11/09/2025
እንኳን አደረሳችሁ ልበል
አመታትንና ቀናትን ሳስብ ለሚያምኑ እንኳን አደረሳችሁ ከሚለው ይልቅ ጌታ ይርዳችሁ ማለት የሚበጅ ይመስለኛል። ምክንያቱም እግዚአብሔር በእየለቱ ልንሰራው የሚገባን ኃላፊነት ስለሰጠን ይህንን የምንፈፅምበት የአደራ ዘመን ስለሆነ ይህንን ባንሰራ እዳ ስላለብን ከመደሰት ይልቅ ቆም ብለን ማሰብ አለብን እላለሁ። መፅሐፍ እንደሚል ዘመኑን ዋጁት፣ ቀኖች ክፉዎች ናቸው፣ እንዲሁም ለቀኑ ክፋቱ ይበቃዋል። ይህ ከሆነ መልካም ዘመን ሳይሆን ክፉ የሆን አመት ነው እየገባንበት ያለው ነገር ግን ይህንን ዘመን ክፋቱንና አመፁን በመልካም የልጅነት ህይወት በመኖር የጌታን መልካምነት እንድንገልጥበት በአደራነት ተሰጥቶናል። በእያንዳንዱ ቀን በጌታ መንፈስ እየተሞላን መኖር ስለሚጠበቅብን እንንቃ።
ተባረኩልኝ ታማኝ አድርጎ ስለቆጠረን የአገልግሎት ቀናትን የጨመረልን ጌታ ይባረክ።
"ጌታችንም ኢየሱስ ክርስቶስ ከቅዱሳኑ ሁሉ ጋር ሲመጣ፥ በአምላካችንና በአባታችን ፊት በቅድስና ነቀፋ የሌለበት አድርጎ ልባችሁን ያጸና ዘንድ፥ እኛ ደግሞ ለእናንተ እንደምንሆን ጌታ እርስ በእርሳችሁ ያላችሁን ለሁሉም የሚሆን ፍቅራችሁን ያብዛ ይጨምርም።"
1ኛ ተሰሎንቄ 3:12