Christ Army tv worldwide

Christ Army  tv worldwide ☞ኢየሱስ ለጥያቄ ሁሉ መልስ ነው!!!

03/01/2026

🎯እምነት ምሰሉአቸው🎯
“የእግዚአብሔርን ቃል የተናገሩአችሁን ዋኖቻችሁን አስቡ፥ የኑሮአቸውንም ፍሬ እየተመለከታችሁ በእምነታቸው
ምሰሉአቸው።” (ዕብ.13፥7)
........✝️የሣራ እምነት✝️.......

“ሣራም ተስፋ የሰጠው የታመነ እንደሆነ ስለ ቈጠረች፥ ምንም እንኳን መካን ብትሆን፥ ዕድሜዋ እንኳ ካለፈ በኋላ
ዘርን ለመፅነስ ኃይልን በእምነት አገኘች።” (ዕብ. 11፡ 11)
አብርሃም “ዘርህ እንደ ሰማይ ከዋክብት እንዲሁም እንደምድር አሸዋ ይበዛል” የሚለው ተስፋ በተሰጠው ጊዜ
ሚስቱ ሣራ መካን ነበረች።
ነገሩን የበለጠ ከባድ ያደረገው ደግሞ ተስፋው ለመፈጸም ጊዜ ሲወስድ የመውለጃዋ እድሜ እያለፈ መሆኑ ነበር።
እናም ሣራ እግዚአብሔር የሰጣቸውን ተስፋ በተጠራጠረች ጊዜ ከአገልጋይዋ ከአጋር አብርሃም እንዲወለድ
ሁኔታዎችን አመቻቸች።

እግዚአብሔር ግን የራሱን ዕቅድ የሚተገብርበት ጊዜ ነበረው። ታዲያ ልጅ የመውለጃዋ ጊዜ ደርሶ ከመለኮት የዛሬ
አመት ልጅ እንደምትወልድ መልዕክት ሲመጣ ሣራ “ይህ እንዴት ሊሆን ይችላል” ብላ ሳቀች። ለማመን ከበዳት።
“አብርሃምና ሣራም በዕድሜአቸው ሸምግለው ፈጽመው አርጅተው ነበር፥ በሴቶች የሚሆነውም ልማድ ከሣራ
ተቋርጦ ነበር። ሣራም በልብዋ እንዲህ ስትል ሳቀች፦ “ካረጀሁ በኋላ በውኑ ፍትወት ይሆንልኛልን? ጌታዬም

ፈጽሞ ሸምግሎአል።” እግዚአብሔርም አብርሃምን አለው፦ “ካረጀሁ በኋላ በውኑ እወልዳለሁን? ስትል ሣራ ለምን
ሳቀች? በውኑ ለጌታ የሚሳነው ነገር አለን? የዛሬ ዓመት እንደ ዛሬው ጊዜ ወደ አንተ እመለሳለሁ፥ ሣራም ልጅን
ታገኛለች።” ሣራም ስለ ፈራች፦ “አልሳቅሁም” ስትል ካደች። እርሱም፦ “አይደለም፥ ሳቅሽ እንጂ” አላት።” (ዘፍ.
18፡ 11-15) ይገርማል!
ምንም እንኳን ሣራ በመጀመሪያ በጥርጣሬ የሳቀች ቢሆንም “በውኑ ለጌታ የሚሳነው ነገር አለን?” የሚለው ቃል

ምነት ሆናት። ተስፋ የሰጠው የታመነ እንደሆነ ስለ ቆጠረች፣ ለመፀነስ ኃይልን በእምነት አገኘች።
እኛም እንደ ሣራ እግዚአብሔርን በመጠራጠር ለብዙ ኪሳራ ተዳርገን ቢሆን እርሱ ትላንት እንዲህ ነበራችሁ
በማለት ተስፋ አይቆርጥብንም፤ ድካማችንንም በማስተዋል እምነታችንን የሚያበረታን ቃል ይሰጠናል። በእርሱም
ብንታመን እኛም እንደ ሣራ በእምነት ኃይልን እናገኛለን።
ከሣራ እምነት በመነሳት እግዚአብሔርን ስለ እምነት በጸሎት ምን ትጠይቁታላችሁ ?
የፀሎት ርዕሳችሁን ከዚህ🛐
በታች ዘርዝሩና ቀኑን ሙሉ በልመና መንፈስ ይዋሉ።
.......P/john............
t.me/borforiconn
t.me/yekal_sink

.......✝️የአብርሃም እምነት✝️..........                ዕብ 13:7 “አብርሃም እግዚአብሔር በፈተነው ጊዜ፣ ይሥሐቅን መሥዋዕት አድርጎ በእምነት አቀረበ፤” (ዕብ.11:17...
02/01/2026

.......✝️የአብርሃም እምነት✝️..........
ዕብ 13:7

“አብርሃም እግዚአብሔር በፈተነው ጊዜ፣ ይሥሐቅን መሥዋዕት አድርጎ በእምነት አቀረበ፤” (ዕብ.11:17)
በዕብራውያን ምእራፍ አስራ አንድ ላይ ስማቸው ከተዘረዘሩት የእምነት አርአያዎች መካከል በሰፊው የተነገረለት
አብርሃም እንደሆነ እናያለን። በእርግጥም አብርሃም የእምነት አባት ተብሎ የሚታወቅም ሲሆን ስለ እምነት
የተጻፈው እንዲህ ይነበባል፦

1. አብርሃም ወዴት እንደሚሄድ ባያውቅም እሺ ብሎ በእምነት ታዞ ሄደ
"አብርሃም ርስት አድርጎ ወደሚቀበለው ስፍራ እንዲሄድ በተጠራ ጊዜ በእምነት ታዘዘ፤ ወዴት እንደሚሄድ
ባያውቅም፣ ዕሺ ብሎ ሄደ። በባዕድ አገር እንዳለ መጻተኛ በተስፋዪቱ ምድር በእምነት ተቀመጠ፤ የተስፋውን ቃል
ዐብረውት እንደሚወርሱት እንደ ይሥሐቅና እንደ ያዕቆብ በድንኳን ኖረ፤ ምክንያቱም መሠረት ያላትን፣
እግዚአብሔር የሠራትንና የፈጠራትን ከተማ ይጠባበቅ ነበር።" (ቁ. 8-9)

2. አብርሃም ምንም እንኳ ዕድሜው ቢገፋ ሚስቱም መካን ብትሆንም በእምነት የልጅ አባት ለመሆን በቃ።

✅“አብርሃም ምንም እንኳ ዕድሜው ቢገፋም፣ ሣራም ራሷ መካን ብትሆንም፣ ተስፋን የሰጠውን ታማኝ አድርጎ ስለ
ቈጠረ በእምነት የልጅ አባት ለመሆን በቃ። ስለዚህ እንደ ሞተ ሰው ከሚቈጠር ከዚህ ከአንድ ሰው፣ እንደ ሰማይ
ከዋክብት የበዛና እንደ ባሕር ዳር አሸዋ ተቈጥሮ የማያልቅ ዘር ተገኘ።” (ቁ. 11-12)

✅. አብርሃም ልጁን ይስሐቅን አምላኩን በመታዘዝ በእምነት አቀረበ።
አብርሃም እግዚአብሔር በፈተነው ጊዜ፣ ይሥሐቅን መሥዋዕት አድርጎ በእምነት አቀረበ፤ የተስፋን ቃል
የተቀበለው እርሱ፣ አንድ ልጁን ሊሠዋ ዝግጁ ነበር፤ ይህም እግዚአብሔር፣ ✅“ዘርህ በይሥሐቅ ይጠራል” ያለለት
ነበር። አብርሃም እግዚአብሔር ሙታንን ሊያስነሣ እንደሚችል ተገንዝቦ ነበር፤ ይሥሐቅንም ከሞት የመነሣት
አምሳያ ሆኖ አገኘው። (ቁ. 17-19)
አዎ፣ ከአብርሃም እውነተኛ እምነት በእግዚአብሔር ላይ በመደገፍ እርሱ አድርጉ የሚለንን በመታዘዝ የምንኖረው
ሕይወት እንደሆነ ቁልጭ አድርጎ ያሳየናል።
ጥያቄ ?
🎯ከአብርሃም እምነት በመነሳት
እግዚአብሔርን ስለ እምነት በጸሎት ምን ትጠይቁታላችሁ ?
የፀሎት ርዕሳችሁን🛐
ከዚህ በታች ዘርዝሩና ቀኑን ሙሉ በልመና መንፈስ ይዋሉ።

...........P/john...........
t.me/yekal_sink
t.me/borforiconn

በዚህ ቻናል በየእለቱ የቃል ስንቅ አዳድስ እና ቆየት ያሉ መዝሙሮች እናም የተለያዩ ፕሮግራሞች ይቀርባሉ። 😒አይኔን አንስቼ ከሰው ላይ፣😔 ሀዘኔን ረሳው ኢየሱስን 😳ሳይ😁 ለአስተያየ....

01/01/2026

የኖኅእምነት

"ኖኅ ገና ስለማይታየው ነገር እግዚአብሔር ባስጠነቀቀው ጊዜ፣ እግዚአብሔርን ፈርቶ ቤተ ሰዎቹን ለማዳን
መርከብን በእምነት ሠራ፤ በእምነቱ ዓለምን ኰነነ፤ በእምነትም የሚገኘውን ጽድቅ ወራሽ ሆነ።" (ዕብ. 11:7)
በአዳም የዘር ሃረግ አስረኛው ትውልድ ላይ የሚገኘው ኖኅ በዘመኑ የኀጢአት ጽዋ ሞልቶ፣ እግዚአብሔርም ሰውን
በመፍጠሩ ያዘነበት እጅግ አሳዛኝ ደረጃ ደርሶ ነበር። ታዲያ የውሃ ጥፋትን አምጥቶ ምድርን የማጽዳት እቅዱን
ለኖኅ በነገረው ጊዜ ኖህ ደግሞ ምንም እንኳን ዝናብ ከዚያ በፊት ዘንቦ የማያውቅ፣ የጎርፍ መጥለቅለቅም ምን
እንደሚመስል ያላየም ቢሆን በእምነት የአምላኩን ቃል አመነ። በእምነትም ሦስት ነገሮች አደረገ።

1.) በእምነት መርከብ ሠራ
የእግዚአብሔርን ቃል ከማመኑ የተነሳ አድርግ የተባለውን ለማድረግ ምንም አላቅማማም። በወቅቱ እርሱ
የሚሰራው ስራ የሌሎች መሳለቂያ ያደረገው ቢሆንም፣ በራሱ ከመደገፍ ይልቅ በአምላኩ ላይ መታመንን
ምርጫው አደረገ። ምንም ነገር በሌለበት በደረቅ መሬት ላይ መርከቡን ሰራ።
2. )በእምነቱ ዓለምን ኮነነ
ኖኅ ታዛዥ ሆኖ መርከቡን በመስራቱ እና ለሌሎችም እርሱ እንደታዘዘ እነርሱም እንዲታዘዙ ጥሪ አደረገ።
እግዚአብሔር አላማው ሰውን ማጥፋት ሳይሆን ማዳን እንደሆነ አሳየ። በዚህም በአለም የነበሩት ሰዎች
ለመጥፋት የበቁት በራሳቸው ምርጫ ብቻ መሆኑን ለመገንዘብ ይቻላል። ኖኅ በእምነት የወሰደው እርምጃ
በጥፋት ጎዳና ለመሄድ ላመጹት ሁሉ በእርግጥም ኩነኔ ነበር።

3.)ምነትም የሚገኘውን ጽድቅ ወራሽ ሆነ
ኖኅ በራሱ መልካምነት ያገኘው ምንም ነገር አልነበረም። ይልቁንም በአምላኩ ላይ በመታመኑ በኀጢአት
በዘቀጠች አለም ውስጥ እርሱ ግን ከመለኮት ጋር መጣበቅ ቻለ። አምላካችን እግዚአብሔር ከእኛ የሚፈልገው
እርሱን እንድንመርጠው ብቻ ነው። በእርሱ የሚያምኑትን ሁሉ የሚያጸድቅ የፍቅር አምላክ አለንና።፡
ከኖኅ እምነት በመነሳት እግዚአብሔርን ስለ እምነት በጸሎት ምን ትጠይቁታላችሁ ? የፀሎት ርዕሳችሁን ከዚህ
በታች ዘርዝሩና ቀኑን ሙሉ በልመና መንፈስ ይዋሉ።

........ተባረኩ🙏.............
P/john

t.me/yekal_sink
t.me/borforiconn

24/11/2025


#ጴንጤዎች ሼር Jesus Christ for all nations tv worldwide

21/11/2025


#ጴንጤዎች ሼር

05/11/2025


3:30-7:00/ሰኞ 11:30-2:30/ሀሙስ 11:30-2:30/አገልግሎቱን ለመደገፍ 100007930...

23/10/2025

ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነዉ ‼️

30/09/2025
08/09/2025

አሉ አበው🤔🤔

17/08/2025

16/08/2025

♥️♥️♥️♥️♥️♥️

Address

Algeria Street
Addis Ababa
2776/1000

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Christ Army tv worldwide posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to Christ Army tv worldwide:

Share