ምስካየ ኅዙናን መድኃኔ ዓለም ገዳም

ምስካየ ኅዙናን መድኃኔ ዓለም ገዳም Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from ምስካየ ኅዙናን መድኃኔ ዓለም ገዳም, Convent and monastery, Addis Ababa.

ከአዲስአበባ ሀገረ ስብከት አጣሪ ኮሚቴ የተሰጠ ማሳሰቢያ፤የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ በአዲስአበባ ሀገረ ስብከት የተከሰተውን የመልካም አስተዳደር ችግር አጣርቶ ከ...
25/08/2026

ከአዲስአበባ ሀገረ ስብከት አጣሪ ኮሚቴ የተሰጠ ማሳሰቢያ፤

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ በአዲስአበባ ሀገረ ስብከት የተከሰተውን የመልካም አስተዳደር ችግር አጣርቶ ከመፍትሔ ሐሳብ ጭምር የሚያቀርብ ኮሚቴ አቋቁሞ ወደ ሥራ እንዲገባ ማድረጉ ይታወቃል።

ይህንን ተከትሎ የተቋቋመው ኮሚቴ መረጃዎችን ለመሰብሰብ፣
ለማደራጀትና ለመተንተን ያስችለው ዘንድ ቀደም ሲል ባደረገው ጥሪ መሠረት መረጃዎችን ማሰባሰብ መጀመሩ ይታወቃል።

ይሁንና አንዳንድ መረጃ ያቀረቡ ሰዎች ከግንቦት 2017 ዓ.ም
እስከ ሐምሌ 2018 ዓ.ም ድረስ ብቻ ያሉ መረጃዎችን መስጠት ሲገባቸው ከሁለት ዓመታት በፊት በሀገረ ስብከቱ በደል ደርሶብናል የሚሉ ጭምር ማስረጃዎቻቸውን እያደረሱን መሆኑን ተመልክተናል።

ስለሆነም አጣሪ ኮሚቴው ከግንቦት 2017 ዓ.ም እስከ ሐምሌ 2018 ዓ.ም ድረስ በደል ደርሶብናል የሚሉ በርካታ ማረጃዎችን እየተቀበለ መሆኑን ከመግለጽ ጋር በቀሪዎቹ ሦስት ቀናት ብቻ ቀረ የምትሉትን ማስረጃ ለኮሚቴው እንድታደርሱ እያስታወቅን ከአርብ ነሐሴ 22 ቀን 2018 ዓ.ም በኋላ የተሰበሰቡትን መረጃዎች በመተንተን ወደ ጭብጥ በመቀየር የጥናቱ ግብዓት የማድረግ ሥራ ብቻ የሚያከናውን ስለሆነ ማስረጃዎችን የማይቀበል መሆኑን ከወዲሁ ይገልጻል።

አጣሪ ኮሚቴው
ነሐሴ19 ቀን 2018 ዓ.ም
አዲስአበባ -ኢትዮጵያ

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ በመሆን ለተመደቡት ለመልአከ ብርሃን  ሰሎሞን በቀለ  በሀገረ ስብከቱ አዳራሽ በደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው ።   ነሐሴ 19 ቀን 2018 ዓ.ም...
25/08/2026

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ በመሆን ለተመደቡት ለመልአከ ብርሃን ሰሎሞን በቀለ በሀገረ ስብከቱ አዳራሽ በደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው ።
ነሐሴ 19 ቀን 2018 ዓ.ም
ምስካየ ኅዙናን መድኃኔ ዓለም ገዳም
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ ከነሐሴ 8 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ በመሆን ለተመደቡት ለመልአከ ብርሃን ሰሎሞን በቀለ አቀባበል ተደረገላቸው ።
በአቀባበሉ ላይ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ የራያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ የደቡብ ምዕራብ ሸዋ እና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፣ብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ የዳውሮ ኮንታ ከንባታና አላባ ጠንባሮ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት መምሪያ ኃላፊዎች የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ልዩ ልዩ ክፍል ኃላፊዎችና ሠራተኞች የክፍላተ ከተማ ኃላፊዎችና ልዩ ልዩ ሠራተኞች የአድባራትና ገዳማት አስተዳዳሪዎችና አገልጋዮች ተገኝተዋል ።
መርሐ ግብሩ በጸሎተ ወንጌል ተጀመረ ሲሆን ለሥራ አስኪያጁ የሥራ ዘመን መመሪያ ይሆን ዘንድ በማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 20 ከቁጥር 26 ጀምሮ ተነቦ ለመርሐ ግብሩ ተስማሚ የሆነ ወረብ በቦሌ ኆኅተ ብርሃን ቅድስት ማርያም ሊቃውንት መዘምራን
ቀርቧል ።
የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ ክቡር መልአከ ብርሃን ሰሎሞን በቀለ የሢመት ደብዴቤ ከተነበበ በኋላ የሀገረ ስብከቱ ክፍል ኃላፊዎች እና የክፍላተ ከተማ ቤተክህነት ሊቃነ ካህናት በጉባኤው ፊት ቀርበው ትውውቅ ተደርጓል ። በሊቃውንትም ቅኔ ተበርክቷል ።
የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ስብከተ ወንጌልን፣ ሰበካ ጉባኤን ፣ሰንበት ትምህርት ቤትን በማደራጀትና በማስፋፋት ፣ ቤተክርስቲያንን ጠብቆ በማስጠበቅ ሁለንተናዊ ልማትን እንዲያጠናክሩ ፣ ሕገ ቤተክርስቲያንን ጠብቀው የመልካም አስተዳደር ችግርና ሙስናን እንዲቀርፉ ኃላፊነት ተሰጥቶአቸዋል።

ክቡር ሊቀ ሊቃውንት ቆሞስ አባ ተ/ሃይማኖት ወልዱ ሰለ ሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ያላቸውን የሥራ ክህሎት በመግለጽ ቤተ ክርስቲያንን አብረን እናሻግራት ማሻገር ባንችል ባለቤት ሆኖ የመሠረታት ክርስቶስ ያሻግራታል እኛ ሰጥመን እንዳንቀር ሲሉ ማስጠንቀቂያ አዘል ምክራቸውን ለግሰዋል።

የቦሌ ኆኅተ ብርሃን ቅድስት ማርያም ተወካይ ክቡር መልአከ ብርሃን ሰሎሞን በደብራችን ዘርፈ ብዙ ሰዋዊ እና የመሠረተ ልማት ተግባሮችን አከናውነዋል በማለት በዝርዝር የሠሯቸውን ሥራዎች አቅርበዋል።

መልአከ ብርሃን ሰሎሞን በቀለ ከቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጣቸውን ኃላፊነት በታማኝነት እንደሚወጡ በሢመቱ ላይ የተነበበውን ዝርዝር መመሪያ በማንሳት አሁን ላይ ሀገረ ስብከቱን የተጋረጡበትን ተግዳሮቶች በጋራ እንቀርፋለን ብለዋል።

ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ በሮሜ 3፣ 11 በመጥቀስ ወንጌል የሰውን ልጅ በኃጢአቱ እንደምትከስ በመጥቀስ ከውድቀታችን በንስሐ ልንመለስ ይገባል ብለዋል።
ብፁዕነታቸው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ጥንታዊነትና ታሪካዊ መሆኗን በመጥቀስ
" ተሿሚው ወንድምና ልጃችን ወደፊት በሚያከናውኗቸው ተግባራት ከብሔርና ከቡድን አሠራር ነጻ የሆነ መዋቅር ቤተክርስቲያንን ብቻ ማዕከል ያደረገ አድሏዊ ያልሆነና እውነተኛ የመንፈስ ቅዱስ ሀሳብን በአሠራር በመዘርጋት የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔና ልዕልና በማክበር የበላይ አካል መመሪያና ለሀገረ ስብከቱ የተሰጠውን ደንብ ጠብቀው በቴክኖሎጂ የታገዘ አሠራር የፋይናንስና ንብረት አስተዳደሩን ግልጽ፣ ዘመናዊና ቁጥጥር የሚደረግበት በማድረግ ሙስናንና ብልሹ አሠራርን ፈጽመው እንደሚያጠፉ ትልቅ ተስፋና አደራ ጭምር ጥለንባቸዋል።"
ብለዋል።
የኢኦተቤ መገናኛ ብዙኀን አገልግሎት ሥርጭት ድርጅት/ EOTC Broadcasting Service Agency/

ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁና ብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ በዓለምገና ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ለ272 ደቀ መዛሙርት ሥልጣነ ክህነት  ሰጡ።  ነሐሴ 17 ቀን 2018 ...
23/08/2026

ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁና ብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ በዓለምገና ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ለ272 ደቀ መዛሙርት ሥልጣነ ክህነት ሰጡ።

ነሐሴ 17 ቀን 2018 ዓ/ም
ምስካየ ኅዙናን መድኃኔ ዓለም ገዳም
በሸገር ከተማ ሀገረ ስብከት፣ በሰበታ ገላን ጉዳና ፉሪ ክፍለ ከተማ ቤተ ክህነት ሥር በሚገኘው በዓለምገና ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ነሐሴ 17 ቀን 2018 ዓ.ም ለ272 ደቀ መዛሙርት ሥልጣነ ክህነት ተሰጠ። በዕለቱም ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ የደቡብን ምዕራብ ሸዋ እና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ፣ በመንበረ ፓትርያርክ ጠ/ቤተ ክህነት የማኅበራት ምዝገባና ክትትል መምሪያ ኃላፊ ፣የራያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ ለ238 ዲያቆናት፣ ለ33 ቅስና እና ለአንድ የቁምስና ሥልጣነ ክህነት ተሰጥቷል።

ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ በዕለቱ ለተሾሙት አዳዲሶች አገልጋዮች ባስተላለፉት አባታዊ መመሪያ የክህነትን ታላቅነትና የማዕረጉን ሰማያዊነት አብራርተዋል፦
Miidiyaa Biyya Lallabaa Shaggar/የሸገር ሀገረ ስብከት ሚዲያ/
ክህነት ምድራዊ ማዕረግ ሳይሆን የሰማያዊው ንጉሥ የአምላካችን አገልግሎት፣ የኃጢአት ሥርየት የሚሰጥበት፣ የሚያስርና የሚፈታ ታላቅ ሰማያዊ ሥልጣን ነው። ሥልጣነ ክህነት ተቀብሎ ለመቀመጥ ሳይሆን እግዚአብሔርንና ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን በቅንነት፣ በታማኝነትና በቅድስና ለማገልገል የተሰጠ አደራ ነው። ቤተ ክርስቲያን ሁልጊዜም የምታገለግል በመሆኗ ተተኪ ትውልድ ያስፈልጋታል። የቀደሙ አባቶቻችን በተመቻቸ ሁኔታ ውስጥ ሳይሆኑ ፈተናዎችን ሁሉ በትዕግሥት አልፈው አደራውን አስረክበውናል፤ እኛም ጊዜያችንን ሳናባክንና መከራውን ሳንፈራ ማገልገል አለብን በማለት አባታዊ አደራና መምሪያ አስተላልፈዋል።

በመቀጠልም ብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ "ጌታ ሆይ ይህን ኃጢአት አትቁጠርባቸው ብሎ በታላቅ ድምፅ ጮኸ" (ሐዋ. 7፥60) የሚለውን ኃይለ ቃል መነሻ በማድረግ ሰፊ አስተምህሮ ሰጥተዋል፦

የቀዳሚ ሰማዕት ቅዱስ እስጢፋኖስ ከመጀመሪያዎቹ ሰባት ዲያቆናት አንዱ የሆነው ቅዱስ እስጢፋኖስ በክርስቶስ በነበረው ፅኑ እምነት ሰማያት ተከፍተው ያየ የሐዲስ ኪዳን የመጀመሪያው ሰማዕት ነው። ዲያቆናትም በቃል ብቻ ሳይሆን በተግባር፣ ክፋትን በመልካም በማሸነፍና ድንጋዩንም ስድቡንም ሳይፈሩ እግዚአብሔርን እያመሰገኑ ማገልገል እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።

የሰማዕታት ደም የቤተ ክርስቲያን ዘርና በረከት በመሆኑ፣ ልብን ለክርስቶስ መስጠትና እምነትን ለአዲሱ ትውልድ በአደራ ማሸጋገር እንደሚገባ አሳስበዋል።

በዚህ ዘመን መንፈሳዊ አባት መሆንና ማገልገል መከራው ብዙ መሆኑን ገልጸው፤ ተያያዥነት የሌላቸውና የሐሰት ዜናዎችን በመልቀቅ ምዕመናንን ለማደናገር ከሚሠሩ መናፍቃዊ አሠራርና ሚዲያዎች ምዕመናን በጥንቃቄ እንዲጠበቁ አሳስበዋል።

ዲያቆን ማለት አገልጋይ፣ ጠባቂና በመቅደስ ውስጥ ከካህናት ጋር በመቆም ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ለምዕመናን የሚያቀርብ የመንፈስ ቅዱስ ንዋይ ነው። ስለሆነም በዛሬው ዕለት ይህንን ሰማያዊ አደራ የተቀበላችሁ ዲያቆናት ሁሉ የተቀበላችሁትን ሰማያዊ ሥልጣን በመጠበቅ ቤተ ክርስቲያንንና ምዕመናንን በቅድስናና በታማኝነት አገልግሉ።

እንደ አባታችን ቅዱስ እስጢፋኖስ እምነታችሁን በተግባር ግለጡ፤ በሚመጣው ፈተናና መከራ ሳትበገሩ ቤተ ክርስቲያንን በቅንነት ጠብቁ።

በስተመጨረሻም ብፁዕነታቸው ባስተላለፉት መልእክት ምዕመናንን በየቋንቋቸው በማስተማርና ከአባቶቻችን የተቀበላችሁትን የእምነት አደራ ሳይበረዝ ለተተኪ ትውልድ በማስተላለፍ የጽድቅ ፍሬ አፍሩ በማለት አባታዊ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።

22/08/2026

Enjoy the videos and music you love, upload original content, and share it all with friends, family, and the world on YouTube.

ከመ ትንሣኤ ወልዳ: እንደ ልጇ ትንሣኤ ተነሣች:ዐረገችየእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም የዕርገቷ መታሰቢያ ክብረ በዓል በለገጣፎ ኆኅተ ገነት ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ካቴድራል ብፁዕ አቡነ ...
22/08/2026

ከመ ትንሣኤ ወልዳ: እንደ ልጇ ትንሣኤ ተነሣች:ዐረገች

የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም የዕርገቷ መታሰቢያ ክብረ በዓል በለገጣፎ ኆኅተ ገነት ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ካቴድራል ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ የሸገር ሀገረ ስብከት እና የደቡብ ምዕራብ ሸዋ ሀገረ ሰብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ የራያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የገዳማት እና አደባራት አስተዳዳሪዎች በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ምዕመናን በተገኙበት እየተከበረ ይገኛል።

የኢኦተቤ መገናኛ ብዙኀን አገልግሎት ሥርጭት ድርጅት/ EOTC Broadcasting Service Agency/

በኢትዮጽጵያ  ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቦተ ክርስቲያን በዩ ዓሙቱ በደመቀ ሁኔታ የሚከበረው የእናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የዕርገቷ በዓል በምስካየ ኅዙናን መድኃኔዓለም ገዳም ሥርዓተ ቅዳሴ  በ...
22/08/2026

በኢትዮጽጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቦተ ክርስቲያን በዩ ዓሙቱ በደመቀ ሁኔታ የሚከበረው የእናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የዕርገቷ በዓል በምስካየ ኅዙናን መድኃኔዓለም ገዳም ሥርዓተ ቅዳሴ በመጋቤ ኅሩያን አባ ኤልያስ በልሁ የገዳማችን አበምኔት መሪነት

የፎቶ ግራፍ ማስታወሻ
ነሐሴ 10 ቀን 2018 ዓ/ ም

21/08/2026

📍 ልዩ የሆነችዋን ፆመ ፍልሰታ አስራ አምስተኛ ቀን በገዳማችን በምስካየ ኅዙናን መድኃኔ ዓለም ገዳም የሱባኤውን መጠናቀቅ ምክንያት በማድረግ
ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ በጠቅላይ ቤተ ክህነት የመንበረ ፓትርያርክ ዋና ስራ አስኪያጅ የምስካየ ኅዙናን መድኃኔ ዓለም ገዳም የበላይ ኃላፊ የደቡብ ምዕራብ ሸዋ እና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ያስተላለፉት መልዕክት ።

በምስካየ ኅዙናን መድኃኔ ዓለም ገዳም  የጾመ ፍልሰታ ፍጻሜ  በብፁዕ ጠቅላይ ስራ አስኪያጅ ቡራኬ ሰጪነት እጂግ ባማረ እና በተወደደ መልኩ  ተጠናቀቀ !!!         ነሐሴ 15 ቀን 201...
21/08/2026

በምስካየ ኅዙናን መድኃኔ ዓለም ገዳም የጾመ ፍልሰታ ፍጻሜ በብፁዕ ጠቅላይ ስራ አስኪያጅ ቡራኬ ሰጪነት እጂግ ባማረ እና በተወደደ መልኩ ተጠናቀቀ !!!

ነሐሴ 15 ቀን 2018 ዓ/ ም
ምስካየኅዙናን መድኃኔ ዓለም ገዳም

ልዩ የሆነችው የጾመ ፍልሰታ አሥራ እምሥተኛው የሱባኤው ፍጻሜ ሥርዓተ ቅዳሴ ገዳማችን በምስካየ ኅዙናን መድኃኔ ዓለም ገዳም በብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ በጠቅላይ ቤተ ክህነት የመንበረ ፓትርያርክ ዋና ስራ አስኪያጅ የምስካየ ኅዙናን መድኃኔ ዓለም ገዳም የበላይ ኃላፊ የደቡብ ምዕራብ ሸዋ እና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና መጋቤ ኅሩያን አባ ኤልያስ በልሁ የገዳማችን አስተዳዳሪ ፣ ሊቀ ሥዩማን ሳሙኤል ፍቃደሥላሴ የገዳሙ ዋና ፀሐፊ አበው መነኮሳት፣ ወንድሞች ዲያቆናት ፣ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ፣ በርካታ ምዕመናን በተገኙበት በፍቅር አሳልፈናል።

ነሐሴ 01 የጀመረው የጾመ ፍልሰታ ሱባኤ የተጠናቀቀ ሲሆን በሱባኤውም በሌሊት የሰዓታት፣ የውዳሴማርያምና ቅዳሴ ማርያም አንድምታ ትርጓሜ ፣ ሥርዓተ ቅዳሴ ፣ ከዓመት ዓመት በልዩ ሁኔታ የማይቋረጠው የሠርክ ጸሎት እንዲሁም በምሽት ጾሙን ምክንያት በማድረግ የተዘጋጀው ልዩ ጉባኤ በልዩ ሁኔታ እና ባማሩ መልኩ ተከናውኖ አልፏል ።

በመጨረሻም ብፁዕ አባታችን አቡነ ሳዊሮስ መልዕክት በማስተላለፍ እና ቡራኬ ሰጭነት በጸሎት ተጠናቋል ።

አስጀምሮ ላስፈጸመን ለልዑል እግዚአብሔር ክብር ምስጋና ይገድባችል የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ረድኤት በረከት አይለየን !!!

ነሐሴ 15 ቀን 2018 ዓ/ ም
ምስካየ ኅዙናን መድኃኔ ዓለም ገዳም

ልዩ የሆነችው የጾመ ፍልሰታ ሲከናወን የነበረው ልዩ ጉባኤ እጅግ ባማረ እና በተወደደ መልኩ ተጠናቀቀ !!!          ነሐሴ 14 ቀን 2018 ዓ.ም ምስካየ ኅዙናን መድኃኔ ዓለም ገዳም  ...
20/08/2026

ልዩ የሆነችው የጾመ ፍልሰታ ሲከናወን የነበረው ልዩ ጉባኤ እጅግ ባማረ እና በተወደደ መልኩ ተጠናቀቀ !!!
ነሐሴ 14 ቀን 2018 ዓ.ም
ምስካየ ኅዙናን መድኃኔ ዓለም ገዳም

በምስካየ ኅዙናን መድኃኔ ዓለም ገዳም ስብከተ ወንጌል ክፍል ዘጋጅነት የእናታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ጾመ ፍልሰታ ምክንያት በማድረግ ለተከታታይ 14 ቀናት ተዘጋጅቶ የነበረው ልዩ ጉባኤ ፍጻሜውን አገኘ ።

በመርሐ ግብሩም ላይ መጋቤ ኅሩያን አባ ኤልያስ በልሁ የምስካዬ ኅዙናን መድኃኔዓለም ገዳም አስተዳዳሪ ፣ መልአከ ብርሃናት ዶክተር አባ ጴጥሮስ ሰለሞን የስብከተ ወንጌል ክፍል ኃላፊ እና የገዳሙ አስተዳደር ቦርድ ፀሐፊ ፣ ሊቀ ሥዩማን ዲ/ን ሳሙኤል ፍቃደ ሥላሴ የምስካዬ ኅዙናን መድኃኔ ዓለም ገዳም ዋና ፀሐፊ ፣ የስብከተ ወንጌል ክፍል አገልጋዮች ፣ የተምሮ ማስተማር ሰንበት ትምህርት ቤት አገልጋዮች እንዲሁም በርካታ ማህበረ ምዕመናን በተገኙበት ተከናውኗል ።

በጉባኤውም ላይ ለተከታታይ አሥራ አራት ቀናት ፀጋው የበዛላቸው መምህራን እና ዘማሪያን ትምህርተ ወንጌል እና ዝማሬ ተከናውኗል።

የገዳሙ ስብከተ ወንጌል ከሚያዘጋጃቸው ልዩ ጉባኤዎች በተጨማሪ ወር በገባ በአራት በአካባቢ ወጣቶች ስም የሚዘጋጅ በ14 ከምዕመናን ለተጠየቁ ጥያቄዎች መልስ የሚሰጥበት እና በ27 የመድኃኔ ዓለም ወርሃዊ ጉባኤዎች የሚከናወኑ ሲሆን ጉባኤው የተሰበሩ የሚጠገኑበት የራቁ የሚቀርቡበት፣ ያዘኑ የሚጽናኑበት ትምህርተ ወንጌል እጅግ የተወደደ ልዩ ጉባኤ ነው።

በመርሐ ግብሩ ፍጻሜ ላይ መልአከ ብርሃናት ዶ/ር አባ ጴጥሮስ ሰለሞን ጉባኤው ተጀምሮ እንዲፈጸም ልዩ ትብብር ሲያደርጉ የነበሩትን ምስጋና አቅርበዋል ።

በመጨረሻም መጋቤ ኅሩያን አባ ኤልያስ በልሁ የገዳሙ አስተዳዳሪ ቃለ ምዕዳን ቡራኬ እንዲሁም መልዕክት በማስተላለፍ በጸሎት የጉባኤው ፍጻሜ ሆኗል ።

ልዩ የሆነችው  የጾመ ፍልሰታ አሥራ አረተኛው  የሱባኤው ፍጻሜ  ሥርዓተ ቅዳሴ ገዳማችን በምስካየ ኅዙናን መድኃኔ ዓለም ገዳም ቡዙ ምዕመናን በተገኙበት ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ በጠቅላይ ቤተ ክህ...
20/08/2026

ልዩ የሆነችው የጾመ ፍልሰታ አሥራ አረተኛው የሱባኤው ፍጻሜ ሥርዓተ ቅዳሴ ገዳማችን በምስካየ ኅዙናን መድኃኔ ዓለም ገዳም ቡዙ ምዕመናን በተገኙበት ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ በጠቅላይ ቤተ ክህነት የመንበረ ፓትርያርክ ዋና ስራ አስኪያጅ የምስካየ ኅዙናን መድኃኔ ዓለም ገዳም የበላይ ኃላፊ የደቡብ ምዕራብ ሸዋ እና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ መሪነት በፍቅር አሳልፈናል።

አስጀምሮ ላስፈጸመን ለልዑል እግዚአብሔር ክብር ምስጋና ይገባል የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ረድኤት በረከት አይለየን !!!
የፎቶ ግራፍ ማስታወሻ
ነሐሴ 11ቀን 2018 ዓ/ ም
ምስካየ ኅዙናን መድኃኔ ዓለም ገዳም

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ምስካየ ኅዙናን መድኃኔ ዓለም ገዳም posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share