ምንተ ንግበር-ዘዮቶር

ምንተ ንግበር-ዘዮቶር ይህ ገጽ ስለ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ወቅታዊ ?

የመርሐ ግብር ማሳሰቢያርእሰ ነገር፡-   ማኅበረ ዮቶርና አነጋጋሪ የአቋም መግለጫው  ከአመራሮቹ አንደበት - በወሣኝ ወቅት ወሣኝ ዓላማ እንግዳ፡-   ዲያቆን የበበ ዓለሙ    ይታገሱ ሀብተ ...
27/01/2022

የመርሐ ግብር ማሳሰቢያ

ርእሰ ነገር፡- ማኅበረ ዮቶርና አነጋጋሪ የአቋም መግለጫው ከአመራሮቹ አንደበት - በወሣኝ ወቅት ወሣኝ ዓላማ

እንግዳ፡- ዲያቆን የበበ ዓለሙ
ይታገሱ ሀብተ ወልድ

ቀን፡- ሐሙስ፡- ጥር ፲፱ - ፳፻፲፬ ዓ.ም.

ሠዓት፡- ከታች ያለው መጥቀሻ (link) ሊጀመር ስንት ሠዓት ወይም ደቂቃ እንደቀረው ይገልጽልዎታል፡፡ እስከዚያው እያዛመቱ ይጠብቁን!

https://youtu.be/btC0rkIv3C0

ጽዋዕ ዘሀገር ዓባይ ኢትዮጵያ

YouTube
ማኅበረ ዮቶርና አነጋጋሪ የአቋም መግለጫው - ከአመራሮቹ አንደበት - በወሣኝ ወቅት ወሣኝ ዓላማ
, , 'e

, , 'e

24/01/2022
ውድ ቤተሰቦቻችን ሁሌም እንደምንለው የምንወያየው ለመወያየት ብቻ ሳይሆን ለተግባር ነው። ትግባር የሚጀመረው ቅድሚያ በውይይት ነው። ያለበለዚያ የጨበሬ ተስካር ነው የሚሆነው። ሁሉም እኔ ልናገ...
13/05/2021

ውድ ቤተሰቦቻችን

ሁሌም እንደምንለው የምንወያየው ለመወያየት ብቻ ሳይሆን ለተግባር ነው። ትግባር የሚጀመረው ቅድሚያ በውይይት ነው። ያለበለዚያ የጨበሬ ተስካር ነው የሚሆነው። ሁሉም እኔ ልናገር፣ እኔ የምለውን ብቻ ስሙ ማለትን ያስከትላልና። እኛ ግን የምንወያየው በሕብረት ሆነን እንወያያለን እንዲሁም ውይይታችን እንተገብራለን።

በሚዲያ ዘርፍ የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ድምጽ ለማጥፋት በይፋ የተንቀሳቀሰውን ኢሳት የቴሌ ቪዥን ጣቢያን በቅድሚያ ተቃውሟችንን በመግለጽ እንዲሁም ለዚህ የሚዲያ ተቋም የሚደረጉ ማንኛውም ድጋፍ እንዳይደረግ ማድረግ።

ይበልጥ በውጪ ሀገር ለሚኖሩ ኦርቶዶክሳዊያን የቤተ ክርስቲያንን ድምጽ ለማፈን በአላማ እየሰራ ለሚገኘው ኢሳት ምንም አይነት ድጋፍ እንዳያደርጉ ሁላችንም እንጣር።

መልካም ምሽት

ህጻናትን ወደ እኔ ይመጡ ዘንድ አትከልክሏቸውበእውነት የሰው ልጅ ዘላለማዊ ሕይወትን እንዲያገኝ እንደ ህጻን መሆን ይጠበቃል። እንደውም ጌታችንን ሲጠይቁት እንግዲያስ እኛም ዘላለማዊ ሕይወት እ...
12/05/2021

ህጻናትን ወደ እኔ ይመጡ ዘንድ አትከልክሏቸው

በእውነት የሰው ልጅ ዘላለማዊ ሕይወትን እንዲያገኝ እንደ ህጻን መሆን ይጠበቃል። እንደውም ጌታችንን ሲጠይቁት እንግዲያስ እኛም ዘላለማዊ ሕይወት እንድናገኝ ምን እናድርግ ሲሉት ልክ እንደዚህ ህጻን ሁኑ አላቸው።

መቼም አዳም በገነት ሰባት ዓመት ከአራት ወር ከአስር ቀን እንደኖረ ይታወቃል። ነገር ግን የአምላኩን ቃል ባለመጠበቁ ክብሩን አጣ። እንግዲህ በአጭሩ ይህን ክብር ለሁላችንም እስከ ዘለዓለም እንድናገኝ እንደዚህ ህጻን ልጅ ሁኑ ያላቸው። በእውነት ሁላችንም ህጻን ሆነን የመንግስቱ ወራሽ ያድርገን።

ነገር ግን በሥራ ህጻን ሳንሆን በስም ብቻ ህጻን ከሆንን በእውነት ጎርምሰንም፣ አርጅተንም ያው የስም ህጻን ነን።

እውነተኛው ህጻን በሕይወቱ ልምድ ሰለሌለው ፊደልን ሰካክቶ ቃላትን መስርቶ አረፍተ ነገር እስኪሰር ድረስ ብዙ ይገድፋል። ይህ ህጻን ቃላት ቢነጥፉበት ፊደል ቢስት ይበረቱታል እንጅ አይነቅፉትም።

ነገር ግን የስም ህጻን የሆኑ ለአባቶቻቸው ክብር የማይሰጡ ወደ ታች ሊያድጣቸው ሲገባ ወደ ላይ የሚወድቁ የስም ህጻኖች በጭራሽ እኛ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆችን አይወክሉምና ከአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ከጽሐፊ ኃላፊነታቸው በአስቸኳይ እንዲነሱ ምንተ ንግበር ታሳስባለች።

ውድ የምንተ ንግበር ቤተሰቦቻችን እንግዲህ የስም ህጻን የሆኑት አባ ህጻን ከኃላፊነታቸው እንዲነሱ በምናደርገው ጥሪ እንድትሳተፋ ከወዲሁ እናሳስባለን።

ወላዴ አእላፍ የኔታ ጥበቡ ታዬ በአንድ ወቅት ወደ ጢስ አባይ አካባቢ የሚገኙ የአብነት ት/ቤቶችን ለመጎብኘት (ለዶክመንተሪ ስራ) ባቀናንበት ወቅት የሄድንበትን ስራ ጨራርሰን ስንመለስ ጀንብሯ...
01/05/2021

ወላዴ አእላፍ የኔታ ጥበቡ ታዬ

በአንድ ወቅት ወደ ጢስ አባይ አካባቢ የሚገኙ የአብነት ት/ቤቶችን ለመጎብኘት (ለዶክመንተሪ ስራ) ባቀናንበት ወቅት የሄድንበትን ስራ ጨራርሰን ስንመለስ ጀንብሯ እያዘቀዘቅሽ ነበር።

እኛም ወደ ባህር ዳር ሄደን መማደር ስንፋጠን ከመንገዱ ላይ አንድ ከተበላሸ ቅጥቅጥ መኪና የወረዱ አንድ ጥምጣም ያደረጉ እጃቸውን ዘርግተው እባላችሁ አቁሙልኝና ወደ ከተማ ውሰዱኝ በሚል ምልክት ስናይ ለዘወሪው እባክህን ጫናቸው አልነው።

እርሱም እጃቸውን ተመልክቶ ስለነበር ወደ ዳር ሲያቆም ከሾሼሩ አጠገብ የነበረው ወዳጃችን ይምጡ የኔታ አላቸውና ለክብራቸው ስል ወርዶ ሊያስገባቸው ሲል አይሆንም እኔ ከኃላ እሆናለሁ እግዚአብሔር ይስጥልን እንዳይመሽብኝ አድርጋችኃል ብልው ከሹፌሩ ጀርባ ካባለው ወንበር ላይ ሰቀመጡ መኪናው ተበላሽቶ ነው ውይንስ ሌላ ችግር ነው ብሄ ስጠይቃቸው አዎን መጀመሪያ እታች ጎማው ፈንድቶ እቆመን አሁንድ ደግሞ ለሁለተኛ ጊዜ እኳ ነው የሆነ ነገር ሰብሮ ነው የቆመው ብለውን የወረድነው።

እንደው እግዚአብሔር እናንተን ጣለልኝ ብለው ደግመው አመሰገኑው ጨዋታቸውን ቀጠሉንል።

እንደው እዚህ ለአገልግሎት መጥቼ እኮ ነው ይህ መኪና ተበላሽቶ እናንተንም ያስቸገርኳችሁ ሲሉን። አረ ምንም አይደል ምንም አላደርግንም እኛም የመጣነው በዚህ አካባቢ ያሉትን ጉባኤ ቤቶች ለማየት መሆኑን ስንነግራቸው።

በጣም ደስ ብሏቸው ደግመው እግዚአብሔርን አመስግነው እርሳቸውም በተለያዩ ጉባኤ ቤቶች ገብተው የተማሩ ቢሆንም በዛራ ቅዱስ ሚካኤል ከወላዴ አእላፍ የኔታ ጥበቡ ታዬ የተማሩት የሕይወትና የቅኔ ትምህርት ትልቁ ስፍራ እንዳለው ይበልጥ በዛራ ቅዱስ ሚካኤል የቅኔ ጉባኤ ቤት ደቀ መዝሙር በነበሩበት ወቅት የየኔታ ጥበቡ አርድእት (አገልጋይ/ተላላኪ) ስለነበሩ የየኔታን ሕይወት በደንብ የሚያውቅ ቢሆንም በአንድ ወቅት የተፈጠረው ክስተት ግን የየኔታን መገር እጅጉን አስገርሞቸው ነበር።

ነገሩ እንዲህ ነው። ያው አርድግት እንደመሆኔ የሚቀምሱትን የምሰራው፣ የሚጠጡትን የማቀርበው፣ የሚለብሱትን የማጥበው እንዲሁም ሌሎች ተግባራትን የምከውነው እኔ በመሆኔ ከለታት በአንድ ቀን ወጥ ሰራሁና ከእንጀራ ጋር አቀረብኩላቸው።

እርሳቸውም የቀረበላቸውን ተመግበው ጨረሱ። እኔም የዚያን ቀን ትንሽ ሆዴን ከሌላው ቀን ሞርሞር አድርጎኝ ነበር ታዲያ ሁሌ እንደማደርገው ከእርሳቸው የተረፈውን የበረከት ምግብ እንደ ሌላው ቀን የመጀመሪያውን ጉርሻ ወደ እፌ ላኩት። አንዴ በጥርሴ እንዳኘኩት እንደ መኪና ተስፈንጥሬ ወደ ውጪ ወጣሁና በአፌ የያዝኩትን ከአጥሩ ጥግ ተፋሁት። አንዴ የቀመስኩበት ምላሴ በአንዴ ነፈረ።

በጣም ደነገጥኩ የኔስ ማላስ ይቆረጥ የኔታን ገደላኳቸው አልኩና አንገቴን ደፍቼ የኔታ ይቅር በሉኝ። ጨው መጨመሬን ረስቼ ደግሜ ደጋግሜ ወጡ ውስጥ ጨው ጨምሬበት ነበር። እኔ አንዴ እኳ ጎርሼ ምላሴ ተንገበገብ። እርስዎ ግን ገደልኳት ስላቸው የመለሱልኝ መልስ እጅጉን ይበልጥ አስደነገጠኝ። ልጄ አትደንግጥ ምንም ጨው አልበዛበትም ለኔ እንደ ሌላው ቀን ነው አሉኝ። ቀስ ባለ ድምጻቸው።

የወላዴ አእላፍ የኔታ ጥበቡ ታዬ በርካታ ሊቃውነት ቤተ ክርስቲያንን ያፈሩ ታላቅ አባት ሲሆን ከእንነዚም ውስጥ በጥቂቱ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ፣ ብፁዕ አቡነ ኤልሣዕ፣ ብፁዕ አቡነ እንድርያስ ፣ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስና ሌሎች ብፁአን አበው ሊቃነ ጳጳሳትን እና ሊቀ ሊቃውንት ዕዝራን ጨምሮ በርካታ ሊቃውንትን ያስተማሩና ለቤተ ክርስቲያን ያፈሩ አባት ናቸው።

የወላዴ አእላፍ የኔታ ጥበቡ ታዬ የቀብር ሥነ ስርዓት አርብ መጋቢት 22 ቀን 2013 ዓ.ም ከ57 ዓመታት በላይ ባስተማሩበት ዛራ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን በታላቅ ክብር ተፈጽሞል።

የአባታችን በረከት ከሁላችንም ጋር ትሁን።

ቡራዩ ለኩ የሚገኘው የቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ላይ በዶዘር ከፍተኛ ግፍ እየደረሰበት ይገኛል።  እንኳንስ አጥሩን ቤተ ክርስቲያንንም አፈርሰዋለሁ ነው የተባለው።በተቀናጀ መልኩ በቅድስት ...
24/03/2021

ቡራዩ ለኩ የሚገኘው የቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ላይ በዶዘር ከፍተኛ ግፍ እየደረሰበት ይገኛል። እንኳንስ አጥሩን ቤተ ክርስቲያንንም አፈርሰዋለሁ ነው የተባለው።

በተቀናጀ መልኩ በቅድስት ቤተ ክርስቲየን ላይ እየተፈጸመ ያለው ሕገ ወጥ ድርጊት በአስቸኳይ እልባት እንዲሰጠውና በቤተ ክርስቲየኑ ላይ የተፈጸመው ሕገ ወጥ የአጥር ማፍረስ ስራ ላይ የተሰማሩ ኃላፊዎች አላግብልብ ስልጣናቸውን በመጠቀም ለፈጸሙት ተግባር ተገቢውን ቅጣት እንዲያገኙና ለደረሰውም ጉዳት ተመጥልጣኝ ካሳ እንዲከፈል ምንተ ንግበር ታሳስባለች።

በዚህ የምርጫ ወቅት እንደዚህ አይነት እኩይ ተግባር መፈጸም ዋጋ የሚያስከፍል መሆኑን ሊታወቅ ይገባል። ድምጻችንን ለቤተ ክርስቲያናችን እንስጥ የምንለው ከጥቂቱ ጉዳት እስከ ከፍተኛ የሕይወት ወጋ እያስከፈለን የምንገኘው በመንግስት መዋቅር ውስጥ የቤተ ክርስቲያን ልጆች በጉልህ ስላልተገኙ የቤተ ክርስቲያን ጉዳት እንዲይልይል ምክንያት ሆኗል።

እርጥብ እንጨት አግኝተው እንዲ ካደረጉ ደረቅማ ቢሆን ምን ሊያደርጉት ነበር። ሕጋዊ የሰነድ ማስረጃ ያለውን ይህን ቤተ ክርስቲያን እንደዚህ መዳፈር ባለበቱን ካልናቁ አጥሩን አይነቀንቁ ነውና ተረቱ የተፈጸመው ተግባር ሕገ ወጥ በመሆኑ በአስቸኳይ እንዲቆም እናሳስባለን።

መረጃው ለሌሎች እንዲደርስ ሼር ያድርጉ።

18/03/2021

አቧራ የጠገበን ምንጣፍ በዱላ የምትመታው አቧራውን ለማራገፍ እንጂ ምንጣፉን ለመጉዳት አይደለም ።
==========================

በሕግ ትምህርት ውስጥ አንድ በጉልህ የሚነሳ ቃል አለ። ይህም ( intention) ሃሳብ የሚለው ቃል ነው። ይህ ቃል በሕግ ሥርአት ውስጥ በዋናነት በወንጀል ሕግ ትልቅ ትርጉም አለው።

ለምሳሌ አንድ ሰው አልሞ አቅዶና ፈቅዶ አብሮ አደጉን ወይም ሌላ ሰውም ቢገድለው የዚህ ሰው (intention) በክፋት ተነሳስቶ በማወቅ የፈጸመው ወንጅል የእስር ጊዜውን እንዲከብድ ያደርግበታል።

ነገር ግን እንኳንስ በእግዚአብሔር አምሳል የተፈጠረን ክብር የሰው ልጅ ይቅርና እጽዋትን ሲቆርጥ የሚሰቀው ባላወቀው፣ ባልገመተው ፍጽም ምንም ሃሳብና ፍላጎት ሳይኖረው የሰው ሕይወት ቢያልፍበት የእስር ጊዜው ይቀንሳል፣ የተለያዩ ጉዳዮች ይታዩለታል።

እንደሚታወቀው ከፊታችን ትልቅ ሀገራዊ እንገብጋቢና እንቅልፍ የማያድተኛ ጉዳይ አለብን። ይህውም ሀገራዊ ምርጫ ነው። በዚህ ታሪካዊና አስፈላጊ ምርጫ ላይ ለመሳተፍ ምን እያሰቡ ይገኛሉ።

ይህ ምርጫ ለኛ ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታዮች በሙሉ ትልቅ ትርጉም ያለው ምርጫ ነው። ባሳለፍነው ጥቂት ዓመታት ውስጥ የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ልጆች ከፖለቲካው ስፍራ በአንድም ሆነ በሌላ ምክንያት በመራቃቸውና ይህንንም የአመራር ስፍራ በከፍተኛ ሁናቴ ቸል በማለታቸው ትላንትና የተከፈለው አላስፈላጊ መስእዋት እንዲከፈልና ምእመናን እንዲታረዱ፣ እንዲሰደዱና እንዲንገላቱ ምክንያት በመሆኑ የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ልዕልና በሰነፎች እንድትመዘን ምክንያት ሆኗል።

ይህም በመሆኑ የአንድ ቀበሌ አስተዳደር የአደባባይ በዓላቷን የሚፈቅድና የሚከለክል እንዲንሆን ከማድረጉ በተጨማሪ የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን አገልግሎት በተደራጀ መልኩ እንዲዳከም የበኩላቸውን እንቅስቃሴ እያደረጉና አገልግሎቶን እንዲጎዱ የተቻላቸውን እያደረጉ ይገኛሉ።

እኛ የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ልጆች ይህንን በግልጽ የተጋረደብንን ክፉ ጥላ ከላያችን ላይ እንዲነሳ ማድረግ የምንችለው አንድም በምርጫ ነውና ይህንን ምርጫ ለኛ ለኦርቶዶክሳውያን ልዩ የሚያደርገው ምክንያት ይህ ነው።

ይህንንም የምናደርገው አቧራ የጠገበን ምንጣፍ በዱላ የምትመታው አቧራውን ለማራገፍ እንጂ ምንጣፉን ለመጉዳት አይደለም እንደሚባለው ሁሉ ማንንም ለመጉዳት ሳይሆን አቧራ ሆነው ከምንጣፉ ላይ የተጣበቁትን ጥቃቅን አቧራዎች በምርጫ ካርዳችን በማራገፍ በቤተ ክርስቲያናችን ላይ የሚያሴሩትን ሴራ እርቆ ለመጣል ነው።

ይህ ምርጫ ለኛ እጅግ ከፍተኛ ዋጋ ያለው በመሆኑ ሁሉም የምርጫ ካርዱን በመውሰድ ድምጹን ለቤተ ክርስቲያን ሊሰጥ ድግ ይላል።

15/03/2021

ስለታም ምላጭ ዛፍ አይቆርጥም ጠንካራ መጥረቢያ ጸጉር አይላጭም።
================================

ብዙ አይነት ምላጭ በገበያ ላይ እናገኛለን። እነዚህ ምላጮች በስም፣ በቅርጽ ወይም በሌላ የምላጭ አይነቶች ቢገኙም ጸጉርና መሰል ነግሮችን ከመቁረጥ፣ ከመላግ፣ ከመቅረጽ የተለየ ሌላ አገልግሎት የሚሰጥ ምላጭ አይገኝም።

ዛሬ አዲስ ምላጭ ነው ያልነው ነገ በተለያዩ ሁኔታ ዶልዱሞ ወይም ዝጎ በመገኘቱ ከቆሻሻ ውስጥ እንዲጣል ምክንያት ይሆናል።

ከእነዚህ ምላጮች ትንሽ ተሽለው የተገኙ እርስ በራሳቸው እየተሳሳሉ የመቁረጫ ጊዚያቸውን በማራዘም ከቆሻሽ መጣያ ስፍራ እንዳይገኙ ይጥራሉ።

ጥረታቸውም ውጤት አምጥቶ ከቆሻሻ ገንዳ ከመጣል ያድናሉ።
እነዚህ ምላጮች አላማቸውን ሳይፈጽሙ ደንዘው ወይም ዝገው ከቆሻሻ መጣያ በጭራሽ አይወድቁም።

እነዚህ ምላጮች በቆይታቸው ጊዜ ከራሳቸው አልፎ ለሌሎች ምላጮች አለመደንዘዝንና አለመዛግን አስተምረው ያልፋሉ። ያልታደሉት ግን ራሳቸው ዝገው ሌሎችን ሊያደነዝዙ ይሞክራሉ።

ታዲያ ነገር የገባቸው የወደፊት ጊዜያቶችን አስቀድመው መገመት የቻሉ ንቁ ምላጮች የሚያዝጋቸውን እርጥበት እንዲሁም ኬሚካል ካጠገባቸው በማራቅ የመላጨት ስራቸው እንዳይታጎል ያደርጋሉ።

እነዚህ ምላጮች ጊዜውን ይዋጁታል። ለስላሳ ጸጉር ሲያጋጥማቸው አንዳይንሸራተት አድርገው ይላጩታል። ከርዳዳም ከሆነ ተጠንቅቀው በብልሀት ያነሱታል። ራሰ በርሃ እንኳን ቢሆን ምላጩን ከጆሮ ግንዱ አጠገብ ያስቀምጡትና ጸጉርህ ካደገ ከጎንህ ነኝ ይሉታል።

እነዚህ ምርጥ ምላጮች የተፈጥሮ ህጋቸው ሲፈጸም ያኔ በክብር ይቀመጣሉ። ይህንንም የሚያደርጉት ግን ጥቂቶች ናቸው።

የእነዚህ ምላጮች በክብር መቀመጥ ለቀጣይ ትውልዶች አብነት እንዲሆኑ ምክንያት ናቸውና።

እነዚህ ልዩ ምላጮች እያንዳንዱን ነገር በንቃት በመከታተል ከውስጥም ከውጪም ያሉትን አላስፈላጉ ጸጉር እየቆረጡ ወይም እየላጩ ያስወግዳሉ።

ይበልጥ የእነዚህ ምላጮች ዋነኛ ተግባራቸው እኔሆን እኔሆን እያሉ ጸጉሮች በሚጨነቁ ጊዜ የቆሸሸውን ወይም ያልተመረጡትን እየቆረጡ ከቆሻሻ ገንዳ ውስጥ እንዲወድቅ ያደርጉታል።

የመጥረቢያም ሥራ ይህ ነው። የደረቀውን፣ የማይበቅለውን፣ ከራሱ አልፎ ሌላውን የሚያቀጭጨውን ከራሱ ተገኝቶ ይቆርጠዋል።

እኛም በቅድሚያ ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን፣ ለምእመናን፣ ለሀገር ቅድሚያ የማይሰጠውን በምርጫ ካርድ ምላጫችን እንቁረጠው። ከራሱ አልፎ ሌሎችንም ስለሚያበላሽ፣ ስለሚያጠፋ።

እኛ ደግሞ እንደ ጅል ዝም ብለን እግዚአብሔር ያውቃል እያልን የምንጠፋ ሞኞች ሳንሆን እንደ ርግብ የዋህ እንደ እባብ ብልጥ በመሆን ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንን፣ ሀገራችንን የምጠብቅ የቅዱሳን አባቶቻችን ልጆች ነን።

ስለዚህ በፍየል ዘምን በግ ሆኖ መገኘት ያለምንም ጥቅም ዝም ብሎ ለመታረድ ነውና።

ድምጻችንን ለቤተ ክርስቲያናችን እንስጥ እንላለን።

ጃንሜዳ አጊጣለች። ማንቂያ ደወል ሥራውን ቀጥሏል። ሕዝቡም በነቂስ ወጥቶ እንዲህ ድምቅ ብሏል። ለቤተ ክርስቲያን የሚጮኹ ኦርቶዶክሳውያን ተሸልመዋል። በስደት ያሉትም ታስበዋል።ሕዝብ የሚፈልገው...
28/02/2021

ጃንሜዳ አጊጣለች። ማንቂያ ደወል ሥራውን ቀጥሏል። ሕዝቡም በነቂስ ወጥቶ እንዲህ ድምቅ ብሏል። ለቤተ ክርስቲያን የሚጮኹ ኦርቶዶክሳውያን ተሸልመዋል። በስደት ያሉትም ታስበዋል።
ሕዝብ የሚፈልገው መሪ ነው፤ ሕዝብ መሪውን ካገኘ ይከተላል። በተለይ ኦርቶዶክሳውያን መሪ የለንም እንጂ ሲኖረንማ እንደኛ የሚመች ማን አለ?
የወጣቶችና ጎልማሶች ኅብረት ከማንቂያ ደወል ኮሚቴ ጋር ይህንን የመሰለ መርሐ ግብር ስላዘጋጃችሁ ምስጋና ይገባችኋል።..ገፃችንን like በማድረግ መረጃዎችን ይጋሩ...

28/02/2021

የኦርቶዶክሳውያን ፌስቡክ በሚዘጋው በፌስቡክ ካምፓኒ ሳይሆን በኢትዮጵያ መንግሥት ነው። የፌስቡክ ካምፓኒ ሓላፊነቱን ለኢትዮጵያ መንግሥት ስለሰጠ የፈለገውን የመዝጋት መብት አለ። የኦርቶዶክሳውያንን የፌስቡክ አካውንት በተመለከተ ከኦርቶዶክሳውያን የተወከሉ ሆድ አደሮች አሉ። እነዚያ ሆድ አደሮች መንግሥት ለወከላቸው የፕሮቴስታንት ቡድኖች ሪፖርት ያቀርባሉ። ወዲያውኑ የፈለጉትን እርምጃ ይወስዳሉ።
በእነዚህ ቡድኖች መሠረት መንግሥትን ከመሳደብ ሌሎች ቤተ እምነቶችን መተቸት እጅግ ያስቆጣል። ግብረ ሰዶምን መንቀፍም ያስቀጣል።

28/02/2021

የጃንሜዳው ጉባኤ የመናፍቃን ነው አትሂዱ!
በዚህ ጉባኤ ከተገኛችሁ የአበውን ትእዛዝ እንደተላለፋችሁ ቁጠሩት!
እኔ በማስተዳድረው ቤተ ክርስቲያን ጉባኤው እንዳይካሄድ ከልክያለሁ!
የጃንሜዳ ወጣት እንደነዱት የሚነዳ በግ ነው!
አባ ነአኲቶ ለአብ.............................
በሽውጥ ምእመንንና ካህናትን በማስፈራራት ሲመዘብር የኖረውና ሰአሊተ ምሕረት ቤተ ክርስቲያንን ርቃኗን ያስቀራት የቀድሞ የሰአሊተ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ፣ በአሁኑ የገነተ ኢየሱስ (41 ኢየሱስ) ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ አባ ነአኲቶ ለአብ አያሌው ምእመናን በጃንሜዳው ጉባኤ እንዳይሄዱ አሳሰቡ። በዛሬው ዕለት በጃንሜዳ በመምህር ምሕረተ አብ በሚዘጋጀው የማንቂያ ደወል ላይ ምእመናን እንዳይገኙ ጥሪ ያቀረቡት አስተዳዳሪው፣ ጉባኤው የመናፍቃን ነው ብለዋል። አክለውም የፈረንሳይ ወጣት እንደነዱት የሚነዳ በግ ነው ሲሉ ዘለፋ ተናግረዋል። የማንቂያ ደወል ከወር በፊት እርሳቸው በሚያስተዳድሩት ቤተ ክርስቲያን መካሄዱ የታወቀ ቢሆንም፣ የዛሬውን ጉባኤ የከለከሉበት ምክንያት አልታወቀም። አማሳኙና ገንዘብ በቃኝ የማይሉት አስተዳዳሪው፣ በፍቅረ ነዋይ ከመለከፋቸው አንፃር በገንዘብ ለመጣባቸው ምሕረትና ርሕራሔ እንደሌላቸው ይነገራል። ከቅዳሴ መልስ ሕዝበ ክርስቲያኑ በተሰበሰበበት ይህንን መልእክት ማስተላለፋቸው፣ በምእመናን ላይ ግርታን ፈጥሯል።

Address

Addis Ababa

Telephone

+251911154589

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ምንተ ንግበር-ዘዮቶር posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to ምንተ ንግበር-ዘዮቶር:

Share