08/04/2021
?
ልትሄድ መንገድ ጀምረኻል ? እንድግዲኽ በምትሄድበት በህይወት መንገድ ላይ ሶስት ሰዎች ይገጥሙካል።
#1አንደኛው ወገን መድረስህን በጉጉት የሚጠባበቁ ይደርሳል ይላሉ ከምትሄድበት የሕይወት ምዕራፍ እንደምትደርስ ላገኙት ሁሉ ይናገሩልሃል ።
#2ሁለተኛው ወገን ከምትሄድበት ልትደርስ የማትችልበትን ምክንያት ነው ያሉትን ሁሉ እንደማስረጃና እንደ መረጃ በማቅረብ ከግብህ እንደማትደርስና ተሰነካክለክ እንደምትቀር በመገመት ብቻ ሳይሆን እርግጠኛ በመሆን ጉዞክን ቀላል ሊያደርጉልክ የሚችሉትን ደጋፊና አጋዦችክን በተከሸኑ ቃላት ሊያደክሙ ይታትራሉ ።
#3ሶስተኛው ወገን በአንተ መቆምና መቀጠል (መሄድ) ምንም አይነት አስተዋጽኦ የማያደርግ ካሸነፍክ ከአሸናፊነትክ ተጠቃሚ ለመሆን የተዘጋጀ ከተሸነፍክ /ከመንገድክ ተሰነካክለክ ከቀረክ ከመቅረትክ ተጎጂ መሆን የማይፈልግ
ዳር ሆኖ ከአንተ ጋር ሳይሆን ከውጤትክ ጋር መኖር የሚፈልግ ሆኖ ስሜቱን፣እይሉን፣ጊዜውን እና ገንዘቡን ሊሰጥክ አይችልም።
#ስለዚህ ከሶስቱ አንዱን መምረጥ ውጤታማ ያደርገኛል ብለህ የአንዱ ጠላት የአንዱ ወዳጅ እንዳትሆን ልብህን ጠብቅ ሶስቱም የሚሆኑትን የሆኑት ከአንተ ተነስተው አይደለም ። ይልቁን የተያዙበት ማንነታቸው ውጤት እንጂ፥
ጌታ ኢየሱስ በበዛ ደግነቱና በማይለወጥ ፍቅር ሲኖር የአስቆሮቱን ይሁዳ አሳብ ካላስለወጠው ፤ ጌታውን አሳልፎ ከመስጠት ካልተከለከለ ልትከለክላቸው አትችልም።በጭራሽ!!
እልምህን እነርሱም እልማቸውን መኖራቹን ስትቀጥሉ አንተ ትኩረትክን በእልምክና በጉዞክ ላይ ብቻ ካደረክ በድጋፍ ስላጀመርክ በተቃውሞ አትቆምም። መንገድክን እና መዳረሻክን ብቻ ትኩረት ካደረክ ካሰብክበት (ከታየልክ) እርግጠኛ ሁን ትደርሳለክ ።