Goro Sefera Full Gospel Believers Church: ጎሮ ሰፈራ ሙሉ ወንጌል ቤ/ክ

Goro Sefera Full Gospel Believers Church: ጎሮ ሰፈራ ሙሉ ወንጌል ቤ/ክ በጎሮ ሰፈራ ሙሉ ወንጌል ቤተክርስቲያን የተከናወኑ እና የሚከናወኑ ፕሮግራሞችን መከታተያ Page ነው፡፡

ማክሰኞ ሁላችሁም ተጋብዛችኋል
04/01/2026

ማክሰኞ ሁላችሁም ተጋብዛችኋል

22/09/2025
22/09/2025
17/09/2025
የግንቦት ወንጌል ተኮር ጉባኤ በምስል(ቀጥቂቱ)
18/06/2025

የግንቦት ወንጌል ተኮር ጉባኤ በምስል(ቀጥቂቱ)

ቀን 30ኢየሱስ መንግስተ ሰማይን ሲያስረዳ - የተከፈተ በር ግን ደግሞ ተከፍቶ የማይቀር እንደሆነ ይነግረናል።በተሰጠን ጊዜ እንድንገባ ኑ ይለናል። ጥሪው በጣም ግልፅ ነው።መግቢያ መንገዱም እ...
07/06/2025

ቀን 30

ኢየሱስ መንግስተ ሰማይን ሲያስረዳ - የተከፈተ በር ግን ደግሞ ተከፍቶ የማይቀር እንደሆነ ይነግረናል።በተሰጠን ጊዜ እንድንገባ ኑ ይለናል። ጥሪው በጣም ግልፅ ነው።መግቢያ መንገዱም እሱ ነው ግን ምርጫው ያንተ ነው በቶሎ ምረጥ

“በጠበበው በር ለመግባት ተጋደሉ፤ እላችኋለሁና፥ ብዙዎች ሊገቡ ይፈልጋሉ አይችሉምም።”
— ሉቃስ 13:24

የእግዚአብሔር መንግስት አሁን ክፍት ነው መግባት ደግሞ የሚቻለው በኢየሱስ በኩል ነው እናም ለነገ ቀጠሮ አትስጥ። በቋ ተብሎ ሚዘጋበትን ቀን አናውቅምና።



በኢትዮጵያ ሙሉወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን የጎሮ-ሰፈራ አጥቢያ

Tiktok | Facebook | Instagram|

ቀን 29ገነት አለ ....ሲኦልም አለ። ኢየሱስም ቢሆን ሳይነግረን አልተወውም። እንደውም በትክክል ገልጦልናል። ሲኦል ከእግዚአብሔር ጋር ተለይቶ መኖር እና የፍርድ ቦታ ነዉ። መልካሙ ዜና ግን...
06/06/2025

ቀን 29
ገነት አለ ....ሲኦልም አለ። ኢየሱስም ቢሆን ሳይነግረን አልተወውም። እንደውም በትክክል ገልጦልናል። ሲኦል ከእግዚአብሔር ጋር ተለይቶ መኖር እና የፍርድ ቦታ ነዉ። መልካሙ ዜና ግን እዛ መግባት አይጠበቅብህም።ኢየሱስ ከዛ ሊያድንህ ነው የመጣውና።

“ሥጋንም የሚገድሉትን ነፍስን ግን መግደል የማይቻላቸውን አትፍሩ፤ ይልቅስ ነፍስንም ሥጋንም በገሃነም ሊያጠፋ የሚቻለውን ፍሩ።”
— ማቴዎስ 10:28

እግዚአብሔር ማንም እንዲጠፋ ፍላጎት የለውም።ለዛም ነው እኛን ከቅጣት ለማዳን ኢየሱስ የሞተው። ሲኦል አለ እውነት ነው የእግዚአብሔርም ፍቅር እንደዛው። ምርጫው ያንተ ነው ሳይረፍድ ወደ ኢየሱስ ና



በኢትዮጵያ ሙሉወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን የጎሮ-ሰፈራ አጥቢያ

Tiktok | Facebook | Instagram|

ቀን 28ገነት ተረት ተረት፣ህልም፣ወይንም እንዲሁ ምልክት አይደለም። ገነት በእርግጥም አለ።ኢየሱስም ቃል ገብቷል። ቦታው በሰላም በደስታ እና ለዘላለም በሆነ የእግዚአብሔር መገኘት የተሞላ ነው...
05/06/2025

ቀን 28
ገነት ተረት ተረት፣ህልም፣ወይንም እንዲሁ ምልክት አይደለም። ገነት በእርግጥም አለ።ኢየሱስም ቃል ገብቷል። ቦታው በሰላም በደስታ እና ለዘላለም በሆነ የእግዚአብሔር መገኘት የተሞላ ነው።ሚገቡትም በስራቸው የተመሰገኑ ሳይሆኑ በኢየሱስ ያመኑት ናቸው። እና ቦታ አዘጋጅቷል እና ኑ እያለ ነው።

ዮሐንስ 14
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
² በአባቴ ቤት ብዙ መኖሪያ አለ፤ እንዲህስ ባይሆን ባልኋችሁ ነበር፤ ስፍራ አዘጋጅላችሁ ዘንድ እሄዳለሁና፤
³ ሄጄም ስፍራ ባዘጋጅላችሁ፥ እኔ ባለሁበት እናንተ ደግሞ እንድትሆኑ ሁለተኛ እመጣለሁ ወደ እኔም እወስዳችኋለሁ።

ኢየሱስ ቦታ እያዘጋጀልህ ነው ግን እሱን ለመከተል መወሰን አለብህ።ገነት አለ የኢየሱስ ግብዣም እንደዛው። ግብዣውን ተቀበል የመንግስቱም ተካፋይ ሁን



በኢትዮጵያ ሙሉወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን የጎሮ ሰፈራ አጥቢያ

Tiktok | Facebook | Instagram|

Address

Goro
Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Goro Sefera Full Gospel Believers Church: ጎሮ ሰፈራ ሙሉ ወንጌል ቤ/ክ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share