Ethio Mujahid - ኢትዮ ሙጃሂድ

Ethio Mujahid - ኢትዮ ሙጃሂድ The bravest heart is the one that stays close to Allah, Even when it's in Pain

ጁምዐ ሙባረክቁባ መስጂድ (መሐል አምባ) ወለኔ ጉራጌ ዞን, ኢትዮጵያየ Ethio Mujahid - ኢትዮ ሙጃሂድ  Facebook ገፅ Follow/Like በማድረግ እንዲሁም ሌሎችን በመጋበዝ ቤተ...
16/12/2022

ጁምዐ ሙባረክ

ቁባ መስጂድ (መሐል አምባ) ወለኔ ጉራጌ ዞን, ኢትዮጵያ

የ Ethio Mujahid - ኢትዮ ሙጃሂድ Facebook ገፅ Follow/Like በማድረግ እንዲሁም ሌሎችን በመጋበዝ ቤተሰብ ይሁኑ!!

15/12/2022

የ Ethio Mujahid - ኢትዮ ሙጃሂድ Facebook ገፅ Follow/Like በማድረግ እንዲሁም ሌሎችን በመጋበዝ ቤተሰብ ይሁኑ!!

የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት(Amhara Region Islamic Affairs Higher Council)  በም/ቤቱ ፕሬዝዳት ሼኽ ጀውሃር ሙሃመድ እና በምክትላቸው ሼኽ ሙሀመድ...
15/12/2022

የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት(Amhara Region Islamic Affairs Higher Council) በም/ቤቱ ፕሬዝዳት ሼኽ ጀውሃር ሙሃመድ እና በምክትላቸው ሼኽ ሙሀመድ አንዋር ጁነይድ የተመራ ልዑክ በዛሬው እለት የሰሜን ጎንደር ዞን የእስልምና ጉዳዮች ምክር ቤትን በደባርቅ ከተማ በተሳካ ሁኔታ አዋቅሯል።

የ Ethio Mujahid - ኢትዮ ሙጃሂድ Facebook ገፅ Follow/Like በማድረግ እንዲሁም ሌሎችን በመጋበዝ ቤተሰብ ይሁኑ!!

15/12/2022

ለስራ ጉዳይ ወደ ሳውዲ አረቢያ ያቀናው የጠቅላይ ምክር ቤታችን ልዑክ ከሳኡዲ አረቢያ የእስልምና ጉዳዮች ሚኒስትር ጋር ተወያየ

ታህሳስ 06/2015

በሳኡዲ አረቢያ የስራ ጉብኝት እያደረጉ ያሉት በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝደንት ሼይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ የተመራው ከፍተኛ ልዑክ የሳኡዲ አረቢያ እስልምና ጉዳዬች ሚኒስትር ሼይኽ ዶ/ር አብዱለጢፍ ቢን አብድልአዚዝ አል ሼይኽ ጋር ተወያይቷል:

በውይይቱ ላይ ከክቡር ሚኒስትሩ በተጨማሪ የሳኡዲ የእስልምና ጉዳዮች ሚኒስቴር ተጠባባቂ ምክትል ፀሃፊ ዶ/ር አዋድ ቢን ሰዓብቲ አል-አንዚ እና በሚኒስቴሩ የስትራቴጂዎች ጠቅላይ ኮሚቴ ዋና ፀሃፊ ዶ/ር አህመድ አል-ፋሪስ ተካፍለዋል::

ከጠቅላይ ምክር ቤቱ በኩል ደግሞ ከፕሬዝደንቱ በተጨማሪ የጠቅላይ ምክር ቤቱ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት ሼክ አብዱልከሪም ሼይኽ በድረዲን፣ ዋና ፀሀፊው ሼክ ሀሚድ ሙሳ ፣ የፕሬዝዳንቱ አማካሪ ኡስታዝ አቡበክር አህመድ ፣ሼይኽ ሱልጣን አማን የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝደንት፣ ሼህ ኢድሪስ አሊ፣ ዶ/ር ጀማል መሐመድ ፣የኢፌዲሪ ቆንስል ጀኔራል አብዱልባሲጥ ከድር እና ሌሎች የልዑኩ አባላት ታድመዋል::

ክቡር ሚኒስትሩ ለመጅሊሱ አመራሮች መልካም አቀባበል ያደረጉላቸው ሲሆን የሳኡዲ አረቢያ እና የኢትዮጵያ ግንኙነት ለረጅም አመታት የዘለቀ እና በጠንካራ መሰረት ላይ የተገነባ መሆኑን አንስተው የኢትዮጵያ ሙስሊሞችን ከሚወክል ተቋም ጋርም ተቀራርቦ መስራት እና መተባበር አስፈላጊ መሆኑን ገልፀዋል::

ክቡር ሚኒስትር ዶ/ር አብዱልለጢፍ አል ሼይኽ የሳዑዲ መንግስት በቅን መሪዎቹ አማካኝነት በመላው አለም ለሚገኙ ሙስሊሞች ድጋፍ እና እርዳታ እንደሚያደርግ ጠቅሰው በሐይማኖታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ድጋፍ ለማድረግ ከጠቅላይ ምክር ቤቶች ጋር የግንኙነት ድልድዮችን መዘርጋቱን ጠቅሰዋል::

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሼይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ በበኩላቸው ሳዑዲ አረቢያ የአለም ሙስሊሞች መመኪያ መሆኗን በማረጋገጥ ለአለም ሙስሊሞች አንድነት እና መቀራረብ ከመስራት ጎን ለጎን በመልካም ግዜ ብቻ ሳይሆን በችግር እና በአደጋ ጊዜም ድጋፍ በማድረግ ቀዳሚ መሆኗን ገልፀዋል::

ሳዑዲ አረቢያ የሁለቱ ቅዱሳን መስጂዶች የበላይ ጠባቂ ሃገር እንደመሆኗ ለሁጃጆች የምታደርገው መስተንግዶ እና እንክብካቤ በቃላት ለመግለፅ የሚከብድ ነው ያሉ ሲሆን ይህን ታላቅ ተግባሯን ማንም ሊክድ አይቻለውም ብለዋል::

ክቡር ሚኒስትሩ ለሼይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ እና ለልዑክ ቡድናቸው ሳዑዲ አረቢያን እንዲጎበኙ፣ ኡምራም እንዲያደርጉ እና በተለያዩ ኢስላማዊ ዘርፎች ላይ በትብብር ለመስራት እንዲቻል ምክክር ለማድረግ ላደረጉላቸው ግብዣ እና መስተንግዶ ምስጋናቸው አቅርበዋል::

ከክቡር ሚኒስትሩ ጋር በነበረው ቆይታ ጠቅላይ ምክር ቤቱ ለመስራት ያቀዳቸውን ኢስላማዊ ፕሮጀክቶች ያቀረበ ሲሆን በቀረበው ፕሮጀክቶች ዙሪያም ሰፊ ውይይት እና ምክክር ተደርጎባቸዋል::

በውይይቱ ማጠቃለያ ላይም የጋራ መግባባት መድረስ ተችሏል::

በተመሳይይም በሳኡዲ አረቢያ በስራ ጉብኝት ላይ የሚገኘው የጠቅላይ ምክር ቤቱ ልዑክ በመካ የሚገኘውን የአባጅፋር የሑጃጆች ማረፊያ ያለበትን ሁኔታ የተመለከተ ሲሆን ማረፊያው ለኢትዮጵያውያን ሁጃጆች የተሻለ አገልግሎት መስጠት በሚችልበት ሁኔታ ላይም ከሚመለከተው አካል ጋር ምክክር አድርጓል::

© Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council

የ Ethio Mujahid - ኢትዮ ሙጃሂድ Facebook ገፅ Follow/Like በማድረግ እንዲሁም ሌሎችን በመጋበዝ ቤተሰብ ይሁኑ!!

የሂክማ እስላማዊ ዩኒቨርሲቲ የግንባታና አለም አቀፍ የገቢ አሰባሰብ ማስጀመሪያ ፕሮግራም በወራቤ ስታዲየም በመካሄድ ላይ ነው።በስልጤ ዞን ወራቤ ከተማ ለሚገነባው ሂክማ እስላማዊ ዩኒቨርሲቲ አ...
10/12/2022

የሂክማ እስላማዊ ዩኒቨርሲቲ የግንባታና አለም አቀፍ የገቢ አሰባሰብ ማስጀመሪያ ፕሮግራም በወራቤ ስታዲየም በመካሄድ ላይ ነው።

በስልጤ ዞን ወራቤ ከተማ ለሚገነባው ሂክማ እስላማዊ ዩኒቨርሲቲ አለም አቀፍ የገቢ አሰባሰብ ማስጀመሪያ ፕሮግራም ላይ ለመካፈል በሸህ ሀጂ ኢብራሂም ቱፋ የተመራ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ልኡክ ወራቤ ከተማ የገባ ሲሆን የስልጤ ዞን አስተዳደር አቶ አሊ ከድር አቀባበል አድርገውላቸዋል::

ፕሮግራሙን የስልጤ ዞን አሊሞች እንዲሁም ዱዐቶች እና የወራቤ ከተማ ሙስሊም ማህበረሰብ በወራቤ ስታዲየም በመገኘት በመታደም ላይ ይገኛል::

የ Ethio Mujahid - ኢትዮ ሙጃሂድ Facebook ገፅ Follow/Like በማድረግ እንዲሁም ሌሎችን በመጋበዝ ቤተሰብ ይሁኑ!!

05/12/2022

እከሌ አወገዘ? 🤔

ሰሞኑን በወለጋ ከተፈፀመ አሳዛኝ ክስተት ጋር ተያይዞ በሞቱ ሰዎች የፖለቲካ ትርፍ እንዲሁም ሴራ የሚጎነጉን አካል እየተመለከትን ነው:: ከነዚህም መካከል ሀገሪቱ በኡስታዞች የምትመራ እስከሚመስል ድረስ "ኡስታዞች አወገዙ ወይ?" የሚሉ ጩኸቶች ናቸው:: ይህንን ከሚያራግቡ መካከል ዋነኞቹ ሙስሊም ያልሆኑ ለእስልምና እና ለሙስሊሞች ግልፅ የሆነ ጥላቻ ያላቸው አካላት ሲሆኑ ሁለተኛዎቹ ደግሞ በእነዚህ አካላት ፕሮፓጋንዳ Brain wash የተደረጉ (ሙስሊሞችንም ያካትታል) ግለሰቦች ናቸው::

አንደኛ ሙስሊም ያልሆኑ "ኡስታዞች አወገዙ ወይ?" ለሚሉ በአጭሩ ዲያቆኖቻቹ ቄሶቻቹ አወገዙ ወይ በሚል መልስ ጥያቄያችሁን ልመልሰው:: ወደ ዝርዝሩ ስገባ "ኡስታዞች አወገዙ ወይ?" የሚሉ ግለሰቦች ከሚሞቱ ሰዎች በላይ የኡስታዞች ማውገዝ አለማውገዝ አጀንዳ ሊያደርጉት የሚፈልጉት ለፖለቲካዊ ግባቸው ነው:: ከነዚህም መካከል አንደኛው እስላማዊ ወንድማማችነት ነው:: እንደሚታወቀው እስልምና አለም አቀፋዊ ሀይማኖት ነው:: ድንበር ቋንቋ ዘር አይገድበውም ረሱል ﷺ ‹‹አንድ ሙስሊም ለሙስሊም ወንድሙ ነው፤ አይበድለው፣ ለሌሎችም አሳልፎ አይስጠው፤ በወንድሙ ጉዳይ ላይ የዋለ (የወንድሙን ጉዳይ የፈፀመ ሰው አላህ በርሱ ጉዳይ ላይ ይሆንለታል (ጉዳዩን ይሞላለታል)፤ ከሙስሊም አንዲትን ጭንቀት ያስወገደ በርሷ (ሰበብ) አላህ ከቂያማ ቀን ጭንቀቶች አንዲትን ያስወግድለታል፡፡ የሙስሊም ነውርን የሸፈነ አላህ የቂያማ ቀን ነውሩን ይሸፍንለታል፡፡›› ብለዋል:: እንኳን በአንድ ሀገር የሚኖሩ ህዝቦች ቀርቶ ባህር ተሻግሮ ያለ ሙስሊም ወንድማችን ነው:: እነዚህ በእስልምና እና በሙስሊሞች ጥላቻ የተሞሉ አካላት ከምንም በላይ ሊበጥሱት ከሚፈልጉት ነገር መካከል በሙስሊሞች መሀል ያለ እስላማዊ ወንድማማችነትን ነው:: ለዚህም ብሔር የምትባል ካርድ ከወቅቱ ጋር አመቺ ሆና ስላገኟት ሊመዟት ወደዋል:: እነሱ በብሔር ምክንያት የሀይማኖት ወንድማማችነትን ቆርጠው ተበታትነዋል ወደ ሙስሊሞች ስንመጣ በተሻለ መልኩ እስላማዊ ወንድማማችነትን ተጠብቆ አለ:: ይህ ከምንም በላይ እንቅልፍ ይነሳቸዋል:: የሙስሊሞች አንድነት ለእነርሱ ከምንም በላይ ስጋት ነው:: ይህን አንድነት ለማፍረስ ያልፈነቀሉት ድንጋይ የለም ከዚህም በቅርቡ መጅሊሱን አስታኮ የእከሌ ብሔር መጅሊሱን ተቆጣጠረው መጅሊሱ ለሁለት ተሰነጠቀ የሚል ጫጫታ ለመፍጠር ሞክረው ነበር:: አሁን ደግሞ እከሌ ኡስታዝ ያላወገዘው ብሔሩ እንዲህ ስለሆነ ነው አንተ ብሔርህ እህ ነው እያሉ ሆድ እያስባሱ ከሙስሊም ማንነቱ ለመነጠል እና ሁሉ ነገርን በዘር መነፅር እንዲመለከት እየጎተቱት ነው:: አንደኛ ግባቸውን እስላማዊ ወንድማማችነት መበጠስ በሚል እዚህ ጋር እንደምድመው::

ሁለተኛ ሟችም አንተ ገዳይም አንተ

በምዕራቡ አለም ሙስሊሞች ከሚገጥማቸው ጉዳዮች መካከል በሽብርተኞች ለሚፈፀሙ ጥቃቶች ከፊት ወጥታቹ ለምን አታወግዙም የሚሉ ናቸው:: ሙስሊሞች ምንም እጃቸው ለሌለበት አንዳንዴም ከሚኖሩበት ሀገር ርቆ ለተፈፀመ ጥቃት ሙስሊሞች እንዲያወግዙ የሚል የምዕራባውያን የድንቁርና ንግግር ነው:: ከሰሞኑ ኡስታዞች ለምን አላወገዙ የሚል ድንቁርና ተመሳሳይ ነው:: ከሙስሊሞችም ሆነ ከእስልምና ምንም የማይገናኝ አካል ለፈፀመው ወንጀል ኡስታዞች ግዴታ ማውገዝ አለባቸው የሚል ነው ዲያቆናት እና ቄሶች ለምን አያወግዙም:: ይህ ሀሳብ የሚመነጨው ካላወገዙ ቀጥሉ እንወንጅላቸው የሚል ቁማር ነው:: ለዚህም በማህበራዊ ሚዲያ የሚዘዋወሩ አክራሪ መምህራኖቻቸው የሚፅፉትን ማየት በቂ ነው:: ወለጋ ላይ ትሞታለህም ከዛም ትከሰሳለህም:: ሟችም አንተ ገዳይም አንተ ትሆናለህ::

ሶስተኛ ጎንደር ላይ ያወገዙ አሁን እንዴት አላወገዙም

አንድ በርካታ ተከታይ ያለው የ Facebook ገፅ ባህር ዳር ላይ ያለ የመጅሊስ አጥር እንዴት ፈረሰ ሲሉ የነበሩ ኡስታዞች የት አሉ ይላል ይህ የሚመነጨው ነገ እንኳን አጥሩን ህንፃውን ወይም አናትህን ባፈርሰው እንዴት አፉን አዘጋዋለው የሚል calculation ነው:: ብሎም ለፈጸሙት ወንጀል ነው justification ማቅረቢያ ነው:: ከዛም አለፍ ሲል በዚህ brainwashe ያደረጉት ግለሰብ ቢጠቃም አፉን ይዞ እንዲቀመጥ በዳዮቹን እምቢ የማለት ሞራል እንዳያገኝ ነው::

በመጨረሻም በየትኛውም አካባቢ በሙስሊሞች ብሎም በሌሎች ዜጎች ላይ የሚፈፀም ግድያ መፈናቀል ያመናል ያሳስበናል በወለጋ እየተፈፀመ ያለ ዘርን መሰረት ያደረገ ጥቃት ሊቆም ይገባል::

"ጠንካራ የሓላል ቁጥጥር ስርዓት ለተሻለ ጤና እና ኢኮኖሚ ልማት" በሚል ርዕስ በሸራተን አዲስ ሆቴል በኦሮሚያ መጅሊስ አዘጋጅነት ሲምፖዚየም እየተካሄደ ነው።ላለፉት 25 ዓመታት ከኢትዮጵያ ወ...
03/12/2022

"ጠንካራ የሓላል ቁጥጥር ስርዓት ለተሻለ ጤና እና ኢኮኖሚ ልማት" በሚል ርዕስ በሸራተን አዲስ ሆቴል በኦሮሚያ መጅሊስ አዘጋጅነት ሲምፖዚየም እየተካሄደ ነው።

ላለፉት 25 ዓመታት ከኢትዮጵያ ወደ ተለያዩ ሀገራት ኤክስፖርት የሚደረጉ ሥጋዎችን የሀላልነት ቁጥጥርና ማረጋገጫ በመስጠት ላይ የሚገኘው የኦሮሚያ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ነው ሲሆን በኳታር ለተዘጋጀው የዓለም ዋንጫ ከኡጋንዳ ሀገር የተላኩ ስጋዎችን የሀላልነት ማረጋገጫ የተሰጠው በምስራቅ አፍሪካ ብቸኛ እውቅናና ልምድ ባለው በኦሮሚያ መጅሊስ መሆኑ ተገልጿል። ለዚህም የኦሮሚያ መጅሊስ ባለሞያዎች ወደ ኡጋንዳ በማቅናት የኡጋንዳ ቄራዎች፣ አስተራረዱንና ጥራቱን ከፈተሹ በኋላ የሀላል ማረጋገጫውን መስጠታቸው ተጠቁሟል።

© Harun media ሃሩን ሚዲያ

የ Ethio Mujahid - ኢትዮ ሙጃሂድ Facebook ገፅ Follow/Like በማድረግ እንዲሁም ሌሎችን በመጋበዝ ቤተሰብ ይሁኑ!!

የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ኮንስታብል አንቡላ ኡቴን እንዴት በዋስትና ለቀቀው? ዋስትና ማለት አንድ በወንጀል የተከሰሰ ወይም የተጠረጠር ሰው የገንዘብ የሰው ወይም የንብረት ዋስ በ...
02/12/2022

የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ኮንስታብል አንቡላ ኡቴን እንዴት በዋስትና ለቀቀው?

ዋስትና ማለት አንድ በወንጀል የተከሰሰ ወይም የተጠረጠር ሰው የገንዘብ የሰው ወይም የንብረት ዋስ በማስያዝ ለግዜው ከእስር የሚፈታበት ስረዓት ሲሆን ተጠርጣሪውም ጉዳዩን ከእስር ውጭ ሆኖ የሚከታተልበት ሰርዓት ነው::

ዋስትና የተጠርጣሪ ወይም የተከሳሽ መስረታዊ መብት ቢሆንም ነገር ግን በህግ በተደነገጉ ልዩ ሁኔታዎች መሰረት የዋስትና መብቶች ሊከለከሉ ወይም ገደብ ሊደረግባቸው እንደሚችል ህገ- መንግስቱ በግልጽ ያስቀምጣል::

ከነዚህም ውስጥ

1.ተጠርጣሪው ወይም ተከሳሹ በዋስ ቢወጣ የሚጠፋ ይሆና ብሎ ካመነ ፍርድ ቤቱ ዋስትና የሚከለከል ሲሆን ይህም በወንጀንለኛ መቅጫ ስነስርዓት ህግ አንቀጽ 67(ሀ) ላይ መረዳት ይቻላል::

2.ተጠርጣሪው ወይም ተከሳሹ በዋስ ቢወጣ ምስክር ያባብላል ያስፈራራል ማስረጃ ያጠፋል ተብሎ ከተገመተ ዋስ ሊያስከለክል የሚችል መሆኑንን ከወንጀለኛ መቅጫ ስነ ስርዓት ህግ አንቀጽ 67(ሐ) ድንጋጌ መርዳት ይቻለል::

በተጨማሪ ሌሎች ህጎች ያሉ ሲሆን ለዚህ ጉዳይ እነዚህን ካነሳን ይበቃል:: በኮንስታብል አንቡላ ኡቴን የዋስትና ጉዳይ በፌደራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ 2ኛ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት ላይ ፖሊስ ግለሰቡ ሰዎችን ሊያስፈራራ ይችላል የዋስትና መብት ሊፈቀድለት አይገባም ሲል ተከራክሮ የነበረ ሲሆን ፍርድ ቤቱ ግን ጥያቄውን ውድቅ አድርጎታል:: በተጨማሪም እንዲህ ባለ በርካታ ህዝብ በታደመበት በዓል የሁከት መንስኤ ለበርካታ ንብረቶች መውደም በበዓሉ የታደሙ ሰዎች የአካል እና የስነ-ልቦና ጉዳት ምክንያት የሆነን ግለሰብ እንዲህ በቀላሉ በዋስትና መልቀቅ የፍርድ ቤቱን ውሳኔ ጥያቄ ውስጥ ይከታል::

የ Ethio Mujahid - ኢትዮ ሙጃሂድ Facebook ገፅ Follow/Like በማድረግ እንዲሁም ሌሎችን በመጋበዝ ቤተሰብ ይሁኑ!!

በኢድ አልፈጥር በዓል የጭስ ቦምብ በማፈንዳቱ ምክንያት በፍርድ ሂደት ላይ የሚገኘው ኮንስታብል አንቡላ ኡቴ መጥፋቱ ተዘገበ::የፌደራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል አድማ ብተና ዘርፍ ባልደረባ የሆ...
02/12/2022

በኢድ አልፈጥር በዓል የጭስ ቦምብ በማፈንዳቱ ምክንያት በፍርድ ሂደት ላይ የሚገኘው ኮንስታብል አንቡላ ኡቴ መጥፋቱ ተዘገበ::

የፌደራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል አድማ ብተና ዘርፍ ባልደረባ የሆነው ኮንስታብል አንቡላ ኡቴ ሚያዚያ 24 2014 ዓ.ል የኢድ አል-ፈጥር በዓል ላይ ባፈነዳው አስለቃሽ ጭስ ቦንብ ጋር ተያይዞ በፍርድ ሂደት ላይ የነበረ ሲሆን በተከሳሽ ጥያቄ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዋስትና የፈቀደለት ሲሆን ነገር ግን ግለሰቡ በቀጠሮው መሰረት ሳይቀርብ ቀርቷል:: በዚህም ፍርድ ቤቱ ፖሊስ ግለሰቡን አፈላልጎ በቁጥጥር ስር እንዲያውለው የጠየቀ ሲሆን ግለሰቡ በቁጥጥር ስር እስኪውል ድረስ ለጊዜው ክሱ እንዲቋረጥ ወስኗል::

ሚያዚያ 24 በተከሰተው ሁከት ኮንስታብል አንቡላ ኡቴ ጨምሮ በወቅቱ ክትትልና ቁጥጥር ባለማድረግ የስራ ኃላፊነታቸውን አልተወጡም በተባሉ የፌደራል ፖሊስ የኃይል አመራሮች በሆኑት ምክትል ኢኒስፔክተር ወዴ ከፈለ እና ዋና ሳጅን ስንታየሁ ዘሪሁን ላይ የወንጀል ክስ ተመስርቶ በፍርድ ሂደት ላይ ይገኛሉ::

የ Ethio Mujahid - ኢትዮ ሙጃሂድ Facebook ገፅ Follow/Like በማድረግ እንዲሁም ሌሎችን በመጋበዝ ቤተሰብ ይሁኑ!!

ጁምዐ ሙባረክኑር መስጂድ (አላባ ቁሊቶ) ደቡብ ክልል, ኢትዮጵያየ Ethio Mujahid - ኢትዮ ሙጃሂድ  Facebook ገፅ Follow/Like በማድረግ እንዲሁም ሌሎችን በመጋበዝ ቤተሰብ ...
02/12/2022

ጁምዐ ሙባረክ

ኑር መስጂድ (አላባ ቁሊቶ) ደቡብ ክልል, ኢትዮጵያ

የ Ethio Mujahid - ኢትዮ ሙጃሂድ Facebook ገፅ Follow/Like በማድረግ እንዲሁም ሌሎችን በመጋበዝ ቤተሰብ ይሁኑ!!

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአፋር ክልል ሰመራ ባወጣው የስልጠና እና የስራ ቅጥር መስፈርት ወንዶች ሙሉ በሙሉ ፂማቸውን እንዲላጩ ሴቶችም ሂጃባቸውን እንዲያወልቁ ጠየቀ::በኢትዮጵያ አየር (Et...
01/12/2022

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአፋር ክልል ሰመራ ባወጣው የስልጠና እና የስራ ቅጥር መስፈርት ወንዶች ሙሉ በሙሉ ፂማቸውን እንዲላጩ ሴቶችም ሂጃባቸውን እንዲያወልቁ ጠየቀ::

በኢትዮጵያ አየር (Ethiopian Airlines) መንገድ ተወዳድረው የፅሁፍ ፈተና ወስደው ያለፉ ግለሰቦች ለቃለመጠይቅ ስትመጡ ማሟላት ካለባችሁ መስፈርቶች መካከል ወንዶች ሙሉ በሙሉ ፂማችሁን እንድትላጩ ሴቶችም ሂጃባችሁን እንድታወልቁ ወይንም እንደ አየርመንገዱ አገላለፅ መደበኛ የፀጉር እና የአለባበስ ስታይል እንድትከተሉ ሲል አሳስቧል::

አየርመንገዱ በተመሳሳይ መልኩ በአዲስ አበባ ተወዳድረው ያለፉ ሙስሊም ሴቶችን በሂጃባቸው ምክንያት ስራ እንደነፈጋቸው የሚታወስ ነው:: በጉዳዩም የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት (Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council) ቅሬታውን እንደገለፀ የአየርመንገዱ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው በም/ቤቱ በአካል በመገኘት አየርመንገዱ ለጉዳዩ እልባት እንደሚሰጠው መግለጻቸው ይታወሳል:: ነገር ግን አየርመንገዱ ጉዳዩን ከመፍታት ይልቅ በጉዳዩ እንደገፋበት እና ሙስሊሞች ላይ አግላይ መመሪያዎችን ማውጣት እና ማስተግበር መቀጠሉ መረዳት ይቻላል::

አየርመንገዱ ያወጣው መስፈርት አስተያየት መስጫው ስር ተያይዟል

Update:- አየር መንገዱ በአፋር ክልል ሰመራ ያወጣው መስፈርት በተመሳሳይ መልኩ በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ አውጥቷል

የ Ethio Mujahid - ኢትዮ ሙጃሂድ Facebook ገፅ Follow/Like በማድረግ እንዲሁም ሌሎችን በመጋበዝ ቤተሰብ ይሁኑ!!

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethio Mujahid - ኢትዮ ሙጃሂድ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share