Gold Orthodox

Gold Orthodox https://youtube.com/-0701?si=TrGcUfD6Z6scAyoV
ኦርቶዶክስ ለዓለም ትዳረስ
www.tiktok.com/

ወንድምየው ዛሬ ልደቱ ነው እንኳን ተወለድክ በሉት ጆ መልካም ልደትጆሲ የገብርኤል
19/10/2025

ወንድምየው ዛሬ ልደቱ ነው እንኳን ተወለድክ በሉት ጆ መልካም ልደት
ጆሲ የገብርኤል

18/10/2025

የመስቀል ስጦታ

18/10/2025

መምህሬ

17/10/2025

ልደተቃል

መምህር የማርያምወርቅ ተሻገር እንደፃፈው"ቄርሎስ" ከመባሉ በፊት "ያሬድ" ተብሏል!!!=========================በማኅበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪ ከኾኖ ወንድሞች መካከል አንዱ ያያ...
17/10/2025

መምህር የማርያምወርቅ ተሻገር እንደፃፈው

"ቄርሎስ" ከመባሉ በፊት "ያሬድ" ተብሏል!!!
=========================

በማኅበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪ ከኾኖ ወንድሞች መካከል አንዱ ያያ ዘልደታ ወይም ያሬድ ወልደ ጻድቅ ነው። የልደታ ልጅ ነው። ለሃይማኖቱ ቀናተኛ ነው። ፍርሐት የሚባል አልፈጠረበትም። በተለያዬ ዘመን ከ ስድስት ጊዜ በላይ ታሥሯል። በተለይ በዚኽ በ ቲክቶክ እና በፌስቡክ ፕላትፎርም ከም*ን*ፍ*ቅ*ና አስተምህሮ ጋር በገባው እና በሚችለው ልክ ጉርምቦ ለጉርምቦ እየተናነቀ በዚያኛው ጓራ ከሚጠሉ ("ጠ" ይጠብቃል) ኦርቶዶክሳውያን ወጣቶች አንዱ ነው። እናም አንድ ራሱን የቻለ የሚጠላው ቡድን እንዳለ ኹሉም የሚያውቀው ሐቅ ነው። አሁንም ድኾችን እና ቤተክርስቲያንን ለማገዝ ከፊት እንደማይጠፋ መራር ዕውነት መኾኑ ኹሉም ያውቃል።

ያ ማለት ግን እንደ መልአክ ንጹሕ፣ እንደ ጨረቃ የጠራ፣ እንደ ኮከብ የደመቀ እንከን የለሽ ፍፁም ሰው ነው - ማለት እንዳልኾነ ወዳጆቹም ጠላቶችም ታውቃላችኹ፤ ያያ ሰው ነው። ያለማል፤ ያጠፋል፤ ይወድቃል፤ ይነሣል፤ ጽድቅ ይሠራል፤ ኃጢአት ይፈጽማል። በቃ ይኽንን ጽሑፍ እንደምታነበው እንደአንተ እንደአንች - ማለት ነው። ከአንተ፣ ከአንች የሚያንስበትን እናንተ ታውቁታላችሁ። እናንተ ራሳችኹ ናችኹ የራሳችኹን ንጽሕና የምታውቁት። ሳንወሻሽ ደግሞ፤ ለድሃ ፈጥኖ በመድረስ፣ ለተቸገሩት አድባራት እና ገዳማት አለሁ በማለት፣ መ*ና*ፍ*ቃንን እግር በእግር እየተከተለ እኩይ ተግባራቸውን በማጋላጥ ዋጋ መክፈሉን ካለመናችኹ-ምንም ማድረግ አይቻልም። የሚያውቁት ግን ይመሰክሩለታል። ይኽንን መግቢያ ይዘን ወደ ዋናው ጉዳይ እንዝለቅ።

ታደያ ከሰሞኑ ጎንደር ላይ በነበረው የገቢ ማሰባሰቢያ
"ለሥዕልሽ እንሰግዳለን
ቤትሽንም እንሠራለን"

(በእመቤታችን ድንግል ማርያም ጠ*ላ*ቶ*ች ዘንድ ብዙ ጫጫታ መፍጠሩ ልብ ይሏል። ) በሚል ግዙፍ መርሐግብር ተካኺዶ በስኬት መጠናቀቁ ተሠማ። በዚኽን ጊዜ በበጎ ተግባሩ ለመሳተፍ የዘገዩ፣ ሕጸጽ ለማውጣት ብቻ እንቅልፍ ለዐይናቸው እረፍት የመይሹ ጥቂት ሰዎች ከስኬቱ ይልቅ ያያ ዘልደታ ለምን በመርሐግብር መሪው "ቄርሎስ" ተብሎ ተጠራ ብለው ያዙኝ ልቁኝ አሉ። እኔም በአገልግሎት ምክንያት ከረቡዕ እሰከ አርብ አልነበርኩም። ገዳም ነበርኩ። ስመለስ አንዳንድ ወዳጆቼ "ለምን በዚኽ ጉዳይ አትጽፍም" አሉኝ። "እሽ" አልኩና የሚከተለውን ልል ወደድኩ፤

፩. ያያ ዘልደታ ትክክለኛ ስሙ ያሬድ ነው፤
ስለ ያሬድ ዘፍ ፭÷፲፭ አንብቡ። ከሞዛርት እና ከቬትሆቨን የሚልቀውን ኢትዮጵያዊውን ቅዱስ ያሬድ አታውቁትም ማለት ግብዝነት ስለሚኾንብኝ አልፈዋለኹ። እንግዲኽ ያያ ዘልደታ ያሬድ ተብሎ ሲጠራ ቀድሞ ለአንተ ይኼ ስም አይገባም ብላችኹ ለምን አልተንጫጫችኹም? ብትንጫጬም በጥቂት ሰዎች ፍላጎት የሚቀየር ስም የለም። ይኽ ያሬድ የሚለው ስም የእድሜ ልክ መጠሪያው ነው። ወዳጆቹም ጣላቶቹም በዚኽም ሲጠሩት ይኖራሉ። እናም ቄርሎስ ከመባሉ በፊት ያሬድ ተብሏልና ምን ማድረግ ይቻላል? ነው ወይስ ያሬድ ይገባዋል ቄርሎስ አይገባውም ነው? እንደዚያ ከኾነ ደግሞ በራሳችኹ ጊዜ ብዙ ጠላት ታፈራላችኹ። ቄርሎስን እና ያሬድን እያነፃፀሩ እና እያወራረዱ የቅድስና ደረጃ ማውጣት ከአንድ ኅያሲ እና ሊቅአይጠበቅም። ልዩነቱ ያሬድ የሚለው ስም ዘለዓለማዊ መጠሪያው ነው። ቄርሎስ ደግሞ እንደማጀገኛ በመርሐግብር መሪው ከዚያች መድረክ ውጭ የማይጠራበት ስሙ ነው። እናማ ወዳጆቼ የዕድሜ ዘመን መጠሪያ ይበልጣል? ወይስ አንድ ሽልማት እየተሸለመን ያለን ሰው ለማረታቻ ለደቂቃዎች ብቻ ተጠርቶ የሚቆም ስም? መልሱን ለእናንተው፤

፪. ቋንቋ ዐሥር ባሕርያት አሉት:: ከእነሱ መካከል አንዱ ዘፈቀዳዊነት ነው። ይኽ ትምህርት። የመጀመሪያ ዳግሪ ላይ የዛሬ ፲፭ ዐመት አካባቢ Introduction linguistics ስንማር ፩ኛ ዓመት ኮርስ ውስጥ ትገኛለች። ምን ማለት መሰላችኹ፤ በስያሜው እና በተሰያሚው መካከል ምንም ዐይነት ተፈጥሯዊ ዝምድና የለም ማለት ነው። ለምሳሌ ፀሐይ በሚለው ፊደል፣ በዕለተ ረቡዕ ከተፈጠረችው ፀሐይ እና እኔና እናንተ በሠፈራችን በምናውቃት ፀሐይ መካከል ምንም ዐይነት ተፈጥሯዊ ዝምድና የለም። ያለው ውክልና ነው። ውክልና ደግሞ ውስንነት አለው። ምክንያቱም "ሰማይ" ላይ ያለችውን ፀሐይ የሰፈራችን ፀሐይ ወክላት እኛም ስንጠራት። አንች ፀሐይ ልትባይ አይገባሽም ብለናት አናውቅም። ምክንያቱም ምድር ላይ ባለችው ፀሐይ እና "ሰማይ" ላይ ባለችው ፀሐይ መካከል ያለውን ልዩነት ሳንረዳው ቀርተን ሳይኾን። መጠሪያ ወይም ውክልና እንደኾነ ስለምናውቅ፤

፫. ስም:- ሰመየ ከሚል የግእዝ ቃል የወጣ ሲሆን ትርጉሙም መታወቂያ፣ መለያ፣ መጠሪያ ማለት ነው፡፡
በብዙ መንገድ ይከፈላል፤
የተጸውኦ ስም፣ የባርህይ፣ የግብር ፣ የተቀብኦ እና ምዕላድ ብሎ መክፈል ይቻላል። ብዙ የሚከፈልበት መንገድ ቢኖርም ቅሉ።

የተጸውኦ ስም ለሰው የሚያገለግል ሁኖ ግን አንድን ሰዉ ልንለይበት የምንችልበት ስም ነው፤ ለምሳሌ ያሬድ፣ ማርያም፣ ቄርሎስ፣ ማቴዎስ ወዘተ። የግብር ስም የአንድን ሰዉ ስራ የሚገልጽ የስም አይነት ነዉ፡፡
ምሳሌ፡- ሀኪም፣ አናፂ፣ቀራጭ፣ አርታኢ ወዘተ። የባህርይ ስም ለምሳሌ የእግዚአብሔር ስም፣ የተቀብኦ ስም ገብረ ክርስቶስ ፣ ወለተ ማርያም ወዘተ።

፪. ከዚኽ ተነስተን ቄርሎስ የምን ስም ነው ካልን የተጸውኦ ስም ነው። ማንም ይኽንን የፈለገ ሰው ስሙን ሊወስድ ይችላል። መሠረታዊው ነገር የቄርሎስን ሕይወት ይኖረዋል ወይስ አይኖረውም ነው ጥያቄው። መታወቅ ያለበት ነገር ብዙዎቻችን የተዋሕዶ ልጆች በቅዱሳን ስም የምንጠራ ነን ነገር ግን የዚያን ቅዱስ ሕይወት ሙሉውን እንተወው ግማሹን ኑረነዋል? በፍፁም። ይኽንን ራሳችን፣ ንስሐ አባቶቻችን እና እግዚአብሔር እናውቀዋለን። ታዲያ ያያ ቄርሎስ የተባለውን ቅዱስ አባት ስም ለምን ተጠራበት ብሎ ያስጮኽን በሰው ሰወኛው ያያ እኛን በኃጢአት ስለበለጠን ለምን ይጠራበታል እንጂ ሁላችንም ኃጢአተኞች ን። ነገር ግን ኹላችንም በቅዱሳን ስም እንጠራለን። ከራሳችን ያለውን ግመል የሚያኽል ኃጢአት ተሸክመን የሰውን ኃጢአት ለምን እንመለከታለን።

፫. st cyril ቄርሎስ ማን ነው? የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳስ ነው። የስሙ ትርጓሜ ማኅቶት ማለት ነው። ከ378- 444 ዓ.ም በዚኽ ምድር ላይ 66 ዓመት ኑሯል። የመናፍቃን መዶሻ ነው። ዓምደ ሃይማኖት ነው። ሊቀ ጉባኤ ነው። ክስተት ነው። በ431 ዓ.ም የኤፌሶንን ጉባኤ የመራ፤ ንስጥሮስን ከ ፪፻ ሊቃውንት ጋር በኤፌሶን ተከራክሮ የረታ፣ አውግዞ የለየ፣ ከስህተት ትምህርቱ እንዲመለስ በፍቅር የለመነ ድንቅ እና ወደር የሌለው አባት ነው።

፬. ያያ ሦስተኛው ቄርሎስ ነው ላላችኹ የዋኾች እልል በሉ ብላችኹ ለተዘባበታችኹ አንድ ነገር እንንገራችኹ። ያያ አንድ ሚልየነኛ ቄርሎስ ነው። ለመሳደብ እና ለመተቸት ትሮጣላችኹ እንጂ በዚኽ ስም የሚጠሩ በዓለም ላይ ብዙ ቅዱሳን፣ ብፁዓን አባቶች አሉ። እንዲኹም ግለሰቦች የትየለሌ ናቸው። ሥላሴ ዩኒቨርስቲ መጽሐፍት ቤት ቅርብ ነው አንብቡ። በአማርኛ ቄርሎስ ብላችኹ፣ በእንግሊዝኛው st cyril ብላችኹ ጎግል አድርጉ። ምን ያኽል በራሳችኹ ወገኖች እና ወንድሞች ጨካኝ እንደኾናችኹ ይገባችኋል።

፭. ያያ ቄርሎስ እንጂ የተባለው፤ ቅዱስ ቄርሎስ አልተባለም። ያያ ያሬድ እንጂ የተባለው ቅዱስ ያሬድ አልተባለም።

፮. ዐውድ
ከመ. ና.ፍ.ቃ.ኑ ጋር የሚያጣላን ምንድን ነው። ዐውድ አያውቁም፣ አንድምታ አያውቁም። ትርጓሜ አያውቁም፣ ባህል አያውቁም፣ ዘይቤ አይጠነቅቁም። መጽሐፍ ቅዱስን በቀጥታ መረዳት እንችላለን ስለሚሉ ብዙ ይሳሳታሉ።

ለያያም የተነገረበት ዐውድ የሽልማት መርሐግብር ነው። ዐውዱ ለከፈለው ዋጋ ከመምህር ታደሰ እና ከጋዜጠኛ ነጋሽ ቀጥሎ ከመ*ና*ፍ* ቃ ኑ እና ከአጽራረ ቤተክርስቲያን ጋር ባደረገው ግብግብ ለደረሰበት መታሠር፣ መሳደድ፣ መወገዝ፣ መጠላት ሞራል መስጫ፣ ማትጊያ፣ ማጠንከሪያ የአደራ እና የግረ መንገድ ቃል እንጂ ሠርተፍኬት ተዘጋጅቶ በብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ተፈርሞበት አንተ ከዛሬ ጀምሮ ቄርሎስ ተብለህ እንድትጠራ ተወስኗል አለተባለም። ኢየሱስ ክርስቶስ በተጠራበት የይኹዳ አንበሳ እኮ ጥሩ ሥራን የሠራን ሰው አንበሳ ነህ ኮ እንላለን እንዴ? አያችኹት ወዳጆቼ ለሁሉም ዐውድ አለው። ቦታ፣ ጊዜ እና ኹኔታ አለው። ይኼም ቦታው ጎንደር፣ ጊዜው ሌሊት፣ ኹነቱ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐግብር አልቆ የሽልማት ሥነ ሥርዓት ላይ፤ አሁንስ ገባችኹ?!

፯.. ያያ በዕለቱ አንበሳ ጀግና ቄርሎስ በዚያች ቅፅበት ታለፈ። መጠሪያ ስሙ ግን ያሬድ ነው። ቄርሎስን ብትሸሹ ከያሬድ አታመልጡም። ቄርሎስ መጠሪያው አይደለም። ያሬድ የሚለው ስም በቂው ብቻ ሳይኾን ሲበዛበት ነው። እኔም አናንተም የተሸከምነው ስም ሲበዛብን ነው። እንደስማችን ለመኖር እግዚአብሔር ይርዳን። ከዚኽ ይልቅ። አንድ ነገር ልጠቁማችኹ። የያሬድ አየር ላይ የቀረ ነው። በማኅተም ተደግፎ በትልልቅ ወረቀቶች ፣ በፍሬም ተሸፍኖ የተሰጠ ስም ከአጥቢያ እሰከ ጠቅላይ ቤተክህነት አለ። ከደብረ እሰከ መንበረ ፓትርያርክ ግቢ እሱን ብዘምቱበት ለነፍሳችኹም ለሥጋችኹም ይኾናል። መልአከ ኹከቱን መልአከ ሰላም። ደብረ በጥብጡን ደብረ ጽዮን፣ ሊቀ ጥራዝ ነጠቁን ሊቀ ማእምራን፣ እልፍ ስሞች አሉ። አህያው እያለ ደውላው?

ደግሞም በዚኽ በተነሣው ርእሰ ጉዳይ ስህተት የሌለውን፤ ቢኖር እንኳ
በአደባባይ ከምንወራወር
በጓዳ ብንመካከር መልካም ነበር

ነገር ግን በአደባባይ ስለኾነ የኄሳችኹት፤ በአደባባይ ምላሽ ተሰጧል። ምክንያቱም። ዝምታ ትርጉሙ ብዙ ነው። አንድም የናቅናችኹ እንዳይመስላችኹ። ኹለትም የፈራን እንዳይመስላችኹ፣ ሦስትም ምላሽ የመስጠት ብቃት የሌለን እንዳይመስላችኹ። አራተኛው ስህተታችንን አምነን ዝም ያልን እንዳይመስላችኹ ነው እንጂ - ዝም እንል ነበር።

የመጨረሻ መልእክቴ ነው፤
በአደባባይ ከምወራወር- በጓዳ እንመካከር
መናገር መመለስ አልፈለግኩም ነበር።
"ውኃን ምን ያናግረዋል ቢሉ ድንጋይ"

ተፃፈ
መኪና ላይ- ከገዳም ስመለስ
፯/፪/፳፻፲፰
የማርያምወርቅ ተሻገር (መ/ር)
ያያ ዘልደታ ያሬድ

ይህንን ቦታ የሚያውቀው?
17/10/2025

ይህንን ቦታ የሚያውቀው?

17/10/2025

መስቀል ሃይላችን ነው

እመእጏል ቅዱስ ዑራኤልFasil Yirga
17/10/2025

እመእጏል ቅዱስ ዑራኤል
Fasil Yirga

ጉዞ ወድ እመጏ ቅዱስ ኡራኤልFasil Yirga
15/10/2025

ጉዞ ወድ እመጏ ቅዱስ ኡራኤል
Fasil Yirga

15/10/2025

በመስቅል

15/10/2025
በጓደኛዋ መሰሪ ሴራ የተነሳ በሀገረ ቻይና ኮኬይን የተሰኘው የተከለከለ እጽ ተይዞባት ወህኒ ቤት የምትገኘው ኢትዮጵያዊቷ ወጣት "ናዝራዊት--አበራ በምህንድስና ሙያ ተመርቃ ለሀገሯ ብዙ ነገር ...
15/10/2025

በጓደኛዋ መሰሪ ሴራ የተነሳ በሀገረ ቻይና ኮኬይን የተሰኘው የተከለከለ እጽ ተይዞባት ወህኒ ቤት የምትገኘው ኢትዮጵያዊቷ ወጣት "ናዝራዊት--አበራ በምህንድስና ሙያ ተመርቃ ለሀገሯ ብዙ ነገር የምትሰራ ተስፈኛ ቆንጆ፤ ዛሬም በሩቅ ምስራቅዋ የሞንጎል ምድር በሚገኝ ጨለማ ሽለቆ ውስጥ ተዘግቶባት..... አይምሬው የቻይናዊያን ህግ የሚጥልባትን የሞት ቅጣት በመጠባበቅ ላይ ስትሆን፤ አሁን የተሸመቀቀው ገመድ ወደ አንገቷ እየቀረበ ጉዳይዋ አሳሳቢ ምዕራፍ ላይ ይገኛል።

የልጃቸው ባልተጠበቀ ሁኔታ እና በማታውቀው ጦስ መዘፈቅን ተከትሎ ወላጅ እናቷ በድንጋጤ ፓራላይዝድ እስከመሆን ደርሰዋል። ይሄ ሰብዓዊነት ላለው ሰው በሙሉ ክፉኛ የሚያም አሳዛኝ ክስተት ሲሆን፤ ናዝራዊት የመኖር እጣ ፈንታዋን ንጽህናዋን በሚያውቀው እግዚአብሔር የሚወሰን ቢሆንም፤ እንደ-ሰው ግን የቻልነውን ሁሉ ብንረባረብላትና የኢትዮጵያ መንግስት እስከ ጥግ ድረስ የዲፕሎማሲ ጥረት አድርጎ አንድ መፍትሔ እንዲፈጥርላት ተፅህኖ መፍጠር ያለብን እኛ ወገኖቿ ነን።
....ለ-ናዝራዊት ምንም ነገር ሳንሞክርላት የተፈራው ቅጣት ቢያገኛት መፀፀታችን አይቀርም። ስለዚህ ውድ ወገኖቼ እና ይሄን ፅሁፍ ያነበባችሁ ኢትዮጵያዊያን በሙሉ በአንዲት ጣታችሁ ብቻ ሼር የምትለዋን በመጫን ጉዳዩን ብሔራዊ አጀንዳ የማድረግ ኃይሉ እንደዜጋ አላችሁና፤ ከምንም ጉዳይ አስቀድማችሁ........"ስለ-ናዝራ ዊት" መልዕክቱን ተቀባብላችሁ ለሚመለከተው የመንግስት ቢሮ እንዲበቃ አርጉት! በጸሎታችሁም አስቧት።

Address

Bole Road
Addis Ababa
10000

Telephone

+251988478889

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gold Orthodox posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to Gold Orthodox:

Share