AAU - Muslim Students Union

AAU - Muslim Students Union The Official Page of AAU - MSU

Telegram: t.me/aaumsu
Twitter: twitter.com/aaumsu12
(1)

የፌደራል መጅሊስ ፕሬዚዳንት ሸይኽ ሐጂ ኢብራሒም ቱፋ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች ላይ እየደረሰ ስላለው የመብት ጥሰት ከ19 ወራት ቡሃላ የመጀመሪያ ንግግራቸውን አድርገዋል። እ...
21/04/2026

የፌደራል መጅሊስ ፕሬዚዳንት ሸይኽ ሐጂ ኢብራሒም ቱፋ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች ላይ እየደረሰ ስላለው የመብት ጥሰት ከ19 ወራት ቡሃላ የመጀመሪያ ንግግራቸውን አድርገዋል። እርሳቸው እንደተናገሩት ከዶክተር ሳሙኤል እና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት አድርገዋል። የሀሩን ሚዲያ ዘገባ እንደሚያመላክተው ደግሞ ስለጨቋኙ መመሪያ የተናገሩት ነገር የለም።

አሁንም ጥያቄያችን ግልፅ ነው። መጅሊስ ሀላፊነቱን በአግባቡ ይወጣ። የተበደሉ ተማሪዎች አስፈላጊው ካሳ ይሰጣቸው። ጨቋኙ መመሪያ ይሻሻል።

ጥያቄ አለን _ መልስም እንፈልጋለን!!!

AAU - Muslim Students Union

የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች ሕብረት ዩኒቨርስቲው በሙስሊም ተማሪዎች ላይ እያደረሰ ባለው የመብት ጥሰት ዙሪያ የፍትሕ ሚኒስቴር አስቸኳይ የሕግ ጣልቃ ገብነት እንዲያደርግ ጠየቀ ...
20/04/2026

የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች ሕብረት ዩኒቨርስቲው በሙስሊም ተማሪዎች ላይ እያደረሰ ባለው የመብት ጥሰት ዙሪያ የፍትሕ ሚኒስቴር አስቸኳይ የሕግ ጣልቃ ገብነት እንዲያደርግ ጠየቀ ! ! !

--------------------------------------
ሚያዚያ 12 / 2018 ዓ.ል
--------------------------------------

አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ፍትሕን የሚያጓድል መመሪያ አውጥቶ ለ19 ወራት ያክል በሙስሊም ተማሪዎች ላይ የመብት ጥሰት ሲፈፅም እንደነበር ይታወቃል። ፍትሕ ይሟላ ዘንድም ሙስሊም ተማሪዎች ያለፉትን ጊዜያት በሰላማዊ መንገድ ደጋግመው ለመጠየቅ ቢሞክሩም በዶክተር ሳሙኤል ፕሬዚዳንትነት የሚመራው የዩኒቨርስቲው አመራር የውይይት በርን ዘግቶ በበደሉ ላይ ቀጥሏል። የፍትሕ ሚኒስቴር የሕግ የበላይነትን የማረጋገጥ እና የዜጎችን ሕገ-መንግስታዊ መብቶች የማስከበር ያለበት ተቋም እንደመሆኑ አስቸኳይ የሕግ ጣልቃ ገብነት አድርጎ በሙስሊም ተማሪዎች ላይ እየደረሰ ያለውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት እንዲያስቆም እና ኢ- ሕግመንግስታዊው መመሪያ እንዲሻሻል አስተዋፅዖ እንዲያደርግ ተጠይቋል።

ጥያቄ አለን _ መልስም እንፈልጋለን !

AAU - Muslim Students Union

የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች ሕብረት ዩኒቨርስቲው በሙስሊም ተማሪዎች ላይ እያደረሰ ባለው የመብት ጥሰት ዙሪያ የትምህርት ሚኒስቴር አስቸኳይ የሕግ ጣልቃ ገብነት እንዲያደርግ ጠየ...
20/04/2026

የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች ሕብረት ዩኒቨርስቲው በሙስሊም ተማሪዎች ላይ እያደረሰ ባለው የመብት ጥሰት ዙሪያ የትምህርት ሚኒስቴር አስቸኳይ የሕግ ጣልቃ ገብነት እንዲያደርግ ጠየቀ ! ! !

--------------------------------------
ሚያዚያ 12 / 2018 ዓ.ል
--------------------------------------

አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የሙስሊም ተማሪዎችን ሰብዓዊ መብት በመጋፋት የሐይማኖት ነፃነት መብታቸውን የሚጋፋ መመሪያ አውጥቶ ላለፉት 19 ወራት ተማሪዎችን ለእንግልት እና ለስነ-ልቦና ጫና ሲዳርግ እንደቆየ ይታወቃል። ይህንን ተከትሎም ሙስሊም ተማሪዎች የተፈፀመው የመብት ጥሰት ቆሞ ተማሪዎች ነፃነታቸው ተከብሮላቸው ይማሩ ዘንድ ተደጋጋሚ ጥሪዎችን ቢያደርጉም አሻፈረኝ በማለት ለተማሪዎቹ ቅሬታ ጆሮዳባ ልበስ ብሏል።

የውይይት በር መዘጋቱ የመብት ጥሰቶቹ ተደጋግመው እንዲፈፀሙ መደላድል ከመስጠቱ ባሻገር ተማሪዎችን አላስፈላጊ ለሆኑ ጫናዎች እየዳረገ ነው። ይህ በቶሎ ቆሞ ችግሮች በውይይት ይፈቱም ዘንድ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች ሕብረት በዛሬው እለት ለትምህርት ሚኒስቴር ደብዳቤ አስገብቷል። በደብዳቤውም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ፦

1ኛ፦ የዩኒቨርስቲው አድሏዊ መመሪያ የዜጎችን የመማር መብትና ሕገ- መንግስታዊ ነፃነት በሚፃረር መልኩ የወጣ በመሆኑ፤ በአስቸኳይ እንዲነሳና መመሪያው እንዲሻሻል ጥብቅ ትዕዛዝ እንዲሰጥ።

2ኛ፦ ዩኒቨርስቲው ለደህንነት ፍተሻ ያቀረብናቸውን ዘመናዊ እና ሐይማኖታዊ መብትን የማይጋፉ አማራጮች ተግባራዊ እንዲያደርግ ግፊት እንዲደረግ

3ኛ፦ ኒቃብ ለባሽ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው ሳይሰተጓጎሉ እኩልነታቸው ተከብሮ እንዲማሩ ክትትል እንዲደረግ

ተጠይቋል።

ጥያቄ አለን _ መልስ እንፈልጋለን !

AAU - Muslim Students Union

የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሙስሊም ሴቶች በዩኒቨርሲቲው እየደረሰባቸው ስላለው የሰብዓዊ መብት ጥሰት ድምፅ ይሆኗቸው ዘንድ በEBC እና ፋና ዋና ፅ/ቤት በመገኘት አቤቱታ አቀረቡ ! ! !----...
31/03/2026

የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሙስሊም ሴቶች በዩኒቨርሲቲው እየደረሰባቸው ስላለው የሰብዓዊ መብት ጥሰት ድምፅ ይሆኗቸው ዘንድ በEBC እና ፋና ዋና ፅ/ቤት በመገኘት አቤቱታ አቀረቡ ! ! !

--------------------------------------------
መጋቢት 22 / 2018 ዓ.ል
--------------------------------------------

ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት ከሆኑ ቡሃላ የሙስሊም ተማሪዎችን ሒጃብ (ኒቃብ) የመልበስ ሰብዓዊ መብት የሚከለክል ኢ- ሕገመንግስታዊ መመሪያ ወጥቶ ተማሪዎች ለመጠነ ሰፊ እንግልት መዳረጋቸው የሚታወቅ ነው። ይህንንም ተከትሎ ላለፉት 18 ወራት ዘርፈ ብዙ እንቅስቃሴዎች የተደረገ ሲሆን ባለፉት ሳምንታት ውስጥ በማህበራዊ ሚዲያ በተደረገ ዘመቻ የሁሉም ኢትዮጵያዊ የጋራ ሐብት የሆኑት እነ EBC: FANA እና ሌሎች ሚዲያዎች የተማሪውን ድምፅ እንዲያስተጋቡ፤ ዩኒቨርሲቲውን እና አመራሩንም ተጠያቂ እንዲያደርጉ ሲጠየቅ ነበር።

ሆኖም ምላሽ ባለመገኘቱ በዛሬው እለት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ሴት ተማሪዎች በሚዲያዎቹ ጽ/ቤት በመገኘት ሚዲያዎቹ ሚዛናዊ እና ፍትሐዊ ዜናዎችን በመስራት እና ዘገባዎችን በማውጣት በሙስሊም ተማሪዎች ላይ እየደረሰ ስላለው የመብት ጥሰት ድምፅ ሆነው ሀላፊነታቸውን ይወጡ ዘንድ ጠይቀዋል።

በአላህ ፈቃድ መሠል እንቅስቃሴዎች በሙስሊም ተማሪዎች ላይ እየደረሰ ያለው ግፍ እስኪቆም ድረስ የሚቀጥል ይሆናል። በቀጣይ የሚኖሩ እንቅስቃሴዎችን እና ውጤቶችንም የምናሳውቃችሁ ይሆናል።

ጥያቄ አለን: ዛሬም ነገም!
ጥያቄ አለን: ፍትሐዊ መልስ እስኪመጣ!!
ጥያቄ አለን: ቢሮ ውስጥም በአደባባይም!

AAU - Muslim Students Union

Gaaffii Qabna !በዳይ በደሉን እስኪያቆም፤ ጨቋኝ ጭቆናውን እስኪገታ፤ ፍትሕ ሰፍኖ ተበዳይ እስኪካስ ጥያቄ አለን።We Have A Question We Want An Answer !!!ጥያቄ ...
24/03/2026

Gaaffii Qabna !

በዳይ በደሉን እስኪያቆም፤ ጨቋኝ ጭቆናውን እስኪገታ፤ ፍትሕ ሰፍኖ ተበዳይ እስኪካስ ጥያቄ አለን።

We Have A Question
We Want An Answer !!!

ጥያቄ አለን ! ! !

AAU - Muslim Students Union

19/03/2026

ጥያቄ አለን፦ በሁሉም ኢትዮጵያዊ ሀብት የተገነባው አንጋፋው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሙስሊም ተማሪዎችን መብት የሚጥስ መመሪያ ለምን እንዳወጣ ጥያቄ አለን! መማር ማስተማሩ በሰላም እየሄደ ባለበት ድንገት ተነስቶ ሒጃብ ለባሽ ሙስሊም ተማሪዎችን በር ላይ፤ ካፌ ውስጥ ብሎም በመማሪያ ክላስ ለምን ሊያንገላታ እንደፈለገ ጥያቄ አለን!!

ጥያቄ አለን፦ በሕዝብ ሐብት የተቋቋሙ የሕዝብ ሚዲያዎች (EBC: Addis media network ወዘተ...) ፤ ለሕዝበ ሙስሊም ድምፅ ይሆኑ ዘንድ የተቋቋሙ ሚዲያዎች ፤ ስለ ሰብዓዊ መብት ይገደናል የሚሉ አለምአቀፍ ሚዲያዎች (DW, BBC, Anadolu, TRT, Al-jezira etc...) ብሎም በሀገር ውስጥ ያሉ ተፅዕኖ ፈጣሪ የማህበራዊ ሚዲያ አውታሮች (ቲክቫህ፣ ATC etc..) እንዲሁም ሌሎች የሚመለከታቸው ሁሉ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ላይ ከአመት በላይ ሕገ-ወጥ መመሪያን ተገን ያደረገ የመብት ጥሰት ሲካሄድ ተገቢውን የሚዲያ ሽፋን ለምን እንዳልሰጡ ጥያቄ አለን!!!

ጥያቄ አለን፦ ስለ ሴቶች ተብሎ በሚኒስቴር መስሪያ ቤት ደረጃ የተቋቋመው የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳዮች ሚኒስቴር የሙስሊም ሴቶች መብት ሲጣስ ለምን ዝም እንዳለ ጥያቄ አለን። ስለ ሰብዓዊ መብት ተብሎ የተቋቋመው የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ሰብዓዊ መብት ሲጣስ አስቸኳይ እርምጃ ስለምን እንዳልወሰደ ጥያቄ አለን።

መልስም እንፈልጋለን። መልስ ፍትሐዊ መልስ እስኪሰጡም በሁሉም መንገድ እንጠይቃለን። መብታችን ስለሆነ። ተቋማቱ የእኛም ጭምር ስለሆኑ። መጠየቅ ግዴታችን ስለሆነ። መመለስም ግዴታቸው ስለሆነ።

ለመጠየቅ ዝግጁ ናችሁ? ለመጠየቅ ዝግጁ ነህ? ለመጠየቅ ዝግጁ ነሽ?

ዓለም አቀፍ የኢስላሞፎብያ መከላከያ ቀን (March 15, 2026) !  በተባበሩት መንግስታት መሪነት በአለምአቀፍ ደረጃ እየተሰራጨ ያለውን ሙስሊም ጠልነት ለመግታት ያለመ ፕሮግራም በድርጅቱ...
17/03/2026

ዓለም አቀፍ የኢስላሞፎብያ መከላከያ ቀን (March 15, 2026) !

በተባበሩት መንግስታት መሪነት በአለምአቀፍ ደረጃ እየተሰራጨ ያለውን ሙስሊም ጠልነት ለመግታት ያለመ ፕሮግራም በድርጅቱ አዳራሽ በየአመቱ March 15 ላይ ይካሄዳል። ከትላንት ወዲያም ቀኑ ነበርና በአዳራሹ የተገኙ ሰዎች መልዕክቶችን አስተላልፈዋል። እኛም በአሁኑ ሰዓት አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊሞችን የሚያገል መመሪያ ከማውጣት ጀምሮ ሙስሊም ተማሪዎች ላይ የሚፈፅመውን በደል ታሳቢ በማድረግ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ካስተላለፉት መልዕክቶች ጥቂቱን ለማስፈር ወደድን። መልዕክቱ በቀጥታ ለዩኒቨርሲቲው የተላለፈ ይመስላልና እንደወረደ አንብቡት።

መልዕክት 1:-

"...አድሎአዊ ትረካዎች በስልጣን ላይ ባሉ አካላት ሲስተጋገቡ፣ ጥላቻ እንደ ተለመደ ነገር ይቆጠራል። የተዛቡ አመለካከቶች (Stereotypes) ሳይታገሉ ሲቀሩ፣ ወደ ፖሊሲነት ይጠነክራሉ። ፍርሃት ውሳኔዎችን እንዲመራ ሲፈቀድ ደግሞ ኢፍትሃዊነት ይከተላል...”

ዋና ጸሐፊው አክለውም በእያንዳንዱ ሰው፣ በሁሉም ቦታ ለሚገኝ እኩልነት፣ ሰብአዊ መብትና ክብር” አዲስ ቁርጠኝነት እንዲኖር አሳስበዋል፤ እንዲሁም እየናረ የመጣውን ሙስሊም ጠልነትና ለሙስሊሞች ያለ ክፉ አመለካከትን ማዕበል ለማጥፋት እርምጃዎች እንዲወሰዱ ጥሪ አቅርበዋል።

እኛም የሚከተለውን እንላለን:- በስልጣን ላይ ባሉ ሰዎች አድሏዊ ትረካ፣ በእነርሱ የተዛባ አመለካከት እና በሌሎች ፍርሐት የወጣው አድሏዊ መመሪያ የሚሻርበት ጊዜ አሁን ነው። ለዚያ ደግሞ የእኛ የተስተካከለ ግንዛቤ፤ የተቀናጀ አካሄድ እና ቁርጠኝነት ያስፈልጋል። በዚህም የተስተካከለ እና ፍትሐዊ ከባቢን ለመጪው ትውልድ የምናወርስ ይሆናል።

ጥያቄዎቻችን ምን ምን ናቸው?1) በመመሪያ የተከሰከሰው የሙስለም ተማሪዎች ሒጃብ (ኒቃብ) በመመሪያ አውቅና ይሰጠው፡ መሠል የመብት ጥሰቶች ሲፈፀሙ የሚቀጣ ድንጋጌም ይውጣ፤2) ከጁምዓ የሶባት...
15/03/2026

ጥያቄዎቻችን ምን ምን ናቸው?

1) በመመሪያ የተከሰከሰው የሙስለም ተማሪዎች ሒጃብ (ኒቃብ) በመመሪያ አውቅና ይሰጠው፡ መሠል የመብት ጥሰቶች ሲፈፀሙ የሚቀጣ ድንጋጌም ይውጣ፤

2) ከጁምዓ የሶባት ሰዓት ጀምሮ አስከ ተራዊህ አና ተሐጁድ ድረስ ሴሚስቴር በሴሚስቴር፡ አመት በአመት ጭቅጭቅ አየተነሳ ስለሆነ ያንን የሚቀርፍ አወቃቀር ይዘርጋ፤

3) ላለፋት 18 ወሪት ጨቋኙ መመሪያ መውጣቱን ተከትሱ በደል ለደረሰባቸው ሙስሊም ተማሪዎች ካሳ ይሰጥ፤

4) ባለፋት 18 ወራት ጨቋኝ መመሪያን ከማውጣት ጀምሮ በሙስሊም ተማሪዎች ላይ በደል ሲፈፅሙ የነበሩ የዩኒቨርሲቲው አካላት ተጠያቂ ይሁኑ፤

5) ለለፋት ጊዜያቶች በዩኒቨርሲቲው አመራሮች አናውቅህም በመባል ሕውናው ለተገፈፈው መስለም ተማሪ እና ተወካዮቹ አውቅና ይሰጥ፤

6) ስለ ሙስሊም ተማሪዎች ጥያቄ በማንሳታቸው ብቻ በዩኒቨርሲቲው ክስ የተመሰረተባቸው ተማሪዎችን ዩኒበርሲቲው በይፋ ይቅርታ ይጠይቅ፤

7) በዩኒቨርሲቲ ውስጥ የሚሰሩ መሰረተ ልማቶች ኒቃብ የሚለብሱ ሴት ሙስሊም ተማሪዎችን ባገናዘበ እና ባካተተ መልኩ ይሁን።

ጥያቄዎቻችን አነኚህ ናቸው፡፡ አስቸኳይ አና ፍትሐዊ መልስ እንፈልጋለን። አስቸኳይ እና ፍትሐዊ መልስ አስኪመጣ ድረስ አንጠይቃን። አስፈላጊ በሆነው መንገዱ ሁሉ። ዛሬም ነገም፤ ቢሮም በአደባባይም፤ በሁሉም ጊዜ በሁሉም ቦታ እንጠይቃበን ፤ ጥያቄ አለን አንላለን።

13/03/2026

አላውቃችሁም እያለ የነበረው ዩኒቨርሲቲያችን ራሱ ባዘጋጀው ኢፍጣር፤ አመራሮቹ ባሉበት ጅግና እህቶቻችን ጥያቄ አለን! ብለው ከፍ ብለዋል።

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በግቢው የሚገኙ ሙስሊም ተማሪዎች ፊርማቸውን አሰባስበው ላስገቡት የመብት ጥያቄ አሰራርን የጣሰ፤ አሳፍሪ እና ለተማሪዎቹ ቦታ እንደሌለው የሚያሳይ ምላሽ ሰጠ!በቁጥር ...
13/03/2026

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በግቢው የሚገኙ ሙስሊም ተማሪዎች ፊርማቸውን አሰባስበው ላስገቡት የመብት ጥያቄ አሰራርን የጣሰ፤ አሳፍሪ እና ለተማሪዎቹ ቦታ እንደሌለው የሚያሳይ ምላሽ ሰጠ!

በቁጥር 1,141 የሚሆኑ፣ ማንነታቸው በውል የሚታወቅና በዩኒቨርሲቲው መዝገብ ላይ ያሉ ተማሪዎች፤ መብታችን ይከበር ብለው ያቀረቡትን አቤቱታ አስተዳደሩ በፌዝ መልሶታል። በደብዳቤው ላይ በጥቁር ስክሪቢቶ ስርዝ በማድረግ "እንደዚህ የሚባል ክበብ በዩኒቨርሲቲው ውስጥ አናውቅም። ተመላሽ ይደረግ!" የሚል አሳፋሪ ምላሽ ሰጥቷል። አስተዳደሩ የሰረዘው የወረቀት ላይ ፅሁፍ ሳይሆን የ1,141 ተማሪዎችን ህያው ድምፅ ነው።

በመጀመሪያ ደረጃ ተማሪዎች ፒቲሺን ፈርመው ሲያስገቡ የመጀመሪያቸው አይደለም። ከበፊት ጀምሮ ቅሬታ ሲኖራቸው ከዩኒቨርሲቲው ጀምሮ አስከ ጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት ድረስ አስገብተው ያውቃሉ። አሁን ላይም የተፈረመውን ፒቲሽን አልቀበልም ብሎ የመለሰው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ብቻ ነው። ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶችን ጨምሮ የሐይማኖት ተቋማት ድረስ ገብቷል።

በሁለተኛ ደረጃ 1141 የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች መብታችን ተነካ ብለው ስለመብታቸው ቅሬታ ያስገቡት በክበብ ደረጃ ተደራጅተው አይደለም። ክበብ ነኝ ብሎ ያልሄደን አካል እንዲህ የሚባል ክበብ አላውቅምና ምላሽ አልሰጥም ማለት ከግንዛቤ የራቀ ነው።

መጅሊስን ጨምሮ የሚመለከታችሁ የመንግስት አካላት፤ ዩኒቨርሲቲው የያዘው ይህ ግትርና ተማሪን አግላይ አካሄድ እንዲቆም፣ እንዲሁም የሙስሊም ተማሪዎችን መብት የሚያከብር መመሪያ እንዲያወጣ የበኩላችሁን እንድታደርጉ እንጠይቃለን።

እኛ "ክበብ" አይደለንም፤ እኛ የዚህ ተቋም ግማሽ አካል የሆንን ተማሪዎች ነን! ጥያቄያችን ህያው ነው፣ መልስም እንፈልጋለን!

ጥያቄ አለን!
መልስ እንፈልጋለን!

🌟 AAU Quran Competition 2025 – Final Round! 🌟Recite the Quran, for indeed, it will come on the Day of Judgment as an int...
24/04/2025

🌟 AAU Quran Competition 2025 – Final Round! 🌟

Recite the Quran, for indeed, it will come on the Day of Judgment as an intercessor for its companions. – Sahih Muslim

After weeks of heartfelt preparations and an incredible preliminary round competitions, the final round of the Addis Ababa University Quran Recitation Competition is here! 📖

🗓 Date: Sunday, April 27
🕜 Time: 01:30 PM – 05:30 PM (07:30 – 11:30 LT)
📍 Venue: Al-Aqsa Masjid, 6 Kilo

All AAU students are warmly invited to attend this blessed gathering and witness the top finalists as they showcase their love for the Quran.

Let’s come together to celebrate their dedication, sincerity, and talent.

Don't miss this spiritually uplifting event – prizes, unity, and beautiful Quranic recitation await!

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when AAU - Muslim Students Union posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to AAU - Muslim Students Union:

Share