Focus on Christ Jesus

Focus on Christ Jesus Jesus is the answer for every question.

31/08/2020
የዮሐንስ ወንጌል 154፤ በእኔ ኑሩ እኔም በእናንተ። ቅርንጫፍ በወይኑ ግንድ ባይኖር ከራሱ ፍሬ ሊያፈራ እንዳይቻለው፥ እንዲሁ እናንተ ደግሞ በእኔ ባትኖሩ አትችሉም። 5፤ እኔ የወይን ግንድ ...
29/08/2020

የዮሐንስ ወንጌል 15
4፤ በእኔ ኑሩ እኔም በእናንተ። ቅርንጫፍ በወይኑ ግንድ ባይኖር ከራሱ ፍሬ ሊያፈራ እንዳይቻለው፥ እንዲሁ እናንተ ደግሞ በእኔ ባትኖሩ አትችሉም። 5፤ እኔ የወይን ግንድ ነኝ እናንተም ቅርንጫፎች ናችሁ። ያለ እኔ ምንም ልታደርጉ አትችሉምና በእኔ የሚኖር እኔም በእርሱ፥ እርሱ ብዙ ፍሬ ያፈራል።

ወደ ሮሜ 831፤ እንግዲህ ስለዚህ ነገር ምን እንላለን? እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ከሆነ ማን ይቃወመናል?
29/08/2020

ወደ ሮሜ 8
31፤ እንግዲህ ስለዚህ ነገር ምን እንላለን? እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ከሆነ ማን ይቃወመናል?

06/05/2020

🟠ፅድቅ #ደመወዝ ሳይሆን #ስጦታ ነው🟠

⚔️ በመፅሐፍ ቅዱስ ጽድቅና መዳን የማይነጣጠሉ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታዎች ናቸው። ምክንያቱም ያለ ጽድቅ የሰው መዳን የማይታሰብ ስለሆነ ነው።

📙“ሰው በልቡ አምኖ #ይጸድቃልና በአፉም መስክሮ #ይድናልና።”
— ሮሜ 10፥10

⚔️ እዚሁ ክፍል ላይ ከፍ ብለን ስናነብ አንድ ሰው ለመጽደቅ ብሎም ለመዳን የኢየሱስን #ትንሳኤ ማመን እንዳለበት ይናገራል ። በርግጥ በትንሳኤው ያመነ ሁሉ በውስጥ ታዋቂነት በሞቱ ያምናል መቼም ሳይሞቱ ትንሳኤ ብሎ ነገር የለም።

📙“ኢየሱስ ጌታ እንደ ሆነ በአፍህ ብትመሰክር እግዚአብሔርም ከሙታን #እንዳስነሣው በልብህ ብታምን ትድናለህና፤”
— ሮሜ 10፥9

⚔️ በሮሜ መጽሐፍ ኢየሱስ ስለ #ሀጢያታችን እንደሞተ ይናገራል ነገር ግን በዚህ አይቋጨውም ይቀጥልና እኛን #ስለማጽደቅ ደግሞ ሞትን ድል አድርጎ ተነስቷል ይላል።

📙“.....ስለ በደላችን አልፎ የተሰጠውን እኛን ስለ ማጽደቅም የተነሣውን ....”
— ሮሜ 4፥24

💫በሞት ና ትንሣኤው
🕳 ሀጢያታችን 〰️በጽድቅ
🕳 ሞታችን 〰️በህይወት
🕳 እርግማናችን 〰️በበረከት
ሙሉ በሙሉ ተለውጧል ።

⚔️ይህ ሁሉ የሆነው በእግዚአብሔር ቸርነት ነው።
ፅድቅ ደመወዝ ሳይሆን ስጦታ ነው::

📙⁸ ጸጋው በእምነት አድኖአችኋልና፤ ይህም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው እንጂ ከእናንተ አይደለም፤
⁹ ማንም እንዳይመካ ከሥራ አይደለም።
---ኤፌሶን 2÷8

___________🙌🏼🙌🏼🙌🏼__________

____ኮሮና ቫይረስ የእግዚአብሔር ቁጣ ነውን?____ብዙ ሰዎች እንዲሁም ክርስቲያኖችንም ጨምሮ  #ኮሮና ቫይረስ የአምላክ ቁጣ ነው እንዲያውም አንዳንዶቹ ፈጣሪ እኛን ለማንቃት ያመጣው ነው ሲ...
25/03/2020

____ኮሮና ቫይረስ የእግዚአብሔር ቁጣ ነውን?____

ብዙ ሰዎች እንዲሁም ክርስቲያኖችንም ጨምሮ #ኮሮና ቫይረስ የአምላክ ቁጣ ነው እንዲያውም አንዳንዶቹ ፈጣሪ እኛን ለማንቃት ያመጣው ነው ሲሉ እንሰማለን።
ሌሎችም ይህን በጥቅስ አስደግፈው
📚 “በስሜ የተጠሩት ሕዝቤ ሰውነታቸውን አዋርደው ቢጸልዩ፥ ፊቴንም ቢፈልጉ፥ ከክፉ መንገዳቸውም ቢመለሱ፥ በሰማይ ሆኜ እሰማለሁ፥ ኃጢአታቸውንም ይቅር እላለሁ፥ ምድራቸውንም እፈውሳለሁ።”
— 2 ዜና 7፥14
ከእንደዚህ አይነት የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል በመነሳት እግዚአብሔር ከኛ አልፎ ስለምድሪቱ ሀጢያት እየጠየቅን ነው ሚሉም ብዙ ናቸው ። ስለዚህም ስለመፍትሔው ሲናገሩ ራሳችንን አዋርደን ንስሐ እንግባ ይላሉ ።
👉 በርግጥ ብዙ ሰዎች ልብ ባይሉም በኛ ዘመንና በሚጠቅሱአቸው የብሉይ ኪዳን ጥቅሶች ዘመን መካከል አንድ ትልቅ ክስተት አለ :- የኢየሱስ ክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ።
በዛው በ 2 ዜና 7÷5 መፅሐፍ ስንመለከት ንጉስ ሰለሞን በሺዎች የሚቆጠሩ በሬዎችንና በጎችን ሲሰዋ እንመለከታለን። እኛ ግን አሁን ይህን ማድረግ አአይኖርብንም ኢየሱስ ተሰውቷል ።ዮሐንስ ሲፅፍ
📚“በነገው ዮሐንስ ኢየሱስን ወደ እርሱ ሲመጣ አይቶ እንዲህ አለ፦ እነሆ የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር #በግ።”
— ዮሐንስ 1፥29

👉ስለ እኛ ኢየሱስ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ መስዋዕት ሆኖ ራሱን አቅርቧል ።
📚“አንድ ጊዜ በማቅረብ የሚቀደሱትን #የዘላለም ፍጹማን አድርጎአቸዋልና።”
— ዕብራውያን 10፥14

👉ለአለም ሁሉ ሀጢያት በቂ ከበቂም በላይ የሆነው መስዋዕት(ኢየሱስ) ከቀረበ በኋላ እግዚአብሔር ከአለሙ ጋር ታርቋል።
📚“እግዚአብሔር በክርስቶስ ሆኖ ዓለሙን ከራሱ ጋር #ያስታርቅ ነበርና፥ በደላቸውን አይቆጥርባቸውም ነበር፤ በእኛም የማስታረቅ ቃል አኖረ።”
— 2ኛ ቆሮ 5፥19

👉እግዚአብሔር ከክርስቶስ መስዋዕትነት በኋላ ዓለሙን ሁሉ ታርቆ እኛ ደግሞ ለዚህ ዕርቅ ምላሽ እንድንሰጥ በትዕግሥት ይጠብቃል።
📚“እንግዲህ እግዚአብሔር በእኛ እንደሚማልድ ስለ ክርስቶስ መልክተኞች ነን፤ ከእግዚአብሔር ጋር ታረቁ ብለን ስለ ክርስቶስ እንለምናለን።”
— 2ኛ ቆሮ 5፥20

👉ልብ በሉ እግዚአብሔር ከዐለሙ ሁሉ ጋር በልጁ ደም ታርቆ በአንጻሩ የኛን ምላሽ እየጠበቀ ነው።
በዚሁ አጋጣሚ አኔ ሀጢያተኛ ስለሆንኩ እግዚአብሔር በዚህ በሽታ ሊቀስፈኝ ነው ለምትሉ:- እግዚአብሔር የአንተን ቁጣ ሁሉ በልጁ ላይ አኑሮታል ምንም እንኳን ልጁ ፍፁም ፃድቅ ቢሆንም ስለአንተ ኃጢያት ሞቶ እዳህን ሁሉ ከፍሏል ከአንተ የሚጠበቀው በልጁ ማመን ነው።
👉መፅሐፍ ቅዱስ እግዚአብሔር ሰዎችን ወደንስሐ ለማምጣት በሽታንና መቅሰፍቶች ተጠቅሞ እንደሆነ አይናገርም ይልቁንም በመልካምነቱና በቸርነቱ እንጂ።
ልብ ብላችሁ ይህን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ተመልከቱ:-

📚“ወይስ የእግዚአብሔር ቸርነት ወደ ንስሐ እንዲመራህ ሳታውቅ የቸርነቱንና የመቻሉን የትዕግሥቱንም ባለጠግነት ትንቃለህን?”
— ሮሜ 2፥4

👉 እግዚአብሔር ሰዎች ሁሉ እንዲድኑ ይፈልጋል:-
📚“ሰዎች ሁሉ ሊድኑና እውነቱን ወደ ማወቅ ሊደርሱ በሚወድ በእግዚአብሔር በመድኃኒታችን ፊት መልካምና ደስ የሚያሰኝ ይህ ነው።”
— 1ኛ ጢሞቴዎስ 2፥3-4
📚“ለአንዳንዶች የሚዘገይ እንደሚመስላቸው ጌታ ስለ ተስፋ ቃሉ አይዘገይም፥ ነገር ግን ሁሉ ወደ ንስሐ እንዲደርሱ እንጂ ማንም እንዳይጠፋ ወዶ ስለ እናንተ ይታገሣል።”
— 2ኛ ጴጥሮስ 3፥9
👉 እንግዲህ ሁሉ እንዲድኑ የሚፈልገው ጌታ ሰዎችን ከመዳናቸው በፊት በወረርሽኝ ሊያጠፋ አይነሳም።
ይልቁንም መፅሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይለናል :-
📚“፥ ዲያብሎስ ጥቂት ዘመን እንዳለው አውቆ በታላቅ ቍጣ ወደ እናንተ ወርዶአልና።”
— ራእይ 12፥12
👉በወደቀ አለም እንደምኖር አትዘንጉ : ብዙ ጦርነት፣ ዘር ማጥፋት፣ ወንጀል ፣ ስርቆት ፣ በሽታ... ወዘተ ሁሌም የሚከሰትበት አለም ውስጥ እየኖርን ሲሆን ይህ ደግሞ የሰይጣንን መገኘት እንጂ በፍጹም የእግዚአብሔርን ህልውና አያመለክትም ።

🗝ነገር ግን የእግዚአብሔር ቁጣ ነው በማለት የኢየሱስን ሞትና ትንሳኤ ከንቱ የሚያደርግ ንግግር መንፈስ ወቅዱስ ያሳዝናል ።

🗝 በፀሎት ውጤት ማምጣት እንችላለን ደግሞ እናመጣለን።

_______________ኢየሱስ ጌታ ነው !!______________

ፈውስ የእግዚአብሔር ፈቃድ ነውን ???🤔🤔🤔የእግዚአብሔር ሀይል የሚለቀቀው ሁልጊዜ ፈቃዱ በሚታወቅበት ቦታ ነው። ለአንድ ሀጢያተኛ ሰው ወንጌል ያድንሃል ከማለታችን በፊት የርሱ መዳን የእግዚአ...
18/03/2020

ፈውስ የእግዚአብሔር ፈቃድ ነውን ???🤔🤔🤔

የእግዚአብሔር ሀይል የሚለቀቀው ሁልጊዜ ፈቃዱ በሚታወቅበት ቦታ ነው። ለአንድ ሀጢያተኛ ሰው ወንጌል ያድንሃል ከማለታችን በፊት የርሱ መዳን የእግዚአብሔር ፈቃድ መሆኑን ልናሳምነው ወይንም ሊያውቅ ይገባል።
👉እምነት የሚጀምረው ሁል ጊዜ የእግዚአብሔር ፈቃድ ሲታወቅ ነዉ።
የእግዚአብሔር ፈቃድ የተመረጡ ጥቂት ሰዎችን የመፈወስ የተቀሩትን ደግሞ በበሽታ ሊያስተምር አለያም ሊቀጣ ከሆነ, የትኛውም ሰው ታሞ ለፈውስ እግዚአብሔርን ከማመኑ በፊት እርሱ እንዲፈወስ እግዚአብሔር መፍቀዱን አለያም ከሚፈወሱ ጥቂት ሰዎች መሀከል መሆኑን ማረጋገጥ ይኖርበታል።
👉እምነት የሚመሰረተው በእግዚአብሔር ፈቃድ ላይ እንጂ በኛ ፍላጎት ወይም ምኞት ላይ አይደለም።
👉እንደውም ትክክለኛ እምነት በእግዚአብሔር መቻል ላይ ሳይሆን ፈቃደኝነት ላይ የተመሰረተ ነው። እግዚአብሔርማ ያለጥርጥር ሁሉን ቻይ 💪💪💪ኤልሻዳይ ነው።
ፈውስ በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ በመዋጀት ለሁላችንም የተቸረ ስጦታ ሆኖ ሳለ፤ ብዙዎች ግን አሁንም ''የእግዚአብሔር ፈቃድ ይሁን'' በማለት መንፈሳዊ በሚመስል የሀይማኖት ሐረግ ከበሽታቸው ተላቀው በእግዚአብሔር ፈቃድ ውስጥ ለመኖር ሲቸገሩ እናያለን።

17/03/2020

“ኢየሱስ ክርስቶስ ትናንትና ዛሬ እስከ ለዘላለምም ያው ነው።”
— ዕብራውያን 13፥8

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Focus on Christ Jesus posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share