Kingdom Disciple's International Church

Kingdom Disciple's International Church we preach christ the crucified !

To all my Face Book friends all around the world"But God destroyed the trap of death and raised him up, because death wa...
16/04/2023

To all my Face Book friends all around the world

"But God destroyed the trap of death and raised him up, because death was not able to hold him."
- Acts 2:24

Happy Easter to our Lord and Savior Jesus Christ.

Happy Holidays!

በመላው አለም ያላችሁ የፊት ገጽ ጓደኞቼ“እግዚአብሔር ግን የሞትን ጣር አጥፍቶ አስነሣው፥ ሞት ይይዘው ዘንድ አልቻለምና።”  — ሐዋርያት 2፥24እንኳን ለጌታችን እና ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ...
16/04/2023

በመላው አለም ያላችሁ የፊት ገጽ ጓደኞቼ

“እግዚአብሔር ግን የሞትን ጣር አጥፍቶ አስነሣው፥ ሞት ይይዘው ዘንድ አልቻለምና።”
— ሐዋርያት 2፥24

እንኳን ለጌታችን እና ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ መታሰቢያ ቀን አደረሳችሁ።

መልካም በዓል!

17/01/2023
“ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋልና።”  — ሉቃስ 2፥11በእስራኤል ብዙ ልጆች ቢወለዱም  ለእኛ ሀጢያት ቤዛ የሚሆን የህግና የነብያት  ፍጻሜ  አዳኝ ጌ...
07/01/2023

“ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋልና።”
— ሉቃስ 2፥11
በእስራኤል ብዙ ልጆች ቢወለዱም ለእኛ ሀጢያት ቤዛ የሚሆን የህግና የነብያት ፍጻሜ አዳኝ ጌታ ኢየሱስ ግን ተሰጠን።
እንኳን ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት መታሰቢያ ቀን በሰላም አደረሳችሁ ።

Subscribe
30/11/2022

Subscribe

Love never fail!1Cor.13:8ፍቅር ለዘወትር አይወድቅም !1ቆሮ.13:8

“እኛም ሁላችን በመጋረጃ በማይከደን ፊት የጌታን ክብር እንደ መስተዋት እያብለጨለጭን መንፈስ ከሚሆን ጌታ እንደሚደረግ ያን መልክ እንመስል ዘንድ ከክብር ወደ ክብር እንለወጣለን።”  — 2ኛ ...
10/11/2022

“እኛም ሁላችን በመጋረጃ በማይከደን ፊት የጌታን ክብር እንደ መስተዋት እያብለጨለጭን መንፈስ ከሚሆን ጌታ እንደሚደረግ ያን መልክ እንመስል ዘንድ ከክብር ወደ ክብር እንለወጣለን።”
— 2ኛ ቆሮ 3፥18

“ሳሙኤልም አንድ ድንጋይ ወስዶ በምጽጳና በሼን መካከል አኖረው፤ ስሙንም፦ እስከ አሁን ድረስ እግዚአብሔር ረድቶናል ሲል አቤንኤዘር ብሎ ጠራው።”  — 1ኛ ሳሙኤል 7፥12
03/11/2022

“ሳሙኤልም አንድ ድንጋይ ወስዶ በምጽጳና በሼን መካከል አኖረው፤ ስሙንም፦ እስከ አሁን ድረስ እግዚአብሔር ረድቶናል ሲል አቤንኤዘር ብሎ ጠራው።”
— 1ኛ ሳሙኤል 7፥12

✉የተሰቀለ ክርስቶስ እየተሰበከ ነውን?  በመስቀል ባህል (በአል) ማግስት....☞ሰላም ለእናንተ ይሁን።የእግዚአብሔር ተወዳጆች የአባት ቡሩካን በልጁ ልጆች የሆናችሁ ሁሉ እንዴት አላችሁልኝ!✍...
28/09/2022

✉የተሰቀለ ክርስቶስ እየተሰበከ ነውን?

በመስቀል ባህል (በአል) ማግስት....

☞ሰላም ለእናንተ ይሁን።የእግዚአብሔር ተወዳጆች የአባት ቡሩካን በልጁ ልጆች የሆናችሁ ሁሉ እንዴት አላችሁልኝ!

✍የዛሬየን እንካችሁ!

☞በአብዛኛው መድረኮቻችን ላይ ዛሬ ዛሬ የምንሠማቸው ስብከቶች ሁሉ መነሻቸው ከመድረሻቸው የማይገናኝ ዉል የለሽ እየሆኑ ክርስቶስ ተኮር ሳይሆን ጥቅም እና ፍላጎትን ያማከሉ እየሆኑ ነው፡፡ከተሰራልን ይልቅ ሊያደርግልን ያለ ምኞታችንን እና ፍላጎቶቻችንን ለመስማት ሆኗል ጉጉታችን።አንዳንዱ ጌታ መልእክቴን አሰቀየረኝ ብሎ ሁኔታ አይቶ ሲለውጥ አንዳንዱ ደግሞ አንድ ስፍራ የሠበከውን ሌላ ቦታ እየደገመ በብዙ ትኩረት ተኮር መሆንን ይካንበታል፡፡ሁሉም ልክ ሊሆኑ ይችሉ ይሆናል፡፡ነገር ግን ለተላከ ሰው ዋና ጉዳይ አይለወጥም ባይ ነኝ እኔ፡፡የእግዚአብሔር ዋና ጉዳይን የማያውቅ መልእክተኛም ካለ መላኩን ማረጋገጥ አለበት።

እናንተም እንደ እኔ ታዝባችሁ ይሆን?

✡ልብ በሉ ስለዳዊት እና ጎልያድ ተሰብከን:ደም ስለሚፈሳት ሴት ተነግሮን:ስለአብርሃም ልጅ ምትክ መሠዋእት ተተርኮልን:ባዶ ገምቦ ስለሚሞላ ዘይት አጓጉተውን:ስለወፍራም ቅባት ተቀባጥሮልን.....ምኑ ቅጡ...ብዙ ብዙ ተብለን ብዙ ሰምተን አንዱን ሳናውቅ መጨረሻም በጥሪ ጌታን ሳናይ ጥቅም ሽተን ጌታን እንቀበልና 'ክርስቲያን' እንደረጋለን እንጂ አንሆንም፡፡ከዚያም ስላለንበት ህብረት ውስጠ ደንብ እንጅ የመፅሀፋን ክርስቶስ ስንተዋወቅ እሱንም ሳናውቅ እናድጋለን፡፡

"መልህቅ ውሀ ውስጥ ዘመን ባስቆጠረ:

ተዘፈዘፈ እንጅ መቼ ዋና ተማረ "....እንዲሉ እንዲሁ መኖር ብቻ እንኖራለን።

ወደ መጽሃፋ እንመለስ! ምን ይለናል ቃሉ?
..ከእናንተ ጋር ሳለሁ በሙሴ ሕግና በነቢያት በመዝሙራትም ስለ እኔ የተጻፈው ሁሉ ይፈጸም ዘንድ ይገባል ብዬ የነገርኋችሁ ቃሌ ይህ ነው አላቸው...ሉቃስ ወንጌል 24:44

☞ከሙታን የተነሳው ጌታ በተነሳ ቀን እራሱን እያሳየ የተናገረው ይህንን ነው፡፡

...እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው...ማቴ 28:19-20

☞ምን ነበር ያዘዘው?ምንስ ነበር ያስተማረው?ይሄ ጌታ ወዳጆቼ መቼም እንደሲና ተራራ የሙሴን ህግ እንደማትሉኝ ተስፋ አደርጋቸዋለሁ፡፡

☞በአጠቃላይ ሙሉው መፅሀፍ ቅዱስ 66ቱ መፅሐፍ በአንድ ላይ አንድ ቢሆንም አንድ መልእክት አንድ መልክ ክርስቶስ ስላለው ነው አንድ መፅሐፍ የሆነው፡፡

በዚህ የአዲስ ኪዳን ዘመን ህይወታችንም ኑሮችንም መልእክታችንም በህግ:በመዝሙራት እና በነብያት እየተነገረለት የነበረ አንድ መሲህ እርሱም ስለ ሁሉ የተሰቀለ ክርስቶስ ኢየሱስ ብቻ ሊሆን ይገባዋል፡፡

እርሱ በመፅሀፍ እንደተፃፈው እንደቃሉ ለእግዚአብሔር የማዳን መንገድ ለሠው ዘር ሁሉ ደግሞ የመዳን ተስፋ ነው፡፡እርሱ ብቻ!
..በመካከላችሁ ሳለሁ ከኢየሱስ ክርስቶስ በቀር እርሱም እንደተሰቀለ ሌላ ነገር እንዳላውቅ ቆርጬ ነበርና...1ኛ ቆሮንቶስ 2:2 እንዳለው ቅዱስ ጳውሎስ።

☞በዳኑት ወገኖቻችን መሀከል ሁለ በየአጥቢያዎች በየጊዜው እና በየጉባኤው የምናስተምረው የተለያየ ርእሰ ጉዳይ የለም : አይኖርምም አላልኩም እንደዛም አላምንም፡፡መፅሀፉ ስለሁሉም ነገር የሚለው ነገር አለው፡፡ነገር ግን አሁን አሁን በየአውደምህረቱ የሚቀርቡት ስብከቶች በየኮንፈራንሱ የምንሰማቸው ቃሎች እና በይሆንላችኋል የሚነገሩን ድምፆች የምንመለከታቸውም ተግባራት ሁሉ ምን እንደሆኑ ለማሳየት ነው፡፡

☞የስነመለኮት ተምህርት ቤቶችም የመፅሐፍ ትርጓሜ ላይ ቢያስቡበት ከነቀፋና ከቀውስ ከእርስበርስ ጥላቻ እና ከታሪክ እና የቀዳሙ መረጃዎች አምልጠን የተባረከው ተስፋችን መጠበቅ ይበዛልን ዘንድ መጻሕፍትን ቢተረጉሙልን መልካም ነው፡፡'የእኛ ልክ' 'የእኛ ልክ' ከሚል ውድድር ወጥተን የእግዚአብሔር ልክ ክርስቶስን ለመግለጥ ጊዜ ይሆንልንም ነበር፡፡ይህን ስል ማንም ለማክበር ማንም ለማዋረድ ስራና ድካማቸውንም ለማቅለል ምንምም አልሠሩም ለማለትም አይደለም፡፡ለመሆኑ ውረደት አለ እንዴ ኢየሱስ እሰከ ሲኦል ሄዶበት የለ? እንዴ ክብርስ አለ ከአብ ቀኝ መቀመጥ በላይ?

☞ጎበዝ እናስተውል:-

ለምሳሌ በትንቢት እና በነብያት ቢሮ ውስጥ በስጦታው የሚያገለግሉ የትንቢትን አገልግሎት ለማድረግ የሚያስችልን እና የሚመቻቸውን ነገር ብቻ ብለው ሲጨርሱ ጌታን የምትቀበሉ ሲሉ ማየት የተለመደ እየሆነ ነው አይደለም?

☞ሌላው ደግሞ የሚገርመኝ በተለያዩ ኮንፈረንስ ማስታወቂያ ላይ የሚታይ ግን የማይታይ ነገርን በተደጋጋሚ ታያላችሁ፡፡"ወንጌል ይሰበካል!" የሚል። ከብዙ ድርጊቶች መሀል ያለ አንድ ነገር የማስታወቂያ ማሟያ ሆኖ ግን በስፍራው ስትሆኑ እና ስትገኙ ያ ወንጌል (GOSPEL) የምሰራች ጭራሽ የለም።የሚነገራችሁ የይሆናል ተስፋ ብቻ። ተስፋ የምስራች ነው ወይ ያሰኛችኃል፡፡

☞በፈውስ በትንቢት በተአምራት ስጦታ ሁሉ አምናለሁ ጌታ ይገለጥብኛልም፡፡በዚህም ብዙ ምስክርነቶች በህይወቴ አይቻለሁ፡፡ነገር ግን ከቅርብ ዘመናት ወዲህ በየምስክርነቶች ስነሰማ ይህን ያህል በሽተኛ ተፈወሰ ለእከሌ ትንቢት መጣ ይህን ያህል አጋንንት ወጣ ተብሎ ይነገራል እንጅ የተሠበከውን ቃል ምንነት አንሰማም፡አይነገርም፡፡በየቴሌቭዢንም ስናይ እኛም ጋር ይሄም አለ ኑ ጠበል ቅመሱልኝ አይነት ይመስላል፡፡

ደግሞ ትንቢቶችንም እንዳንመረምር ዘመን አመጣሹ ኮረና ብዙ አሳይቶናል።
..እኛ ግን የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብካለን፤ይህም ለአይሁድ ማሰናከያ ለአሕዛብም ሞኝነት ነው...1ኛቆሮንቶስ 1:23

☞ይህ ጳውሎስ የሚሠብከው የተሰቀለ ክርስቶስ ማነው?

1-በእግዚአብሔር እቅፍ የነበረ አንድያ ልጅ
..መቼም ቢሆን እግዚአብሔርን ያየው አንድ ስንኳ የለም፤በአባቱ እቅፍ ያለ አንድ ልጁ እርሱ ተረከው...ዮሐንስ ወንጌል 1:18

2-ስለሠው ልጆች ዋጋ ሊከፍል ቃል ስጋ የሆነ
..ቃልም ሥጋ ሆነ፤ጸጋንና እውነትንም ተመልቶ በእኛ አደረ፥አንድ ልጅም ከአባቱ ዘንድ እንዳለው ክብር የሆነው ክብሩን አየን...ዮሐንስ ወንጌል 1:14

3-አለማትን ሁሉ በስልጣን ቃል የፈጠረ
..ሁሉን ወራሽ ባደረገው ደግሞም ዓለማትን በፈጠረበት በልጁ በዚህ ዘመን መጨረሻ ለእኛ ተናገረን...ዕብራውያን 1:2

4-እግዚአብሔር የነበረ
..በመጀመሪያው ቃል ነበረ፥ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፥ቃልም እግዚአብሔር ነበረ...ዮሐንስ ወንጌል 1:1

5-ከእግዚአብሔር ጋር እኩል የነበረ
..እርሱ በእግዚአብሔር መልክ ሲኖር ሳለ ከእግዚአብሔር ጋር መተካከልን መቀማት እንደሚገባ ነገር አልቈጠረውም...ፊልጵስዩስ ሰዎች 2:6
..ብዙ ብዙ ማለት ይቻላል፡፡ነገር ግን ይህ መሲህ ወይም የተቀባ ይመጣል ተብሎ የሚጠበቅ ክርስቶስ ኢየሱስ ሆኖ መጣ፡፡እና በድካም ሞተ በሀይል ተነሳ፡፡የሠውን ልጅ የእግዚአብሔር ልጅ ለማድረግ የእግዚአብሔር ልጅ የሠው ልጅ ሆነ እና ሁሉን ዋጋ ከፈለ ጨረሰ አጠናቀቀ ተፈጸመ አለም።
..ሐዋርያ ሊሆን የተጠራ የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያ ጳውሎስ በነቢያቱ አፍ በቅዱሳን መጻሕፍት አስቀድሞ ተስፋ ለሰጠው ለእግዚአብሔር ወንጌል ተለየ።ይህም ወንጌል በሥጋ ከዳዊት ዘር ስለ ተወለደ እንደ ቅድስና መንፈስ ግን ከሙታን መነሣት የተነሣ በኃይል የእግዚአብሔር ልጅ ሆኖ ስለ ተገለጠ ስለ ልጁ ነው፤እርሱም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው...ሮሜ 1:1-4

☞ይህ ነው ወንጌል፡፡በሞቱ ሀጢያትን በሽታን እርግማንን ሰይጣንን ህግን አለምን ሁሉ ሰውንም ጭምር ገድሎ ሁሉን አድርጎ ተነሳ፡፡አሮጌ ነገር አለፈ አዲስ ነገር ሆነ የምስራች!
..ስለ በደላችን አልፎ የተሰጠውን እኛን ስለ ማጽደቅም የተነሣውን ጌታንችንን ኢየሱስን ከሙታን ባስነሣው ለምናምን ለእኛ ይቈጠርልን ዘንድ አለው...ሮሜ 4:24-25

ኢየሱስ በመስቀል ሲሞት አሮጌ ማንነት ሁሉ ተወገደ እኛን ለማፅደቅ ሲነሳ ሁሉ አዲስ ሆነ አዲስ አደረገን የምስራች!
..ስለዚህ ማንም በክርስቶስ ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው፤አሮጌው ነገር አልፎአል፤እነሆ፥ሁሉም አዲስ ሆኖአል...2ኛ ቆሮንቶስ 5:17

✞በተሠቀለ ክርስቶስ ካመናችሁ አዲስ ናችሁ!

የመስቀል በአል ሳይሆን የመስቀል ህይወት ይሁንላችሁ!

ሻሎም!

የመንግስቱ ደቀመዛሙርት አ/አ ቤተክርስቲያን

(kingdom Disciples International Church)

Address

Addis Ababa
31717

Telephone

+251902326767

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Kingdom Disciple's International Church posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to Kingdom Disciple's International Church:

Share