Anketse Bitsuan

Anketse Bitsuan አንቀጸ ብጹዓን የደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን አንቀጸ ብጹዓን ሰንበት ትምህርት ቤት

ነሐሴ 16 የእመቤታችን በዓለ ዕርገት በደብረ ብሥራት ቅዱሰ ገብርኤል ቤተክርሰቲያን ተከብሯል።እንኳን አደረሰን፣ አደረሳችሁ!!! ✨🕊️​📖 "ተንስእ እግዚኦ ውስተ ዕረፍትከ አንተ ወታቦተ መቅደ...
22/08/2026

ነሐሴ 16 የእመቤታችን በዓለ ዕርገት
በደብረ ብሥራት ቅዱሰ ገብርኤል ቤተክርሰቲያን ተከብሯል።

እንኳን አደረሰን፣ አደረሳችሁ!!! ✨🕊️

​📖 "ተንስእ እግዚኦ ውስተ ዕረፍትከ አንተ ወታቦተ መቅደስከ" ÷ "አቤቱ ወደ ዕረፍትህ ተነስ አንተና የመቅደስህ ታቦት" (መዝ. 131÷8)

የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በዓለ ንግስ ዛሬ ነሐሴ 16 2018 ዓ/ም ማለዳ በደብራችን እንዲህ በድምቀት ተከብሮ አርፍዷል።

የከርሞ ሰው ይበለን።
#ማርያም #ብሥራተገብርኤል #በዓል

የ አንቀጸ ብፁዓን ሰንበት ትምህርት ቤት በሥራ አመራር አባላት ለሚመሩ የማስተባበሪያ ክፍሎች የአባላት ምደባ አደረገ፡፡++++++አዲስ የተመረጠው የሥራ አመራር እሁድ ነሐሴ 10 ቀን 2018 ...
17/08/2026

የ አንቀጸ ብፁዓን ሰንበት ትምህርት ቤት በሥራ አመራር አባላት ለሚመሩ የማስተባበሪያ ክፍሎች የአባላት ምደባ አደረገ፡፡

++++++

አዲስ የተመረጠው የሥራ አመራር እሁድ ነሐሴ 10 ቀን 2018 ዓ/ም በሰንበት ትምህርት ቤቱ ጽህፈት ቤት ባደረገው የመጀመሪያ ስብሰባ በወደፊቱ የሰንበት ትምህርት ቤቱ የአገልግሎት አቅጣጫ ላይ ሰፊ ውይይት በማድረግ በሥራ አመራር አባላት የሚመሩ የማስተባበሪያ ክፍሎች አባላትን ምደባ አደርጎል፡፡

በዚህም መሰረት የሚከተሉት አባላት ለ ስምንቱ ማስተባበሪያ ክፍሎች ተመድበዋል

1. መሳይ ዘውዴ - ዕቅድ ጥናትና ምርምር ማስተባበሪያ

2. ብንያም ተስፉዬ - ሚዲያና ሕዝብ ግንኙነት ማስተባበሪያ

3. ሰናይት ዮሃንስ - የትምህርትና ዕቅበተ እምነት ማስተባበሪያ

4. ዲ / ን ያሬድ ሹራ - የአባላትና ተቋም አደረጃጀት ማስተባበሪያ

5. ሀብታሙ ኬኔ - መረጃና ወቅታዊ ጉዳይ ማስተባበሪያ

6. ጋሻው ተሾመ- ምጣኔ ሀብትና ማኅበራዊ አገልግሎት ማስተባበሪያ

7. ዮዲት አማረ - ሒሳብና ንብረት ዋና ማስተባበሪያ

8. ብሥራት ትዕዛዙ - ቴክኖሎጂ ትሥሥር ማስተባበሪያ

የሥራ አመራር ጉባኤው ባደረገው ስብሰባ በሌሎች አስቸኳይ የአገልግሎት አዠንዳዎች ላይ ውይይት አድርጎል፡፡

አዲሱን መዋቅር በመተግበር የሰንበት ትምህርት ቤቱን አገልግሎት ለማፋጠን የአፈጻጸም መመሪያ መዘጋጀት እንዳለበት በመታመኑ ከዚህ ቀደም መተዳደሪያ ደንቡን ካዘጋጁ አባላት እና ከክፍላት በተመረጡ ተወካዮች የአተገባበር መመሪያውን እንዲያረቁ 12 አባላትን ምደባ አድርጎል፡፡

በዕለቱም ለሥራ አመራር አባላቱ በአዲሱ መተዳደሪያ ደንብ ላይ የማስተባበሪያ ክፍሎች ተግባር እና ኃላፊነትን በተመለከተ አጭር ገለጻ ተሰጥቷቸዋል፡፡

የደብረ ብስራት ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን አንቀጸ ብፁአን ሰንበት ትምህርት ቤት ለ27ኛ ጊዜ ያሰለጠናቸውን የቅድመ ጋብቻ ተማሪ ጥንዶች አስመረቀ።+++++++ነሐሴ 10 ቀን 2018 ዓም ከ...
16/08/2026

የደብረ ብስራት ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን አንቀጸ ብፁአን ሰንበት ትምህርት ቤት ለ27ኛ ጊዜ ያሰለጠናቸውን የቅድመ ጋብቻ ተማሪ ጥንዶች አስመረቀ።

+++++++

ነሐሴ 10 ቀን 2018 ዓም ከድህረ ጋብቻ የባለትዳርች ጉባኤ ጋር በተከበረው በዚህ ምረቃ ላይ በሰሜን አሜሪካ ሲያትል ግዛት የሚያገለግሉት መጋቤ ሐዲስ ቀሲስ ዘሚካኤል ታደሰ ለተጋቢዎች መልዕክት አስተላልፈዋል።

መምህር ያረጋል አስፋው የዕለቱን ትምህርት የሰጡ ሲሆን የሰንበት ትምህርት ቤቱ ዘማርያን ሜላት ሰርገወርቅ እና ብሩክ ቴኒ በዝማሬ አገልግለዋል።

የሰንበት ትምህርት ቤቱ መልዕክትም በሰንበት ትምህርት ቤቱ ሰብሳቢ ዲያቆን ይበልጣል አያሌው የተላለፈ ሲሆን መምህራኑም በየተራ ለተጋቢዎች ምኞታቸውን ገልፀዋል።

በመጨረሻም ተጋቢዎች በቆይታቸው ያገኙትን መንፈሳዊ እውቀት በሪፖርት በማቅረብ፣
ለምህራኖቻቸው፣ለአስተባባሪዎች እንዲሁም ለሰንበት ትምህርት ቤቱ ስጦታ አበርክተዋል ።

ጋብቻችሁን በሥርዓተ ተክሊል እና በቅዱስ ቁርባን ልትፈፅሙ በሱባኤ ላይ ላላችሁ ተመራቂ ተማሪዎቻችን እንኳን ደስ አላችሁ እንላለን።

#ቅድመጋብቻ #ብሥራተገብርኤል #አንቀጸብጹአን #ሰንበትትምህርትቤት

የገቢ ማሰባሰቢያ ዜና፣የደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን አንቀጸ ብፁዓን ሰንበት ትምህርት ቤት ሐምሌ 26 ምሽት ያዘጋጀው የእራት እና የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ-ግብር በስኬት ተጠናቀ...
03/08/2026

የገቢ ማሰባሰቢያ ዜና፣

የደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን አንቀጸ ብፁዓን ሰንበት ትምህርት ቤት ሐምሌ 26 ምሽት ያዘጋጀው የእራት እና የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ-ግብር በስኬት ተጠናቀቀ።

በደብሩ ስብከተ ወንጌል አዳራሽ በተዘጋጀው በዚህ መርሐ-ግብር እስከ አራት መቶ የሚደርሱ እንግዶች ታድመዋል።
በዕለቱም ቀሲስ ዶክተር አካለወልድ ተሰማ የመገናኛ ብዙሃን ሥርጭት አገልግሎት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣
መጋቤ ጥበባት ቀሲስ ጌቱ ሞቲ የምስራቅ ሸዋ ሃገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ ፣
የደብሩ አስተዳዳሪ መልአከ ገነት መዝገቡ ላቀው፣
የደብሩ ዋና ጸሃፊ ሊቀብርሃናት መአዛ ተክለወልድ ፣
ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እና ለመርሐ-ግብሩ ቲኬት ገዝተው የተገኙ እንግዶች ታድመዋል።

በዕለቱም ለሰንበት ትምህርት ቤቱ ሕንፃ ግንባታ የሚውል ብር 4,500,000 እና ከነ ቲኬት ሽያጩ 5,500,000 ብር መሰብሰብ ተችሏል።
ለዚህ መርሃግብር መቃናት ለተባበራችሁ መርሐ-ግብሩን አጠቃላይ ስፖንሰር በማድረግ፣
ቲኬት በማሰራጨት፣ በቃል መግባት፣ በጨረታ መርሐ-ግብር በመሳተፍ፣
በመስተንግዶ እንዲሁም አጠቃላይ መርሐ-ግብሩን በመምራትና በማሳካት ለተሳተፋችሁ ሁሉ በቅዱስ ገብርኤል ስም ምስጋናችንን እናቀርባለን ።

02/08/2026

የአንቀጸ ብፁአን ሰንበት ትምህርት ቤት ሕንፃ ግንባታ 3ኛ ምዕራፍ ልዩ የእራት ግብዣ እና የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር

02/08/2026

የአንቀጸ ብፁአን ሰንበት ትምህርት ቤት ሕንፃ ግንባታ 3ኛ ምዕራፍ ልዩ የእራት ግብዣ እና የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር።

@እኛ የጀመርነውን የምንጨርሰው እኛ ነን !

#ደብረብሥራት #አንቀጸብጹአን #@ገብርኤል
#ሕንፃውን #የምገነባው #ነህምያ #እኔነኝ

ከሀገር ውጪ ለምትገኙ የሰንበት ትምህርት ቤታችን አባላት በሙሉየዛሬው የገቢ ማሰባሰቢያ መርኃግብር ከምሽቱ 12 ሰዓት ጀምሮ በሰንበት ት/ቤታችን የፌስቡክ እና ዩቲዩብ ቻናሎች በቀጥታ የምናስተ...
02/08/2026

ከሀገር ውጪ ለምትገኙ የሰንበት ትምህርት ቤታችን አባላት በሙሉ

የዛሬው የገቢ ማሰባሰቢያ መርኃግብር ከምሽቱ 12 ሰዓት ጀምሮ በሰንበት ት/ቤታችን የፌስቡክ እና ዩቲዩብ ቻናሎች በቀጥታ የምናስተላልፍ መሆኑን እንገልፃለን።

01/08/2026

የትውልድ አሻራ፣
ቃለ እግዚአብሔርን ላስተማረችኝ ሰንበት ትምህርት ቤቴ እኔ የበኩሌን አበርክቻለሁ፣ አናንተሰ?
#የአንቀጸ #ብፁአን #ሰንበት #ትምህርት #ሕንፃ #እንገንባ #ስብከተ #ወንጌል #ደብረ #ብሥራት

እናንተስ?

የትውልድ አሻራ፣የደብረ ብስራት ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን አንቀጸ ብፁአን ሰንበት ትምህርት ቤት የመጨረሻውን ኮለን ሙሊት አሻራ በአባላትና አገልጋዮች አከናወነ።ቅዳሜ ሐምሌ 25 ቀን ማለዳ...
01/08/2026

የትውልድ አሻራ፣

የደብረ ብስራት ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን አንቀጸ ብፁአን ሰንበት ትምህርት ቤት የመጨረሻውን ኮለን ሙሊት አሻራ በአባላትና አገልጋዮች አከናወነ።

ቅዳሜ ሐምሌ 25 ቀን ማለዳ ለአባላትና አገልጋዮች ታላቅ የማስታወሻ እለት ሆኖ ተመዝግቧል።

ይህንንም ህንፃ ከፍፃሜ ለማድረስ ነገ ሐምሌ 26 ቀን 2018 ዓም ልዩ የእራት እና የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃግብር ላይ በመገኘት ሁሉም የበኩሉን እንዲያበረክት ጥሪ ተደርጓል።

"ዛሬ የምንገነባው ሕንፃ አይደለም፤ ትውልድ ነው!"                           + + + + +እንኳን ለመጨረሻው ኮለን ሙሌት ሥራ አደረሳችሁ!"አንድ ሕንፃ በሲሚንቶና በብረት ይ...
01/08/2026

"ዛሬ የምንገነባው ሕንፃ አይደለም፤ ትውልድ ነው!"
+ + + + +

እንኳን ለመጨረሻው ኮለን ሙሌት ሥራ አደረሳችሁ!

"አንድ ሕንፃ በሲሚንቶና በብረት ይቆማል፤ ነገር ግን ትውልድ የሚገነባው በእምነት፣ በፍቅርና በመሥዋዕትነት ነው። የደብረ ብስራት ቅዱስ ገብርኤል አንቀጸ ብጹአን ሰንበት ትምህርት ቤት፤ ለልጆቻችን የዕምነት መሠረት፣ የእውቀት መብራትና የሥነ- ምግባር መቅረጫ የሚሆን ሕንፃ በታላቅ መሥዋዕትነት እየገነባ ይገኛል።

ለ ሕንፃ ግንባታው ብዙዎች ጉልበታቸውን ሰጥተዋል፣ ብዙዎች ገንዘባቸውን አበርክተዋል፣ ሌሎችም በጸሎት ቆመዋል። ዛሬ ሕንፃው ወደ መጨረሻው ደረጃ ደርሷል፤ በዓሁኑ ሰዓት በካህናት አባቶች የማዕጠንትና ጸሎተ ዕጣን በሕንፃው ዙሪያ፣እየተከናወነ ነው፡፡ ፀለቱም እንዳበቃ የሙሊቱ ሥራ በካህናት ተባርኮ፣ በአባላትና አገልጋዮች ተሳትፎ ይከናወናል፡፡ የቀረው የፊኒሺንግ ሥራ ብቻ ነው። ይህ ተሰርቶ ሲጠናቀቅ ለዛሬ ብቻ አይደለም ከዚህ በኋላ የሚመጡ ሕፃናት በዚህ ቦታ ይማራሉ፣ ይጸልያሉ፣ በእምነት ያድጋሉ፣ ለቤተ ክርስቲያንና ለሀገራቸው የሚጠቅሙ ዜጎች ይሆናሉ።

ልጆቻችን ወደዚህ ሲመጡ፣ "ይህን ሕንፃ አባቶቻችንና እናቶቻችን በፍቅር ገነቡልን" ብለው ይናገራሉ። ያ ከማንኛውም ሀብት የሚበልጥ ትሩፋት ነው።

ዛሬ የምንሰጠው መዋጮ ነገ የአንድ ልጅ መንፈሳዊ ሕይወት ይሆናል፤ ዛሬ የምናኖረው ድንጋይ ነገ የብዙዎች በረከት ይሆናል ፤ ዛሬ የምናሳየው ፍቅር ነገ በትውልድ ልብ ውስጥ ይኖራል ፤ እኛ ከዚህ ዓለም እናልፋለን፤ ነገር ግን የሠራነው በጎ ሥራ ከእኛ በኋላ ይኖራል፤ ልጆቻችን ወደዚህ ሲመጡ "ይህን ሕንፃ አባቶቻችንና እናቶቻችን በፍቅር ገነቡልን" ብለው ይናገራሉ። ያ ከማንኛውም ሀብት የሚበልጥ ትሩፋት ነው።
የተከበራችሁ ኦርቶዶክሳዊያን ምዕመናን ብዙ ሰዎች "ሌላ ሰው ይረዳል" ብለው ያልፋሉ። ነገር ግን የቤተ ክርስቲያን ሥራ የሚጠናቀቀው "እኔ አለሁ" በሚሉ ልጆቿ ነው። የምንሰጠው መጠኑ አይደለም የሚታየው የልባችን መሻት ነው የሚመዘነው። ትንሽ መዋጮ በፍቅር ሲሰጥ በእግዚአብሔር ፊት ትልቅ ነው። ስለዚህ እንላለን፦

• እንደ አቅማችን እንስጥ።

• እንደ ፍቅራችን እንስጥ።

• እንደ እምነታችን እንስጥ። እንምጣ... የቀረውን የፊኒሺንግ ሥራ በአንድነት እናጠናቅቅ።

በመጨረሻ

"ዛሬ የምናቀርበው መዋጮ ነገ የሚጸልይ ትውልድ ይወልዳል።

ዛሬ የምንጨርሰው ሕንፃ ነገ ቅዱሳንን የሚያፈራ ሰንበት ትምህርት ቤት ይሆናል።

ኑ... ለእግዚአብሔር ቤት እንሥራ፤ ለትውልድ የማይጠፋ አሻራ እንተው።"

የአንቀጸ ብጹአን ሰንበት ትምህርት ቤት
ሕንፃ አሰሪ ኮሚቴ
ሐምሌ 25 ቀን 2018 ዓ/ም
አዲስ አበባ፡፡

Address

Adama
1000

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Anketse Bitsuan posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to Anketse Bitsuan:

Shortcuts

Share