Islamic World

Islamic World እስላማዊ ዳዐዋ ,,
እስላማዊ ትምህርት
ሀዲስ , ቁርዓን , ኪታብ
Islamic Dawa'*
Islamic Quotes
Islamic Pictures
Islamic Education

አንድ ደግ ሰው በፈረስ ከሩቅ ሃገር ወደ መንደሩ ሲመለስ  ================በጫካ ውስጥ አንድ ሌባ ሰው የታመመ በመምሰል" ጌታው አትለፈኝ እባክህ?! ከባድ የሆነ ሆድ ቁርጠት ይዞኛል...
15/05/2022

አንድ ደግ ሰው በፈረስ ከሩቅ ሃገር ወደ መንደሩ ሲመለስ ================
በጫካ ውስጥ አንድ ሌባ ሰው የታመመ በመምሰል
" ጌታው አትለፈኝ እባክህ?! ከባድ የሆነ ሆድ ቁርጠት ይዞኛል። በምትወደው ከዚህ ጥለሀኝ ከሄድ እየመሸ ስለሆነ አውሬ ይበላኛል" ብሎ ይማጸነዋል::
ደጉም ሰው ያዝንለትና "አይዞክ ወንድሜ" ብሎ ከፈረሱ ላይ ተሸክሞ ያወጣዋል።
የፈረሱንም ሉጋም ይዞ በእግሩ ፊት ፊት ይመራዋል።
ሌባውም "ጌታው በግርህ ለራስክ ከመሄድ ይልቅ የፈረሱን ልጓም ይዘክ ስትመራኝ ጀንበር እያዘቀዘቀች ስለሆነ እንቅፋት ይመታካል:: ተሰናክለክም ብትወድቅ ጉዳት ይሆናልና እርካቡን አስቆንጥጠሀኝ ሉጋሙን አሲዘኝ ቀስ እያልኩ አዘግማለው" ይለዋል::
የፈረሱም ባለቤት በየዋህነት ፈረሱን ለሌባው ይለቅለታል።
ይን ጊዜ ሌባው ፈረሱን ኮርኩሮ ሉጋሙን አላልቶ ሽምጥ ጋለበ።
በስላቅም እንግዲህ ደህና አምሽ ጌታው ብሎ ተፈተለከ
ሲጋልብም ሳለ ያ ደግ ሰው ተጣርቶ አንተ ሰው ፈረሱንስ ውሰደው ግን እባክህ አንድ ነገር ልንገርህ ስማኝ አለው
ሌባውም እየጋለበ "ምንድነው እሱ?!"
"ይህን ያረከውን ነገር ማንም ሰው እንዳይሰማው ሰው የሰማ እንደሆነ በእውነት ለታመመና ለወደቀ የደግ ሃሳብ ርህራሄ እንዳያደርግለት ይፈራልና ነው!" ብሎ ቢነግረው
ሌባው በዚህ ነገር ልቡ ተነክቶ ተጸጽቶ ፈረሱን መለሰለት ይባላል::

13/05/2022
በአንድ ወቅት ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ቢላል ኢብኑ ረባህን ከኃላው በፍቅር ስሜት እቅፍ አድርገው ይይዙትና ድምፃቸውን ቀይረው... ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) :- "እኔ ማን ነኝ"?ቢላል (ረ.ዐ) :- ዑ...
13/05/2022

በአንድ ወቅት ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ቢላል ኢብኑ ረባህን ከኃላው በፍቅር ስሜት እቅፍ አድርገው ይይዙትና ድምፃቸውን ቀይረው...

 ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) :- "እኔ ማን ነኝ"?

ቢላል (ረ.ዐ) :- ዑመር (ረ.ዐ) ነህ?

 ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) :- አይደለሁም

ቢላል (ረ.ዐ) :- አቡብክር (ረ.ዐ) መሆን አለብህ?

 ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) :- አሁንም ተሳስተሃል

ቢላል (ረ.ዐ) :- በቃ ዑስማን (ረ.ዐ) ነህ?

 ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) :- አላወቅከኝም

ቢላል (ረ.ዐ) :- ዓሊ (ረ.ዐ) ነህ ማለት ነው... እያለ ያቀፈውን ሰው ማንነት ሲጠይቅ ይቆያል። ከዚያም ረሱል (ሰ.ዐ.ወ) ለቀቅ አደረጉትና ከፊት ለፊቱ በመምጣት "ቢላል ሆይ! እውነት እኔ መሆኔን አላወቅክም ነበር እንዴ"? ሲሉ ጠየቁት ቢላልም "የአላህ መልእክተኛ ሆይ!" በደንብ አውቄዎታለሁኝ ነገር ግን ለረጂም ጊዜ እንድታቅፉኝ ስለፈለኩኝ እንጂ ሲል መለሰላቸው።

ሰለዋቱ ረቢ ወሰላሙ አለይከ ያ ረሱሊላህ

“የሰራተኛን ክፍያ ላቡ ሳይደርቅ በፊት የሰራበትን ክፈሉት።” ˙·٠•● ነቢዩ ﷺ ስለአሏሁ አለይሂ ወሰለም ●•٠·˙ ኢብኑ ማጃህ ዘግበውታል (2443)
12/05/2022

“የሰራተኛን ክፍያ ላቡ ሳይደርቅ በፊት የሰራበትን ክፈሉት።”
˙·٠•● ነቢዩ ﷺ ስለአሏሁ አለይሂ ወሰለም ●•٠·˙
 ኢብኑ ማጃህ ዘግበውታል (2443)

«ከእናንተ መልካም ሰው ብሎ ማለት የተራቡ ሰወችን የመገበ ሰው ነው»።ረሱል (ሶለላሁ ዓለይሂ ወሰለም)
12/05/2022

«ከእናንተ መልካም ሰው ብሎ ማለት የተራቡ ሰወችን የመገበ ሰው ነው»።
ረሱል (ሶለላሁ ዓለይሂ ወሰለም)

  (ሶለሏሁ አለይሒ ወሰለም)  ከተናገሩት ተአምራዊ ሀዲስ አንድ...:-ከ1400 አመታት በኋላ ሳይንስ ከደረሰባቸው የረሱል / ሰ.ዐ.ወ/ ተአምራት መካከል፤ የሚከተለው ሀዲስ አንዱ ነው፡፡ረሱ...
10/05/2022

(ሶለሏሁ አለይሒ ወሰለም) ከተናገሩት ተአምራዊ ሀዲስ አንድ...:-
ከ1400 አመታት በኋላ ሳይንስ ከደረሰባቸው የረሱል / ሰ.ዐ.ወ/ ተአምራት መካከል፤ የሚከተለው ሀዲስ አንዱ ነው፡፡
ረሱል /ﷺ/ እንዲህ ብለዋል፡ “የሰው ልጅን

ባጠቃላይ

አፈር ይበላዋል፤ (ዐጅቡ ዘነብ) (coccyx)

ሲቀር፤ የተፈጠረውም ከእሱ ነው (አካሉ የሚገነባውና)

የሚገጣጠመውም ከእሱ ነው” ብለዋል፡፡

ሀዲሱን ያወሩት አቡሁረይራ ናቸው፤ የዘገቡት ደግሞ

ሙስሊም ናቸው፡፡ ምንጭ ሰሂህ ሙስሊም፤ ገፅ 2955፤

ሀዲሱም ሰሂህ ነው፡፡

በአጭሩ የሀዲሱ መልክዕክት፤ የሰው ልጆች አካል፤ አፈር

ይበላዋል ይበሰብሳልም፤ (ዐጅቡ ዘነብ) የጭራ ግንድ

የተባለችው፤ ከጀርባ አጥንታችን ወደታች ስንወርድ ከስር

ጫፍ ላይ፤ ጭራ መብቀል የሚጀምርበት ስፍራ ላይ፤

ሶስት

ማዕዘን መሰል ትንሽዬ አጥንት አለች፤ እሷ ግን

አትበሰብስም፡፡ ሰው ሲፈጠር መጀመሪያ ከእሷ ነው፤

ከሞተም በኋላ በእሷ ላይ ነው እንደ አዲስ እየተገነባ

የሚመጣው፡፡ ለማለት ነው፡፡

ዘመናዊው ሳይንስም የሰው ልጆች ከሞቱ በኋላ ሁሉም

ነገር እንደሚበሰብስና፤ የጭራ ግንድ (ዐጅቡ ዘነብ)

የምትባለዋ አጥንት ግን እንደማትበሰብስ ደርሶበታል፡፡

የጭራ ግንድ (ዐጅቡ ዘነብ) ምንድን ነው??

ይህ የሰው ልጅ ሲፈጠር በመጀመሪያ ደረጃ ላይ እያለ፤

የሚፈጠር የመጀመሪያው አካል ነው፡፡ የመጀመሪያው

ገመድ

በመባል ይታወቃል፡፡ የፅንሱ አካላት በሙሉ ከተፈጠሩ

በኋላ፤ ይህ አካል ከጀርባ አጥንቱ ከስር ጫፍ ላይ ሄዶ

ይረጋል፡፡ በሰዓቱ መጠኑም ምስር ያክላል፡፡ ይህ አካል

የሰው ልጅ ከሞተ በኋላም ህያው ሆኖ ይቀራል፤

በመጨረሻም የሰው ልጅ የቂያማ ቀን የሚቀሰቀስበት ፍሬ

ሆኖ ይቆያል፡፡

ሳይንቲስቶች በተለያዩ መንገዶች ይህን አካል ለመግደል

ብዙ ሙከራዎችን አድርገዋል፡፡ ነገር ግን ህያው ሆኖ ነው

የቆየው፡፡ በሰው ልጅ አዕምሮ ውስጥ ያለ ሴልን

በማስወገድ በሱ ቦታ የጭራ ግንድ (የዐጅቡ ዘነብ)

ሴሎችን ተክተው አይተው ነበር፡፡ ሆኖም ግን የአላህ /

ሱ.ወ/ ታዕምር የሚገርመው፤ እነዚህ ሴሎች ቦታውን

ለቀው ከእምሮ ወደ ቦታቸው፤ ወደ የጀርባ አጥንት ጫፍ

መንቀሳቀስ መጀመራቸው ነበር፡፡

አላህ /ﷻ/ ረሱልን /ﷺ/ አስመልክቶ በሱረት

አልነጅም አንቀፅ 3 ላይ

“ከልብ ወለድም አይናገርም”

ይለናል፡፡

ሰለዋቱላሂ ወሰላሙሁ ዓለይህ!

By ustaz khalid kibrom

[ ሱረቱ አል-ሩም - 31 ]

ወደእርሱ ተመላሾች ሆናቸሁ (የአላህን ሃይማኖት ያዙ)፡፡ ፍሩትም፡፡ ሶላትንም አስተካክላችሁ ስገዱ፡፡ ከአጋሪዎቹም አትሁኑ፡፡

10/05/2022

☞አጭር ..ጣፋጭ..ታሪክ ከ ነብዩ ሙሐመድ
(ሰ.ዐ.ወ) ህይወት
ከእለታት አንድ ቀን የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ)
በመንገድ ላይ ሳሉ አንዲት በእድሜ

የገፉ አሮጊት ሴት እቃ ተሸክመው ይመለከታሉ።

ወደሴትየዋ ጠጋ በማለት እማማ

እቃውን ላግዞት? ሲሉ ጠየቋቸው።

>ሴትየዋ የአላህ መልእክተኛ ስለመሆናችው የሚያወቁት

ነገር አልነበረም፤ እቃውን

ከራሳቸው ላይ አውርደው ሰጧቸው፤ የአላህ

መልእክተኛም (ሰ.ዐ.ወ) እቃውን ተሸክመው

እስከቤታቸው በር ድረስ አደረሱላቸው።

>ሴትየዋም ትንሽ ጠብቀኝ ብላቸው ወደቤታቸው ገቡ፤

የአላህ መልእከተኛም (ሰ.ዐ.ወ)

ሴትየዋ እስኪወጡ ጠበቁ። ሴትየዋም ከቤት በመውጣት

እንዲህ አሉ፡- ?

በማለት የአላህ መልእክተኛን ጠየቋቸው።

>የአላህ መልዕክተኛም እንዴት አልቀበልም ሲሉ መለሱ።

ሴትየዋም ልጄ እኔ አደራ

የምልህ የሙሀመድን ሀይማኖት እንዳትከተል ነው አሉ።

የአላህ መልእክተኛም (ሰ.ዐ.ወ)

እኔ ሙሀመድ ከሆንኩኝስ ምን ይላሉ? ሲሉ ጠየቋቸው።

>ሴትየዋም አንተ ሙሀመድ ከሆንክማ ከአላህ ሌላ አምላክ የለም ሙሀመድም የአላህ

መልእክተኛ መሆናቸውን እመሰክራለው። እንዲህ ነበሩ
የአላህ መልእክተኛ በፀባያቸው
አለምን የገዙት።

10/05/2022

___ ___
*** ***
ከእለታት አንድ ቀን ነብዩ ሙሃመድ (ሰ.አ.ወ) ዘንድ አንድ ከገጠር የመጣ ኑሮዉ ያልሰመረለት ድሃ ግለሰብ #ሰሃን ሙሉ ወይን ስጦታ ያመጣላቸዋል ።

_ነብዩም (ሰ.አ.ወ) ስጦታዉን ተቀብለዉ ወይኑን መብላት ጀመሩ....

_የመጀመሪያ ጎርሰዉ ፈገግ አሉ....

_ሁለተኛዉም ጎርሰዉ ፈገግ አሉ ግለሰቡም እጅጉን ተደሰቱ...

_የነብዩ ጋደኞች #ሰሃቦች ሁሌም ለነብዩ (ሰ.አ.ወ) ስጦታ

ሲመጣላቸዉ ስለ ሚያካፍሏቸዉ ይህንን #ጣፋጭ ወይን እንዲያካፍሏቸዉ በጉጉት ይጠብቃሉ ...

_የአላህ መልእክተኛ ግን ሳያካፍሏቸዉ እያንዳንዱ የወይን ፍሬ እየበሉ እና ፈገግ እያሉ ሁሉንም በልተዉ ጨረሱ.....

_ስጦታ አቅራቢዉ እጅግ በጣም ተደስቶ ስጦታዉንም ስለ ወደዱለት አመስግኖ ሄደ....

አንድ የነብዩ (ሰ.አ.ወ) ጋድ #ሶሃባ ጠጋ ብሎ ነብዩን ጠየቃቸዉ

" የአላህ መልእክተኛ ሆይ ምነዉ ሳያካፍሉን ?>>

_እሳቸዉም ነብዩ (ሰ.አ.ወ) ፈገግ ብለዉ መለሱለት "
_ሰዉዬዉ መደሰቱን አይታችሃል አይደለም ?!
_ወይኑ ስቀምሰዉ በጣም ይመር ነበር....?!!!
_ባካፍላችሁ አንዳችሁ ግለሰቡን የሚያስከፋ እና ደስታዉን የሚያደፈርስበት ነገር እንዳታሳዩት ሰጋሁ !!>

ነቢዩ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፡‐ “ለታናናሾቻችን ያላዘነና የዕድሜ ባለ ፀጐችን ክብር ያላወቀ ከኛ አይደለም”አቡዳውድና ቲርሚዚይ ዘግበውታል
10/05/2022

ነቢዩ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፡‐
“ለታናናሾቻችን ያላዘነና የዕድሜ ባለ ፀጐችን ክብር ያላወቀ ከኛ አይደለም”

አቡዳውድና ቲርሚዚይ ዘግበውታል

10/05/2022

!! 🕌🕌
=======
አቢ ሁረይራ (ረዲየላሁ ዓንሁ) .... :-
የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ አለ፡-
"ድኃ ማን እንደሆነ ታውቃላችሁን? እኛም፡- ከኛ ውስጥ ድኃ ማለት መጠቃቀሚያ ገንዘብ የሌለው ነው አልን፣ እሳቸውም ከኔ ኡመት ድኃ ማለት ነገ የቂያም እለት ሶላቶቹን፣ ጾሙን፣ ሶደቃውን ይዞ የሚመጣና ነገር ግን ያን በመሳደቡ፤ ይሄኛውን በማዋረዱ፣ እሱን ደግሞ ብሩን በመብላቱ፣ የዚህያውንም ደም በማፍሰሱ፣ ይሄንን በመምታቱ ሰበብ ከሐሰናቱ ተወስዶ ለተበዳዮች ይሰጥና የሱ ሐሰናት ሲያልቅበት ከተበዳዮች ኃጢአትን በምትኩ ተሸክሞ በጀሐነም የሚወረወር ነው"።

ሙስሊም ዘግበውታል

10/05/2022

«አደራ መልካም ስነምግባር ይኑርህ፣ ዝምታንም አብዛ፣ ነፍሴ በእጁ በሆነው ጌታ ይሁንብኝ ፍጥረታቶች ከተዋቡባቸው ነገሮች ሁሉ በእነዚህ በመሰሉ ነገሮች አልተዋቡም»።ረሱል ﷺ

ዋኢላት ኢብኑ አል-አስቀዕ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፉት የአላህ መልክተኛ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፡‐ በወንድምህ ላይ በደረሰ ችግር አትደሰት :: አላህ እርሱን ሰላም አድርጎ አንተን ይፈትንሃልና :...
10/05/2022

ዋኢላት ኢብኑ አል-አስቀዕ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፉት የአላህ መልክተኛ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፡‐
በወንድምህ ላይ በደረሰ ችግር አትደሰት :: አላህ እርሱን ሰላም አድርጎ አንተን ይፈትንሃልና ::

 ((ትርሚዚ ዘግቦታል ))

وعن واثلة بن الأسقع رضي الله عنه قال‏:‏ قال رسول الله صلى الله عليه وسلم ‏:‏ ‏

"‏ لا تظهر الشماتة لأخيك، فيرحمه الله ويبتليك‏"‏‏.‏

 ‏(‏‏(‏رواه الترمذي وقال‏:‏ حديث حسن‏)‏‏)‏

◦•●◉✿ ከሐዲሡ የምንማራቸው ቁም ነገሮች ✿◉●•◦

 በሙስሊም ወንድም ላይ በሚደርሰ መከራ መደሰት ሐራም ነው

 ይህን የሚያደርግ ሰው ከመጪው አለም በፊት በዚህች ዓለም ይቀጣል ::

 እውነተኛ ሙስሊም ማለት የሙስሊሞች ስቃይና መከራ እርሱንም የሚያንገበግበውና የሚሰማው ነው።



በየቀኑ የሚለቀቁ ሃዲሶችን ለመከታተል ግሩፑን ይቀላቀሉ ጆይን ያድርጉ

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Islamic World posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to Islamic World:

Share