ቤተ ጊዮርጊስ bete georgis

ቤተ ጊዮርጊስ bete georgis የእግዚአብሔር ፈቃድ ሆኖ ይህን ቻናል ከፍተናል እንደምንማማ?

https://www.youtube.com/watch?v=L5nDjAaskQY
07/10/2020

https://www.youtube.com/watch?v=L5nDjAaskQY

-ETHIOPIA:- እግዚአብሔር እኛን ይወደናል ወጣቶች በህብረት የዘመሩአቸው መዝሙራት ክፍል ፪(2) ETHIOPIAN ORTHODOX TEWAHIDO MEZMUR

07/10/2020

-ETHIOPIA:- እግዚአብሔር እኛን ይወደናል ወጣቶች በህብረት የዘመሩአቸው መዝሙራት ክፍል ፪(2) ETHIOPIAN ORTHODOX TEWAHIDO MEZMUR

05/09/2020

መምህር ጳውሎስ መልካሥላሴ ድንቅ ስብከት MEMHIR PAWLOS MELKASILASE

ዲያቆን ዶ/ር ቴዎድሮስ በለጠ በሀሳቧም በሥጋዋም ድንግል ነች
31/08/2020

ዲያቆን ዶ/ር ቴዎድሮስ በለጠ በሀሳቧም በሥጋዋም ድንግል ነች

አስደናቂ ትምህርት :- ድንግል በህሊናኪ ወድንግል በሥጋኪ ዲያቆን ዶ/ር ቴዎድሮስ በለጠ ክፍል ፪(2)MEMHIR DR TEODROS BELETE

https://www.youtube.com/watch?v=8Xmoe71ZHMo
24/06/2020

https://www.youtube.com/watch?v=8Xmoe71ZHMo

ድንቅ ስብከት ዓለም ተስፋ ያደረግናቸው ሰዎች ለራሳቸው መሆን አልቻሉም ስብከተ ወንጌል የእግዚአብሔር መልአክ በሚፈሩት ሰዎች ዙሪያ ይሰፋል ያድናቸውማል

24/06/2020

ድንቅ ማብራሪያ ጥምቀት በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እንዴት ይተረጎማል አባ ገብረኪዳን ግርማ ABA GEBREKIDAN GIRMA

09/06/2020

አስደናቂ ስብከት በመምህር ዶ/ር ዘበነ ለማ ክፍል ሦስት MEMHIR DR ZEBENE LEMMA SIBKET

support memhir zemedkun bekele by signing this petitionhttps://www.change.org/p/facebook-freedom-of-speech-1fd7aeb…like ...
09/06/2020

support memhir zemedkun bekele by signing this petition
https://www.change.org/p/facebook-freedom-of-speech-1fd7aeb…

like bete georgis page
https://www.facebook.com/ቤተ-ጊዮርጊስ-bete-georgis-107987744016355/?

የተዋህዶ ልጆች ከዚህ በላይ የማንቂያ ደወል የለም።ወደፊት ቤተክርስቲያን በአክራሪ ጽንፈኛ ጸረ ተዋህዶ ኃይሎች የሚደርስባትንና አሁንም እየደረሰባት ያለውን ጥቃት አስመልክቶ እውነቱን በመናገሩና ትክክለኛ የማንቂያ ደወልን ለተዋህዶ ልጆች በሙሉ የሚደውለውን የማንቂያ ደወል ጽሁፍ በመጻፉ ምክንኛት የመምህራችን ዘመድኩን በቀለን የፌስ ቡክ ገጽ እንደተለመደው አስዘግተውታል።ስለዚህ ሁላችንም ተቃውሞአችንን እናሰማ።በተለይ በዚህ ሰዓት በቤተክርስቲያን ተገኝቶ መረጃ የማግኘትና የመወያየት እድል በጠበበት ሰዓት እንደ መምህር ዘመድኩን ያሉ ያለ እረፍትና ያለምንም ክፍያ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ የቤተክርስቲያንን ጉዳይ የሚዘግቡ የፌስ ቡክ ገጾች መዘጋት አደጋው የከፋና ምእመናን በተኩላ እንዲበሉ በር ከፋች ስለሆነ አጥብቀን ልንቃወምና ህብረታችንን ልናሳይ ይገባል።እያልኩኝ ለፌስቡኩ መዘጋት ምክንያት የሆነውን ጽሁፉን እነሆ ብያለው። # # # # # # # #

~ የከርቸሌው የነጋሽ መስጊድና
“ለሁሉም ሽጥ ከራስህ ወገን ብቻ ግዛ”
መ ፈ ክ ራ ቸ ው
*~★★~*

• ጦማሩ አለው። ሆን ብዬ ነው ያስረዘምኩት። አጭሬ የለመዳችሁ ጋር ሂዱ። አይደለም እንዴ ኪሩ?

• አዳሜ ውኃህን እየተጎነጨህ አንብበው። ጎጋ ወሀቢም ሆንክ ጎጋ አፈጠዳቅ ሜካፓምና ሰነፍ ንባብ ማንበብ የሚያቅለሸልሽህ፣ የሚያጥወለውልህ፣ የሚያፋሽክህ፣ የሚያንጠራራህ ሀ ገደሉ አያጅቦ መጣልህ የንባብ ፀር አንተ ክርስቲያኑም ብትሆን ሳታነብ፣ ሳይገባህ በፔጄ ላይ ውርውር እላለሁ ብትል። እ ቀ ስ ፍ ሃ ለ ሁ !!

• እኔ ለፔጄ አለቃ ነኝ። ፔጄን ራሴ ካላስከበርኩ ማንም አያከብርልኝም። ካላጸዳሁትም ማንም አያጸዳልኝም። ቀዥቃዣ ለኮመንት ሟች እቀስፋለሁ። ቢያንስ ከ5 ደቂቃ በፊት ኮመንት የሚሰጥ አባርራለሁ። በደንፉ እንዳትቀሰፍ ተጠንቀቅ።

| ~ “ለሁሉም ሽጥ ከራስህ ወገን ብቻ ግዛ” የምትለዋን የወሐቢዎችን መመሪያና መፈክር እኛም ብንኮርጃት እንዴት ሸጋ ነገር መሰለቻችሁ። “ለሁሉም ሽጥ ከራስህ ወገን ብቻ ግዛ” አሪፍ !!

•••
በረከታቸው ይደርብንና ሟቹ አምስተኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ የነበሩት ብፁዕ አቡነ ጳውሎስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት የሆነ ጊዜ በቁጣ ተመልተው ወደ አዲስ አበባ ከንቲባ ጽሕፈት ቤት ያመራሉ አሉ። በወቅቱ የከተማዋ ከንቲባ የነበረው ከንቲባ አሊ አብዶ የተባለ ደንበኛ ሱፍ የለበሰ አክራሪ የወሀቢይ ሙስሊም ነበር። አሊ አብዶ በተሾመ በዓመቱ የአዲስ አበባን ከተማ ከመኖሪያ ቤቶች እኩል መስጊድ በመስጊድ አደረጋት። ወንድ እናቱ የወለደችው እስላም ነው አባቴ ይሙት። ወሀቢይ ስትሆን ሼም፣ ሕግ፣ ይሉኝታ ብሎ ነገር የለም። እንደ ህጻን ታለቃቅሳለህ፣ በእዬዬዬ ፍላጎትህን በገገማ ታስፈጽማለህ። አሪፍ መንገድ ነው። ላወቀበት አሪፍ መንገድ ነው። አሊ አብዶ ራሱ አብዶ ቤተ ክህነቱን አሳበደው። ለ200 ሺ ሞስሊም 400 መስጊድ ሲሠራ ጊዜ መሬቱን ሁሉ ለመስጊድ፣ መኖሪያ ቤቶችን ሁሉ ሳይቀር ወደ መስጊድነት መቀየሩን ዓይተው በዚህ ጉዳይ ተበሳጭተው ነበር አሉ እነ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ከንቲባ ሃጂ አሊ አብዶን ሊያናግሩት አብዶ ጋ ቱግ ብለው ከጽሕፈት ቤቱ ድረስ የሄዱት።

•••
ሁላቸውም ገቡ። ሰውዬውን ከንቲባውን አገኙት። ብዙም ተወያዩ። በመጨረሽታም ከንቲባ አሊ አብዶ ለእነ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስንና ለቤተ ክህነቱ ልዑካን እንዲህ አላቸው አሉ። “ ከተማዋ አዲስ አበባ ከተቆረቆረችበት ጊዜ አንስቶ ከተማዋን የመምራት ኃላፊነት የእናንተ ሰዎች ኃላፊነት እንደነበር ይታወቃል። ሆኖም ግን ባለፉት መቶ ምናምን ዓመታት እናንተ ሃይማኖታችሁን በማስፋፋቱ በኩል ዕድሉን አልተጠቀማችሁበትም። እኛ የእናንተን ያህል ዘመን አዲስ አበባን የመምራት ዕድል ቢገጥመን ኖሮ አይደለም 200 ምናምን መስጊድ መሥራት የመስጊድ መሥሪያ መሬት ባይኖር እንኳ በየእያንዳንዱ ሙስሊም ጭንቅላት ላይ ሁላ ምን የመሳሰሉ መስጊዶችን እንሠራ ነበር። እናም በሕግ አግባብ ሓላፊነት ላይ እስካለሁ ድረስ ለሃይማኖቴ የፈለኩትን ማድረግ መብቴ ነው። በሉ ንኩት አላህ ወአክበር ! ” ብሎ በትህትና ቃል ተናግሮ ኩም አድርጎ አስተናግዶ ከቢሮው ሸኛቸው አሉ። እነሱም [ እክህደከ ሰይጣን] እያሉ እያማተቡ ወጥተው ሄዱ አሉ። አሁን አሊ አብዶ ማለት በእስልምና አማኞች ዘንድ እንደ ጻድቅ ሰው ነው የሚታየው። የሚቆጠረውም። ይሄን ዕድል ያመቻቸችው ደግሞ ዐማራን የጎዳች መስሏት መርዞ ህወሓት ነበረች። ህወሓት መርዞ ልትፈነቀል ሳምንት ስለቀራት ጮቤ በመርገጥ ላይ ነኝ። በኮሮና ጊዜ ዐመፅ ግን ለህዝቡ ጥሩ ባይሆንም ህወሓት ግን እንደ ጋዳፊ ሲኦል ስትገባ ለማየት ቋምጫለሁ። ተዋሕዶን እንዳስደፈረች መድኃኔዓለም በብልፅግና ያስደፍራት። አሜን።

•••
ወደ እኛ ጉዳይ እንምጣ። የእስላሞቹን የፈጣጣ፣ የገገማ፣ የሰገጤ፣ የሼም የለሽ አካሄድ ለጊዜው እንግታውና እስቲ ራሳችንን እንጠይቅ። እንዲያው ለመሆኑ ኦርቶዶክሳዊው ሥልጣን ሲይዝ እንዲህ እንደ አሊ አብዶ ያደርገዋል ወይ ብለን እስቲ እንጠይቅ። ኦርቶዶክሳዊ ሥልጣን ሲይዝ መጀመሪያ ማዕተቡን ነው የሚበጥሰው። ከዚያ ከቤተ ክርስቲያን ይሸሻል፣ ይርቃል። ጾም መጾም ያቆማል። አርብ ረቡዕ ሁዳዴ ፍልሰታን አይጾምም። ካህን ቄስ ይጸየፋል። ክርስትና ባርነት መስሎ ይታየዋል። እናም ታስሮ እንደተፈታ ጥጃ መዝለል፣ መቦረቅ ብቻ ያምረዋል። እንደ አሊ አብዶ ዓይነት ልብ አይኖረውም። አሊ አብዶ ለሙስሊሞች ጻድቅ ነው። ይኸው ህወሓትም ወርዳ እርሱ ተንፈላስሶ ይኖራል።

•••
ኦርቶዶክሱ ባለሥልጣን ጭራሽ ሥልጣን ሲይዝ በገንዘብም በአምልኮውም እልም ያለ ዘማዊ ነው የሚሆነው። አንድ ሁለት ደህና ሰው እየጠራህ አታዝገኝ። ከሚስቱ ውጪ እንደ ውሻ ካገኛት ጋር ሲጋደምና ሲያመነዝር፣ ከባለ ጉዳይና ከጸሐፊው ጋር ሲዳራ፣ ከሽክና ጠላ፣ ከቡቱሌ ቢራ በአንድጊዜ ወደ ውስኪና ኮኛክ ሲንደረደር፣ አምቡላውን ሲግፍ፣ የሚቀበለውን ጉቦ፣ የሚዘርፈውን ብር፣ የሚሸጠውን መሬት፣ የሚያስለቅሰውንና የሚያስጨንቀውን የደሃ ብዛት ሲቆጥር ይኖራል። እግዚአብሔርን መፍራት፣ ለሃይማኖቱም ለሃገሩም መራራት ብሎ ነገርም አያውቅም። የእኛ ባለ ሥልጣን ማለት እንዲህ ነው። ሃገር ምድሩን ቤተ ክርስቲያን ያድርገው ማለቴም አይደለም። 200 ሺ ሙስሊም 200 መስጊድ፣ ለ5 ሚልዮን ክርስቲያን 180 ቤተ ክርስቲያን አይመጥንም።

•••
ቢያንስ ቢያንስ ለበዓለ ጥምቀት፣ ለልደት፣ ለትንሣኤና ለመስቀል እንኳ በቤተ ክርስቲያን አይገኝም። ሰንበትን እንኳ ከልጆቹ ጋር አያስቀድስም። ነጠላ ለብሶ መታየት ያንዘረዝረዋል። እግዚአብሔር ይመስገን ማለት ያፍራል። ፈሪ፣ ዘማዊ፣ ሌባ፣ ነፍሰ ገዳይ ሆኖ ያርፈዋል። ድግስ ባለበት ቦታ ብቻ ከረባት ሱፉን አሳምሮ ሆዱን በበረኪና ታጥቦ ሲበላ፣ ሲጠጣ ይኖራል። ቀፈቱን አሳብጦ ሲንጎማለል ይውላል። ከዚያ በመጨረሻ ግን እንደሸንኮራ አገዳ ተመጦ፣ እሱ ደግሞ የህዝቡን ደም መጦ፣ መጦ ሲያበቃ ወይ እንደቱሃን ይጨፈለቃል፣ ወይ ቂሊንጦ አልያም ደግሞ እሟጳ ቀሊጦ ሆኖ ይጣላል። ኦርቶዶክሳዊ ባለሥልጣን መጨረሻው ቦርኮ መስሎ፣ አሸቦ የጨው ዕቃ መስሎ፣ ፀጋ መንፈስ ቅዱስ ርቆት እንደ ጉድፍ፣ እንደ መርገም ጨርቅ መጣል ነው ዕጣ ፈንታው።

•••
ኦርቶዶክሳዊ ባለ ሥልጣን ገና ሲመለመል ወኔ ቢሲ፣ የውስጥ ዕቃ የጎደለው፣ አእምሮው እንጭጭ፣ የአሽከርነት ባህሪ ያለው፣ ልምጥምጥ፣ ፈሪ፣ አበልና ሆዱን ከተቻለ ተረግጦ የሚገዛ፣ ከሆዱ ሰፋ፣ ከጭንቅላቱ ጠበብ ያለ ብይ ራስ ድንጉጡ ነው ተመርጦ የሚሾመው። የሁሉንም የክርስቲያን ሹመኞች ጭንቅላት ተመልከቱ። በጣም ትንሽ ነው። ብይ ብይ ነው የሚያክለው። የሚያስቡበት ሚሞሪ በዚያች ጭንቅላት ውስጥ በየት በኩል ቦታ ይኖረዋል። እነ አሊአብዶ ግን እንደዚያ አይደለሉም። ግንብ ራስ ነው። ሰፊ ጭንቅላት ከሰፊ አፍና ሆድ ጋር ነው የሚታደለው። እነ አሊ አብዶ ደፋሮች፣ ይሉኝታ ቢስ፣ ሼም ብለው የማያውቁ፣ ሆን ብለው ተዘጋጅተውና አቅደው ለሃይማኖታቸው ለመሥራት ብለው የሚመጡ፣ ሥልጣኑን ሰከንድ ሳያባክኑ የሚጠቀሙ ናቸው። መሬት ቢያጣ ሙስሊሙ ጭንቅላት ላይ መስጊድ ለመሥራት ፕሮጀክት ነድፎ የሚንቀሳቀስ ነው የእስላም ባለ ሥልጣን። ክፍት መሬት ሲያይ ከመስጊድ ሌላ አይታየውም። ፍልውኃና ካዛንችስ ሰዉ ባይኖርም ሽንት ቤት ላይ ጭምር ከመሥራት አይመለ ሱም። እናም እኛን ይበሉን እሰይ የእጃችንን ነው ያገኘነው። አሹ፣ ደግ አደረጉ። ኤትአባታችንስና።

•••
አንተ የከርቸሌው መሬት ነው የገረመህ አይደል? የከርቸሌውማ ቀላሉ ነው። ይሄ እኮ ከድሮ ጀምሮ የተለፋበት ነው። ዓለምአቀፉ ሆቴል ሲሠራ አጠገቡ መስጊድ መሥራት በሸራተኑ ማየት ነበረብህ እኮ። አሁንም የሆነው እንደዚያው ነው። አፍሪካ ኅብረት ለስብሰባ የሚመጡት እስላም መሪዎች የሚሰግዱበት ቦታ ያስፈልጋል። እናም የእስላም ብር እየበላህ፣ በዐረብ ብር ቤተ መንግሥትህን እያደስክ አናትህ ላይ መስጊድ ባይሠሩ ነው መደነቅ የነበረብህ። አንተ በየሰፈሩ መስጊድ መሠራቱ ነው የገረመህ? ገና ምን አይተህ? የሰላም ሚንስትሯ ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል አንድ ቪድዮ ላይ “ ኢንሽአላህ ገና ምን ዓይታችሁ ዓለም በሙሉ ኢስላም ይሆናል። እናንተ ብቻ ዱአ አደርጉ ስትል የምትሰብክበት የድምጽ መረጃ እጄ ላይ አለ” ዕቅዱ ገና ምን አይተህ ነው። እነሱ በደንብ ተዘጋጅተውበታል። ሕገመንግሥቱ ይከበር፣ እንዴት ቤተ ክርስቲያን ፊት መስጊድ ይሰጣል ብትል ዐቢይ አሕመድ አይሰማሕም። የአባቱን ሃይማኖት በዚህ ጊዜ ካላስፋፋ መቼ እንዲያስፋፋልህ ትፈልጋለህ። ምናምን አይሰሙልህም። አንተ ሕግ ይከበር ብለህ ስለ ሕግ ታወራለህ ወሀቢይ ግን ስለ ሕግ ጉዳዩ አይደለም። እነሱ በደንብ አስበውበት ነው ተዘጋጅተው የመጡት።

•••
ዕድሜ ለህወሓት። ዕድሜ ለመለስ ዜናዊ( ነአ)፣ ዕድሜ ለዓባይ ፀሐዬ፣ ዕድሜ ለስብሐት ነጋ፣ ስዬ አብርሃ፣ ገብሩ አሥራት፣ ለአረጋሽ፣ ለአዜብ መስፍን፣ ለተወልደ፣ ዕድሜ ለትግራይ ፖለቲከኞች። ዐማራን ጎዳን ብለው ኦርቶዶክስን እጅ እግሯን አስረው አስገድደው በሌሎች ላስደፈሯት። አቦ ህወሓት ላይ መዓቱን ያውርድባት፣ አክሱም ጽዮን እሳቱን ታዝንብባቸው። እንዲህ አቅመቢስ እንዳስመሰሉን አቅማቸው ይፍሰስ። ልጆቿ ፊት ነው ቤተ ክርስቲያንን በግሩፕ ያስደፈሯት። አሁን እየዬ መፍትሄ አይደለም። እነሱ ተዘጋጅተውበት፣ በዕቅድ ነው የመጡት። እላይ ብትወጣ፣ እታች በትወርድ ብትፈርጥ ብትነሣ ዋጋ የለህም። ሕግ ይከበር ብለህ ብትሄድ ማመልከቻህን የሚቀበለው ወይ ሙስሊም ወይ ፕሮቴስታንቱ ነው። ቤተ ክርስቲያን በራፍ ቆሞ እንዲነርትህ የሚደረገው ፖሊስ እኮ የጴንጤ መዝሙር ከፍቶ የሚያቅራራ አላህ ወክበር የሚል ወታደር ነው። ሆዳሙ፣ አጋሰሱ ኦርቶዶክሳዊ ነኝ የሚለው ወታደርማ ሶማሌ ላይ ድንበር ነው የሚጠብቀው። በእሱ ቤት ሃገር መጠበቁ ነው። ወገኛ።

•••
አንተ ከእኔ ሰፈር፣ ከእኔ አጥቢያ አካባቢ ሌላ ታቦት፣ ሌላ ቤተ ክርስቲያን እንዳይተከል እያልክ ማመልከቻ ይዘህ ከንቲባው ቢሮ፣ ቀበሌ ለቀበሌ ስትንጦሎጦል እነሱ አዩህ፣ ተመለከቱህ። ቤተ ክርስቲያን በአቅራቢያህ እንዳይተከል ከእስላም ከጴንጤው ይልቅ እርስ በእርስ ስትታገል እነሱ ተመለከቱህ። ገቢ ይሻማብኛል፣ ምእመናንን ይወስድብኛል፣ ሙዳየ ምጽዋቱ ያሳጥርብኛል፣ ያሳሳብኛል እያልክ ክርስትናና ቤተ ክርስቲያን እንዳይስፋፉ ራስህ በራስህ ላይ ምቀኛ ሆነህ ስትደክም እነሱ ቁጭ ብለው ገመገሙህ። ፈጣሪም ጥጋብህን፣ ተንኮልህን፣ ምቀኝነትህን አይቶ ይኸው በቤትህ ቁጥር ልክ የጴንጤ ቸርች፣ በሰፈርህ ቁጥር ልክ የእስላም መስጊድ አናትህ ላይ ተክሎልህ አረፍከው። ይበልህ፣ ይበለን አንተው አይደለህ እንዴ ቀጨኔ መድኃኔዓለም አጠገብ ያለውን ጥቅጥቅ ያለ “ጠብቄ” ተብሎ የሚጠራውን ጫካ የቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ታቦት ይግባበት፣ ይተከልበት ስትባል ገቢ ይሻማኛል ብለህ ያስከለከልከው። ይሄው አንተ እንቢ ያልከውን ህወሓት ለአድቬንቲስት ሚሽን ያንን ጥብቅ የሚያምር ገዳም የመሰለ ደን አሳልፋ ሰጥታለህ ዛሬ ከንፈርህን በቁጭት ስትነክስ ትኖራታለህ። ኤትአባክ ምድረ ምቀኛ ሁላ። ይበለን። ቋ

•••
አባቴ አሁን እነሱ መንግሥቱን፣ ሚድያውን፣ ፓርላማውን፣ ወታደሩን፣ ፎሊሱን፣ ሕግ አውጪውን፣ ሕግ ተርጓሚውን፣ ሕግ አስፈጻሚውን፣ መከላከያውን፣ የክፍለ ከተማም፣ የቀበሌም፣ የወረዳውንም ሁሉ ሥልጣን በሙሉ ተቆጣጥረውታል። ዕቅድ አቅደው፣ ፕላን አውጥተው፣ ብዙ ደክመው፣ ብዙ ለፍተው ስተራቴጂ ነድፈው ነው ሃገሪቱን ከላይ እስከታች የተቆጣጠሩት። አይደለም ከርቸሌ ሚካኤል ገና ደሴ መድኃኔዓለምን መስጊድ ካላደረግን፣ ሀይቅ እስጢፋኖስ ካልሰገድንበት፣ ሐረር መድኃኔዓለም ታቦቱ ወጥቶ ካልሰገድንበት ሞተን ነው ቆመን እያሉህ እኮ ነው። የከርቸሌው ይገርምሃል እንዴ አባዬ። አቢቹ እኮ በአባቱ እስላም ነው። ደመቀ መኮንን እኮ አደገኛ የወሐቢይ እስላም ነው። ሙፈሪያት ካሚል እኮ ከኡስታዝ በላይ የሆነች ኡስታዚት ናት። የፌዴሬሽን ምክር ቤቷ ትግሬዋ የአስመራ ልጅ እኮ አክራሪ እስላም ናት። ታከለ ኡማ ጴንጤ ነው። የኦርቶዶክስ ባለሥልጣን አለ እንዴ? የለም እኮ። አደራህን በፈጠረህ ገዱ፣ ዳግማዊት ምናምን እንዳትለኝ። ከሌለህ ደግሞ የለህም። እናም ይበለን። የእጃችንን ነው ያገኘነው። ይበለን። አትንጫጫ ገና አናትህ ላይ መስጊድ ይሠራል።

•••
እኛ ሀሞተ ቢስ፣ ፈሪ፣ ወኔው የተሰለበ፣ ጫት የጨረሰው፣ የማይጾም፣ የማይጸልይ፣ አሳማ ትውልዶች እያለን ምን እንዳናመጣ? ምን እንዳይፈጠር ብለህ ነው? ኡስስ ዝም በል? ከፍቅር ይልቅ ተለያይተህ፣ ተጣልተህ፣ ተቧድነህ፣ ተቧቅሰህ፣ ተኳርፈህ፣ ኦሮሚያ ውስጥ የኦሮሚያ ኦርቶዶክስና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ብለህ እንድትከፋፈል አድርገው እየነዱህ፣ የኦሮሚያ ቤተ ክህነት እኮ በወሀቢይ እስላም ፋይናንስ፣ በእስላሙ ሚድያ፣ በእኛው ይሁዳ ልጆች ነው የሚመራው። የሰሜኑን ህዝብ ውሻዋ ከልቧ ህወሓት እንዳይታረቅ አድርጋ በቀደደችው መንገድ ጅቡ ብልጽግና ገብቶ እንዳትታረቅ አድርጎ ሲከፋፍለው ይኖራል። እና ገና ተባልተህ አክሱምን ሳይረከቡህ መች ይመለሳሉ ብለህ ነው? እውነቱ ይሄው ነው። እርስ በእርስህ ተጫርሰህ ስታበቃ እነርሱ ደግሞ በተራቸው ገብተው ለያይተው ይጠልዙሃል። አንዲት እስላማዊት ኦሮሚያ የተበጣጠሰ ዐማራና የተወቀጠ ትግሬ ማየት የእነሱ ህልም ነው። ዋጠው።

•••
አሁን ዐማራው በትግሬዋ ህወሓት በደረሰበት ስቃይና ቁስል የህወሓትን መደምሰስ ነው ተስሎ በአንድ እግሩ ቆሞ እየጠበቀ ያለው። በህወሓት ሰበብ ኦርቶዶክሷ ትግራይ እንደምትወድም አያስብም። ህወሓትም ብአዴን ነው ሥልጣኔን ያሳጣኝ ብላ የዐማራን ሞት ነው የምትመኘው። ሁለቱ እርስ በእርስ ሞታቸውን ሲጠባበቁ የብልጽግናው ሙስሊሙ አቶ አደም ትግራይ ላይ ዐማራን የሚያስደስት፣ ጮቤ የሚያስረግጥ መግለጫ እየሰጠ ጮቤ ያስረግጥሃል። ኤት አባክ።

•••
" አንድ ታሪክ ላጫውታችሁ "

እስልምና ከተፈጠረባት መካ መዲና ወደ ሰሜን አፍሪቃና ወደ አውሮፓ ለመዝለቅ የሞከረው በኃይልና በጦርነት መሆኑ ይታወቃል። ለእስልምና በቀላሉ መስፋፋት ደግሞ የክርስትናው ለሁለት መከፈል ትልቅ አስተዋፅኦ አድርጓል። ምዕራባውያኑ ካቶሊክ ነን ሲሉ ምሥራቃውያኑ ደግሞ ኦርቶዶክስ ነን ብለው በአንዱ ኢየሱስ ክርስቶስ ባህሪ ላይ ሙግት ያዙ። አንዱ አንዱን ለማጥፋት ጉድጓድ ይምስ ገባ። እናም ይህን ደካማ ጎን የእስልምናው ጦር በደንብ ተጠቀመበት። ነገሩ እንዲህ ነው።

•••
የእስልምናው ጦር መጀመሪያ ካቶሊኮቹ የሚበዙበትን ሀገራት ወርሮ ሲይዝ ምሥራቃውያኑ ኦርቶዶክሳውያን " እሰይ ይበላቸው። ድሮም ክርስቶስን ሁለት ባህሪይ ነው ብለው እየሰበኩ ይሄ መዓት ባይመጣባቸው ነበር የሚደንቀው እያሉ በካቶሊካውያኑ መወረር፣ መጥፋትና መሞት ይሳለቁ ነበር። ታዲያ የእስልምናው ሠራዊት የካቶሊካውያኑን ይዞታ በቁጥጥሩ ስር ካደረገ በኋል እዚያው ያሰለማቸውን ካቶሊካውያን ወታደር አድርጎ ዘመቻውን ደርሶኝ አይቼዋለሁ። ሕጉ በቤተ እምነቶች መካከል ምን ያህል ርቀት መኖር አለበት ለሚለው ጥያቄም ከ2010 ዓም ጀምሮ ፀድቆ ተግባራዊ እየሆነ ያለው የመሬት ልማት ማኔጅመንት መመሪያ ላይ በተለያዩ ቤተ እምነቶች መካከል ቢያንስ በ500 ሜትር ራዲየስ መራራቅ እንዳለባቸው ያስቀምጣል ከተመሳሳይ ቤተ እምነቶች ደግሞ 3 ኪሎ ሜትር ራዲየስ ነው የሚለው። ይሄም ብቻ አይደለም ከዚህም በተጨማሪ ለአንድ ቤተ እምነት አዲስ ቦታ ሲዘጋጅ የቦታ ስፋት ስታንዳርዱ ከ2000 - 4000 ካ.ሜ እንዲሆን ነው ሕጉ የሚያዘውው። አሁን ግን ሕግም ሕገ መንግሥትም እነጋሽ ታከለን አያዝም። የነገን አላውቅም እንጂ አሁን ላይ ምንም አይመጣም። ጊዜው ዘመኑ የእነሱ ነው። ሲኖዶሱ እንደሆን እነ አባ ወልደ ትንሳኤን፣ እነ አቡነ ማርቆስን፣ እነ አቡነ ቶማስን ይዞልህ ነው ለቤተ ክርስቲያን ክብር የሚሟገተው? ሃሃሃሃሃሃ ። እሱን እርሱት።

•••
መፍትሄው አንድና አንድ ነው። ወስን፣ ቁረጥ፣ ልክ እንደ ሙጂብ አሚኖ፣ እንደነ አህመዲን ጀበል ቁረጥ፣ እንደነ አቡኪ ከእነ የኔታ እሸቱ ጋር ብሔራዊ ቲያትር ስታንዳፕ ኮሜዲ ማሳየቱን ትተህ በሕጋዊ መልኩ እንደ እስላሞቹ ቆፍጠን ብለህ ዋጋ ከፍለህ የተመዘገበ ኦርቶዶክሳዊ የፖለቲካ ፓርቲ መመስረትና ኦርቶዶክሳዊ ብሔረተኝነት አቀጣጥለህ ለፖለቲካ ሥልጣን የሚታገል ሕጋዊ ፓርቲ መስርተህ ታገል። እስላሞቹ ሰባት የሚያህሉ ባንኮች አሏቸው። አንተ ምንም የለህ። ያሉትም ቢሆኑ የፕሮና የእነሱው ናቸው። ባንክ ኢንሹራንስ፣ የፖለቲካ ሥልጣኑ ላይ እንደ ታከለ ኡማ ደፋር፣ አራዳ፣ ወሳኝ ሰው ያስፈልግሃል። ተወው ምናባቱ እንዳይመጣ ነው የሚል ጎበዝ ያስፈልግህሃል። ልክ እንደ ጃዋር ያለ ጾም ሲመጣ የሚጾም፣ ጾም ሲወጣ፣ ሲፈታ ሀገር የሚፈታ። ድብን ያለ ፖለቲከኛ ቀውጢ ነውጢ የሚሆን ሰው ያስፈልጋል። እንደ አህመዲን ጀበል ታከለ ኡማን በሁለት መሥመር ደብዳቤ ወጥ በወጥ የሚያደርግ ኃይል ካልተፈጠረ እመነኝ በቅርቡ አይደለም ከርቼሌ ሚካኤክ ገና አናትህ ላይ መስጊዱን ይሠሩታል። ወሀቢይ እንደሆን ይሉኝታ አያቅም። ሕጉን አይደለም መተርጎም የሚፈልገው። ተጯጩሆ፣ አጯጩሆ ግርግር ፈጥሮ አቅጣጫ አስቶ። ምኞቱን፣ ፍላጎቱን ማሳካት ነው የሚፈልገው።

•••
አሁን የአፍሪካ ኅብረት ጽሕፈት ቤት ጋር የተሰጠው 30 ሺ ሄክተር መሬት ሊያበሳጭህ አይገባም። በመሬቱ ሙስሊሞቹ ራሳቸው ሰርፕራይዝ ነው የሆኑት። ደንግጠዋል። መሬቱን ወስኖ፣ ታከለ ኡማንም አስገድዶ የሰጣቸው ዐብይ አሕመድ ነው። ዐቢይ ሕግ ብሎ ነገር አያውቅም። 3 ቢልየን ብር ከዱባይ ተቀብሏል። መስጊዱን እነ ሸምሱ ይሠሩታል ብለህም እንዳትጠብቅ። ለገሀር በሙሉ ሦስት ወረዳ የሚያህል መሬት ዐረብ ሊሰፍርበት ነው። ከገነት ሆቴል እስከ ከርቸሌም ዐረብ ድረስ ለአረቦች ተሽጧል። አንተን በኮሮናም፣ በኮሌራም፣ በልማትም፣ በስለትም ከቀዬህ አፈናቅሎ ዐረብ ያሰፍርበታል። እናም ዐረቦቹ ደግሞ መስጊድ ያስፈልጋቸዋል። ብር ከፍለውበታል። ደላላው አቢቹ በኢትዮጵያ ስም ሽጦሃል። እናም አርፈህ አፍቅረው፣ አቢቹዬ የኔ አንተን ያየ አይኔ ሌላ ሌላው ለምኔ እያልክ ዝፈንለት። እሱ ይቀረቅርልሃል።

•••
ልብ በሉ እስላሞቹ ለምን መሬት ተሰጣቸው የሚል አንድም ክርስቲያን የለም። አንድም ክርስቲያን አልኳችሁ። ሕጉ ምን ይላል? ነው ጥያቄው። አንድም የሙስሊም ማኅበረሰብ በሌለበት ሥፍራ ካቢኔው ሳይወስን፣ መመሪያም ሕግም ተጥሶ 30ሺ ካሬ መሬት መስጠት ነውር ነው። ህዝብ ቢኖር እንኳ ችግር የለውም። በባዶ መሬት ገና ለገና ዐረቦቹን ለማስፈር ሲባል በቤተ ክርስቲያን ላይ እንዲህ ማድረግ መዘዙ ወደፊት የከፋ ነው። “ለሁሉም ሽጥ ከራስህ ወገን ብቻ ግዛ” አለ ወሀቢያ። የወሀቢይ ደንበኛ ክርስቲያኑ መሆኑን ሳያውቅ ቀርቶ እኮ አይደለም። “ለሁሉም ሽጥ ከራስህ ወገን ብቻ ግዛ” አሪፍ መፈክር ናት። እኛም እስቲ እንሞክራት።

•••
አሁን ተሳዳቢው የወሀቢይ እስላም በዝቷል። ጥጋቡ አናቱ ላይ ወጥቷል። እንደ ህጻን በመጮህ እጅ ማስጠምዘዝን ሥራዬ ብሎ ይዟል። አንተም ያንን መንገድ መሞከር ነው። ምርጫው ሲመጣ ደግሞ አንገት እያየህ መምረጥ ነው። እስከዚያው ግን “ለሁሉም ሽጥ ከራስህ ወገን ብቻ ግዛ” የምትለዋን የወሀቢ እስላምን መፈክር በደንብ አንተም ኮርጀህ ሞክራት። “ለሁሉም ሽጥ ከራስህ ወገን ብቻ ግዛ”

•••
• ካነሰ እያየሁ እጨምራለሁ። እንደ ልቤ፣ የልቤን ተናግሬ በሰላም እፎይ ብዬ እተኛለሁ። በሰላምም እሞታለሁ። ኢትዮጵያዬ እኔ በበኩሌ ምንም ፀፀት የለብኝም። እንደ መምህራኑ፣ እንደ ፕሮፌሰር ዶክተሩ ባልሆንም በመሃይም አንደበቴ እንደ አቅሚቲ በድፍረት መስክሪያለሁ። የአቅሜንም ተፍጨርጭሬያለሁ። ተዋሕዶዬ የእኔ እናት እኔ ልጅሽ በበኩሌ አላሳፍርሽም። እናት ዓለሜ ዕድሜና ጤና ብቻ ለምኚልኝ። ከምሥራቅ ኢትዮጵያ የሐረርጌው ፍሬ እኔ ቆቱው ልጅሽ በብዕሬ ብቻ መቶ ሚልዮኖችን አንቀሳቅሼ እደርስልሻለሁ። እናቴ ቀና ትያለሽ፣ ቀና፣ ቀና፣ ቀና !! ቱ ምን አለ ዘመዴ በሉኝ። ኢትዮጵያም ተዋሕዶም ይነሣሉ።

•••
ይህንንም ራሴው በእጄ ጻፍኩት። 004915215070996 ደግሞ የቴሌግራም የቫይበር፣ የኢሞና የኋትስአፕ መልእክቶችን የምቀበልበት የእጅ ስልኬ ነው።

ሻሎም ! ሰላም !

ዘመድኩን በቀለ ነኝ
ግንቦት 16/2012 ዓም
ከራየን ወንዝ ዳር።

09/06/2020

አባታችን አባ ገብረኪዳን ግርማ ስለ ጥምቀት ያብራሩት
ስለ ጥምቀት ማወቅ ያለባችሁ ነገር
like bete georgis page

memhir zebene lemma sibket
25/05/2020

memhir zebene lemma sibket

አስደናቂ ስብከት:- ምን እንዳደርግላችሁ ትፈልጋላችሁ ቀሲስ ዶ/ር ዘበነ ለማ D.R ZEBENE LEMMA

Address

Adama
1000

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ቤተ ጊዮርጊስ bete georgis posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share