18/08/2026
?
📖
:1-9
በህይወታችን የህይወት ሽግግር ሁሌ ይኖረናል ከልጅነት ወደ ወጣትነት ከጎልማሳነት ወደ ሽምግልና,ከላጤነት ወደ ማግባት ወደ መዉለድ በጣም በብዙ ነገሮች ዉስጥ እናልፋለን ከስራ ማጣት ወደ ስራ ማግኘት እሄ ሁሉ የሚያቆምበት ጊዜም ደግሞ አለ።ኢኮኖሚዉ ይለዋወጣል ጊዜዉ በፈጠነ መልኩ ቅርፁን ይቀይራል
ብዙ Transition አሉ በጊዜዉ እርግጠኛ መሆን አንችልም
ዉስጥ የማይለዋወጠዉን የእግዚአብሔር እዉነት መያዝ አለብን። ይዘን መዝለቅ ያለብን የማይለወጠዉን እግዚአብሔርን ነዉ
እንደ እኛ የህይወት transition ጊዜ ላይ የነበረ ሰዉ አለ #ኢያሱ
#ለክርስቲያን ስኬት ምንድነዉ? መለኪያዉስ ምንድነዉ? ከኢያሱ ምን እንማራለን
ስኬት ላይ እንዳለን መለኪያዉ ዉጪ መዉጣት ነዉ?ገንዘብ መያዝ ነዉ? ብዙ ልጆች መዉለድ ነዉ?
👉የስኬት መለኪያዉ:- የሚያናዉጥ ነገር እየተፈጠረ ከባድ ነገሮች እንኳን እየሆነ በዉስጣችን ዉስጥ ባለዉ ሰላም,በዉስጣችን ባለዉ እረፍት ነዉ ልንለካዉ የምንችለዉ። 👉ስኬት ማለት የሚያናዉጥ ነገር እያለ አለመናወጥ የሚረብሽ ነገር እናለ አለመረበሽ እሱ የስኬት መለኪያ ነዉ።ሰላም በሌለበት ዉስጥ እኔ ሰላም ነኝ ወይ? እሄን ጥያቄ መጠየቅ አለብን
ስኬታችን ከሰላማችን ጋር ስኬታችን ከደስታችን ጋር የተያያዘ ነዉ።ብዙ ገንዘብ ያላቸዉ ሰላምም ደስታም የላቸዉም የማያሳርፍ ነገር ዉስጣቸዉ ዉስጥ አለ።
👉በክርስቶስ ዉስጥ በመሆን ነዉ ስኬታችንን የምናረጋግጠዉ
ያላረፉ ሰዎች አያሳርፉም ደስታችን ምን ላይ የተንጠለጠለ ነዉ? እረፍታችንስ? ,"በጌታ ደግሞ ደስ ይበላችሁ"
እጅ በብዙ ያየ ሰዉ ነዉ እስራኤልን ከግብፅ ከማዉጣት ጀምሮ ያደረገዉን እያየ ያደገ የእግዚአብሔርን ተአምራት እያየም የመጣ ነዉ በዛዉ ልክ ደግሞ የሕዝብን አመፅም ያየ ሰዉ ነዉ።ኢያሱ የነበረበት ጊዜ የሽግግር ጊዜ ላይ የነበረ ሰዉ ነበር። የሽግግሩ ግዜ ለኢያሱ አስደንጋጭ እንደነበረ ማስረጃዉ በርታ ፅና አይዞህን አትፍራ አትደንግጥ እያለ እግዚአብሔር ያበረታታዋል።
ጨረሰ?
ኢያሱ 1:5 በሕይወትህ ዕድሜ ሁሉ ማንም አይቋቋምህም፤ ከሙሴ ጋር እንደ ሆንሁ እንዲሁ ከአንተ ጋር እሆናለሁ፤ አልጥልህም፥ አልተውህም።
(1)
ከሙሴ ጋር እግዚአብሔር ነበር በሚገርም ሁኔታ ግን በሙሴ የተኛን ባህር ነበር የተከፈለዉ በኢያሱ ግን ባለፈ ክብር ነበር እግዚአብሔር የተገለጠዉ ኢያሱ ግን እግዚአብሔር አብሮት ከመሆኑ የተነሳ እየወረደ ያለ ዉሃን ነዉ ያስቆመዉ እሄ የሚያሳየዉ የእግዚአብሔርን አብሮነት መኖሩ ማሳያ ነበር የማይሆን ነገር ሆነ።
የእግዚአብሔር አብሮነት ልዮነት ይፈጥራል መንፈስ ቅዱስን በህይወታችን በማሳዘን ግን በዉስጣችን ፀጥ እንዲል ማድረግ የለብንም።
ሃይላችን እንደ እድሜያችን ነዉ ወይ?ለምንድነዉ የምንፈራዉ የምንረበሸዉ
#የእግዚአብሔር አብሮነት በሁለት ይገለጣል (1 )በሃይል ይገለጣል (2) በታምራት ይገለጣል።በእነዚህ ነገሮች አብሮነቱን ያሳየናል
👉የመንፈስ ቅዱስ ፍሬስ በህይወታችን ይገለጣል ዙርያችን ያሉት ሰዎች የመንፈስ ቅዱስ ፍሬን በእኛ ዉስጥ ያያሉ ወይንስ የሰዎችን ሰላም እናፈርሳለን ሰዎች እንደሚረበሹ እንረበሻለን? የቱ ጋር ነዉ ያለነዉ? በጌታ ቤት እረጅም ጊዜ ኖረናል ግን የምንለይበት ነገር የለንም።ስለዚህ ልዮነት መኖር አለበት እግዚአብሔር በሃይልም በታምራትም ይሰራል
(2)የእግዚአብሔር ቃል አብሬክ እንድወጣ እድገባ ሙሴ የነገረህን የዚህን ፃፈዉ ከእሱ ወደ ግራም ወደቀኝም አትበል ስኬትህ ያለዉ እዚህ ላይ ነዉ ያኔ ይሳካልሃል ይከናወንልሃልም አለዉ።
ነዉ ለኢያሱ እግዚአብሔር የሰጠዉ አንተ ቃሉን ያዝ እኔ ዉጤት እሰጥሃለሁ አለ እግዚአብሔር ።እኛም እያንዳንዱን ነገር በእግዚአብሔር ቃል መመርመር አለብን ዉጤታችን ስኬታችን እሱ ላይ ነዉ።አረማመዳችን ጉዋደኞቻችንን መምረጥ ከቃሉ አንፃር መሆን አለበት።ዉጤታማነታችን በቃሉ ስለሆነ እያንዳንዱን ነገር በእግዚአብሔር ቃል ካደረግነዉ ይሳካልናል።
የምንሰማዉን ሁሉ እንዳንቀበል ማጥለያ የእግዚአብሔር ቃል አለን።
ኢያሱ ምዕራፍ 24 ላይ እግዚአብሔር እንደተናገረ ኢያሱን የዉጤት ሰዉ አደረገዉ ኢያሱም በእግዚአብሔር ያለዉ መተማን ከሁል ጊዜዉ በላይ የበለጠ ሆኖ የምታመልኩትን ምረጡ እኔ እና ቤቴ ግን እግዚአብሔርን እናመልካለን ብሎ በእግዚአብሔር ያለዉን መተማን አሳየ
እንደቃሉ ከሆንን እንደቃሉ እየኖርን ከሆነ ይሳካልናል እንደ እድሜያችን ልክ ዉጤታማ እንሆናልን። #አሜን