12/01/2026
የኒቂያ ጉባኤ
(THE COUNCIL OF NICEA)
የኒቂያ ጉባኤ በ4ኛው ክፍለ ዘመን በ325 ዓ.ም የተደረገ የቤተክርስቲያን ጉባኤ ነው። ይህን ጉባኤ የሰበሰበው ንጉሰ ነገስቱ አፄ ቆስጠንጢኖስ ሲሆን፤ የዚህ ጉባኤ ዋና ዓላማ ከአሌክሳንድሪያ የመጣው አርዮስ የሚባል ቄስ ኢየሱስ (ወልድ) ዘላለማዊ እንዳልሆነ እና ከአብ ጋር እኩል እንዳልሆነ አስተማረ። “ወልድ ያልነበረበት ጊዜ ነበር” በማለት ተናግሯል። ይህ ትምህርት የክርስቲያን ትምህርት ስላልሆነ አባቶች ሊያወግዙት ተሰበሰቡ። አርዮስም ተወገዘ፤ ይህንን ትምህርትም የያዙ ሰዎች "አርዮሳውያን" ተብለው ተጠሩ።
በዚህ ጉባኤ ላይም አርዮስ የራሱን ሙግት እንዲያቀርብ ተጠርቶ ነበር፤ የእርሱም ሙግት፡ "ወልድ በአብ የተሾመ ፍጡር ነው፤ አብ ወልድን ከፈጠረው በኋላ ወልድ ሁሉን እንዲፈጥር ስልጣንን ሰጠው" በማለት ያስቀምጣል። ይህ አስተምህሮ ስሕተት መሆኑን የተረዱት እስክንድርያ እና አትናቲዮስ ለአርዮስ ጥያቄዎችን መሰንዘር ጀመሩ።
አትናቲዮስም እንዲህ ብሎ ተናግሮ ነበር:-
"ኢየሱስ የደህንነቴ ዋስትና ነው፤ ለማዳን የበቃው አምላክ ስለሆነ ነው" በማለት ተናግሯል።
በአጭሩ አርዮስ ወልድ እርሱ ዘላለማዊ አምላክ ሳይሆን አብ በሂደት የፈጠረው ሁሉንም እንዲፈጥር ሥልጣንን የሰጠው ፍጡር ነው በማለት አስተምሯል። እንዲሁም እርሱ ከአብ ጋር እኩል አይደለም በማለት የወልድን መለኮትነት ይክዳል።
በኒቂያ ጉባኤ ላይ የክርስቶስ ኢየሱስ አምላክነት እንዲሁም ዘላለማዊ ልጅነቱ ተረጋግጦል። እንዲህም በማለት ተወስኗል:-
"ዓለም ሳይፈጠር ከእርሱ በተወለደ የአብ አንድያ ልጁ በሚሆን በአንድ ጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ እናምናለን። ከብርሃን በተገኘ ብርሃን፣ ከእውነተኛ አምላክ በተገኘ እውነተኛ አምላክ፣ የተወለደ እንጂ ያልተፈጠረ፣ በመለኮቱ ከአብ ጋር የሚተካከል፣ ሁሉ በእርሱ የሆነ፣ ስለ እኛ ስለ ሰዎች እኛን ለማዳንም ከሰማይ የወረደ፣ በመንፈስ ቅዱስ ከቅድስት ድንግል ማርያም ሰው የሆነ፣ ሰውም ሆኖ በጴንጤናዊው በጵላጦስ ዘመን ስለ እኛ የተሰቀለ፣ የታመመ፣ የሞተ፣ የተቀበረም፣ በሦስተኛውም ቀን ከሙታን ተለይቶ የተነሳ፣ በቅዱሳት መፅሐፍት እንደ ተፃፈ በክብር ወደ ሰማይ የዐረገ፣ በአባቱም ፍፃሜ የለውም።"
ማጠቃለያ:-
የዚህ ጉባኤ ድንጋጌ የክርስቶስን ፍፁም አምላክነት፤ እርሱ ከአብ የማይተናነሰ ዘላለማዊ የእግዚአብሔር ልጅ፤ በሥልጣን ከአብ ጋር እኩል የሆነ፤ መለኮት መሆኑን በደንብ አረጋግጦልናል።
ብሩካን ናችሁ!!!