CHaha yoha

CHaha yoha 0919291211

28/02/2022
16/02/2022

❤ ❤
=================================

✍️ በአዲስ ኪዳን መጽሐፍት ውስጥ #ተደርጋችኋል እና #አደረጋቸው የሚሉ ቃላቶች ትልቅ ትርጉም የያዙ ናቸው። አድራጊው ቅዱሱ እግዚአብሔር ሲሆን ተደራጊወች ደግሞ በክርስቶስ የቤዛነት ስራ ያመኑ ቅዱሳን ሁሉ ናቸው።
ለምሳሌ እኛ በራሳችን መልካም ስራና ጥረታችን የእግዚአብሔር ጽድቅ መሆህ ስለማንችል እግዚአብሔር በክርስቶስ የራሱ ጽድቅ አደረገን። ተደርገን ከሆነ ከእኛ የሆነ ነገር የለም ማለት ነው።

✍️ የጸጋ አለም ውስጥ እግዚአብሔር አድራጊ ነው እኛ ደግሞ ተደራጊ ነን። እግዚአብሔር ሰጪ ነው እኛ ተቀባይ ነን።

✍️ስለ ክህነት መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?
---------------------------------

📌 ካህን ማለት በእብራይስጥ "ኮኸን" በግሪክ ደግሞ "ሂሪዬስ (hiereús)" ማለት ሲሆን ትርጉሙም
ወደ እግዚአብሔር የሚቀርብ ፣ የሚያገለግልና መስዋዕት የሚያቀርብ ማለት ነው።

✍️ በብሉይ ኪዳን ዘመን ለአሮን እና ለአሮን ቤተሰብ ይህ እድል ተሰቷቸው ነበር። ነገር ግን ይህ የአሮን ክህነት በመሀላ ያልጸና ጊዜያዊ ስለነበር ሊቀጥል አልቻለም እግዚአብሔርም በኢየሱስ ክርስቶስ ሞትና ትንሳኤ አስወግዶታል።

✍️በአዲስ ኪዳን ግን በክርስቶስ የቤዛነት ስራ ያመኑ ቅዱሳን ሁሉ ካህናት የሆኑበትና ኢየሱስ ክርስቶስ ደግሞ ሊቀ-ካህናት (የካህናት አለቃ) የሆነበት ዘላለማዊ የክህነት ስርዓት እንደመጣ መጽሐፍ ቅዱስ ይነግረናል።ከዚህም የተነሳ በአዲስ ኪዳን የሚገኝ አንድ አማኝ በብሉይ ኪዳን ከነበረው የአሮን ክህነት በተሻለ ክብር ለማገልገል ተጠርቷል። ዕብ 7:11-28, ዕብ8:1-13

✍️ በሀይማኖቶች ዘንድ ሰዎች ካህን ለመሆን አድርጉ የሚባለውን በማድረግ ፣ አጥኑ የተባለውን በማጥናትና ሐይማኖታዊ ስርአቶችን በመፈጸም ይደክማሉ ይጥራሉ ያም ሆኖ ግን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ካህናት መሆን አልቻሉም።

✍️ መጽሐፍ ቅዱስ ግን ካህን መሆን የሚቻለው በክርስቶስ ደም እንደሆነ ይናገራል። ስለዚህ በመጽሐፍ ቅዱሱ እውነት መሰረት በክርስቶስ ያመኑ ቅዱሳን ሁሉም በክርስቶስ ለሰማይ አምላክ ካህናት ተደርገዋል ይለናል።

#ራእይ 1፡4-6, እና #ራእይ 5:9-10
ለወደደን_ከኃጢአታችንም_በደሙ_ላጠበን፤ መንግሥትም ለአምላኩና ለአባቱም #ካህናት ፥ ለእርሱ ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ ክብርና ኃይል ይሁን፤ አሜን።

ራእይ 5 (Revelation)
9-10፤ መጽሐፉን ትወስድ ዘንድ ማኅተሞቹንም ትፈታ ዘንድ ይገባሃል፥ ታርደሃልና፥ በደምህም ለእግዚአብሔር

ከነገድ ሁሉ ከቋንቋም ሁሉ ከወገንም ሁሉ ከሕዝብም ሁሉ ሰዎችን ዋጅተህ ለአምላካችን መንግሥትና #ካህናት ይሆኑ ዘንድ አደረግሃቸው፥ በምድርም ላይ ይነግሣሉ፡ እያሉ አዲስን ቅኔ ይዘምራሉ።

✍️እነዚህ ጥቅሶች በክርስቶስ የቤዛነት ስራ የተዋጁት ቅዱሳን ሁሉ ካህናት እንደተደረጉ የሚናገሩ ናቸው።

✍️ቅዱሳን ሁለት አይነት የክህነት አገለግሎት እንደተሰጠን ልብ ልንል ይገባናል፦
==================================

📌 1, ቅዱሳን ካህናት፦
----------------------
1ጴጥ 2:4-5
ይህኛው የክህነት አገልግሎት ወደ እግዚአብሔር መንፈሳዊ መስዋዕት የምናቀርብበት ሲሆን። ለአምላክ ብቻ መስዋትን አምልኮን ውዳሴን የምንሰዋበት ሰማይ ተኮር የክህነት አገልግሎት ነው።

1 ጴጥሮስ 2 (1 Peter)
5፤ እናንተ ደግሞ እንደ ሕያዋን ድንጋዮች ሆናችሁ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ለእግዚአብሔር ደስ የሚያሰኝ መንፈሳዊ መሥዋዕትን ታቀርቡ ዘንድ ቅዱሳን ካህናት እንድትሆኑ መንፈሳዊ ቤት ለመሆን ተሠሩ።

📌 2 ,የንጉስ ካህናት፦
-------------------
1ጴጥ 2:9
ይህኛው የክህነት አገልግሎት የእርሱን በጎነት ለሰው ሁሉ የምናውጅበት ነው። ይህኛው የክህነት አገልግሎት የእግዚአብሔር መልካምነት ለሰው ልጆች ያለውን ፍቅር በክርስቶስ የሰራውን ስራ ለሰው ሁሉ በመናገር የምናገለግልበት ክህነት ነው።

1 ጴጥሮስ 2 (1 Peter)
9፤ እናንተ ግን ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃኑ የጠራችሁን የእርሱን በጎነት እንድትናገሩ የተመረጠ ትውልድ፥ የንጉሥ ካህናት፥ ቅዱስ ሕዝብ፥ ለርስቱ የተለየ ወገን ናችሁ፤

✍️ኤፌሶን 1
6፤ በውድ ልጁም እንዲያው የሰጠን የጸጋው ክብር ይመሰገን ዘንድ ይህን አደረገ።

✍️ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን።

የወንጌል እውነት አገልግሎት ጅማ
Gospel Truth Ministry Jimma.

15/02/2022

#እግዚአብሔር ነው ብርሃኔ/Egziabeher new brhane/ፓስተር እንዳለ ወ/ጊዮርጊስ/Pastor Endale w/giorgis/music composer Mezemure Dawit/January 16/2022 Follow us on Facebook: https:...

15/02/2022

DIVINE SHOW

14/02/2022

Address

Etiopio
Addis Ababa

Telephone

+251919291211

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when CHaha yoha posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share