Yohannes kibret cheru

Yohannes kibret cheru 🛑መጠበቅህካልቀረ እግዚአብሔርን ጠብቅ ጠብቀኝ ብሎ የማይቀረዉ እሱ ብቻ ነዉ📞09-25-55-32-02

 #እንኳንለአስተርእዮ ማርያም  ዓመታዊ  ክብረ በዓል በሰላም   አደረሳችሁ 🤲🕯❤✝️  #አስተርእዮ ፦ማለት  መታየት  (መገለጥ )ማለት ነው   ። ቃሉ አስተርእየ ታየ ተገለጠ  ከሚለው  የግ...
28/01/2026

#እንኳንለአስተርእዮ ማርያም ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ 🤲🕯❤
✝️ #አስተርእዮ ፦ማለት መታየት (መገለጥ )ማለት ነው ። ቃሉ አስተርእየ ታየ ተገለጠ ከሚለው የግዕዝ ግሥ የተገኘ ነው ። ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በገባው ቃል ኪዳን መሠረት ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ተወልዶ በሥጋ የተገለጠበት (የታየበት ) ነው ።

✝️አንድም ፦ በዮርዳኖስ ምስጢረ ሥላሴ (ሦስትነቱ) የተገለጠበት ወቅት በመሆኑ ከልደት በዓል እስከ ጥር መጨረሻ በሙሉ ዘመነ አስተርእዮ በመባል ይታወቃል ። የእመቤታችን በዓል ዕረፍት በዘመነ አስተርእዮ ውስጥ ስለ ሚከበር #አስተርእዮ ማርያም ተብሏል።

ከበዓሉ ረድኤት በረከት ያሳትፈን 🙏 የእመቤታችን አማላጅነቷ አይለየን አሜን 🤲🕯🕯❤

 #አስተርእዮ ማርያምእንኳን ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም በዓለ ዕረፍት አደረሰን፤አደረሳችሁ!!! በመ/ር ጌታቸው በቀለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በዚህ ምድር ፷፬ ዓመት ኖራ ...
28/01/2026

#አስተርእዮ ማርያም
እንኳን ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም በዓለ ዕረፍት አደረሰን፤አደረሳችሁ!!!
በመ/ር ጌታቸው በቀለ
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በዚህ ምድር ፷፬ ዓመት ኖራ ያረፈችው ጥር ፳፩ ቀን ነው፤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንም የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ዕረፍት በማሰብ በዓሉን በታላቅ ድምቀት ታከብራለች፡፡ የበዓሉን ታሪክ እንደሚከተለው እንመለከታለን፡፡
አስተርእዮ
አስተርእዮ ማለት መታየት፣ መገለጥ ማለት ነው። ቃሉ አስተርአየ ታየ፣ ተገለጠ ከሚለው የግዕዝ ግሥ የተገኘ ነው /ኪዳነ ወልድ ክፍሌ(1948)፡፡ መጽሐፈ ሰዋስው ወግስ ወመዝገበ ቃላት ሐዲስ፡፡/ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በገባው ቃል ኪዳን መሠረት በሥጋ የተገለጠበት(የታየበት)፣ አንድነት ሦስትነቱም የተገለጠበት ወቅት በመሆኑ ከልደት በዓል እስከ ጥር መጨረሻ ድረስ ዘመነ አስተርእዮ በመባል ይታወቃል። የእመቤታችን በዓለ ዕረፍት “በዘመነ አስተርእዮ” ውስጥ ስለሚከበር “አስተርእዮ ማርያም” ተብሏል።
ወላዲተ አምላክ የአምላክ እናት ብትሆንም ሞተ ሥጋ ለሁሉም ዕጣ ፈንታ በመሆኑ በስድሳ አራት ዓመቷ ከሞት ወደ ሕይወት፣ ከመከራ ወደ ደስታ የተሸጋገረችበት ዕለት ነው፡፡ ታላቁ የቤተክርስቲያን አባት ቅዱስ ያሬድም “ሞትሰ ለመዋቲ ይደሉ ሞታ ለማርያም የአጽብ ለኩሉ፤ ሞት ለማናኛቸውም ሰው ሁሉ የተገባ ነው የማርያም ሞት ግን ሁሉን ያስደንቃል፡፡” በማለት አደነቀ፡፡ በመሆኑም በዓሉ የወላዲተ አምላክ በዓለ ዕረፍት ከመሆኑ የተነሣ ታላቅ በረከት የሚያስገኝ ስለሆነ በየዓመቱ ይከበራል፡፡
ሞት በጥር …
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በዚህ ዓለም የኖረቸው ፷፬ ዓመት ነው፡፡ ፷፬ ዓመት የትና እንዴት እንዳሳለፈች? በጥቂቱ እናያለን፡፡ የአምላክ እናት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በዚህ ምድር ላይ ፷፬ ዓመታትን ከኖረች በኋላ በክብር ዐርፋለች፡፡እመ ብርሃን በእናት ከአባቷ ቤት ሦስት ዓመት፣ በቤተ መቅደስ ፲፪ ዓመት፣ ከተወዳጁ ልጅዋ ጋር ፴፫ ዓመት ከሦስት ወር፣ ከጌታችን ዕርገት በኋላ ከወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ ጋር ፲፭ ዓመት፣ በድምሩ ፷፬ ዓመት በዚህ በኃላፊው ዓለም ኖራ ጥር ፳፩ ቀን በ፵፱ ዓመተ ምሕረት በክብር ዐርፋለች፡፡
የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ሞትና ትንሣኤ አባቶቻችን በጾመ ፍልሰታ ውዳሴ ማርያም ቅዳሴ ማርያም ሲተረጉሙ የዕረፍቷን ነገር እንዲህ ብለው ይተርካሉ።
“የዕረፍቷስ ነገር እንደምን ነው?” ቢሉ ስድሳ አራት ዓመት በዚህ ዓለም ኖራ ጥር ፳፩ በእሑድ ቀን ጌታ እልፍ አዕላፋት መላእክቱን አስከትሎ መጥቶ እናቴ ሆይ ከዚህ ዓለም ድካም ላሳርፍሽ መጣሁ አላት። ልጄ ሰማይና ምድር የማይወስኑህ ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን በማሕፀኔ ተሸክሜ በድንግልና ወልጄህ እሞታለሁን? አለችው። በሲዖል የሚሰቃዩ ነፍሳትን አሳይቶ እናቴ ሆይ ሞትሽ ለእነዚህ ቤዛ ይሆንላቸዋል አላት። እሊህን ከማርክልኝስ ይሁን አለችው። ቅድስት ሥጋዋን ከቅዱስ ነፍሷ ለይቶ በቃለ አቅርንት በዝማሬ መላእክት አሳረጋት። ደቀ መዛሙርቱንም ከያሉበት በደመና ጠቅሶ ካለችበት አድርሶ እመቤታችሁን ስጋዋን በክብር አሳርፉ አላቸው። ሐዋርያት በአጎበር አድርገው ወደ ጌቴሴማኒ ይዘው ሲሄዱ አይሁድ “ቀድሞ ልጇን ተነሳ ዐረገ እያሉ ሲያውኩን ይኖራሉ አሁን ደግሞ እሷን ተነሣች ዐረገች እያሉ ሊያውኩን አይደለምን በእሳት እናቃጥላታለን” ብለው በክፋት ተነሡ። ታውፋንያ የሚባል አይሁዳዊ ተራምዶ አጎበሩን ጨበጠው። መልአክ መጥቶ በሰይፍ ሁለት እጁን ቀጣው ከአጎበሩ ተንጠልጥሎ ቀረ። በድያለሁ ማሪኝ ብሎ ቢማጸናት እጁ ተመልሶለታል። ከዚህ በኋላ ዮሐንስን ጨምሮ በደመና ነጥቆ ከገነት አግብቶ ከዕፀ ሕይወት ሥር አኖራት። ኋላም በልጇ ኃይልና ሥልጣን ከሞት እንድትነሣና እንድታርግ አድርጓታል፡፡ ዕረፍቷም በመልክአ ማርያም “ያለመጨነቅና ያለፃእር ከሥጋዋ ለተለየች ነፍስሽ ሰላምታ ይገባል” እንደተባለው ያለመጨነቅና ያለፃእር ነበር፡፡
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሕይወቷ ከሕፃንነቷ ጀምሮ በብዙ ፈተና የተሞላ ነበር፡፡ በተለይም ስምኦን አረጋዊ በቤተመቅደስ “በነፍስሽ ሰይፍ ያልፋል” ብሎ እንደተነበየላት /ሉቃ.፪፥፴፭/ በግብፅ ስደት፣ በቀራንዮ ስቅለት፣ በአይሁድ ክፋት የደረሰባት መከራና ኀዘን አብቅቶ ወደ ዘላለም ደስታ ትገባ ዘንድ ሞትን ቀምሳለች፡፡ ጠቢቡ ሰሎሞን “ወዳጄ ሆይ ተነሺ፤ ውበቴ ሆይ ነዪ፡፡ እነሆ ክረምት አለፈ፤ ዝናሙም አልፎ ሔደ፡፡ አበቦች በምድር ላይ ተገለጡ፤ የዜማም ጊዜ ደረሰ፡፡ የቍርዬም ቃል በምድር ላይ ተሰማ” /መኃ.፪፥፲-፲፬/ እንዳለ ኀዘኗ ያልፍ ዘንድ ወደ ዘላለም ደስታም ትገባ ዘንድ ዐርፋለች፡፡ ሊቁ ቅዱስ ያሬድ “ከሞት ወደ ሕይወት፣ ከክፉ ዓለም ወደ በጎ ዓለም አሸጋግሯታልና” ያለውም ይህንን ያመለክታል፡፡
ነገረ ክርስቶስ በነገረ ማርያም
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሊቃውንት ነገረ ክርስቶስን (Christology) ከነገረ ማርያም (Mariology) ጋር ያለውን ጥልቅ ምስጢር በመረዳታቸው ምሥጢረ ሥጋዌን ከማስተማራቸው አስቀድሞ ነገረ ማርያምን በጥልቀት ይማሩን ያስተምሩ እንደነበር እናስተውላለን፡፡ ሊቃውንቱ በትምህርታቸው ሁሉ ነገረ ማርያም የሃይማኖት ክፍል (Dogma) መሆኑን አብራርተው ገልጠውታል፡፡ ምክንያቱ ቅድመ ዓለም ከአብ ያለ እናት የተወለደው አካላዊ ቃል 5500 ዘመን ሲፈጸም ያለ አባት ከቅድስት ድንግል ማርያም በኅቱም ድንግልና ተፀንሶ በኅቱም ድንግልና ተወለደ፡፡ ጥንታዊት፣ ሐዋርያዊት የሆነችው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያናችን ይህን ይዛ በዘወትር ሥርዐተ አምልኮቷ ጊዜ በምትገለገልባቸው የተለያዩ የጸሎትና የቅዳስያት መጻሕፍት ሁሉ የነገረ ማርያም አስተምህሮዋን በስፋትና በጥልቀት ትመሰክራለች፡፡

የእመቤታችን ክብሯ ከመላእክትና ከደቂቀ አዳም ከፍ ያለ፤ የባሕርይ አምላክ አካላዊ ቃል ክርስቶስን በኅቱም ድንግልና ፀንሳ በኅቱም ድንግልና የወለደች በመሆኗ ወላዲተ አምላክ (Theotokos – Mother of God)፣ እመ እግዚአብሔር ጸባኦት፣ እመ ብርሃን፣ ማኅደረ መለኮት እያለች ታስተምራለች፡፡ በሥጋዋ በኅሊናዋ ድንግል በክልኤ የተባለች ቅድስት ድንግል ማርያም ቅድመ ፀኒስ ቅድመ ወሊድ፣ ጊዜ ፀኒስ ጊዜ ወሊድ፣ ድኅረ ፀኒስ ድኅረ ወሊድ ጽንዕት ናት፡፡ በመሆኑም አምላክን ስትወልደው ማኅተመ ድንግልናዋ አለመለወጡ አምላክም ሰው ሲሆን ባሕርየ መለኮቱ ላለመለወጡ፣ ዳግመኛም “ድንግል ወእም” ስትባል መኖሯ “አምላክ ወሰብእ” ሲባል የመኖሩን ይህን ታላቅ የሥጋዌ ምሥጢር ያወቅንባት የተረዳንባት መሆኗን ቅድስት ቤተክርስቲያን ታስተምረናለች፡፡

እንደ ማጠቃለያ
በአጠቃላይ ዘመነ አስተርዮ የአምላክ በሥጋ የመገለጡን ዘመን የሚዘክርበት ዘመን ነው።ይሄውም በቤተልሔም መወለዱ እና በጥምቀቱ ደግሞ አንድነቱን እና ሦስትነቱን የገለጠበት ዘመን በመሆኑ ነው።ይህ የተገለጠው ሥጋ ከእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነስቶ በተዋሕዶ ሰው በመሆን ነው። በዘመነ አስተርዮ የጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መገለጥ አንድነትና ሦስትነት የተገለጠበት ብቻም ሳይሆን ጥር ፳፩ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የዕረፍት ቀን በመሆኑ “አስተርዮ ማርያም” በማለት በዓልን አናከብራለን፡፡
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በዚህ ምድር ላይ ፷፬ ዓመታትን ከኖረች በኋላ የዚህን ዓለም መከራና ሥቃይ ለሰዎች ድኅነት የተቀበለችው ክብርት እናታችን በሥጋ ብትሞትም እንደ ልጇ ደግሞ በትንሣኤዋ ተነሥታለች፡፡ ክርስቲያኖችም ይህንን በዓል ልናከብር እንደሚገባ ቅድስት ቤተክርስቲያናችን ሥርዐት ሠርታልናለች፡፡ በዓሉን የምናከብረውም የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ከዚህ ዓለም ድካም ማረፍ በማዘከር ብቻ ሳይሆን አማላጅነቷና ተረዳኢነቷን በማሰብና ተስፋ በማድረግ ነው፡፡ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ልበ አምላክ ክቡር ዳዊት በመዝሙር፣ ቅዱስ ኤፍሬም በውዳሴ፣ አባ ሕርያቆስ በቅዳሴ፣ አባ ጊዮርጊስ በሰዓታት እንዳመሰገኗት ሁሉ፤ ሊቁ ቅዱስ ኤፍሬም ቅድስት ድንግል ማርያምን በሕይወተ ሥጋ በኖረችበት ዘመን ልክ ውዳሴ ማርያምን በ፷፬ አንቀጽ ከፍሎ ፷፬ ጊዜ ሰአሊ ለነ ቅድስት ብለን እንድናመሰግናት አድርጓል፡፡
በዚህ ዓለም በአካለ ሥጋ ያሉ ሰዎችን ልደት በባህላዊ መንገድ ስናከብር በመወለዳቸው ደስ ይላቸው ዘንድ አብረን በመደሰት ነው፡፡ በሕይወተ ሥጋ የተለዩንን ዘመዶቻችንን ስናስብ ደግሞ “ነፍስ ይማር” እያልን በመጸለይ ነው፡፡ የቅዱሳንን እና የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ልደትንና ዕረፍትን ስናስብ ግን እነርሱን እያመሰገንን፣ ተጋድሏቸውን እያሰብን፣ ያከበራቸውን አምላክ እያከበርን፣ ክብራቸውንም እያደነቅን፣ በረከታቸው፣ ረድኤታቸው፣ አማላጅነታቸው ይደርሰን ዘንድ እየተማጸንን ነው፡፡ የእመቤታችንንም ዕረፍት ስናከብር ይህንን እያስተዋልን ሊሆን ይገባል፡፡
የእግዚአብሔር ቸርነት የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት አይለየን፡፡አሜን፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር፡፡
ዋቤ መጻሕፍት
✍️ መጽሐፍ ቅዱስ
✍️ መጽሐፈ ድጓ
✍️ ነገረ ማርያም
✍️ መጽሐፈ ስንክሳር
✍️ ውዳሴና ቅዳሴ ማርያም ትርጓሜ
✍️ መጽሐፈ ሰዋስው ወግስ ወመዝገበ ቃላት ሐዲስ
✍️ መልክአ ማርያም
✍️ ወላዲተ አምላክ በመጽሐፍ ቅዱስ
✍️ ኆኅተ ስብከት ዘቅዱስ ያሬድ ቅጽ አንድ

  የስሙ ትርጓሜ ሚካኤል ማለት ቃሉ የዕብራይስጥ ሲኾን ሚ- ማለት “ማን”፤ ካ- “እንደ”፤ ኤል- “አምላክ” ማለት ነውና  #ሚካኤል ማለት “ ” ( ) ማለት ነው፡፡መልአክ የሚለው ቃል የግእ...
19/01/2026

የስሙ ትርጓሜ ሚካኤል ማለት ቃሉ የዕብራይስጥ ሲኾን ሚ- ማለት “ማን”፤ ካ- “እንደ”፤ ኤል- “አምላክ” ማለት ነውና #ሚካኤል ማለት “ ” ( ) ማለት ነው፡፡

መልአክ የሚለው ቃል የግእዝ ቃል ሲኾን “ለአከ” ማለት (ላከ) ማለት ነው፤ ስለዚኽ መልአክ ማለት መልእክተኛ ማለት ነው፤ ይኸውም ሰው የጸለየውን ጸሎት ያቀረበውን መሥዋዕት ወደ እግዚአብሔር የሚያቀርቡ የእግዚአብሔርን ምሕረት ወደ ሰው የሚያመላልሱ የሚላኩ ስለኾነ የተሰጣቸው ሥያሜ ነው፡፡

ልዑል እግዚአብሔር ሰባቱን ሰማያት ከፈጠረ በኋላ በዚያው በዕለተ እሑድ መላእክትን “እምኀበ አልቦ ኀበ ቦ” (ካለመኖር ወደ መኖር) ማእምራን (ዐዋቂዎች) ለባውያን (አስተዋዮች) አድርጎ ፈጥሯቸዋል፡፡ ከነዚኽ መላእክት ውስጥ አንደኛውና የመላእክት አለቃ የኾነው ቅዱስ ሚካኤል ነው፡፡

ቅዱስ ሚካኤል የሚመራቸው ነገደ ኀይላት የሚባሉ በኢዮር ሰማይ የሚኖሩ መላእክትን ነው፤ ሊቁ ቅዱስ ኤጲፋንዮስም በሥነ ፍጥረት መጽሐፉ ላይ “ወለራብዕ ጾታ ዐሠርቱ ስሞሙ ኀይላት ወሊቆሙ ሚካኤል ወአንበሮሙ በራብዕ ሰማይ” ይላል አራተኛው ዐሥሩን ነገድ ስማቸውን ኀይላት ሲላቸው እነዚኽም ባለሰይፍ ሲኾኑ የእግዚአብሔርን ወዳጆች ሲጠብቁ ጠላቶቹን ይቀጣሉ፤ የእነዚኽ ነገደ መላእክት አለቃቸው ቅዱስ ሚካኤል ሲኾን በኢዮር በአራተኛው ከተማ አስፍሯቸዋል እንዲል፡፡

ሳጥናኤል “እኔ ፈጣሪ ነኝ” ብሎ የስሕተት ንግግርን በተናገረ ጊዜ አስቀድሞ ሰራዊቱን በመያዝ ከነገደ ዲያብሎስ ጋር የተዋጋ መልአክ ነውና፤ ዮሐንስም ስለ ቅዱስ ሚካኤል ኀያልነት በራእ ፲፪፥፯-፱ ላይ፡- “በሰማይም ሰልፍ ኾነ፤ ሚካኤልና መላእክቱ ዘንዶውን ተዋጉ፤ ዘንዶውም ከመላእክቱ ጋር ተዋጋ አልቻላቸውምም ከዚያም ወዲያ በሰማይ ስፍራ አልተገኘላቸውም ዓለሙንም ኹሉ የሚያስተው ዲያብሎስና ሰይጣን የሚባለው ታላቁ ዘንዶ ርሱም የቀደመው እባብ ተጣለ፤ ወደ ምድር ተጣለ መላእክቱም ከርሱ ጋር ተጣሉ” በማለት ዲያብሎስን የተፋለመ መልአክ መኾኑን ገልጾታል፤ በዚኽም “መልአከ ኀይል” ተብሏል (ዳን ፲፥፲፫፤ ፲፥፳፩፤ ፲፪፥፩)፡፡

በመጽሐፈ ሔኖክ ምዕራፍ 20 ላይ እንደምናነበው ከመላእክት በተለየ መልኩ "አካዕ" የሚለው ስመ አምላክ በእጁ ላይ ቀርጾለታል። ደራሲውም "ሰላም ለእራኅከ ስመ መሐላ ዘጸበጠ" (የመሐላ ስምን ለጨበጠ መዳፍኽ ሰላምታ ይገባል) በማለት ያወድሰዋል።

የ99ኙ ነገደ መላእክት አለቃ ስለኾነው ስለ ቅዱስ ሚካኤል ክብር፣ ውበት፣ ምልጃ ማሕቶተ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ያሬድ በመጽሐፈ ድጓው እንዲኽ ይላል፡-
ስለ ቅዱስ ሚካኤል የመላእክት አለቃነቱ ቅዱስ ያሬድ እንዲኽ ይለዋል፡-
“ክብረ ሚካኤል ናሁ ተዐውቀ
በትሕትናሁ ዐብየ ወልሕቀ
ዲበ አእላፍ ዘተሰምየ ሊቀ
ዘይትዐፀፍ መብረቀ ይተነብል ጽድቀ”
(የሚካኤል ክብረ እነሆ አኹን ታወቀ፤ በትሕናውም ፈጽሞ ላቀ ከፍ ከፍ አለ፤ በአእላፍ ነገደ መላእክት ላይ አለቃን የተባለ መብረቅን የሚጐናፀፍ ርሱ ጽድቅን ይለምናል) ይላል።

ኃይላት የተባሉት መላእክትም ሰዎች በዓለም ፈተና ውስጥ ሆነው ሰይጣን ሊያደክማቸው ሲፈልግ ኃይልን ብርታትን የሚሰጡ፣ ይህን ዓለም ንቀው በበርሃ ወድቀው ከሥጋ ምኞት ጋር የሚጋደሉትን፣ በከተማም እየኖሩ መንፈሳዊ ትሩፋት የሚያደርጉትን ደግሞ የሚያበረቱ ናቸው፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ በመልእክቱ ‹እርሱም ወደ ሰማይ ያረገ እግዚአብሔርም ተቀምጦ ያለ መላእክትና ሥልጣናት ኃይላትም የተገዙለት ነው…› ሲል ‹ኃይላት› በማለት ያነሣቸው በኢዮር አራተኛይቷ ከተማ የሚኖሩትን ነው፡፡ በእነዚህ ላይ እግዚአብሔር ቅዱስ ሚካኤልን አለቃቸው አድርጎ ሾሞታል፡፡ (፩ኛጴጥ.፫፥፳፪)

የቅዱስ ሚካኤል ሢመት በነገደ መላእክት ላይ ብቻም ግን አይደለም፤ የእግዚአብሔር ሕዝብ በሆኑት ላይም ጭምር ነው፡፡ ኃያሉ መልአክ ቅዱስ ሚካኤል የስሙ ትርጓሜ በዕብራይስጥ ‹‹እንደ እግዚአብሔር ያለ ማን ነው!›› ማለት እንደሆነ ቅዱሳት መጻሕፍት ይጠቅሳሉ፤ አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ በመዝገበ ቃላት መጽሐፋቸው ላይ እንዳሰፈሩት ደግሞ የስሙን ፊደላት በመተንተን እንዲህ ተርጉመውታል፤ ሚ-መኑ፣ ካ-ከመ፣ ኤል-አምላክ፤ ‹‹መኑ ከመ አምላክ፤ እንደ አምላክ ማን ነው!›› (መጽሐፈ ሰዋስው ወግስ ወመዝገበ ቃላት ሐዲስ)

የሰማይ ሠራዊት ሁሉ አለቃቸው ለፍጥረት ሁሉ የሚማልድ ይህ ኃያል መልአክ ቅዱስ ሚካኤል በብሉይ ኪዳን የእግዚአብሔር ሕዝብ የተባሉትን እስራኤል ዘሥጋን ሲረዳና ሲጠብቅ እንደነበረ ተጽፎልን እናገኛለን፡፡ ለምሳሌ መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል ለኢያሱ በኢያሪኮ ምድረ በዳ እንደተገለጠለት ‹‹… ዐይኑን አንሥቶ ተመለከተ፤ እነሆም፥ የተመዘዘ ሰይፍ በእጁ የያዘ ሰው በፊቱ ቆሞ አየ፤ ኢያሱም ወደ እርሱ ቀርቦ፥ “ከእኛ ወገን ወይስ ከጠላቶቻችን ወገን ነህ?” አለው፡፡ እርሱም “እኔ የእግዚአብሔር ሠራዊት አለቃ ነኝ፤ አሁንም ወደ አንተ መጥቼአለሁ፡፡” ሲል ተናግሯል፡፡ (ኢያ.፭፥፲፫)

እግዚአብሔር አምላክ ሕዝበ እስራኤልን ከግብጽ ባርነት ነፃ ሲያወጣቸው ይመራቸው የነበረ መልአክ ቅዱስ ሚካኤል ነበር፡፡ ‹‹ በመንገድህ ይጠብቅህ ዘንድ፥ ወዳዘጋጀሁልህም ስፍራ ያገባህ ዘንድ፥ እነሆ ፥እኔ መልአኬን በፊትህ እልካለሁ›› እንዲል፤ ሹመቱ በእግዚአብሔር ሕዝብ ላይም በመሆኑ ስለ እነርሱ ከእግዚአብሔር ምሕረትን ይለምንላቸው ነበር፡፡ (ዘፀአት.፳፫፥፳)

ነገር ግን ኃጢአት ሲሠሩ እግዚአብሔር ኃጢአተኞችን ይቀጣልና ሕዝቡን ‹‹ራስህን ጠብቅ፤ ስማው፤ እንቢም አትበለው፤ ስሜ በእርሱ ስለሆነ ይቅር አይልምና›› ብሎ አስጠንቅቋቸው ነበር፤ ይህም ቅዱስ ሚካኤል በእግዚአብሔር ሕዝብ ላይ መሾሙን ያስረዳናል፡፡ (ዘፀ.፳፫፥፳፩)

ነቢዩ ዳንኤል በእግዚአብሔር ሕዝብ ላይ ቅዱስ ሚካኤል ስለመሾሙ ሲመሰክር ‹‹በእውነት በመጽሐፍ የተጻፈውን እነግርሃለሁ፤ በዚህም ነገር ከአለቃችሁ ከሚካኤል በቀር የሚረዳኝ ማንም የለም›› ብሎአል፡፡ ስለዚህም ለኢያሱ የተገለጠውና እስራኤላውያንንም የመራው መልአክ ቅዱስ ሚካኤል መሆኑን እንረዳለን፡፡ (ዳን.፲፥፳፩)

የቅዱስ ሚካኤል አማላጅነት በሐዲስ ኪዳንም እንደነበር ይህ ነቢይ በትንቢቱ ‹‹በዚያም ዘመን ስለ ሕዝብህ ልጆች የሚቆመው ታላቁ ሚካኤል ይነሣል›› በማለት ተናግሮለታል፡፡ ስለዚህም ቅዱስ ሚካኤል እኛን ከሰይጣን አሽክላና ወጥመድ ይጠብቀንና በጸሎቱ በእግዚአብሔር ፊት ይቆምልን ዘንድ በእኛም ላይ ሹም ነው፡፡ ምክንያቱም እኛ የእግዚአብሔር ሕዝቦችና የርስቱ ወራሾች ነንና፡፡ (ዳን.፲፪፥፩)

በመጽሐፈ ስንክሳርም ተመዝግቦ እንደምናኘው ቅዱስ ሚካኤል በየወሩ በዐሥራ ሁለት ቀን ለመታሰቢያው በዓል ተሠርቶለታል፤ እርሱ ስለ እኛ የምድሩን ፍሬ ይባርክልን ዘንድ ዝናሙም በጊዜው እንዲወርድልን የወንዙንም ውኃ እንዲመላልን ነፋሱንም የምሕረት ነፋስ እንዲያደርግልን ሁሉንም የተስተካከለ እንዲያደርግልን ወደ እግዚአብሔር በጸሎት ይማልዳልና፡፡ (ስንክሳር ኅዳር ፲፪)

ስለሆነም በኃጢአት ባርነት ተይዘን በችግር እና በመከራ ውስጥ ተዘፍቀን ለምንኖር ሰዎች ስለ ሕዝበ እስራኤል በእግዚአብሔር ፊት የቆመው ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ለእኛም ያማልደንና ተራዳኢ ይሆነን ዘንድ በጸሎት እንማጸነው። አምላካችን እግዚአብሔርም የምሕረት ፊቱን ወደ እኛ በመመለስ በጸብና በጦርነት ምትክ ፍቅርን፣ ሰላምንና መግባባትን፤ በመለያየት ምትክ አንድነትን እንዲሰጠን በቅዱስ ሚካኤል ስም እንለምን።

ድርሳነ ሩፋኤል ላይ ተጽፎ እደምናገኘው 7 ሊቃነ መላዕክት ሲኖሩ አለቃቸው ቅዱስ ሚካኤል ነው ከእግዚአብሔር ዙፋን ስር ትዕዛዝ በወጣ ግዜ ኪሩቤል ተቀብለው ለሱራፌል ያስተላልፋሉ፤ ሱራፌልም ለሚካኤልና ለገብርኤል ለሩፋኤልም ያደርሳሉ፡፡ ሚካኤል ለፍጥረቱ በጎም ይሁን ክፉ ትዕዛዙን ይፈጽሙ ዘንድ መላዕክትን ያዛቸዋል፤ ኪሩቤልና ሱራፌል መላዕክቱም ሁሉ አቤቱ የእጅህን ስራ አታጥፋ እያሉ ቀንና ማታ ይለምናሉ። የመላዕክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ከዲያቢሎስ ጋር በተከራከረ ጊዜ እግዚአብሔር ይገስፅህ አለው እንጂ የስድብን ቃል አልተናገረውም ሲባል ሰምተናል፡፡ ሊቀ ነብያት ሙሴ እጅግ ታዛዥና የዋህ ስለነበርና ከነዓንን ለማየት ወደ ናባው ተራራ ሲወጣ 2 መላዕክት በአረጋውያን ተመስለው መቃብር ሲቆፍሩ ቢያይ ላግዛቹ ብሎ መቆፈሪያውን ተቀበላቸው፡፡

በመጨረሻ “ሰውየው በአንተ ልክ ነውና እስቲ ገብተህ ለካልን” አሉት፡፡ እሱም በየዋህነቱ ጉድጓዱ ውስጥ ገብቶ እንደተኛ እንደ እንቅልፍ አሸልቦት በዚያው ዐረፈ፤ መላዕክቱም ቀበሩት። እስራኤላዊያን ሙሴን እጅግ ስለሚወዱት የሙሴን መቃብር እንደ ጣዖት እንዳያመልኩት እግዚአብሔር የሙሴን መቃብር ሰወረው፤ ነገር ግን ጠላት ዲያቢሎስ ሊያሳያቸው በመነሳቱ ቅዱስ ሚካኤል ተቃወመው፡፡ በመጨረሻም ቅዱስ ሚካኤል ዲያቢሎስን እግዚአብሔር ይገስጽህ ብሎ ከእርሱም ሰወረበት። በሐዋርያው ይሁዳ መልዕክት ቁጥር 8 የሚገኘው ቃል የቅዱስ ሚካኤልን ትዕግስት ያሳያል፡፡ ዳግመኛም አይሁድ ጌታን ሲሰቅሉት መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል በቁጣ ሰይፉን አወጣ፤ ቅዱስ ሚካኤል ግን በአይሁድ ስራ አዝኖ፣ ፈጣሪን ፍጡራን ሲሰቀሉት የትዕግስቱንና የፍቅሩን ብዛት እያየ በአርምሞና በትዕግስት አያቸው ይላል ድርሳኑ።

መላዕክቱ በክንፋቸው የእግዚአብሔር ስም ስለተፃፈበት ህዝቡን ይጠብቃሉ፤ የመላዕክቱን ስም የመጨረሻውን ፊደል ስናይ ኤል ብሎ ይጨርሳል፡፡ ሚካ-ኤል ገብር-ኤል ኡራ-ኤል፡፡ ይህም “ስሜ በሱ ላይ ነውና” እንደሚል የእግዚአብሔር የምህረት ስም ስለሆነና በክንፎቻቸው ስለተፃፉ መላዕክቱ ይጠብቁናል። “በመንገድህ ሁሉ ይጠብቁህ ዘንድ መላእክቱን ስለአንተ ያዛቸዋል፤ እግርህም በድንጋይ እንዳይሰናከል በእጆቻቸው ያነሱሃል” ተብሎም በመዝሙር 90÷11 ተጽፋልና አህዛብን ጭምር ያለጊዜያቸው እንዳይሞቱ መላዕክት ይጠብቋቸዋል!!! ቅዱስ ሚካኤል ሰኔ 12 ቀን ዲያቢሎስን ጥሎ በምትኩ ሊቀ መላዕክት ሆኖ የተሾመበትና አፎምያንም የረዳበት ቀን ስለሆነ በታላቅ ሥርዓት ይከበራል። ህዳር 12 ሕዝበ እስራኤልን በክንፎቹ ጥላ ከበረሃው ፀሐይ ከልሎ ከግብጽ ምድር እየመራና እየጠበቀ ከንዓን ያገባቸው እለት ነው።

በትንቢተ ዳንኤል 10÷13 እና 10÷21 ደግሞ የስሙ ትርጉም እግዚአብሔር ዳኛዬ ነው የተባለው ነብዩ ቅዱስ ዳንኤልም ስለ ቅዱስ ሚካኤል እንዲህ ሲናገር ከዋነኞቹ አለቆች አንዱ ሚካኤል ሊረዳኝ መጣ፣ በተዘጋ ጉድጓድ ሲያጽናናው ደግሞ “ከሚካኤል በቀር የሚያጽናናኝ የለም” አለ፡፡ ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት በመዝሙር 33÷7 “የእግዚአብሔር መልአክ በሚፈሩት ሰዎች ዙሪያ ይሰፍራል ያድናቸውማል” ይለናል፡፡ በዓለም ፍፃሜም ስለህዝቡ የሚቆመው ሚካኤል ይነሳል። በማለትረ በምዕራፍ 12÷1 ጽፎልናል፡፡ በራዕይ 8÷3 “የቅዱሳኑ ፀሎት ከዕጣኑ ጢስ ጋር ከመልአኩ እጅ ወደ እግዚአብሔር ፊት ወጣ” ተብሎ እንደተጻፈውም መላዕክት የቅዱሳኑን ጸሎት ወደ እግዚአብሔር ያሳርጋሉ፡፡

የሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል አማላጅነትና ተራዳኢነት አይለየን፤ አሜን፡፡

ቅዱስ ሚካኤልን ጨምሮ እነዚኽ ቅዱሳን መላእክት ሰው የጸለየውን ጸሎት ያቀረበውን መሥዋዕት ቅድመ እግዚአብሔር በማድረስ የእግዚአብሔርን ምሕረት ወደ ሰው በማምጣት ሰውን ከአምላካቸው ጋር በማማለድ ጸንተው ያሉ እንደኾኑ በብዙ ሥፍራ ላይ ተዘርዝሯል፡- ለምሳሌ ያኽል ዘፍ 48፥15፤ ዘጸ 23፥20፤ መሳ 6፥11፤ ኢዮ 33፥23፤ መዝ 33፥7፤ 88፥6፤ 90፥11፤ 1ነገ 19፥5፤ 2ነገ 6፥15፤ ዳን 3፥17፤ 4፥13፤ 8፥15-19፤ ዘካ 1፥12፤ ማቴ 18፥10፤ ሉቃ 1፥19፤ 13፥6-9፤ 15፥7፤ ዮሐ 20፥11፤ የሐዋ 12፥6፤ ዕብ 1፥14፤ ራእ 8፥3-4ን ይመልከቱ)፡፡

የመላእክት አለቃ የቅዱስ ሚካኤል በረከት ይደርብን።

 #ጥምቀት♥ #ያመነ የተጠመቀ ይድናል ያላመነ ያልተጠመቀ ግን ይፈረድበታል ማር 16 ÷16አንድ ጌታ አንድ ሀይማኖት አንድት ጥምቀት ኤፌ 4-5🙏በዚያ ወራትም ኢየሱስ ከገሊላ ናዝሬት መጥቶ ከዮ...
19/01/2026

#ጥምቀት♥
#ያመነ የተጠመቀ ይድናል ያላመነ ያልተጠመቀ ግን ይፈረድበታል ማር 16 ÷16
አንድ ጌታ አንድ ሀይማኖት አንድት ጥምቀት ኤፌ 4-5🙏

በዚያ ወራትም ኢየሱስ ከገሊላ ናዝሬት መጥቶ ከዮሐንስ በዮርዳኖስ ወንዝ ተጠመቀ (ማር 1÷9)

አንድ ጌታ አንድ ሃይማኖት አንዲት ጥምቀት (ኤፌ 4÷5)

በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው አለ፡፡ (ማቴ 3:17)

እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሠላም በጤና በደስታና በፍቅር አደርሳችሁ መልካም የጥምቀት በዓል ይሁንላችሁ ።

 #እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሳችሁ!
19/01/2026

#እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሳችሁ!

25/12/2025

#እኔግንእላለሁሁሉምበህግናበስርዓት ብናደርጋቸው መልካም ነው እግዚአብሔርም የህግና የስርዓት አምላክነው ልማድና ዘፈቀደ ቢቀር እላለሁ!!

25/12/2025

#እኔግንየምለው ቅ/ሲኖዶዮስ አጥማቂነን እያሉ የቤተክርስቲያኒቱን ክብር ያዋረዱ ''ነጋደዎችን ለምን አያስቆምም...?

25/12/2025

#እኔ ግን የምለው ቅ/ሲኖዶዮስ አጥማቂነን እያሉ የቤተክርስቲያኒቱን ክብር ያዋረዱ ''ነጋደዎችን ለምን አያስቆምም...?

25/12/2025

#እኔ ግን የምለው ቅ/ሲኖዶዮስ አጥማቂነን እያሉ የቤተክርስቲያኒቱን ክብር ያዋረዱ ''ነጋደዎችን'' ለምን አያስቆምም...?

Address

Addisababa
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Yohannes kibret cheru posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share