Glory to God

Glory to God Wisdom

04/01/2025

በነጋውም ንጉሡ ማልዶ ተነሣ፥ ፈጥኖም ወደ አንበሶች ጕድጓድ ሄደ።
ወደ ጕድጓዱም ወደ ዳንኤል በቀረበ ጊዜ በኀዘን ቃል ጠራው፤ ንጉሡም ተናገረ ዳንኤልንም። የሕያው አምላክ ባሪያ ዳንኤል ሆይ፥ ሁልጊዜ የምታመልከው አምላክህ ከአንበሶች ያድንህ ዘንድ ችሎአልን? አለው።
ዳንኤልም ንጉሡን። ንጉሥ ሆይ፥ ሺህ ዓመት ንገሥ።
በፊቱ ቅንነት ተገኝቶብኛልና፥ በአንተም ፊት ደግሞ፥ ንጉሥ ሆይ፥ አልበደልሁምና አምላኬ መልአኩን ልኮ የአንበሶችን አፍ ዘጋ፥ እነርሱም አልጐዱኝም አለው።
የዚያን ጊዜም ንጉሡ እጅግ ደስ አለው፥ ዳንኤልንም ከጕድጓዱ ያወጡት ዘንድ አዘዘ፤ ዳንኤልም ከጕድጓድ ወጣ፥ በአምላኩም ታምኖ ነበርና አንዳች ጉዳት አልተገኘበትም።
ትንቢተ ዳንኤል 6 : 19-23

28/11/2024

እግዚአብሔርም በደዌ ያደቅቀው ዘንድ ፈከደ፤ ነፍሱን ስለ ኃጢአት መሥዋዕት ካደረገ በኋላ ዘሩን ያያል፥ ዕድሜውም ይረዝማል፥ የእግዚአብሔርም ፈቃድ በእጁ ይከናወናል።
ከነፍሱ ድካም ብርሃን ያያል ደስም ይለዋል፤ ጻድቅ ባሪያዬም በእውቀቱ ብዙ ሰዎችን ያጸድቃል፥ ኃጢአታቸውን ይሰከማል።
ስለዚህም እርሱ ብዙዎችን ይወርሳል፥ ከኃያላንም ጋር ምርኮን ይከፋፈላል፤ ነፍሱን ለሞት አሳልፎ ሰጥቶአልና፥ ከዓመፀኞችም ጋር ተቈጥሮአልና፤ እርሱ ግን የብዙ ሰዎችን ኃጢአት ተሸከመ፥ ስለ ዓመፀኞችም ማለደ።
ትንቢተ ኢሳይያስ 53 : 10-12

02/09/2024

እግዚአብሔርም ኢያሱን። ከሙሴ ጋር እንደ ሆንሁ እንዲሁ ከአንተ ጋር መሆኔን ያውቁ ዘንድ በዚህ ቀን በእስራኤል ሁሉ ዓይን ከፍ ከፍ አደርግህ ዘንድ እጀምራለሁ።

መጽሐፈ ኢያሱ ወልደ ነዌ 3 : 7

16/08/2024

አቤቱ፥ አንተ መብራቴ ነህና፤ እግዚአብሔርም ጨለማዬን ያበራል።
በአንተ ኃይል በጭፍራ ላይ እሮጣለሁና፤ በአምላኬም ቅጥሩን እዘልላለሁና።
የአምላክ መንገድ ፍጹም ነው፤ የእግዚአብሔር ቃል የነጠረ ነው፤ በእርሱ ለሚታመኑት ሁሉ ጋሻ ነው።
ከእግዚአብሔር በቀር አምላክ ማን ነው? ከአምላካችንስ በቀር አምባ ማን ነው?
መጽሐፈ ሳሙኤል ካልዕ 22 : 29-32

13/08/2024

ሰማያት ሆይ፥ አድምጡ፥ እኔም እናገራለሁ፤
ምድርም የአፌን ቃሎች ትስማ።
ትምህርቴ እንደ ዝናብ ትፈስሳለች፥
እንደ ጠል ትንጠባጠባለች፤
በልምላሜ ላይ እንደ ጤዛ፥
በሣርም ላይ እንደ ካፊያ።
የእግዚአብሔርን ስም እጠራለሁና፤
ለአምላካችን ታላቅነትን ስጡ።
እርሱ አምላክ ነው፤ ሥራውም ፍጹም ነው፤
መንገዱም ሁሉ የቀና ነው፤
የታመነ አምላክ፥ ክፋትም የሌለበት፥
እርሱ እውነተኛና ቅን ነው።
ኦሪት ዘዳግም 32 : 1-4



ሰማያት ሆይ፥ አድምጡ፥ እኔም እናገራለሁ፤
ምድርም የአፌን ቃሎች ትስማ።
ትምህርቴ እንደ ዝናብ ትፈስሳለች፥
እንደ ጠል ትንጠባጠባለች፤
በልምላሜ ላይ እንደ ጤዛ፥
በሣርም ላይ እንደ ካፊያ።
የእግዚአብሔርን ስም እጠራለሁና፤
ለአምላካችን ታላቅነትን ስጡ።
እርሱ አምላክ ነው፤ ሥራውም ፍጹም ነው፤
መንገዱም ሁሉ የቀና ነው፤
የታመነ አምላክ፥ ክፋትም የሌለበት፥
እርሱ እውነተኛና ቅን ነው።
ኦሪት ዘዳግም 32 : 1-4

25/06/2024

እግዚአብሔርም ይህን ቃል ሁሉ እንዲህ ብሎ ተናገረ።
ከግብፅ ምድር ከባርነት ቤት ያወጣሁህ እግዚአብሔር አምላክህ እኔ ነኝ።
ከእኔ በቀር ሌሎች አማልክት አይሁኑልህ።
በላይ በሰማይ ካለው፥ በታችም በምድር ካለው፥ ከምድርም በታች በውኃ ካለው ነገር የማናቸውንም ምሳሌ፥ የተቀረጸውንም ምስል ለአንተ አታድርግ።
አትስገድላቸው፥ አታምልካቸውምም፤ በሚጠሉኝ እስከ ሦስተኛና እስከ አራተኛ ትውልድ ድረስ የአባቶችን ኃጢአት በልጆች ላይ የማመጣ፤
ለሚወድዱኝ፥ ትእዛዜንም ለሚጠብቁ እስከ ሺህ ትውልድ ድረስ ምሕረትን የማደርግ እኔ እግዚአብሔር አምላክህ ቀናተኛ አምላክ ነኝና። ፕ
ኦሪት ዘጸአት 20 : 1-6

23/06/2024

በዚያም ጊዜ ሙሴና የእስራኤል ልጆች ይህንን መዝሙር ለእግዚአብሔር ዘመሩ፥ እንዲህም ብለው ተናገሩ። በክብር ከፍ ከፍ ብሎአልና ለእግዚአብሔር እዘምራለሁ፤ ፈረሱንና ፈረሰኛውን በባሕር ጣለ።
ጕልበቴ ዝማሬዬም እግዚአብሔር ነው፥መድኃኒቴም ሆነልኝ
ይህ አምላኬ ነው አመሰግነውማለሁ፥ የአባቴ አምላክ ነው ከፍ ከፍም አደርገዋለሁ።
እግዚአብሔር ተዋጊ ነው፥ ስሙም እግዚአብሔር ነው፥
የፈርዖንን ሰረገሎች ሠራዊቱንም በባሕር ጣላቸው፤
የተመረጡት ሦስተኞች በኤርትራ ባሕር ሰጠሙ።
ኦሪት ዘጸአት 15 : 1-4

21/06/2024

ሙሴም ወደ እግዚአብሔር ዘንድ ወጣ፤ እግዚአብሔርም በተራራው ጠርቶ አለው። ለያዕቆብ ቤት እንዲህ በል፥ ለእስራኤልም ልጆች እንዲህ ንገር።
በግብፃውያን ያደረግሁትን፥ በንስርም ክንፍ እንደተሸከምኋችሁ፥ ወደ እኔም እንዳመጣኋችሁ አይታችኋል።
አሁንም ቃሌን በእውነት ብትሰሙ ኪዳኔንም ብትጠብቁ፥ ምድር ሁሉ የእኔ ናትና ከአሕዛብ ሁሉ የተመረጠ ርስት ትሆኑልኛላችሁ፤
እናንተም የካህናት መንግሥት የተቀደሰም ሕዝብ ትሆኑልኛላችሁ። ለእስራኤል ልጆች የምትነግራቸው ቃል ይህ ነው።
ኦሪት ዘጸአት 19 : 3-6

18/06/2024

ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን በመነሣቱ ለሕያው ተስፋና ለማይጠፋ፥ እድፈትም ለሌለበት፥ ለማያልፍም ርስት እንደ ምሕረቱ ብዛት ሁለተኛ የወለደን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት ይባረክ፤ ይህም ርስት በመጨረሻው ዘመን ይገለጥ ዘንድ ለተዘጋጀ መዳን በእምነት በእግዚአብሔር ኃይል ለተጠበቃችሁ ለእናንተ በሰማይ ቀርቶላችኋል።
በዚህም እጅግ ደስ ይላችኋል፥ ነገር ግን በእሳት ምንም ቢፈተን ከሚጠፋው ወርቅ ይልቅ አብልጦ የሚከብር የተፈተነ እምነታችሁ፥ ኢየሱስ ክርስቶስ ሲገለጥ፥ ለምስጋናና ለክብር ለውዳሴም ይገኝ ዘንድ አሁን ለጥቂት ጊዜ ቢያስፈልግ በልዩ ልዩ ፈተና አዝናችኋል።
እርሱንም ሳታዩት ትወዱታላችሁ፤ አሁንም ምንም ባታዩት በእርሱ አምናችሁ፥ የእምነታችሁን ፍፃሜ እርሱም የነፍሳችሁን መዳን እየተቀበላችሁ፥ በማይነገርና ክብር በሞላበት ሐሤት ደስ ይላችኋል።
1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 1 : 3-9

Address

Adama

Telephone

+251985315794

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Glory to God posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share