አርዱል ሀበሻ-Ardul habesha

አርዱል ሀበሻ-Ardul habesha አርዱል ሀበሻ የአውሊያዎች, የመሻኢኾች መፍለቂያ

ይህንን ወር በደስታ ልንቀበል ይገባል ፣ በቀልባችን በቤተሰባችንም ውስጥ የነቢዩንﷺ ፍቅር መትከል እንዲሁም የርሳቸው ወዳጆችና በርሳቸው የተሳሰሩ ማድረግ አለብን ፣ በርሳቸው ላይ ሶለዋት በብ...
19/08/2026

ይህንን ወር በደስታ ልንቀበል ይገባል ፣ በቀልባችን በቤተሰባችንም ውስጥ የነቢዩንﷺ ፍቅር መትከል እንዲሁም የርሳቸው ወዳጆችና በርሳቸው የተሳሰሩ ማድረግ አለብን ፣ በርሳቸው ላይ ሶለዋት በብዛት ማውረድ እና ህይወታቸውን መማማርም ይገባናል
الحبيب سالم الشاطري -رحمه الله-

13/08/2026

እንኳን ለታላቁ ነቢ ‎ﷺ የዊላዳ ወር ረቢዕ አል አወል በሰላም አደረሳቹህ

ዑስማን ኢብን አፋን - ጠሮ መስጅድ ወጣት ማህበርከ3000  በላይ የአካባቢው ማህበረሰብ ተሰብስቦ በአንድ ድምፅ መስጂዳችንን ያስተዳድሩልን በማለት ሀላፊነት ያስረከባቸው አስተዳደሮች እያሉ እ...
01/08/2026

ዑስማን ኢብን አፋን - ጠሮ መስጅድ ወጣት ማህበር

ከ3000 በላይ የአካባቢው ማህበረሰብ ተሰብስቦ በአንድ ድምፅ መስጂዳችንን ያስተዳድሩልን በማለት ሀላፊነት ያስረከባቸው አስተዳደሮች እያሉ እና የማህበረሰቡ ድምፅም በፊርማ ተሰነዶ የተዘጋጀ ሆኖ ሳለ፤ የአካባቢው ማህበረሰብም ሆነ የመስጂዱ አስተዳደር ኮሜቴ ባለወቁበት ሁኔታ የመስጂዱን ሰላም ለማወክ የተነሱ አካላት የኮሚቴ ቅያሬ አድርገናል የሚል ደብዳቤ የቅጥር ግቢው ግንብ ላይ ለጥፈዋል።

የአንድን ህጋዊ ተቋም አስተዳደር ለመረከብ ለቀድሞው አስተዳደር የማሳወቅያ ደብዳቤ የመፃፍን ህግ ትተው አስተዳደሩን በህጋዊ መንገድ ማሳመን ስላልቻሉ እና ከኮሜቴው መስጂዱን ማስረክበው ሀላፊነቱን ለሰጠኝ ማህበረሰብ ብቻ ነው የሚል ህጋዊ አግባብ ያለው ምላሽ በማግኘታቸው፤ አስተዳደር ቅየራውን ለመስጂዱ ግንብ ማሳወቃቸው ፈገግ የሚያስብል ከመሆኑም ባለፈ ፤
ውሳኔው በግድ የለሽነት እንደተወሰነ የሚያስረዳው ለአስተዳደርነት ከተሰየሙት ግለሰቦች ውስጥ ሶስቱ የመስጂዱ አካባቢ ነዋሪ አለመሆናቸው እና ሁለቱ ደግሞ ከአራት አመት በፊት ለመስጂዱ ፀብ ተንኳሽ ከሆኑ ግለሰቦች ጋር በፍርድ ቤት ጥፋተኝነታቸው ተረጋግጦ ወደ ማረሚያ ቤት እንዲወርዱ የተፈረደባቸው እና በማስጠንቀቂያ የተለቀቁ ታራሚ መሆናቸው ነው።

እንደዚህ አይነት ኢ - ህገ መንግስታዊ የመፈንቅለ አስተዳደር በመስጂዳችን ሲሞከር በትንሹ ለአምስተኛ ግዜ ሲሆን፤ ይህም ሙከራ በህብረተሰቡ ተቀባይነት የሌለው እና በህገወጥ እንቅስቃሴ መስጂዱን ለመረበሽ ከንቱ ሙከራ የምታደርጉ አካላት ከተግባራቹ እንድትታቀቡ በፅኑ እናስጠነቅቃለን!!

ወደአላህﷻ መግቢያ በራችን - በነቢይ ﷺ በኩል ነው ፥ ወደረሱለላህ ﷺ መግቢያችን ደሞ በርሳቸው ላይ ሶለዋት ማውረድ ነው።[الشيخ د. علي جمعة حفظه الله] __
14/07/2026

ወደአላህﷻ መግቢያ በራችን - በነቢይ ﷺ በኩል ነው ፥ ወደረሱለላህ ﷺ መግቢያችን ደሞ በርሳቸው ላይ ሶለዋት ማውረድ ነው።

[الشيخ د. علي جمعة حفظه الله] __

"የማህበረሰብ ምርጫ ይከበር"አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ከሚገኙ ትልልቅ መስጅዶች ዑስማን ኢብን አፋን (ጠሮ) መስጅድ ተጠቃሽ ነው ። ይህ መስጅድ በማህበረሰቡ ያላሰለሰ ጥረት እና ድካም አሁን ...
13/07/2026

"የማህበረሰብ ምርጫ ይከበር"

አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ከሚገኙ ትልልቅ መስጅዶች ዑስማን ኢብን አፋን (ጠሮ) መስጅድ ተጠቃሽ ነው ። ይህ መስጅድ በማህበረሰቡ ያላሰለሰ ጥረት እና ድካም አሁን ያለበት ደረጃ ላይ ይገኛል። የመስጅዱ ማህበረሰብ ከአምስት አመት በፊት መስጅዱ ላይ ሁከት እና ግርግርን ፈጥረው መስጅዱን ባወደሙ አካላት ክፉኛ የልብ ስብራት ቢገጥመውም ያንን ስብራት ተሻግሮ ፊቱን ወደ ልማት በማዞር መስጅዱን እና አካባቢ ችግር በሆኑ የልማት ስራዎች ላይ ተጠምዶ ይገኛል። ለአብነትም በቅርቡ የተጀመረው የከርሰ ምድር የውሀ ፕሮጀክት እጅግ ፈጣን በሚባል አፈፃፀም እየተካሄደ ሲገኝ በቅርቡ ተጠናቆ ለመስጅዱ እና ለአካባቢው ማህበረሰብ ግልጋሎት መስጠት ይጀምራል ።

ነገር ግን ይህንን የልማት እንቅስቃሴዎችን ማደናቀፍ እና የመስጅዱን ሰላም መሆን የማይፈልጉ አልፎ ተርፎ ለዳግም ሁከት እና ብጥብጥ ቅድመ ዝግጅት ላይ ያሉ ጥቂት የአካባቢው ነዋሪዎች የመንግስትን ስልጣን ለግል ጥቅማቸው ከሚያውሉ አንዳንድ የክ/ከተማው የአስተዳደር እርከን ላይ ካሉ ሰዎች ጋር በጋራ በመሆን የማህበረሰቡን የልብ ስብራት ዳግም ለመቀስቀስ እንቅስቃሴዎችን ማድረግ ከጀማመሩ ሰንበትበት ብሏል።

የመስጅዱ ማህበረሰብ ይህን እንቅስቃሴ በአንክሮት እየተከታተለ ሲሆን ለሚመለከተው የመንግስት አካላት አቤቱታውን እያቀረበ ይገኛል። የመስጅዱ ማህበረሰብ ከህፃን እስከ አዋቂ በጉዳዩ ላይ በቂ መረጃ ያለው እና የመስጅዱን ሰላም ለማስከበር እና የጀመረውን የልማት እንቅስቃሴዎችን ከዳር ለማድረስ ቁርጠኛ መሆኑን እንግልፃለን። በመሆኑም ይህንን በጎ ያልሆነ ተግባር በጊ"የማህበረሰብ ምርጫ ይከበር"

አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ከሚገኙ ትልልቅ መስጅዶች ዑስማን ኢብን አፋን (ጠሮ) መስጅድ ተጠቃሽ ነው ። ይህ መስጅድ በማህበረሰቡ ያላሰለሰ ጥረት እና ድካም አሁን ያለበት ደረጃ ላይ ይገኛል። የመስጅዱ ማህበረሰብ ከአምስት አመት በፊት መስጅዱ ላይ ሁከት እና ግርግርን ፈጥረው መስጅዱን ባወደሙ አካላት ክፉኛ የልብ ስብራት ቢገጥመውም ያንን ስብራት ተሻግሮ ፊቱን ወደ ልማት በማዞር መስጅዱን እና አካባቢ ችግር በሆኑ የልማት ስራዎች ላይ ተጠምዶ ይገኛል። ለአብነትም በቅርቡ የተጀመረው የከርሰ ምድር የውሀ ፕሮጀክት እጅግ ፈጣን በሚባል አፈፃፀም እየተካሄደ ሲገኝ በቅርቡ ተጠናቆ ለመስጅዱ እና ለአካባቢው ማህበረሰብ ግልጋሎት መስጠት ይጀምራል ።

ነገር ግን ይህንን የልማት እንቅስቃሴዎችን ማደናቀፍ እና የመስጅዱን ሰላም መሆን የማይፈልጉ አልፎ ተርፎ ለዳግም ሁከት እና ብጥብጥ ቅድመ ዝግጅት ላይ ያሉ ጥቂት የአካባቢው ነዋሪዎች የመንግስትን ስልጣን ለግል ጥቅማቸው ከሚያውሉ አንዳንድ የክ/ከተማው የአስተዳደር እርከን ላይ ካሉ ሰዎች ጋር በጋራ በመሆን የማህበረሰቡን የልብ ስብራት ዳግም ለመቀስቀስ እንቅስቃሴዎችን ማድረግ ከጀማመሩ ሰንበትበት ብሏል።

የመስጅዱ ማህበረሰብ ይህን እንቅስቃሴ በአንክሮት እየተከታተለ ሲሆን ለሚመለከተው የመንግስት አካላት አቤቱታውን እያቀረበ ይገኛል። የመስጅዱ ማህበረሰብ ከህፃን እስከ አዋቂ በጉዳዩ ላይ በቂ መረጃ ያለው እና የመስጅዱን ሰላም ለማስከበር እና የጀመረውን የልማት እንቅስቃሴዎችን ከዳር ለማድረስ ቁርጠኛ መሆኑን እንግልፃለን።

በመሆኑም ይህንን በጎ ያልሆነ ተግባር በጊዚያዊ ጥቅም በመታለል የአካባቢውን ሰላም ለማደፍረስ እንቅስቃሴ ላይ ያላቹ በሙሉ ከድርጊታቹ እንድትቆጠቡ እያሳሰብን ማህበረሰቡ የጀመረውን ሰላማዊ እንቅስቃሴ እስከመጨረሻው እንደሚገፋበት ለማሳወቅ እንወዳለን።ዚያዊ ጥቅም በመታለል የአካባቢውን ሰላም ለማደፍረስ እንቅስቃሴ ላይ ያላቹ በሙሉ ከድርጊታቹ እንድትቆጠቡ እያሳሰብን ማህበረሰቡ የጀመረውን ሰላማዊ እንቅስቃሴ እስከመጨረሻው እንደሚገፋበት ለማሳወቅ እንወዳለን።

የዑስማን ኢብን አፋን (ጠሮ) መስጅድ ወጣት ማህበር

እንኳን ለዒደል አድሀ በዓል በሠላም አደረሰን። كل عام وأنتم بخير وعيد مبارك
26/05/2026

እንኳን ለዒደል አድሀ በዓል በሠላም አደረሰን።

كل عام وأنتم بخير وعيد مبارك

የህይወት ወርቃማ ዘመናቸውን ዲንን በመኻደምና ትውልድ በማነጽ ያሳለፉት ሸይኽ ኸድር ዑመር ወደ አኼራ ተሻግረዋል። ኢናሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑንሸይኽ ከድር ዑመር በኑር መስጅድ የረመዳን ተራ...
09/05/2026

የህይወት ወርቃማ ዘመናቸውን ዲንን በመኻደምና ትውልድ በማነጽ ያሳለፉት ሸይኽ ኸድር ዑመር ወደ አኼራ ተሻግረዋል። ኢናሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን

ሸይኽ ከድር ዑመር በኑር መስጅድ የረመዳን ተራዊህ ዚክሮችን በመምራት፣ በለይለተል ጁሙዓ( ሃሙስ ምሽት) ባለው ሳምታዊ የሰለዋት ፕሮግራም ላይ ሰለዋት በማለት ለረጅም ጊዜ ኑር መስጅድን አድምቀው ኖረዋል። ከዚህ በተጨማሪም በርካታ ደረሳዎችን አስተምረዋል። ለቤተሰባቸው እና መላው ሙስሊም ማህበረሰብ መጽናናትን ለርሳቸው ከፍ ያለ ደረጃን አላህ ይስጥልን።

በትናንትናው እለት ከዙሁር ሶላት በኃላ የአቃቂ ራህማ መስጂድ መበጥበጡ ተሰምቷል::ምክንያቱ:- ከተለያዩ አካባቢዎች ተሰብስበው በመጡ ስብስቦች በመስጂዱ ታሪክ የማይታወቅ እና የአካባቢው ሱፊይ...
04/05/2026

በትናንትናው እለት ከዙሁር ሶላት በኃላ የአቃቂ ራህማ መስጂድ መበጥበጡ ተሰምቷል::

ምክንያቱ:- ከተለያዩ አካባቢዎች ተሰብስበው በመጡ ስብስቦች በመስጂዱ ታሪክ የማይታወቅ እና የአካባቢው ሱፊይ ማህበረሰብ የማይፈልገውን የውሃቢያ ትምህርት በግድ ካልተሰጠ በሚል ነው።

"ከዑስማን ኢብን አፋን (ጠሮ) መስጅድ ማህበረሰብ የተላለፈ መልዕክት"ከለፉት ጥቂት ቀናት ጀምሮ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ መስጅዳችንን አስመልክቶ እየተሰራጨ ባለው እጅግ ከእውነት በራቀ መረጃ ላ...
29/04/2026

"ከዑስማን ኢብን አፋን (ጠሮ) መስጅድ ማህበረሰብ የተላለፈ መልዕክት"

ከለፉት ጥቂት ቀናት ጀምሮ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ መስጅዳችንን አስመልክቶ እየተሰራጨ ባለው እጅግ ከእውነት በራቀ መረጃ ላይ በመስጅዱ ማህበረሰብ የተሰጠ ማብራሪያ ።

ከሰሞኑን የመስጅዳችን ሰላም መሆን በማይሹ አካላት እጅግ ሰላማዊ ሁኔታ ላይ ያለው መስጅዳችንን ወደ ሁከት ቀጠና ለመለወጥ ማህበራዊ ሚዲያን በመጠቀም የመቀስቀስ ብሎም ጥሪ መሰል መልዕክቶችን እየተላለፉ ይገኛል ፤ ማህበረሰቡ ጉዳይን በአንክሮ እየተከታተለ ያለ እና ከዛሬ ነገ ይሻላል በሚል ተስፋ መልስ ከመስጠት የተቆጠበ ቢሆንም እነዚህ አካላት በጉዳዩ ላይ በመቀጠል መስጅዱን ለመረበሽ ያመቻቸው ዘንድ የወጣት ማህበራችን እንዳንድ አባላትን ጨምሮ በመስጅዱ ማህበረስብ ላይ በውሸት የተቀነባበረ የስም ማጥፋት ዘመቻቸውን አጠናክረው ቀጥለዋል ።

የዑስማን ኢብን አፋን (ጠሮ) መስጅድ ማህበረሰብም ጉዳዩን እስከላይኛው እርከን ላይ ላሉ የህግ አካላት ከተጨባጭ ማስረጃ ያሳወቀ ሲሆን ጉዳዩን በትኩረት እና በአንክሮ በመከታተል ሀገራችን ለሀገር አቀፍ ምርጫ እየተሰናድችበት ባለችበት በዚህ ወቅት መስጅዱን ከማንኛውም ሁከት እና ረብሻ ለመከላከል ከህግ አካላት ጋር በትብብር እንደሚሰራ ለማሳወቅ እንወዳለን።

ሙስሊሙ ማህበረሰብም እውነታው ይህ መሆኑን አውቃችሁ በመረጃው በመደናገጥ በስልክም በአካልም የጠየቃችሁ በሙሉ ከልብ የመነጨ ምስጋናችንን እናቀርባለን ፤ የሚመለከተው የህግ አካልም የመስጅዱ እና የአካባቢው ሰላም መሆን በማይሹ ግለሰቦች ዳግም ግጭትን ለመፍጠር በሚመስል መልኩ እየተሰራጨ ባለው መረጃ ማህበረሰቡ ላይ ስጋትን እየፈጠረ በመሆኑ መረጃውን አጣርታችሁ የበኩላችሁን ኃላፊነት እንድትወጡ መልዕክታችንን እናስተላልፋለን።

ሙስሊሙ ማህበረሰብም እውነታው እንዲያውቀው ፖስቱን ሼር እንድታደርጉት በአክብሮት እንጠይቃለን።

የዑስማን ኢብን አፋን (ጠሮ) መስጅድ ወጣት ማህበር

📸 ምስል ፤ የወጣት ማህበራችንን ስም በመጠቀም በተከፈተ ሀሰተኛ ገፅ እየተላለፉ የሚገኙ ሀከት ቀስቃሽ ጥሪ እና የስም ማጥፋት መልዕክቶች ፤ ይህ ገፅ ወጣት ማህበራችንን የማይወክል እና በዚህ በኩል የሚተላለፉ መልዕክቶች የማህበራችን አለመሆኑን እናሳውቃለን ።

እውነት ሰባት ምድር ቢቀ~በር መውጣቱ አይቀርም:: ውሸት ሰባት ሰማይ ቢወጣ መውረዱ አይቀርም:: ~ተቀዳሚ ሙፍቲህ ሐጅ ዑመር እድሪስ ገነቴ ረዲየላሁ አንሁ
29/04/2026

እውነት ሰባት ምድር ቢቀ~በር መውጣቱ አይቀርም:: ውሸት ሰባት ሰማይ ቢወጣ መውረዱ አይቀርም::

~ተቀዳሚ ሙፍቲህ ሐጅ ዑመር እድሪስ ገነቴ ረዲየላሁ አንሁ

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when አርዱል ሀበሻ-Ardul habesha posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to አርዱል ሀበሻ-Ardul habesha:

Shortcuts

Share