዜ
19/08/2026

ቪክትሪ የክረምት ካምፕ VICTORY WINTER CAMP የልጆች የመፅሀፍ ቅዱስ ትምህርት .... የጨዋታ ክፍለጊዜ

18/08/2026

ልጆች ምን ተማርን? .......ቪክትሪ የክረምት ካምፕ VICTORY WINTER CAMP የልጆች የመፅሀፍ ቅዱስ ትምህርት

ዛሬ ምሽት በሚኖረን ልዩ የአምልኮ እና የፀሎት አገልግሎት ላይ በመገኝት ፀጋን ይካፈሉ ዘንድ ተጋብዘዋል። አድራሻችንን ይህንን የጎግል ካርታ መስፈንጠሪያን በመጫን ያገኙታል https://map...
18/08/2026

ዛሬ ምሽት በሚኖረን ልዩ የአምልኮ እና የፀሎት አገልግሎት ላይ በመገኝት ፀጋን ይካፈሉ ዘንድ ተጋብዘዋል።



አድራሻችንን ይህንን የጎግል ካርታ መስፈንጠሪያን በመጫን ያገኙታል https://maps.app.goo.gl/fi3bfRxUVZY4iUPj9?g_st=ic

17/08/2026

We had the absolute joy of catching up with Pastor Jonse, our missionary pastor out in Ola Abadadi. God is doing some amazing things there! The church has grown to 315 members, and it's incredible to see the local youth really stepping up to help lead alongside him. But what absolutely blew us away was what it took for him just to come share this news. He traveled 300 kilometers to see us, and he actually had to walk the first six hours of that trip completely on foot just to reach a road where he could catch a ride. His love for his community and the Gospel is deeply humbling. Please keep Pastor Jonse and this growing branch of our church family in your prayers this week!

ቪክትሪ ፋምሊ ቤተክርስቲያን - Victory Family Church Ethiopia Getinet Teferi

Address

Qore Mekanisa
Addis Ababa
1000

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ቪክትሪ ፋምሊ ቤተክርስቲያን - Victory Family Church Ethiopia posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to ቪክትሪ ፋምሊ ቤተክርስቲያን - Victory Family Church Ethiopia:

Shortcuts

Share